“አትቀስቅሱኝ!”
በምዕራብ ዲሲ አቅጣጫ ማለዳ ላይ ስናልፍ ከወደጥግ አንድ ኩርምት ብሎ የተኛ ሰው አይናችን ገባ። በ50ዎቹ አጋማሽ የሚገመት ሃባሻ ወገን ነው። አቶ አምሳሉ ይባላል። የውስጡን ጉዳት ገፅታው ያሳብቃል።
..አንድ ልጅ ካፈራችለት የ30 አመት ፍቅረኛው ወይም የትዳር አጋሩ ያላሳበው በደል እንደተፈፀመበትና ለጐዳና ህይወት እንደዳረገው ይናገራል። ብዙም ማውራት የማይፈለገውና ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ የሚታይበት አቶ አምሳሉ ከባለቤቱ ጋር ያለያያቸው ድንገት በአደጋ የተገኘ ጠቀም ያለ የኢንሹራንስ ገንዘብ እንደሆነ ይናገራል። አሜሪካ ያስመጣቸው የባለቤቱ እህትና ወንድም እንዲሁም አንዲት ዘመዷ አባሪና ተባባሪ በመሆን እንዲሁም «ሊገድላትና ሊደፍራት ሲል አይተናል» ብለው በሃሰት በመመስከር ትዳሩን እንደበተኑትና በቁም እንደገደሉት ይገልፃል። የ21 አመት ልጁ በአባቱ በተፈፀመው በደል ተበሳጭቶ ሌላ ከተማ ሄዶ እንደሚኖርና የት እንዳለ እንደማያውቅ አምሳሉ ይጠቁማል።
« የ30 አመት ፍቅሬ ሊደፍረኝ…አለችኝ። ይገርማል! ጭራሽ ሊገድለኝ አለች!..በ30 አመት አንድ ቀን እጄን አንስቼባት አላውቅም! አንድ ቀን ሌላ ሴት ጋር ሄጄ አላውቅም! አሳሰረችኝ። አስፈረደችብኝ። ህይወቴን አመሳቀለችው» በሃዘን ስሜት ተወጦ ..ተመልሶ ለመተኛት ያደፈች አንሶላውን ወደፊቱ ጣል እያደረገ « እባካችሁ ተውኝ! አትቀስቅሱኝ! ሞቻለሁ!..»
The post በ30 ዓመት የትዳር አጋሩ የተነሳ በዋሽግንተን ዲሲ የጎዳና ተዳዳሪ ለመሆን የበቃው ኢትዮጵያዊ appeared first on Zehabesha Amharic.