Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የጥረቱ ሂደት ዕድገት፤ # ፬ –አንዱዓለም ተፈራ

$
0
0
ቀን፤     ማክሰኞ፤ ግንቦት ፲፰ ቀን፤ ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት ( 5/26/2015 ) 11፡00 ጠዋት፤ ፓሲፊክ የሰዓት አቆጣጠር
eskemecheአንድ ነገር ጥሩ እየተካሄደ ያለው፤ የመሰባሰቡ አስፈላጊነት በየቦታው ዋና መነጋገሪያ ጉዳይ መሆኑ ነው። ከዚህ አንጻር፤
  • የኢሕአፓ ዴሞክራሲያዊ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ሁለት አባላት መድቦ፤ በቅድመ ዝግጅቱ ላይ ለውውይት ለመሳተፍ ወስነው አሳውቀውኛል።
  • የሸንጎ አባላት በሙሉ ልባቸው ተካፋይ እንደሚሆኑ አሳውቀውኛል።
  • የሽግግር መንግሥት አመራር አባላት ፈቃደኛነታቸውን ከማበረታቻ ቃላት ጋር ልከውልኛል።
  • አብረውኝ እንዲያስተባብሩ ከጠየቅኋቸው መካከል አራቱ ፈቃደኛ ሆነዋል። በአንድነት የሕዝባዊ መገናኛ እስክናበጅ ድረስ፤ ይኼንኑ የኔን የኢሜል አድራሻ ለጊዜው ልንጠቀም ተስማምተናል።
በተጨማሪ፤ ይሄ የመሰባሰብ ጉዳይ የማንም ግለሰብ ሆነ ድርጅት የግል ጉዳይ ስላልሆነ፤
  • ካሁን በኋላ ከማንኛውም ግለሰብም ሆነ የድርጅት ተወካይ ጋር እኔም ሆነ ሌሎች አስተባባሪ አባላት የምናደርገው የስልክም ሆነ ማናኛውም ዓይነት የግንኙነት ልውውጥ፤ ሕዝባዊና ታሪካዊ አስፈላጊነትና ተጠያቂነት ስላለበት፤ የሚቀዳ ነው። የግል ዘመቻ አልያዝንም።
  • የኔን ሆነ የሌሎችን አባላት ማንነት፣ የትምህርት ደረጃ፣ የትግል ተመክሮ፣ የማስተባበር ልምድ ማንም ማወቅ የለበትም። እያንዳንዱ ግለሰብም ሆነ የድርጅት ተወካይ፤ ማወቅ ያለበት፤ ራሱ የሚታገልለትን የግልም ሆነ የድርጅት ዓላማና ግብ፤ ጊዜያዊውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሀቅና የትግል አሰላለፍ፣ አሁን የሚያስፈልገውን ግንዛቤና አጣዳፊ ተግባር ነው። ከዚያ ተነስቶ ነው ማንም ግለሰብ ሆነ ድርጅት፤ ከሌሎች ጋር ሊያደርገው የሚፈልገውን ግንኙነት የሚወስነው። እኛ እንደ አበረታታች እንጂ እንደእንቅፋት መታየት የለብንም።
  • አሁንም ብዙ ግለሰቦች ለኔ ኢሜል እየላካችሁልኝ ነው። አመሰግናለሁ። በያላችሁበትም በመሰባሰብም ሆነ በግል ይሔኑ የመሰባሰብ ጉዳይ ልታራምዱ ይገባል። ሰዓቱ አሁን ነው። መበርታት አሁን ነው።
  • ከግንቦት ሰባት በድርጅት የተሠጠኝ መልስ የለም።
  • ለኢሕአፓ አመራር፤ ተሳታፊ እንዲመድቡ፤ እስካሁን በነበረው ግንኙነት በኩል፤ ጥሪ በዛሬው ቀን እንልካለን።
አሁን፤ የመጀመሪያውን የመግባቢያ ስብሰባ ማድረጊያ ሰዓቱ ነው። መጀመር የግድ ያለበት ጉዳይ፤ “ይጀመራል!” እየተባለ ውሎ ማደር የለበትም። መጀመር አለበት። የምንጀምረው በሚከተሉት ሰዎች ነው። ቀኑ በቅርብ ይወሰናል።
፩ኛ.      አሰባሳቢ ለመሆን ፈቃደኛ የሆኑ አምስት ግለሰቦች፤
፪ኛ.      በግለሰብ ለመገናኘትና ለመሰባሰቡ ፈቃደኛ ሆነ የተገኙ ስድስት አባላት፤
፫ኛ.      ከጊዜያዊው የኢሕአፓ ዴሞክራሲያ አስተባባሪ ኮሚቴ የተወከሉ ሁለት አባላት፤
፬ኛ.      ከሸንጎ አባላት የተወሰኑ ( ቁጥሩ አልተገለጸልኝም )፤
፭ኛ.      ከሽግግር ( ዝርዝሩን ገና አልወሰንም )፤
( ፈቃደኛ ከሆኑ፤ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ የውይይት መድረክም ሆነ የፖለቲካ ስብስብ፤ [EEDN, etc ] ቀርበውና ማንነታቸውን አረጋግጠው ሲገኙ፤ እናስተናግዳለን። )
መመዘኛ ነጥቦቹ፤ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተቀበሉ ናቸው።
፩.  የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋና ጠላት ነው ብሎ የሚያምንና ለማስወገድ የሚታገል፤
፪.  ኢትዮጵያዊያን በሀገራችን የፖለቲካ ሂደት መሳተፍ ያለብን፤ በግለሰብ ደረጃ በኢትዮጵያዊነታችን ተሰባሰቦ ነው፤
፫.  ይህ ትግል ሀገራዊ ስለሆነ፤ ሁላችንም የተካተትንበት አንድ ኢትዮጵያዊ የትግል ማዕከል ያስፈልጋልና እንፍጠር፤
፬.  የኛ ጥረት፤ የሕዝቡን በሀገር ቤት መነሳሳት ለመርዳትና ከጎኑ ተሰልፎ ለድል እንዲበቃና አስተማማኝ እንዲሆን ነው፤
ESKEMECHE

The post የጥረቱ ሂደት ዕድገት፤ # ፬ – አንዱዓለም ተፈራ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>