Gebregziabher Lema /Kitzingen/
የኢትዮጽያ ህዝብ የሞተበት፤ ያዘነበት፤ ፍትህ ያጣበት ፤የተራበበትና የተሰደደበት ግዜአቶች ቢኖሩም አሁን ግን እራሳቸው ከሚያደርሱብን ግፍና በደል በተጨማሪ በባእዳን ሀገራት ተደፍሮና ተነክቶ የማያውቀው ህዝብ አሁን ባለው ስርአት ታሪካችንንና መንነታችንን ለመጥፋት መጠነ ሰፊ ዘመቻ እየተካካሄደብን ነው። ይህ የማንነታችን መደፈር ዛሬ በገሀድ ወጥቶ ሁላችንም እንስማው እንጅ ቀደም ሲል ከእኛ በታች በነበሩ የጎረቤት ሀገራት በነጂቡቲ ፤ሱዳን ና ኬንያ ተዋርደንና ተጠቅተን እንድንኖር ከተደረገ ውሎ አድሮአል ። ዛሬ በኢትዮጽያ ህዝብ ጀርባ ህልውናዋ የቆመው በጂቡቲ እንኮ ኢተዮጺያዊነት ተወርዶ በነሱ ስንገደል ፤ስንታሰር፤ ሴት እህቶቻችን የነሱ መጫወቻ ሲሆኑ፤ ሹፌር ወንድሞቻችን በራሳቸው ላይ በደል ተፈጽሞባቸው እራሳቸው ተቀጭ ፤በንብረቶቻቸው ላይ አደጋ ተፈጽሞባቸው እራሳቸው ከፋይ ፤ግመሎቻቸውና ፍየሎቻቸው ላይ አደጋ ቢደርስ ገና ውደፊት እሰከምትወልደው የልጅ ልጅ እዲከፍሉ በማድረግ ለሚደረገው ህገወጥ ስራወች ሁሉ ለወያኔ አቤት ያልተባለበት ግዜ የለም የገንዘብ ኪሳቸውን ለመሙላት ሲሉ ህዝብን ለባርነት ዳርገውት ይገኛሉ።
ታዲያ ዛሬ ቴወድሮስ አድህኖም ያዞ እንባውን ከየት አመጡት ምን አልበት በሳውዲ መንግስት ከወገኖቻችን አላግባብ የፈሰሰው ደም ፤ በቃየል ላይ እንደ መሰከረበት የአቤል ደም ሆኖባቸው ይሆን ? ወይስ ለሚቀጥለው ምርጫ የቢል ቦርድ ማስታወቂያ ፎቶ እያዘጋጁ ? አዎ ይህ ነው እንጂ ካልሆነማ በስደት በመንገድ ላይ በየኮንተቴይነሩ ለሚያልቁት ፤በሱዳን፤በጂቡቲ፤በየምን ና ኬንያ በባርነት ያሉ ወገኖች ፤ በሀገራቸው በክልላችሁ ሂዱ ተብለው ሀብት ንብረት ካፈሩበትና ወልደው ከዳሩበት አያት ቅድምአያቶቻቸው ለነጻነት አጥትና ደማቸውን ከገበሩበት ሀገርና ቀየ ያንተ አይደለም ተብሎ ሲፈናቀሉ ሌሎች ዘመዶቻቸው እንደጀብድ ሲያወሩት እንደነበር አያውቁም ? ስለዚህ ይህ የውሸት እንባ የኛን አንጀት ያጠነክራል እንጂ የሚያለሰልሰው ፈጽሞ አይሆንም።