Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የሚኒሶታው ሪሳላ ኢንተርናሽናል በምዕራብ አርሲ፣ በኮፈሌና አከባቢዋ መንግስት በሙስሊሞች ላይ የፈጸመው ግድያ እንዳስቆጣው ገለጸ

$
0
0

Risala International
በምዕራብ አርሲ ዞን በኮፈሌና አከባቢዋ በሙስልሙ ማህበረሰብ ላይ የደረሰውን ግደያ እስራትና እንግልት ለመቀወም የወጣ የአቋም መግለጫ፨
ሪሳላ ኢንተርናሽናል ሚኒሶታ
በሃገራችን ሙስሊም ማህበረሰብ የምፈጸምበትን የሃይማኖትና ሰብአዊ የመብት ጥሰት ለመቀወም ሰላማዊ ትግል ከጀመረ ሁለት አመታት ተቆጥረዋል። በዚህ ህደት ዉስጥ ህብረተሰቡ ፊጹም ሰላማዊነቱንና ህጋዊነቱን ጠብቆ ይገኛል።በተቃራኒው የመንግስትን ስልጣን የተቆጣጠረው ወገን በተደጋጋሚ የመብት ጥሰትን ሲያከናዉን ማያቱ የተለመዳ ክስተት ሆኗል ።ከቅርብ ግዜ ወዲህ መነግስት ተብየው አካል በገርባ፣ በአሳሳ፣በሀረር፣ ያደረሰዉን ግድያና በተለያዩ አካባቢዎች የማፈጸመው እስራትና እንግልት ከመጠኑ ያለፈና በመህበረሰባችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል። በሙስሊሙ የቀረበው ህጋዊና ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ ግልጽ እና በቀላሉ ምላሽ ሊሰጠው የሚገባው ሆኖ ሳላ በመንግስት እየተገበረ ያለው ግን ወደማይፈለግ ግጭትና ያለመረጋጋት አቅጣጫ የሚወስድ እጅግ አሳዛኝና ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው። በአሁኑ ወቅት በምዕራብ አርሲ በኮፈሌና አከባቢዋ የበርካታ ሙስሊም ወገኖቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሞት የአካል ጉዳትና እንግልት በመንግስት ታጣቂ ሀይሎች መፈጸሙ እጅጉን አስቆጥቶናል።
ይህም የስርዓቱን ማንነት ለመላው ዓለም በግልጽ የሚያሳይ ነው።እኛም በሚኒሶታና አካባቢዋ የምንገኝ ሙስሊሞች ይሄን አሰቃቂ ተግባር በጥብቅ እያወገዝን ሰላምና ዲሞክራሲ ወዳድ የሆኑ ወገኖች ሁሉ ይህን ኢሰብኣዊ ድርጊት ከጎናችን ሆነው እንዲቀወሙ ጥሪኣችንን እናቀርባለን። በተጨማሪም የሀገርን ሉዓላዊነትን ለማስከበር የተዋቀረው የመከላከያ ሰራዊት በወገኑ ላይ በዚህ መልኩ መዝመቱን አጥብቀን እናወግዛለን።
በዚህ የግፍ ጭፍጨፋ ህይወታቸውን ያጡትን ሰመዕታት(ሸሂድ)ወገኖቻችንን በከፍተኛ ሀዘን እየዘከርን ፈጣሪ አላህ ነፍሳቸውን በጀነቱል ፍርደውስ እንድያኖርልን እንጠይቃለን።ለሟችና ተጎጂ ቤተሰብን ፈጣሪ አላህ መጽናናቱን እንድሰጥልን እንለምናለን።በዚህ አጋጣሚ ይህን መሰረታዊ የሀይማኖት መብት ለማስከበር እየታገላ ላሉት ወገኖቻችን የሚያሳየው የአላማ ጽናትና ቆረጥነት ከልብ አርክቶናል።ህዝባዊ ትግሉንም በተገቢ ስልትና ድሲፕሊን እየመራ ያለው ድምጻችን ይሰማ በሚሰጠው በሳል አመራር አድናቆታችን ከፍተኛ ነው።በመጨረሻም ሪሳላ ኢንተርናሽናል በመንግስት ስልጣን ለያዘው አካልና ለመላው ማህበረሰባችን የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል።
• ያላ አግባብ በግፍ የተገደሉ ወገኖቻችንን አስመልክቶ የግድያ መንስኤና ፈጻሚ በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ በአጥፍወች ላይ ህጋዊ እርማጃ እንድወሰድ አጥብቀን እንጠይቃለን።
• በሙስሊሙ ላይ በዘመቻ መልክ የተከፈተው ግድያ፣እስራት፣ግርፋት፣የእምነት መዕከል የሆነውን መስጊድ መድፈር፣ያላ ህጋዊ ፈቃድ የግለሰብ ቤት መፈተሽ፣ወዘተ የመሳሰሉት ህገወጥ ድርጊቶች ቤስቸኳይ ቁመው ህብረተሰቡ በነጻነት እምነቱን እና እለታዊ ኑሮውን እንዲመራ እንዲደረግ አበክረን እናሳስባለን።
• ያላ አግባብ የታሰሩት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮምቴ አባላት በተለየዩ የሀገሪቱ ክልሎች በስፋት የታገቱ ሙስሊሞች በሙሉ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በነጻ እንድፈቱ እንጠይቃለን።
• የሙስሊሙ ማህበረሰብም የጀመረውን ሰላማዊ የመብት ማስከበር ትግል ድምጻችን ይሰማ በሚያስተላልፈው በሳል አመራር በመከተል አጥብቆ እንዲገፉበት እያሳሰብን ለዚህም የፈጣርያችን እገዛ እንዳይለየው የዘወትር ጻሎታችን ነው።
• በውጭ የምንገኝ ሙስልሞች ከመቼውም ግዜ ይበልጥ በኣንድነት ተቀናጅተን ስልት በመንደፍ ተጨባጭ ተግባራትን ማከናወን የሚገባን ስለሆና በአላህ ስም ለሁሉም ወገን የትብብር ጥሪኣችንን እናስተላልፋለን።
ኢስላም የሰላም ሀይማኖት ነው።
አንድነታችን ሀይላችን ነው።የህዝብን ሰብኣዊ መብት በግፍ ግድያና በማሸበር ማፈን አይቻልም።
መንግስታዊ አሸባሪነትን እናወግዛለን።
በሃይማኖት ጉዳይ አሁንም የመንግስት ጣልቃ ገብነት ይቁም።
አላሁ አክበር አላሁ
አክበር አላሁ ኣክበር !!!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles