በእጃችን ያለውን መፍትሄ ወደ ጎን በመተው ተቃራኒ ፆታን ለመማረክ አቅሙ ጎድሎን ከሆነ ከራሳችን ውጪ ማንንም ተጠያቂ ማድረግ አንችልም፡፡ የፍቅር ግንኙነታችንን ከሚወስኑና ተቃራኒ ፆታን የመማረክ ደረጃችንን ማሳደግ ከሚረዱን መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል ጊዜና አቅሙ በሚፈቅድልን መጠን አካላችንን በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማጎልበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ በእርግጥ ፍቅርና እርስ በርስ መተሳሰብ የግንኙነት ማጠናከሪያ መሰረታዊ ነጥቦች መሆናቸውን የዘነጋ አይደለም ምክረ ሐሳባችን፡፡ ይልቁንም ከፍቅረኛና የትዳር አጋር ጋር የሚደረግን ጉዞ ጥርጊያውን የሚያበጅ እንደሆነ በማሰብ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት ዓብይ ጉዳያችን ፍቅር፣ ወሲብ፣ ልጅ፣ ገንዘብ እና ዕድሜን ስለሚወስነውና ሴቶችን ወንዶች ስለተሰሩበት ልዩ ቀመር ከምርምር ሐሳቦች በመነሳት አንባቢዎች ያሉበትን ቦታ እንዲመለከቱ ያስቻለ ሐሳብ ቀርቧል፡፡ በቀረበው ጽሑፍ ከአብባቢያን ለደረሱን ገንቢ ሐሳቦች በማመስገን ወደ ልዩ ቀመሩ የሚመራንን ምክረ ሐሳብ እንድናመለክታቸው ጠይቀውናል፡፡
ወንዶች ለሴቶች የመከታነታቸውና፣ የወንዳ ወንድነታቸው ውጤት የሆነው ወርቃማው ቁጥራቸው 1.6 መሆኑን ባለፈው ሳምንት ተመልክተናል፡፡ ለፆታ ተጣማሪያቸው መከታና አጋርነታቸው ማሳያ ተደርጎም የተወሰደ ሲሆን፣ መለኪያው ወንዱ የወንዱ ፆታና ባህሪ እንዲኖረው የሚያደርገው የቴስቴስትሮን ሆርሞን ትክክለኛ ምጣኔ በውስጣቸው እንዳለ የሚጠቁም ነው፡፡ በቀረበው ሐሳብ ታዲያ፣ ይህ ቁጥር ትከሻና ደረተ ሰፊ ወንዶች ጋ የመገኘት ምጣኔው ሰፊ መሆኑን ነው የተመከተው፡፡
በዚህ ሳምንት ከተፈጥሯዊው አጋጣሚ ውጪ ወደዚህ ቁጥር ሊያመጡን ከሚችሉ መንገዶች መካከል፣ ለወንዶች ብቻ የሚመከረውን የደረት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ቀላል በሆነ መንገድ ማካሄድ የሚችሉበትን መንገድ 12 በሚደርሱ ሐሳቦ ልናመለክታችሁ ወድደናል፡፡
1. ትዕግስት፡- ከመጽሔቶች እና ከተለያዩ ፀሀፍት ጡንቻን ፈጣን በሆነ ሂደት መገንባት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ በርካታ ሐሳቦ ቀርበው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ተግባር መግባትን እንደ አማራጭ ከወሰድን፣ ሂደቱ ዝግመታዊ ስለመሆኑ በቅድሚያ ግንዛቤ መያዝ ያስፈልግዎታል፡፡ ምናልባት የአንድ ዓመት የልፋት ውጤት ይጠይቀናል የሚሉት ባለሙያዎች፣ በዚህ ዓመት አሊያም እየተቃረበ ባለው ሌላኛው ዓመት ትልቅ ደረት ከፈለጉ ልንረዳዎት አንችልም ባይ ናቸው፡፡ ‹‹የትዕግስት ጉዳይ አሳሳቢ ከሆነብዎት ከዚህ ምክረ ሐሳብ ይልቅ 97 ዶላር የሚያስከፍለውን big muscle shortcuts.com›› ፕሮግራምን ቢጎበኙ ያዋጣዎታል፡፡ በአንፃሩ ረዥም ደረት በረዥም ጊዜ መስራትን ከመረጡ ያለምንም ክፍያ ደረተ ሰፊነትና ጠንካራነትን በምን መልክ ማምጣት የሚችሉበትን መንገድ ላሳያችሁ ይሏችኋል ባለሙያዋ፡፡
2. የማሟሟቂያ እንቅስቃሴ ማድረግን አይዘንጉ፡፡ የደረት ስፖርትን በሚያከናውኑበት ወቅት፣ በርካቶች ወንበርና ክብደቶችን መግፋት ብቻውን በቂ እንደሆነ በማሰብ ከፍተኛ ስህተት ይፈጽማሉ፡፡ ምንም አይነት የክብደት መግፋት ስፖርት ውስጥ ተሳትፈው የማያውቁ ሰዎች ሳይቀሩ፣ ፊልሞች ላይ በሚመለከቱት ብቻ እንቅስቃሴውን ማድረግ ላይከብዳቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን ትክክለኛውን መንገድ ላያውቁት ይችላሉ፡፡ ጀማሪዎች ለጤና ጠንቅ በሆነ መንገድ የክብደት እንቅስቃሴ ውስጥ ሊገቡ ሁሉ ይችላሉ፡፡ ቀደም ሲል እንደተቀመጠው በፊልሞች እና በተለያዩ አጋጣሚዎች ሌሎች አካላት ስላደረጉት ብቻ የምንፈልገውን ዓይን ሳቢና ጠንካራ ደረቅ ለማምጣት የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎችን በቅድሚያ ማድረግ ነው፡፡
