Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: ጃክ ዊልሼር ከዕድሜው በላይ በስሏል

$
0
0

– ግን ሲጋራ ለምን ያጨሳል?
– ለልጆቹ ከፍተኛ ፍቅር አለው

የትንሹ ጃክ ማርሻል ፀሐይ እየጠለቀች ነበር፡፡ በምድር ላይ የሚያሳልፈው ጥቂት ጊዜ ቀርቶታል፡፡ ሳምንታት ቢበዛ ወራት፡፡ አንድ ታዳጊ እግር ኳስ ተጫዋች ወደ ሌላኛው ዓለም ለመሄድ እየተዘጋጀ ላለው ልጅ የተወሰነ ምቾት ሰጠው፡፡ ለተጨነቁ ወላጆቹ መጠነኛ እፎይታ አስገኘላቸው፡፡ በ2011 ጃክ ዊልሼር እራሱ ገና ታዳጊ ነበር፡፡ ተግባሩ ግን ብስለት እና ርህራ ተገልፆበታል፡፡ ድርጊቱ በየትኛውም ዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ አብዛኞቹ ሰዎች በላይ ነበር፡፡
ዊልሼር የልጁን አሳዛኝ ታሪክ የሰማው (ከማርሻል) እናት ነው፡፡ ገና ስድስት ዓመቱ ቢሆንም በአዕምሮ ካንሰር እየተሰቃየ ነበር፡፡ ዌይን ሩኒ እና ሪዮ ፈርዲናንድን የመሳሰሉ ሌሎች እግር ኳስ ተጨዋቾችም ለልጁ ርህራ አሳይተዋል፡፡ ፊት ሊነሱት የማይቻል በእግር ኳስ ፍቅር የወደቀ ተወዳጅ ልጅ ነው፡፡ ዊልሼር የቤተሰቦቹን ህመም ለማስታገስ የሚችለውን አድርጓል፡፡
jack arsenal

ወደ ለንደን ጋበዛቸው፡፡ በቤቱ ቆይተው ደጅ ላይ የፍም ጥብስ ተቋደሱ፡፡ በኢምሬትስ ተገኝተው ጨዋታ የሚከታተሉበትን ምቹ አጋጣሚ ፈጠረ፡፡ በዚያ አይነቱ ሀዘን እና ህመም አቅራቢያ መቆየት ቀላል አይደለም፡፡ ብዙዎች ከዚህ ያለፈ ነገር አይፈፅሙም፡፡ ዊልሼር ግን ያንን ማድረግ አልመረጠም፡፡ በስከንቶርፕ ወደሚገኘው የማርሻል መኖሪያ ቤት ያለመቋረጥ እየሄደ ጠይቆታል፡፡ ቤተሰቦቹ ስለማርሻል ህመም ግንዛቤ ለመፍጠር ያደረጉትን ዘመቻ አግዟል፡፡ የትንሹን ማርሻል ታላቅ ወንድም ልጆች በትምህርት ቤት ሊተናኮሉት ሊረዳው ወደ ስሜት ተጉዟል፡፡ በአካባቢው በሚገኝ መናፈሻ ከጆሽ ጋር አብሮ ኳስ በመጫወት የተተናኮሉት ልጆች ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ጋር ወዳጅነት ያለው መሆኑን እንደሚመለከቱ አድርጓል፡፡

ከዚህ በኋላ በተከተሉት ዓመታት ብዙ ለውጦች ተከስተዋል፡፡ ዛሬ ላይ ዊልሼር 23 ዓመት መልቶታል፡፡ የሁለት ልጆች አባት ሆኗል፡፡ የባለፀጎች መንደር በሆነው ሄርትፎርድሻዬር በሚገኘው ቤቱ የፊት በር ወደ ውስጥ ሲዘልቁ በመጀመሪያ ወደ ዓይንዎ የሚገባው ልጆቹ ወደ ደረጃዎች ለመውጣት እንዳይሞክሩ የሚከለክል ጠንካራ የደህንነት በር ነው፡፡ አርኪዮ የሶስት ዓመት ልጅ ነው፡፡ ደሊላ ደግሞ ከአምስት ወራት በኋላ ሁለት ዓመት ይሞላታል፡፡ በሌላ ክፍል ደግሞ ጎኑ ላይ ስማቸው የተፃፈበት የመጫወቻ አሻንጉሊቶችን የያዘ ሳጥን ይገኛል፡፡

