Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሰብለ ዲትሪች (ሚሚ ሾ) የግድያ ምርመራ አንድ ሰው ታሰረ * ምርመራውን ሲያደናቅፍ ቆይቷል ተብሏል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኦንላይን ላይ እንዲሁም በኢቢኤስ ቴሌቭዥን “ሚሚ ሾው” የሚል ከፍታ ወገኖቿን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ስታገለግል የከረመችው ሰብለ ዲትሪች (ሚሚ) ለኦንታሪዮው ገልፍ ፖሊስ መጥፋቷ ሪፖርት የተደረገው ጁላይ 10 2014 ነበር::
Sebele Mimi
የሰብለ መጥፋትን ሪፖርት ያገኘው ፖሊስ የጠረጠራቸውን ሁሉ ሲመረምር ቆይቷል:: ትናንት ማክሰኞ ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ከአንድ ዓመት በኋላ በሰብለ ግድያ የተጠረጠረ ግለሰብን ከሷል:: ፖሊስ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይኸው ከዚህች ኢትዮጵያዊት ግድያ ጋር በተያያዘ የተከሰሰው ግለሰብ በተለያዩ ጊዜያት የፖሊስን ምርመራ ሲያደናቅፍ ቆይቷል::

የ39 ዓመቷ የካፊቴሪያ ባለቤት ሰበለ የ 3 ልጆች እናት ነበረች::
ፖሊስ አሁንም በዚህች ኢትዮጵያዊት ግድያ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ እንደሚፈልግ አስታውቆ የስልክ ቁጥሮችን አስቀምጧል:: ቲና ራያንን በስልክ ቁጥር 519-824-1212 ext 7329 ወይም ራስዎን ደብቀው መረጃ መስጠት ከፈለጉ Crime Stoppersን 1-800-222-TIPS ማግኘት ትችላላችሁ::

The post በሰብለ ዲትሪች (ሚሚ ሾ) የግድያ ምርመራ አንድ ሰው ታሰረ * ምርመራውን ሲያደናቅፍ ቆይቷል ተብሏል appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>