Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Hiber Radio: በኢትዮ- ኬኒያ ድንበር ላይ ውጥረት ነግሷል

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ህብር ሬዲዮ ዕሁድ   ነሐሴ 5 ቀን 2005 ፕሮግራም

<<…በቤኒን መስጊድ ተቃውሞ ላይ ተሳትፌያለሁ።ባንዲራ ያቃጠለ የለም።የሰሩት የተቀነባበረ ድራማ ነው።ያቆሙት የተሰበረ ታክሲ ሁሉ ድራማ ነው።ፊልሙን ልብ ብሎ ላየው በአንዋር መስጊድ ከተቀረጸ ተቃውሞ  ሆን ተብሎ የተቀናበረ  ነው። ሕዝቡ ሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ ተንኮላቸውን ተረድቷል። የሸሪያ መንግስት ይቋቋም ብሎ የጠየቀ የለም።የተጠየቀው ቀላል  ጥያቄ ነበር።ቀላል መልስ ነው ያለው። ይሄ ሁሉ ሽብር አያስፈልገውም…  በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ በርካታ ንጹሃን ላይ ጉዳት አድርሰዋል።በሺህ የሚቆጠሩ ታስረዋል።የኔም  አባትና ወንድሜ ታስረዋል።ይሄ ግፍ ነው።ይንን ሁሉም ሊቃወመው ይገባል…መጅሊሱ ውስጥ መንግስት ያስቀመጣቸው አንዳንዶቹ ለሕይወታችን ፈርተን እንጂ እየተደረገ ያለውን አንደግፍም የሚሉም አጋጥመውኛል…>>

አቶ አክመል ሸሪፍ የቬጋስ የሙስሊሞች ኮሙኒቲ ዋና ጸሐፊ በቅርቡ ከአገር ቤት እንደመጡ ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<<…እኔም ትራይቮን ማርቲን ነኝ  ብዬያለሁ። ለሴነተሮች፣ለኮንግረስ ይሄ ራስን መከላከል በሚል ከለላ የተቀመጠ ሕግ እንዲሻሻል የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ጠይቄያለሁ። የሟቹን ምስል የያዘ ካኔተራ ለብሼ በአደባባይ አዎ እሄዳለሁ። የሚደግፉም ደስ የማይሰኙም አሉ…>>

የሎስ አንጀለስ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ኢኢዮ አሜሪካውያን የመብት ጥሰት ሲያዩ ዝምታ አያዋጣም ይላሉ(ቆይታ አድርገናል)

ሙጋቤ በዓለም ላይ ረጅም ዘመን ስልጣን ላይ ያሉ መሪ ናቸው።33 ዓመት ስልጣን ይዘው በ89 ዓመታቸው ለአምስት ዓመት ተመርጫለሁ ብለዋል። የአፍሪካ አምባገነኖች የተለማመዱት የሚመስለው የምራባውያን ወቀሳዎች እና የአፍሪካውያን አቻዎቻቸው ተራ ሽመንገላዎችን እያስተናገዱ ነው። የሳቸው ተመርጫለሁ ማለትን ተከትሎ የተጀመረው የቃላት ጦርነት ወደ ከፋ ደረጃ ይቀጥል ይሆን? (ልዩ ዘገባ)

ተጨማሪ ቃለ መጠይቆች ተካተዋል

ዜናዎቻችን

በኢትዮ- ኬኒያ ድንበር ላይ ውጥረት ነግሷል

ኬኒያ አራት ፖሊሶቿን በታጣቂዎች ጥቃት አጣች

በኢትዮጵያ ሰሞነኛው እስራት ወደ ጋዜጠኞቹም ዞሯል

ሁለት ጋዜጠኞች ከሙስሊም ጉዳዮች ጋር በተያያዘ አ/አበባ ውስጥ ታሰሩ

በሙስሊሙ ህ/ሰብ ላይ እየተወሰደ ያለው የሀይል እርምጃ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተቃውሞ አስከትሏል

በአፈሳ ከታሰሩት ውስጥ ጥቂቶች እየተለቀቁ ነው

በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ፎቶ ግራፎች ይፋ መሆን ቀጥሏል

በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ የቬጋስ ታክሲ አሽከርካሪዎች ይግባኝ ውድቅ ሆነ

አንድነት በአዲስ አአበባ የተሳካ ሕዝባዊ ስብሰባ አደረገ

የታሰሩ አባሎቹና አመራሮቹ በፖሊስና ደህንነቶች ጫና በሀሰተኛ ክስ ላይ እንዲፈርሙ እየተገደዱ ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉን


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>