አማካይ በዓለም ዋንጫ ተሰልፏል፡፡ አንፀባራቂ ተሰጥኦ ታድሏል፡፡ ፈጣን እግሮች አሉት፡፡ ኳስ የሚቆጣጠርበት እና የሚያቀብልበት መንገድ ድንቅ ነው፡፡ ወደፊት ገስግሶ የመሄድ አቅም እና እይታው የእንግሊዝ ተስፋ ሆኖ እንዲቀጥል ይረዳዋል፡፡ ምንም እንኳን ተደራራቢ ጉዳቶች እድገቱን ቢያስተጓጉልበትም የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሮይ ሆጅሰን ተቀዳሚ ምርጫ ነው፡፡

የውድድር ዘመኑን የጀመረው ተስፋ ሰጪ በሆነ መንገድ ነበር፡፡ ሆኖም የማንቸስተር ዩናይትዱ ፓዲ ማክኔይር የወረደው የዘገየ ሸርተቴ ለቁርጭምጭሚት ጉት ዳረገው፡፡ አርሰን ቬንገር በመጪው ክረምት ይሸጡታል የሚል ጭምጭምታ አለ፡፡ ነገር ግን ረቡዕ ዕለት ሰንደርላንድን ሲገጥሙ ከስድስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ተካትቶ ቀርቧል፡፡ በመጪው ቅዳሜ በኤፍ.ኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ አስቶን ቪላን ሲገጥሙ በቋሚነት በሚሰለፉት 11 ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ ለመግባትም ጠንክሮ እየሰራ ነው፡፡
‹‹ባለፉት ሶስት እና አራት ዓመታት ብዙ ተለውጬያለሁ፡፡ አርኪዬን ሳገኝ 19 ዓመቴ ነበር፡፡ ሰዎች የልጅ አባት ለመሆን ዝግጁ አይደለህም ይሉኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ለ19 ዓመት ወጣት የልጅ አባት መሆን ትልቅ ነገር ነበር፡፡ በየዕለቱ ወደ እግርኳስ ሜዳ እሄድ ነበር፡፡ የሚያስጨንቀኝ ነገር አልነበረም፡፡ በድንገት የምንጨነቅለት ወንድ ልጅ አገኘሁ፡፡ እንድትበስል ይረዳሃል፡፡ 19 ዓመት ልጅ ሳለሁ የምኖረው ከወላጆቼ ጋር ነበር፡፡ ሕይወቴን የምመራው ቀለል አድርጌ ነበር፡፡ ሳላስበው ስለ ልዳ መጨነቅ ጀመርኩ፡፡ ከዚያም ከእናታቸው ጋር ተለያየን፡፡ ይህን ጊዜ ህይወት ሙሉ በሙሉ ተቀየረ፡፡ ልጆቼን በምን ያህል ጊዜ ላገኛቸው እንደምችል ጥሩ ስምምነት ላይ ደረስን፡፡ ከልጆቼ ጋር የማሳልፈው ጊዜ በሳምንቱ ውስጥ እጅግ ምርጡ ነው፡፡››

