የ1986ቱ የዓለም ዋንጫ ኮከብ አርጀንቲናዊው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ዮርዳኖስን በጎበኘበት ወቅት በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቋል፡፡ በቅርቡ የተካሄደው የፌፋ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ የሚወዳደሩትን ዮርዳኖሳዊውን ልዑል አሊ ቢን አል ሁሴን ድጋፍ ለማሰባበሰብ ወደ ዮርዳኖስ አምርቶ የነበረው ማራዶና ከ24 ዓመቷ እጮኛው ሮኮ ኦሊቫ ጋር በመሆን መጠመቁን ተዘግቧል፡፡
የ24 ዓመቷ የማራዶና እጮኛ ኦሊቫ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ስትሆን ወደ ዮርዳኖስ መግባታቸውን ምክንያት በማድረግ እየሱስ ክርስቶስ በተጠበቀበት ወንዝ አብረው እንዲጠመቁ ማድረጓ ተገልጧል፡፡ የ54 ዓመቱ ጎልማሳ ማራዶና እ.ኤ.አ በ1986 የሜክስኮው የዓለም ዋንቻ ላይ በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ላይ በእጁ ያገባትን ጎል ‹የእግዚአብሔር እጅ› ብሎ መሳለቁን ተከትሎ በእንግሊዛውያን ዘንድ ጥርስ እንደተነከሰበት ሲሆን በዮርዳኖስ ባደረገው ጎብኝት ወቅት ወደ እንግሊዝ ለማምራት የነበረውን እቅድ መሰረዙ ታውቋል፡፡
ከሰሞኑ፡- ቁም ነገር መፅሔት 14ኛ ዓመት ቁጥር 205 ግንቦት 2007 ፡፡
The post Sport: ማራዶና በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ appeared first on Zehabesha Amharic.