በስደት ላይ የሚገኘው ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በባልቲሞር ሜሪላንድ 41ኛው ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሲኖዶሱ ያወጣው መገለጫ ይጠቁማል።በዚሁ መገለጫ ላይ ሲኖዶሱ ራሱን አይሲስ ብሎ በሚጠራው ቡድን የተሰዉትን ወጣቶች የኢትዮጵያውያን ሰማዕታት በሊቢያ ምድር መሰየማቸው እንደዚሁም ቤተሰቦቻችው እርዳታ የሚያሰባስብ በሊቀ ጳጳስ የሚመራ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ያስረዳል። በተጨማሪም በዚህ የፈተና ወቅት መለያየቱ እንደማይበጅ አስረድቶ ራሳቸውን በገለልተኛነት መድበው የሚንቀሳቀሱ አብያተ ክርስቲያናትን ከህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር አብረው እንዲሰሩ ጥሪ ያቀርባል።
ይህ በእንደዚህ እንዳለ ራሱን ለህጋዊ ሲኖዶስ ተቆርቋሪ በማስመሰል ግን ህጋዊውን ሲኖዶስ ላይ ማህበራዊ ሚዲያ መርዝ የሚረጭ ወጣት አሉባልተኛ ከወደ ላስቬጋስ ብቅ ብሏል።በሳውዝ አፍሪካ የወያኔ ኤምባሲ ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ የነበረው ጉደኛ ወደ ላስቬጋዝ ብቅ ብሎ ጃኬቱን ገልብጦ የወያኔ ተቋዋሚ የሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ደጋፊ ሆኖ ተገኝቷል። ህጋዊ ሲኖዶስ ደግሞ የሚደግፈው በሲኖዶሱ ጥላ ስር ሆነው በመላው ሰሜን አሜሪካ፣በአውሮፓ፣በአውስትራልያና በአፍሪካ እየተዘዋወሩ የተሰደደው ኢትዮጵያውያንን እንደዚሁም ህጋዊውን ሲኖዶስ በትጋት የሚያገለግሉትን የወንጌል ገበሬዎችን በመሳደብና በማዋረድ እንደዚሁም ህጋዊ ሲኖዶስ ያልወሰነውን ውሳኔ በማንበብ ነው።በተጨማሪም ሕጋዊው ሲኖዶስ የገንዘብ አያያዝን አስመልክቶ ብክነት እንዳለ የሀሰት ወሬዎችን በማሰራጨት ነው። ዓይናችሁን ጨፍኑ እናሞኛችሁ ነው ነገሩ።
ወያኔ በዘመናችን የኛ የምንለው ነገር እንዳይኖረን የቤት ስራውን ጨርሷል። የኛ የምንላቸውን ተቋሟት ሰርጎ በመግባት ከፋፍሏል፣ የኛ የምንለውን ሲኖዶሱንም እየተጋለ ይገኛል፣ የሲኖዶስን ዓይን የሆኑትን የስደተኛውን አባቶች እያሳደደ ይገኛል። በዚህ ወቅት ነው አክቲቪስትና ጋዜጠኛ አበበ በለው መሰረቱን ዋሽንግተን ዲሲ ባደረገው የሬዲዮ አገልግሎት ይህንን ነገር ተከታትሎ ያጋለጠው። የመለስ ትሩፋት ጸሃፊ አቶ ኤርሚያስ እንዳሳሳበን ወያኔ ወጣቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት አሰልጥኖ የሃሰት መረጃ በማቅረብ የአንድነት የኢትዮጵያ ሃይሎችን መከፋፈል ዓይነተኛ ምግባራቸው ነው። በመሆኑም የበግ ለምድ ለብሰው የመጡትን የወያኔ ጀሌዎች እንደ አበበ በለው በየማእዘኑ እናጋልጣችው። ለማንኛውም ጋዜጠኛ አበበ በለው ከሁለት የኃይማኖት አባቶች ጋር ያዘጋጀው ፕርግራም እነሆ ተከታተሉት።
The post የአዲስ ድምጽ ሬድዮ አዘጋጅ ጋዜጠኛ አበበ በለው የወያኔ ማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊትን አጋለጠ appeared first on Zehabesha Amharic.