በዘመናዊ እግርኳስ ተጫዋቾች ህይወት ስለ እነርሱ በሚታሰበው እና በእውነታው መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ ይህ የተለመደ ታሪክ ነው፡፡ ዊልሼር ለዚህ ጥሩ አብነት መሆን ይችላል፡፡ እራሱን በአግባቡ እንደማይጠበቅ ተገልጿል፡፡ የማይጨበጥ ፀባይ ያለው ወጣት ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡ በምሽ ክበቦች እና በመዋኛ ገንዳዎች ዙሪያ በሚሚጋጁ ፓርቲዎች ላይ የማይጠፋ አመለ ብልሹ እንደሆነ ተለፍፏል፡፡ ከቡድኑ ለእረፍት በተለየ ወቅት ሲያጤስ ታይቷል በሚል ክፉኛ ተብጠልጥሏል፡፡ በጣም በቅርቡ ደግሞ የሼሻ ዕዛ ይዞ የሚያሳይ ፎቶግራፍ መውጣቱ ብዙ አነጋግሯል፡፡
Jack arsenal2

እውነታው ግን ዊልሼር ከዕድሜው በላይ በሳል መሆኑ ነው፡፡ ሁልጊዜም እንደዚህ ነበር፡፡ አባቱ አንዲ ቁም ነገረኛ እና አሳቢ ሰው ነው፡፡ ዊልሼርም ከእርሱ አይለይም፡፡ ምናልባት ይሄ በስፋት ከሚታወቀው የተጫዋቹ ገፅታ ጋር አይጣጣም ይሆናል፡፡ ነገር ግን በአብዛኛው የእግርኳስ አፍቃሪ የሚታወቅበት መንገድ ከእውነታው የራቀ እና አሳሳች ነው፡፡

እውነታው ግን ዊልሼር ከዕድሜው በላይ በሳል መሆኑ ነው፡፡ ሁልጊዜም እንደዚያ ነበር፡፡ አባቱ አንዲ ቁም ነገረኛ እና አሳቢ ሰው ነው፡፡ ዊልሼርም ከእርሱ አይለይም፡፡ ምናልባት ይሄ በስፋት ከሚታወቀው የተጫዋቹ ገፅታ ጋር አይጣጣም ይሆናል፡፡ ነገር ግን በአብዛኛው የእግርኳስ አፍቃሪ የሚታወቅበት መንገድ ከእውነታው የራቀ እና አሳሳች ነው፡፡

የአብዛኞቹን የፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች አይነት ህይወት ይመራል፡፡ ውብ ቤት አለው፡፡ የፑል መጫወቺያ እና መሰል ነገሮችን የያዘ የወንዶች ክፍል በቤቱ ሰገነት ላይ ይገኛል፡፡ በክፍሉ ግድግዳ ላይ የዓለማችን ታላላቅ ተጨዋቾች በአንድ ወቅት ለብሰዋቸው የነበሩ ማልያዎች ተሰቅለዋል፡፡ የተወሰኑ ምርጥ መኪኖች አሉትት፡ ነገር ግን እዩኝ እዩኝ አይልም፡፡ ግልፍተኛ አይደለም፡፡ አይለፈልፍም፡፡ በአንድ ቃል ምላሽ መስጠትን አይጠላም፡፡ ቁጥብ ነው፡፡ ጠያቂው እንዲለፋ ያስገድዳል፡፡ የሚናገረው ቃላት በጥንቃቄ እየመረጠ ነው፡፡ በአብዛኛው ንግግሩ የሆነ አይነት ቅኔ እና ዜማ ይነበብበታል፡፡

