Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ወደ ሳኡዲ አደንዛዥ እጽንና መጠጥን ለማስገባት የሞከሩ ሰዎች ተያዙ ከመካከላቸዉም አንዱ ታጣቂ ተገደለ ተባለና በሰዎቹ ማንንነት ላይ ኢትዮጵያዊ የሚል ታፔላ ተለፈጠበት ለምን?

$
0
0

ምኒልክ ሳልሳዊ

Sadityህወሃት የራሱን ሰዎች በጣም ይፈራል፤ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸዉ እንዳይገኛኙም በጣም ይጥራል፤ህወሃት ስልጣኑንን ከለቀቀም ከሰሜን የኤርትራ ህዝብና ከትግራይ ዉጪ ያለዉ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ተወላጆችን እንደሚያጠቃም ይስፈራራል።

ህወሃት የለዉጥ ብስራትን የሚሹ የትግራይ ልጆች ኤርትራ ካለዉ የተቃዋዊ ሐይል ጋር ያብሩብኛል የሚልም ስጋት ስላለዉ የትግራይ ወጣት ይሰደድ ዘንድም ሁናቴዎችን ሲያመቻች ቆይቷል። ስለዚህ ብዙ የትግራይ ወጣቶች በየመን አድርገዉ በሳዉዲዋ የጀዛን ግዛት ወደ ሳኡዲ በመግባት ወደ ተለያዩ ከተሞች ተበታትነዋል።ለሳኡዲ ባህልና ሐይማኖታዊ ህግ በቂ የስነልቦና ግንዛቤ የሌላቸዉ ወጣቶችም ያገሪቱን ህግ በመጣስ በኢትዮጵያዊነት መለዮ ላይ ቀዉስን ፈጥረዋል የሚል ቅሬታ ይደመጣል።

በተለይ በሪያዷ የመንፉሃ ክፍለ ከተማ በመጠጥና በአደንዛዥ እጽ ህገወጥ ስራ ላይ የተሰማሩት ወጣቶች በህወሃት ፖለቲካዊ እኩይ ተግባር ሰለባ የሆኑ ለመሆናቸዉ መረጃዎች መዉጣት ከጀመሩ አመታት ቢቆጠሩም ችግሩ ገንፍሎ አንባገነናዊዉ የሳኡዲ መንግስት ዜጎቹ ያነጣጠሩበትን የለዉጥ ኢላምን አቅጣጫ ለማስቀየር እስኪጠቀምበት ድረስ ሃይ ባይ አልነበረም።ይህ ጥቂት ኢትዮጵያዉያን የተሰማሩበት ህገወጥ ተግባር ያለ ሳኡዲ የደህንነትና የህግ አስከባሪ ሐይላት ትብብር እዉን ያልሆነ በመሆኑ የሳኡዲ መንግስትም ከተጠያቂነት አይድንም። ሳኡዲ ዉስጥ ካለዉ ኢትዮጵያዊ ቢያንስ ዘጠና ስምንት ከመቶዉ ለፍቶ አዳሪ ሲሆን በጣም ጥቂት የሆነዉ ኢትዮጵያዊ ባቋራጭ እድገትን ፈላጊ የሚሆንበት አጋጣሚ ይታያል።

ስደተኛ ወይም ስራ ፈላጊ የሆኑ ኢትዮጵያዉያን በነቂስ በሳኡዲ ዜጎች  ጥርስ መግባታቸዉ፣መደብደባቸዉ፣መገደላቸዉ፣የአስገድዶ መድፈር ሰለባ መሆናቸዉ የሳኡዲ መንግስት እራሱ ላወጣዉ ያገሩ ህግ  ወይም አለማቀፋዊ ህግ ደንታ የሌለዉ መሆኑን ፍንትዉ አርጎ ያሳያል። የሳኡዲ መንግስት ለፈጸማቸዉ ኢሰብዓዊ ተግባራት ተጠያቂ ከመሆኑም ባሻገር የደም፣የሞራል፣የጉዳትና የሰራተኞችን የልፋት ዋጋ በካሳ መልኩ እንዲከፍል ኢትዮጵያዉያኑ በጋራ ሊሰሩበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ ነዉ።

ኢትዮጵያዉያኑ በሳኡዲ የደረሰዉን ግፍ ለመታደግ በመላዉ አለም ያሳዩት እምርታዊ ተቃዉሞ እሰየዉ የሚያስብል ቢሆንም፤በየሰልፎቹ መሃከል በጥቂት የጥላቻ አቀንቃኞች የታየዉ ጸረ-ኢስላምና ጸረ-አረብ አቋም የኢትዮጵያን ህዝብ በቢሊዮን ከሚቆጠሩ የአላማችን ዜጎች ጋር የሚያጣላ ሃላፊነት የጎደለዉ ተግባር በመሆኑ ከፋፍሎ የሚገዛዉን ህወሃትን ከመጥቀም ባሻገር ፋይዳ አይኖረዉምና ካማረዉ  የአንድነት ማሳ ላይ የጥላቻዉን አረም ማረሙ ተገቢም ነዉ።

ኢራን ከሳኡዲ አረቢያ ጋር ስር የሰደደ ፖለቲካዊና መልከ-አምድራዊ የሆነ ታሪካዊ  ባላንጣነት አላት። እንደ አንዳንድ የሳኡዲ የመገኛና አዉታሮች አገላለጽ በኢራን የተመለመሉ ኢትዮጵያዉያን ደህነቶች በሳኡዲ አረቢያ ዉስጥ ይገኛሉ የሚል ስጋት አለ። ስጋቱን የሳኡዲ መንግስት ሆን ብሎ የፈጠረዉ ሊሆን ቢችልም፤ የራሱን የዉስጥ  ቅዋሜ ለማርገብ የሚኳትነዉ ህወሃት የለዉጥን ብስራት ፈላጊ የሆኑ  ወጣቶችን ለመሰል ተልእኮ አሳልፎ አይሰጥም ለማትም አዳጋች ይሆናል።

ሁለት አንባገነናዊ ስርዓቶች በጥምረት አንባገነናዊ ተዉሳክን ለማስረጽ ሲዳክሩ፤ በመሃል የሚጠቁትን ኢትዮጵያዉያን ለመታደግ ፍቅር፣አንድነት፣ትብብር ያሻልና በሳኡዲ የሚንቆረቀረዉን የወገን እንባ አባሽ እንሁን። ልብ ያለዉ ልብ ይበል!

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles