Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የሳዑዲ ጉዳይ የዛሬ አዳዲስ መረጃዎች –በነብዩ ሲራክ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከ40 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ገብተዋል ይሉናል፤ የሳዑዲ ባለስልጣናት ደግሞ 28 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ነው ወደ ሃገራቸው የላክነው ይላሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ 13 ሺህ ሰው ከየት ሸቅበው ነው?… ለማንኛውም ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የሚሰጠንን አዳዲስ መረጃዎች ይመልከቱ…

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በፌስቡክ ገጹ እነዚህን አዳዲስ ነገሮች አካፍሎናል፦

* ጅዳ …. ትናንት ከጅዳ ቆንስል አካባቢ ወደ ሽሜሲ ማቆያ እስር ቤት ከሌሊት እስከ ምሽት የሔዱት ወገኖች ቁጥር 1.500 እንደሆነ ታውቋል። መሔዳቸውን ተከትሎ በርካታ የተጨበጡና ያልተጨበጡ መረጃዎች እየተሰራጩ ነው ።
saudi arabia today
በሚቀርቡት ቅሬታዎችን ለማረጋገጥ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እዚያው ሺሜሲ ካሉት ጥቂት እህቶች አነጋግሬ ነበር። የምግብና የውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለና ፣ ምግብ እና ውሃ ሲታድ ጉልበት ያለው ብቻ ተጋፍቶ እንደሚበላ እና እንደሚጠጣ ገልጸውልኛል። የሻንጣ ኪሎውን ክፍያ ጉዳይም ነግረውኛል ። እዚህ ላይ እኔም ግራ የተጋባሁ ቢሆንም በቀጣይ ሰአታት ሁሉም ግልጽ ይሆናል። ምሬታቸውን ግን ለሚመለከታቸው አሳውቄያለሁ። ትልቁ ነገር በአሁኑ ሰአት ሰነዶች እየተሰሩላቸውና አሻራ በወረፋ እየሰጡ መሆኑን ከሃላፊዎች የሰማሁትን ከእህቶች ማረጋገጤ ነው! በአጠቃላይ ጅዳ ያለው ሁኔታ በተሻለ መንገድ መሔድ መጀመሩን ከሚደርሱኝ መረጃዎች ተነስቶ መናገር ይቻላል። ምክርና ዝክሩ ሰሚ ቢያገኝ በሽሜሲ ያለውን ሃይል አጠናክሮ በአጭር ጊዜ የበለጠ መስራት ይቻል ይመስለኛል !

* መካና መዲና … በትናንትናው እለት በመካ “ወደ ሃገራችን እንግባ! ” በሚል ተከስቶ የነበረው ድጥጫና አለመግባባት ዛሬ ገብ ብሎ ታይቷል ። በተመሳይ ሁኔታ በተከሰተው የትናንቱ ፍጥጫ ለየት ያለ እንደነበርና በሁከቱ ምክንያት ሰበብ አጠይባ ዩኒቨርሲቱ ተዘግቶ እንደ ነበር ተመልክቷል።

ሪያድ … ባሳለፍናቸው ስምንት ቀናት 28.000 ኢትዮጵያውን ወደ ሃገር ቤት መሸኘታቸውን የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይህ በእንዲህ አንዳለ በርካታ ኢትዮጵያውያን በየመጠለያው የመጸዳጃ ፣ የምግብና የውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለ ችግሩ በሰፊው እንዳለ ወደሚነገርበት አሚራ ኑራ መጠለያ ስልክ በመደወል ያነጋገርኳቸው ሳይቀር ገልጸውልኛል። በሪያድ ሃላፊዎችን ላማነጋገር ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም ።

* ደማም … ወደ ሳውዲ ሰራተኛ መላክ አቁሟል ቢባልም በኤጀንሲዎች መሰሪ የተቀነባበረ ሴራ ዜጎች ወደ ሳውዲ እየገቡ ነው ። 60 ያህል በአብዛኛው ኦሮምኛ እንጅ ሌላ ቋንቋ የማይናገሩ እህቶች በኩዌት በኩል ወደ ሳውዲ ደማም መግባታቸውንና መኖሪያና የስራ ፈቃድ ለመውሰድ ምርመራ ማከናዎናቸውን መረጃ ደርሶኛል። ወደፊት ዘርዘር አድርገን እናወራዋልን …

ቸር ያሰማን

ነቢዩ ሲራክ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>