በመጪው ክረምት ለማንቸስተር ሲቲ ሊፈርም ይችል የሚለው ጭምጭምታ ምን ያህል እውነት ነው? የሚል ጥያቄ ቢቀርብለት ለመመለስ አልጣደፈም፡፡ ሜሱት ኢዚል፣ አሮን ራምሴይ፣ ሳንቲ ካዞርላ እና አሌክሲስ ሳንቼዝን በያዘው የአርሰናል አማካይ ክፍል እርሱን እንደ ትርፍ በመቆጠር አርሰን ቬንገር ሊሸጡት አስበዋል መባሉም ያስጨነቀው አይመስልም፡፡ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የመክፈቻ ዕለት በአርሰናል እሆናለሁ ብለህ ታስባለህ? የሚል ጥያቄ ሲሰዘነር ለጥቂት ሰከንዶች አስበና ‹‹አዎን›› የሚል ምላሽ ሰጠ፡፡ ራሂም ስቴርሊንግ በሊቨርፑል የተከተለውን መንገድ የሚደግምበት ምንም አይነት ዕድል የለም፡፡ የሊቨርፑሉ ተጨዋች ሊቨርፑልን ለመልቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ልብ በሉ፡፡ የዊልሼር አቋም ፈፅሞ የተለየ ነው፡፡ ከክለቡ ጋር እንደተቆራኘ ያስባል፡፡ ከዘጠኝ ዓመቱ ጀምሮ በአርሰናል ነበር፡፡ ‹‹የሚሸጡኝ ከሆነ ቅስሜ ይሰበራል፡፡ አርሰናል እንዲፈልገኝ እፈልጋሁ፡፡ የማይፈልገኝ ከሆነ ስሜቴ እጅግ ይጎዳል፡፡ ለሌላ ክለብ መጫወት እንግዳ ስሜት ይፈጥራል፡፡ በውሰት ወደ ቦልተን ሄጄ ተጫውቼያለሁ፡፡ ግር የሚል ስሜት ይፈጥራል፡፡

‹‹አሁን ለመጫወት ዝግጁ እንደሆንኩ ይሰማኛል፡፡ ይህ መቼም ቢሆን አይለወጥም፡፡ የውድድር ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት ተጨማሪ ደቂቃዎችን መጫወት እፈልጋለሁ፡፡ ከዚያም እስከ መጪው የውድድር ዘመን ሊከሰት ስለሚችለው ነገር አስባለሁ፡፡ አሰልጣኙ ለእኔም ሆነ ለቡድኑ ምን አይነት እቅድ እንዳለው ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ የመድፈኞቹ አማካይ አስተያየቱን ይቀጥላል፡፡
Jack-Wilshere

‹‹ለዋናው ቡድን መጫወቴን መቀጠል እፈልጋለሁ፡፡ በፕሪሚየር ሊግ እና በቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ መሆንም እሻለሁ፡፡ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አካል ሆኜ መቀጠል ምኞቴ ነው፡፡ ያ መሆን ካለበት በክለብ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ይኖርብኛል፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ሌሎች እንግሊዛውያን አማካዮች ድንቅ ብቃት በማሳየት ላይ በመሆናቸው ቦታዬን አስከብሬ ለመቀጠል ጠንክሬ መሥራት አለብኝ፡፡

‹‹መላ ምቶችን ማስቆም አይቻልም፡፡ ከአሰልጣኜ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ፈፅሞ አልተነጋገርንም፡፡ በጭራሽ ሃሳቡን አላነሳብኝም፡፡ እኔም ያልኩት ነገር የለም፡፡ ስለ እኔ መፃኢ ጊዜ መወራት የጀመረው በጉዳት ላይ በነበርኩበት ወቅት ነው፡፡ ትኩረቴን ሰብስቤ ወደ ቀድሞ ብቃቴ ለመመለስ ጠንክሬ እሰራለሁ››

ዌልሼር ስለ ኦዚል የሚናገረው ፊቱ ፈክቶ ነው፡፡ እርሱ ሲጫወት መመልከት ያስደስተዋል፡፡ በጫና ውስጥ በሚሆንበት ወቅት የሚያሳየውን የሚያስገርም የተረጋጋ መንፈስ ያደንቃል፡፡ ‹‹በበርካታ ተጨዋቾች ተከብቦ እንኳን ቀና ብሎ በተረጋጋ መንፈስ አማራጮችን ይፈልጋል›› በማለት እንግሊዛዊው ለቡድን ጓደኛው ያለው ክብር ይገልፃል፡፡ በቀጣዩ የውድድር ዘመን አርሰናል ለዋንጫ የሚፎካከር ቡድን ይሆናል የሚል ተስፋም ሰንቋል፡፡

