Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሃያአራት አመት ጊዜ ያለወጠው አዙሪት! ከአዙሪት ለመውጣት .. (ምንሊክ ሳልሳዊ)

$
0
0

tplfበሕወሓት የበላይነት የሚተዳደረው የኢሕአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ ላለፉት ሃያአራት አመታት እጅግ ከፍተኛ ወንጀሎችን በሕዝብ ላይ በመፈጸም ንጹሃንን በማሰር ሰርቶ አገር ሊለውጥ የሚችለውን ትውልድ በማሰደድ እምቢኝ ያሉትን በመግደል…በተከታታይ እና በተደጋጋሚ በሚፈጽማቸው አሰቃቂ ግፎች ስልጣን ላይ ለመቆየት በሚያደርገው ትንቅንቅ እጅግ ዘግናኝ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል በዜጎች ላይ ፈጽሟል እየፈጸመ ነው::ወንጀል መፈጸሙ ሳያንሳ የራሱን የደም እጆች በሌሎች ላይ ለማቀባባት በመሞከር ራሱን ነጻ ለማውጣት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ቢረጭም አልተሳካለትም::

እያንዳንዳችን ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ቆም ብለን ልናስብበት የሚገባ እድሎችን በመተቀም ለዘላቂ መፍትሄ ራሳችንን በማዘጋጀት እንዲህ አይነቱን አምባገነን መንግስት ልናስወግድ ይገባል::እስከዛሬ በሰቀቀን እና በ እ ህ ህ ያሳለፍነው ዘመናችን ችግሩ ማነው ብለን ልናጤነው እና ችግሩን በዘላቂነት ልናስወግድ የዜግነት ግዴታችን ነው::የወያኔው ስርአት በፈጠረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ግድፈት ሕዝቦች በከፍተኛ ደረጃ በኑሮ ውድነት ከመሰቃየታቸውን አልፎ ጥቂት የባለስልጣናት እና የዘመዶቻቸው ቱጃርነት የብዙሃን ድህነት ሲንሰራፋ ሙስና የስር አቱ ዋና መገለጫ መሆኑ የአደባባይ ሃቅ ነው::የኢኮኖሚ ፖሊሲው ኑሮ ውድነትን ብቻ ሳይሆን ስራ አጥነትንም በሰፊው አንሰራፍቷል::የዚህ ስራ አጥነት የፈጠረው ችግር ትኩሱን የስራ ሃይል ወደ ሰው አገር ከመሰደዱም በላይ ከፍተኛ ብሄራዊ ውርደትን አስከትሏል::

በመላው ኢትዮጵያ መብራት፣ ውሃና ኔትወርክ የለም የለም ብቻ ሳይሆን ላለመኖሩ ሰበብ ከሚፈጥር ውጪ ችግሩን የሚፈታ መንግስት የለም::በመላው አገሪቱ በተለይ በከተሞች አከባቢ የመንግስት ሰራተኞች ተማሪዎች የግል ተቀጣሪዎች በትራንስፖርት ችግር እየተንገላቱ ነው:ለዚህም መፍትሄ የሚሆን ነገር የሚያመጣ መንግስት ስለሌለ ሕዝቡ ራሱን እያስተዳደረ መሆኑ እሙን ነው::በጉልበት የሕዝብን ስልጣት ይዞ አለቅም ያለ ፓርቲ የመልካም አስተዳደር ችግር በመፍጠሩ ሕዝብ አቤት የሚልበት እና ችግሩን የሚፈታበት ቦታ በማጣቱ ቤቱ ተቀምጧል::በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ነጻ ሚዲያዎች በነጻነት መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ግማሹ ለስደት ግማሹ ለእስር ግማሹ ለሞት ግማሹ ሰርቶ እንዳይበላ ተደርጎ በአምባገነኖች ተኮላሽቷል::ተቃውዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሁኑ የሲቭክ ማህበራት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሚፈለገው መልኩ በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻሉም::ይህ ሁሉ የፈጠረው የስር አቱ ፖሊሲዎች በርካቶችን ለሞት እና እስር እንዲሁም በርካታ ዜጎች ህይወታቸውን ለአደጋ በሚዳርግ መልኩ እየተሰደዱ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ለቁጥር የሚታክቱ ምሬቶችና አቤቱታዎች ከየአቅጣጫው በየጊዜው ይሰማሉ፡፡

ያለው ስርአት በሃገር እና በሕዝብ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን በፍጹም እንደማይፈታ የታወቀ ነው::ከመፍታት ይልቅ በሰበብ እና በሌሎች ላይ በመላከክ ስለተጠመድ የህዝብን አቤቱታ መስማት በፍጹም ፍቃደኛ ባለመሆኑ ባለፉት 24 አመታት ባለበት ዛቢያ እየዞረ ምንም ነገር ስላለወጠ ካለ አዙሪት ለመውጣት የወያኔን የሰከረ ፖለቲካዊ ስርአት በሰበብ እና በሌሎች ላይ የሚላከኩ ጉዳቸውን አሸክሞ ከኢትዮጵያ ማስወገድ ችላ ሊባል የማይገባ ወሳኝ ወቅት ላይ ስለሆንን አፋጣኝ እርምጃዎችን በመውሰድ በሕዝባዊ አመጽ በአንድነት ስርአቱን ታግለን ልናስወግድ ግዴታ አለብን::

The post ሃያአራት አመት ጊዜ ያለወጠው አዙሪት! ከአዙሪት ለመውጣት .. (ምንሊክ ሳልሳዊ) appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>