Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አሊ አብዶ ክፉኛ የሚጠላው ‹አበበ ቀስቶ›› በኤርሚያስ ለገሰ አይን

$
0
0

በዳዊት ስለሞን

አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዩች ሚኒስትር ዴኤታ የመለስ ‹‹ትሩፋቶች››በማለት በሰየመው መጽሐፉ ዛሬ በወህኒ ቤት ስለሚገኘው የኢድአፓ አመራር ክንፈ ሚካኤል (አበበ ቀስቶ)እንዲህ ብሏል፡፡ አበበ በሽብርተኝነት ተከሶና ፍርድ ተላልፉበት በዝዋይ ወህኒ ቤት ይገኛል፡፡በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ቆይታው በደረሰበት ድብደባ የቀኝ ጆሮው ጉዳት የደረሰበት መሆኑና ህክምና እንዳያገኝ መደረጉ ከዚህ ቀደም መነገሩ አይዘነጋም፡፡መንፈሰ ጠንካራ ስለ ነበረውና በቀረበለት ገንዘብ ሳይደለል ለህሊናው ዘብ በመቆሙ የሚያከብረው ኤርሚያስ አበበን አስታውሶታል፡፡
abebe kesto
————–
ይህ ደግሞ የክንፈ ሚካኤል (አበበ ቀስቶ )ታሪክ ነው
አበበ ቀስቶ ገራሚ ሰው ነው፡፡በካድሬነት ዘመኔ ኢህአዴግን የሚንቅ እንደሱ አጋጥሞኝ አያውቅም ፡፡ብዙሃኑ በፍራቻ አቁማዳ ውስጥ ተደብቆ በነበረበት ሰዓት ኢህአዴግን በአደባባይ በመቃወም ፣ሌቦችን በማጋለጥ ፋና ወጊ ነበር፡፡ስለብዙዎቹ ባለስልጣናት የማያውቀው ሚስጥር የለም፡፡በምርጫ 92 በተቃራኒ መስመር ብንሰለፍም መቀራረብ ፈጥረን ነበር፡፡
ብዙ ነገሮችን አጫውቶኛል፡፡በሂደት ሳጣራው የተጋነኑ ነገሮች ቢኖሩም አብዛኞቹ ትክክል ነበሩ፡፡
በተለይ የህዝቡን ስሜት ከማንበብ አንጻር ከፍተኛ ብቃት ነበረው፡፡ቀበሌዎችን በቁጥር እየጠራ ፣‹‹በዚህ ታሸንፉኛላችሁ ፣በእነዚህ ደግሞ በዝረራ አሸንፋለሁ››ይለን ነበር፡፡እያደር የአበበ አሸናፊነት ፍንትው ብሎ ወጣ፡፡ከምርጫው ፉክክር ገለል የሚልበት አማራጮች ታሰቡ፡፡እሱን ማስፈራራት የሚታሰብ አልነበረም፡፡ምድር ቢንቀጠቀጥ የሚፈራ ሰው አይደለም፡፡በቁጥጥር ስር ለማዋል ደግሞ ወንጀል ሲሰራ እጅ ከፍንጅ መያዝ አለበት፡፡ስለዚህ የቀረው የመጨረሻ አማራጭ በገንዘብ መደለል ሆነ፡፡
ለመደለያ የሚሆን ገንዘብ ማግኘት አስቸጋሪ አልነበረም፡፡እናም ከዶክተር ቶፊቅ አምሳ ሺህ ብር ተመደበለት፡፡አግባብተው እንዲሰጡት ደግሞ ዳኛ ልኡልና ኪሮስ ተመራጭ ሆኑ፡፡ሁለቱ ሰዎች ገንዘቡን ይዘው አበበን ማግባባት ቀጠሉ፡፡እያደር ለኢህአዴግ የምርጫ ኮሚቴ ተስፋ ሰጪ መልእክቶች መደመጥ ጀመሩ፡፡
ምርጫው ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀረው አበበ ውሳኔውን አሳወቀ‹‹የተጋበዝኩትና ብራችሁን የተጠቀምኩት እናንተ ጋር የማይነጥፍ የብር ማምረቻ ስላለ ነው፡፡ምርጫ የምወዳደረው ግን ለገንዘብ ሳይሆን ይህን አስከፊ ስርዓት ለመጣልና ለነጻነቴ ነው፡፡በዚህ ላይ ለመደራደር ህሊናዬ አይፈቅድም››፡፡
አበበ ተወዳደረ ግን አሸንፎ ተሸነፈ፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ አበበ የህዝብ ብሶት የሚያመው ትንታግ ታጋይ ነበር፡፡ከጅማ ሰፈር እስከ ሜክሲኮና ስድስት ኪሎ በእግሩ እየሄደ የሚያስተጋባ ፡፡አበበ የህዝብ አይንና ጆሮ ነበረ፡፡የነዋሪውን ምሬትና እንግልት በአደባባይ የሚያጋልጥ ፡፡አበበ የኢህአዴግ ካድሬዎችን ንቅዘት እየተከታተለ የሚያጋልጥ አሸባሪ ነበር፡፡
የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበረው አሊ አብዶ ከሚፈራቸው ሰዎች አንዱ አበበ ቀስቶ ነበር፡

The post አሊ አብዶ ክፉኛ የሚጠላው ‹አበበ ቀስቶ›› በኤርሚያስ ለገሰ አይን appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>