‹‹ባለፉት ጥቂት የውድድር ዘመናት ዋነኛው ችግራችን የስነ ልቦና ነበር፡፡ ትልልቅ ቡድኖችን ለመግጠም ስናመራ ማሸነፍ ለመቻላችን እንጠራጠር ነበር፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን ብዙ ለውጥ ታይቷል፡፡ በግልፅ ምክንያቱ ይህ ነው ለማለት ይቸግረኛል፡፡ ምናልባት ልዩነቱን የፈጠሩት ወደ ቡድኑ የቀላቀልናቸው አዳዲስ ተጨዋቾች ይሆናሉ፡፡ ስብስቡ ረዘም ላለ ጊዜ አብሮ መቆየቱ እና የተወሰነ ወርልድ ክላስ ተጨዋቾች ቡድኑን መቀላቀላቸው የፈጠረው ተፅዕኖ ሊሆን ይችላል፡፡ እየበሰልን ነው፡፡ ፕሪሚየር ሊጉንም በተሻለ ተገንዝበነዋል፡፡ በተለይ በትልልቆቹ ጨዋታዎች ላይ ከፍተኛ መሻሻል አሳይተናል››

ከቬንገር ጋር ያለው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ያምናል፡፡ ይበልጥ እየጠኘከረ እንደሚሄድም ተስፋ ያደርጋል፡፡ ‹‹በእርሱ ስር ለመጀመሪያ ጊዜ ልምምድ የሰራሁት በ14 ዓመቴ ነው›› በማለት ዌልሼር አጋጣሚውን ያስታውሳል፡፡ ‹‹ለረዥም ጊዜ እንተዋወቃለን፡፡ አጨዋወቱ እንዴት እንደነበር ልጠይቃቸው እና በታማኝነት ሐቁን ሊነግሩኝ ከሚችሉ ጥቂት ሰዎች አንዱ እርሱ ነው፡፡ በእኛ መካከል ድብብቆሽ የለም፡፡ እንተማመናለን፡፡ መጫወት ስለምፈልግበት ቦታ በግልፅ እንነጋገራለን፡፡ እንደማስበው እንደምንጊዜው ይተማመንብኛል፡፡ ያንን እምነት ጠብቄ ማቆየት አለብኝ፡፡››

ዌልሽር ለእረፍት ላስ ቬጋስ በነበረበት ወቅት ሲጋራ ሲያጨስ የሚያሳይ ፎቶ መውጣቱ የአርሰናሉን አለቃ አላስደሰተም፡፡ ሆኖም የ23 ዓመቱ ተጨዋች አጪያሽ አለመሆኑን ክለቡ ያምናል፡፡ ዊልሼር ስለጉዳዩ የሚከተለውን አስተያየት ይሰጣል፡፡ ‹‹ወቀሳውን እቀባላለሁ፡፡ ጫናውን ተቋቁሜ ማለፍ የምችልበትን መላ አውቄያለሁ፡፡ ማድረግ የማይገባኝን ነገር በመፈፀሜ የጋዜጦች ርዕስ ስሆን የመጀመሪያ ጊዜዬ አይደለም፡፡ በሜዳ ላይ የማሳየው አቋም ሙሉውን ታሪክ እንዲናገር ማድረግ ተክኜበታለሁ፡፡ ነገር ግን ለቤተሰቦቼ ፈታኝ ነው፡፡ እያጨስክ የተነሳኸው ፎቶ ይፋ መውጣት በዓለም እጅግ አስከፊው ነገር አይደለም፡፡ ነገር ግን እንደ ፕሮፌሽናል አትሌት እና ታዳጊዎች እንደ አርአያ የሚመለከቱኝ ተጨዋች እንደመሆኔ ያንን ማድረግ አልነበረብኝም፡፡

