Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት የታሪክ ምሁሩን ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል አዲስ መፅሃፍ እንዳያስመርቁ አዳራሽ መከልከሉ ታወቀ

$
0
0

BBN Breaking News
ሰበር ዜና ቢቢኤን ሰኔ 4/2007
ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት የታሪክ ምሁሩን ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል አዲስ መፅሃፍ እንዳያስመርቁ አዳራሽ መከልከሉ ታወቀ
መፅሃፉ በጃሊያ አዳራሽ ረመዳን 4 ፣ ሰኔ 14/2007 ይመረቃል::

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባልና የታሪክ ምሁር አቶ አደም ካሚል የ27 አመታት የጥናት ውጤታቸውን አስመልክቶ የፃፉት አዲስ መፅሃፍ በሀገር ፍቅር ቲያትር አዳራሽ ለማስመረቅ ሙሉ ዝግጅታቸውን የጨረሱ ቢሆንም ሀገር ፍቅር ቲያትር ውሉን በማፍረስ ከእምነት ጋር የተያያዙ መፅሃፎችን በአዳራሻችን አናስመርቅም በሚል ተልካሻ ምክኒያት የታሪክ ምሁሩ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው መፅሃፍ እንዳይመረቅ ማድረጉ ታውቋል።

ሀገራችን ኢትዮጲያ በአለም ከሚያስጠሯትና ከሚያኮሯት ታሪኳ ለነብዪ ሙሃመድ (ሰአወ) ሶሃቦች መጠለያ መስጠቷ ፣ ይህ የሁሉም ኢትዮጲያዊ አኩሪ ታሪክ ሁኖ እያለ ቲያትር ቤቱ እንዳይመረቅ መከልከሉ አሳፋሪ ተግባር ነው ተብሏል። የታሪክ ምሁሩ አህመዲን ጀበል የታሪክ መፅሃፍ በዚሁ ቲያትር ቤት መመረቁ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን ቲያትር ቤቱ ለምን እንከለከለ አልታወቀም። ይሁንና የረዳት ፕሮፌሰር መፅሃፍ በጃሊያ አዳራሽ በእለተ እሁድ በጃሊያ አዳራሽ እንደሚመረቅ ታውቋል። ማንኛውም ኢትዮጲያዊ በምረቃው ላይ መገኘት እንደሚችል ታውቋል።

The post ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት የታሪክ ምሁሩን ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል አዲስ መፅሃፍ እንዳያስመርቁ አዳራሽ መከልከሉ ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>