የቱርኩ የዜና ወኪል ትናንት ዘግይቶ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ በአዲስ አበባ ከሚገኙ 23 ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ በ 16ቱ የድምጽ ቆጠራው ተጠናቆ ይፋ መደረጉን ተናግሯል፡፡ የምርጫ ቦርድ ምንጮቼ ነገሩኝ ያለው መረጃው በዚህ ቆጠራ ሂደትም ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል በ 70 ከመቶ እየመራ እንደሚገኝ ነው ይፋ ያደረገው፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ካሉ ምርጫ ጣቢያዎችም እንደሚሰማው ከሆነ ገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ሀገሪቱን መምራቱ የተረጋገጠ ይመስላል ሲል ነው የዜና ምንጩ የተናገረው፡፡
The post ኢህአዴግ በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል በ 70 ከመቶ ድምጽ እየመራ መሆኑ ተነገረ appeared first on Zehabesha Amharic.