‹‹ይፋ የሚወጡ አንዳንድ የእግርኳስ ተጨዋቾች ፎቶግራፎች በቅርብ ወዳጆች የተነሱ መሆናቸው ያስታውቃል፡፡ ባለፉት ሰባት ዓመታት ባለመተማመን ምክንያት በርካታ ሰዎችን አጥቼያለሁ፡፡ በአሁኑ ወቅት እንደ እውነተኛ ጓደኞች የምቆጥራቸው ሰዎች ከአራት ወይም ከአምስት አይበልጡም፡፡ ግራ ትጋባለህ፡፡ በዙሪያ ያሉትን ሰዎች ልታምናቸው ይገባል፡፡ ቤተሰቦቼን፣ ወንድሜን እና የተወሰኑ የቅርብ ሰዎችን ከአጠገቤ አድርጌያለሁ፡፡ የምትቀርባቸውን እና አብረሃቸው የምታሳልፋቸውን ሰዎች መምረጥ ይኖርብሃል፡፡››
ዊልሼር የጉዳት ታሪኩ ያለፈ መሆኑን ያምናል፡፡ ቁርጭምጭሚቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጎዳው ሰውነቱ ገና እያደገ በነበረበት ወቅት በደረሰበት ጫና ነው፡፡ ሆኖም ዳንኤል አገር እና ማክኔይር የፈፀሙት ጥፋት ለባስ ችግር እንደዳረገው አይካድም፡፡ ነገር ግን ያን ያህል የሚያስጨንቀው ድክመት የለበትም፡፡

‹‹አጨዋወቴን መቀየር እንዳለብኝ የሚገልፁ ፅሑፎችን አንብቤያለሁ፡፡ ብዙ መሮጥ እና ለፍትጊያ መጋፈጥ ችግር ሊፈጥርብኝ እንደሚችል ተገልጿል›› ዊልሼር ማብራራቱን ይቀጥላል፡፡ ‹‹ያንን ባደርግ እንደ አሁን አይነት ተጨዋች አልሆንም፡፡ ታዳጊ እያለሁ መጀመሪያ ጋጣመኝ ጉዳት ለስምንት እና ዘጠኝ ወራት ከሜዳ ስርቅ በተመሳሳይ ደረጃ መጫወት እችል ይሆን? እያልኩ አስብ ነበር፡፡ በዚያ ውስጥ ካለፍኩ በኋላ በትጋት ወደ ቀድሞ ብቃቴ መመለስ እንደምችል ተገንዝቤያለሁ›› በማለት አማካዩ ከተሞክሮ ያገኘውን ልምድ ያካፍላል፡፡

መጪው ዘመን ምን ይዞለት እንደሚመጣ ባያውቅም ዊልሼር በተጫዋችነት ዘመኑ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡ ሊያስብበት ተዘጋጅቷል፡፡ ሊያጣጥመው ቆርጧል፡፡ እጅግ የሚኮራበት ነገር ምን እንደሆነ ሲጠየቅ ለአፍታ እንኳን አላመነታም፡፡ ‹‹ልጆቼ›› አለ፡፡ ‹‹የ17 ወይም 18 ዓመት ልጅ ሳለሁ ከእግርኳስ በላይ እጅግ አስፈላጊ ነገር ያለ አይመስለኝም ነበር፡፡ ለቀድሞው የአርሰናል የቡድን ጓደኛዬ ሴባስቲያን ስኩላቺ ሁልጊዜም እግር ኳስን ከሁሉም ነገር በላይ አስቀድማለሁ እንዳልኩት አስታውሳለሁ፡፡ የእርሱ ምላሽ አይዘነጋኝም፤ ልብ በል… ከምንም ነገር በላይ ልጆችህን ታስቀድማለህ አለኝ፡፡ እስክታጣጥመው ድረስ ልትገነዘበው አትችልም፡፡ እንደዚያ አይነቱ ፍቅር ስለመኖሩም አታስብም›› በማለት ሃሳቡን ያጠናቅቃል፡፡

The post Sport: ጃክ ዊልሼር ከዕድሜው በላይ በስሏል appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>