Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሳዑዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የሚፈጽሙ “ነብሰ ገዳዮችን”ትፈልጋለች

$
0
0

በአንድ ዓመት ውስጥ በ15 ሚልዮን ሙስሊሞች የምትጎበኘው ነዳጅ ላይ የተኛችው ሃገር ሳውዲ አረቢያ ከሠሞኑ የዓለማችን
ትልቁን ሆቴል ልትገነባ መሆኑን ሰምተናል፡፡ መካ ከተማ ውስጥ የሚገነባውና አብራጁ ኩዳይ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሆቴል 10 ሺህ መኝታ ክፍሎች ይኖሩታል፡፡ 70 ሬስቶራንቶች አሉት፡፡ 2.25 ቢሊዮን ፓውንድ ወጭ ይደረግበታል፡፡
saudi
ወግ አጥባቂዋ ሀገር የዓለማችን ትልቁን ሆቴል ልትገነባ መሆኑን ስንሰማ ተገርመናል፡፡ ለምን ቢሉ ሳውዲ አረቢያ እንደሌሎቹ ሀገራት በነጻነት የመዝናናት መብትን ለሁሉም ነዋሪዎች የምትሠጥ አይደለችም፡፡ ሃብታም ዜጎቿ እንኳ ወደ ውጭ ሀገራት ሄደው መዝናናትን የሚመርጡ ናቸው፡፡

የሆቴሉ ግንባታ ጉዳይ የሰሞኑ ትልቅ ርዕስ ሆኖ በመገናኛ ብዙሀን ሲነገር ነበር፡፡ ይሁንና ከዚህ ሁሉ በላይ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘው ሃገሪቱ በየዓመቱ በፍርድ ቤቶቿ እያስወሰነች በሰይፍ የምትቀላቸው ሰዎች ቁጥር መበርከቱ ነው፡፡ ይሄን ተከትሎም የግድያ ተግባሩን የሚፈጽሙ ሰዎችን ለመቅጠር ማስታወቂያ እያስነገረች ነው፡፡ 8 በሰይፍ አንግ የሚቀሉ እና እጅ የሚቆርጡ ሰዎች ይፈለጋሉ፡፡
በሸሪያ ህግ የምትተዳደረው ሳውዲ አረቢያ እ.ኤ.አ በ2014 ፍርድ ቤቶቹ ባሳለፉት ውሳኔ መሠረት ወንጀለኛ የተባሉ 87 ሰዎችን አንገት በሰይፍ ቀልታለች፡ ፡ ከሠሞኑ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ደግሞ በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ የተገደሉት ሠዎች ቁጥር ገና ካሁኑ 88 ደርሷል፡፡ ይህ ሁኔታ እንደአምነስቲ ኢንተርናሽናል ያሉ የሠብአዊ መብት ተሟጋቾችን በእጅጉ ያሳሰበ ይመስላል፡፡ ደርጅቱ በይፋ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡

የሳውዲ አረቢያ መንግስት የውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በሠጠው መረጃ መሠረት ከ88 ሰዎች መካከል መጨረሻ ላይ የተገደሉት ሁለቱ ሠዎች አዋድ አልሮዋ እና ላፊ አልሻግሪ ይባላሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ግለሰቦች የተገደሉበት ምክንያት አምፌታማይን የተባለ አበረታች መድኀኒት ሲያዘዋውሩ በመገኘታቸው ነው፡፡ መሀመድ አልሺሂሪ የሚባል ሌላም ሰው በሰው መግደል ወንጀል ተፈርዶበት አንገቱ ላይ ሰይፍ አርፏል፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደጻፈው በዚህ ዓመት ከተገደሉት ሰዎች መካከል አነጋጋሪ የነበረው የኢንዶኖዥያዊቷ የቤት ሠራተኛ ሲቴ ዘይናብ ጉዳይ ነበር፡፡ የአዕምሮ ህመም እንዳለባት የተገለጸችው ዘይናብ በሰው መግደል ወንጀል ተጠርጥራ ከተፈረደባት በኋላ አንገቷ በሰይፍ ተቀልቷል፡፡ ይሄን ተከትሎ የሃገሯ መንግስት ከሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ቁጭ ብሎ ተነጋግሯል፡ ፡ የተፈጸመው ድርጊት ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ተቃውሞ አሰምቷል፡፡

በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ ከሚፈጸምባቸው ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው፡፡
በዚህ ዓመት ከተገደሉት 88 ሰዎች ውስጥ 8 የመናውያንና 10 ፓኪስታናውያንን ጨምሮ የሶርያ፣ ዮርዳኖስ፣ ማይናማር፣ ፊሊፒንስ፣ ህንድ፣ ቻድ፣ ኤርትራና ሱዳን ዜጎች ይገኙበታል፡፡

አምነስቲ ባወጣው መረጃ መሠረት እ.ኤ.አ በ2014 ብቻ በመላው አለም የሞት ፍርድ የተፈጸመባቸው 607 ሰዎች ናቸው፡፡ ከነዚህ መካከል 289 የሚሆኑት የሞት ፍርድ የተፈጸመባቸው ቻይና ውስጥ ነው፡፡ ሰሜን ኮርያ፣ ኢራን፣ ሳውዲ አረቢያና አሜሪካ በየአመቱ ብዙ ሰዎች የሞት ፍርድ ከሚፈጸምባቸው ሀገራት ውስጥ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡ ፡
በአጠቃላይ በ2014 ብቻ 22 ሀገራት የሞት ፍርድን ተፈጻሚ አድርገዋል፡፡ በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ አፈጻጸም የሚከናወነው ህዝብ በተሰበሰበበት በሰይፍ አንገትን በመቅላት ሲሆን በአብዛኛው ክስ ከሚቀርብባቸው ሰዎች መካከል ምህረት የሚደረግላቸው አይኖርም፡፡

በሳውዲ አረቢያ ህግ መሠረት ምህረት የማይደረግላቸውና በቀጥታ ለሞት ፍርድ የሚዳርጉ ወንጀሎች ተብለው የተቀመጡት አደገኛ እጽ ማዘዋወር፣ አስገድዶ መድፈር፣ ሰው መግደልና ከባድ የዝርፊያ ወንጀል፣ ወዘተ ናቸው፡፡
መቀመጫውን በርሊን ያደረገው በአውሮፓ የሳውዲ ሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት የተባለ ተቋም እንደሚለው ብዙዎቹ ሠዎች ወንጀል የሚፈጽሙት በድህነት ምክንያት ነው፡፡ በተለይ አደገኛ ዕጾችን በማዘዋወር ወንጀል የሚከሠሡና የሞት ፍርድ የሚተላለፍባቸው ሰዎች አብዛኞቹ የገንዘብ ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ ፍትሃዊ ያልሆነ የሃብት ክፍፍል ሌላኛውና መሠረታዊው የሳውዲ አረቢያውያን ፈተና መሆኑ ይነገራል፡፡ ሞት ከፊታቸው ቆሞ እንኳ ወንጀልን ለመፈጸም አይግደረደሩም፡፡

ይህ ጽሁፍ በቁምነገር መጽሔት ላይ ታትሞ ከወጣ በኋላ ለዘ-ሐበሻ የተላከ ነው::

The post ሳዑዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የሚፈጽሙ “ነብሰ ገዳዮችን” ትፈልጋለች appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>