ባለሙያዋ በዚህ ረገድ ወደ ተግባር የሚገቡ አካላት የደረታቸውን አካባቢ በማቀያየር የማፍታታት ስራዎችን እንዲሁም የመግፋት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማስቀደም እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ፡፡
3. በየቀኑ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ በትከሻቸውና በደረታቸው ላይ የሚሰሩ አካላት ከፍተኛ የግፊት እንቅስቃሴ ስለሚጠይቅ እና በትከሻ ላይ ድካ ስለሚያስከትል፣ ደረታችን ላይ የምንፈልገውን ለውጥ ለማምጣት አቅም እንድናጣ ምክንያት ይሆናል፡፡
4. አቅምዎን ይወቁ፡- ብዙ ሰዎች ትልቅ ደረትን ማምጫው መንገድ የእጅ እና የደረት እንቅስቃሴን በሚል ይደክማሉ፡፡ ግን እንቅስቃሴው ትልቅ ስህተት ተብሏል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ካሉም በፍጥነት ትክክለኛውን መንገድ ይከተሉ ዘንድ ባለሙያዎች ይመክሩዎታል፡፡ ፑሽአፕ ደረትን ለማጠንከር እንኳን በራሱ ተመራጩ ስፖርት አለመሆኑን በማስመር፡፡ የደረት ስፖርትን በማከናወን ተጠቃሚ የሚሆኑ ሁለት አይነት ክፍሎች መሆናቸውን ነው ባለሙያዋ የሚያስቀምጡት፡፡ የመጀመሪያዎቹ ፋት ነክ የሆኑ ምግቦች ተጠቃሚዎች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ አዲስ ገቢዎች የተባሉት ደግሞ በእንቅስቃሴው ውስጥ መሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ጀማሪዎች ናቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ማለትም ፋት ነክ ምግቦችን የሚጠቀሙ ሰዎች፣ በኬሚካል በመታገዝ ከእንቅስቃሴው በቶሎ ለማገገም አቅም የሚፈጥርላቸው ሲሆን፣ ቀጣዩን የደረት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ በተፈጥሯዊ መንገድ በደረት ግንባታ ላይ ከተሰማሩት በላይ ከፍተኛ ዕድል አላቸው፡፡
ሌሎቹ በዚህ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ተጠቃሚ የሚሆኑ ጀማሪዎች መሆናቸው ነው ጥናቱ የሚያመለክተው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ወገኖች በምን አይነት ፍጥነት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው የሚለዩበት ጊዜ ላይ ስለማይደርሱ መሆኑ ነው የተጠቀሰው፡፡
5. የደረት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ጊዜና አቅምዎን በከፍተኛ መጠን ይጠቀሙ፡፡ በርካቶች በዚህ ረገድ ስኬታማ አይደሉም፡፡ በጊዜ ምክንያት እንቅስቃሴውን ከሌሎች የሰውነት አካላቸው ጋር በመቀላቀል አልያም በቂ እረፍት ላያደርጉ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ የቀኑን እንቅስቃሴ በ30 ደቂቃ ውስጥ ለማጠናቀቅ ይጣደፋሉ፡፡ ባለሙያዋ እንደሚሉት ታዲያ በደረት የተፈቀደውን እንቅሰቃሴ በከፍተኛ ትጋት በቀን ከ50-60 ደቂቃ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ትልቅ ደረትን በመገንባት እንቅስቃሴውን በኃይል እና በመጠን በየጊዜው ማሳደግ ይጠይቃል፡፡ በዚህ ሂደት ታዲያ ትከሻን ጨምሮ ሌሎች የሰውነት ክፍሎቻችንን የሚያሰሩ እንቅስቃሴዎችን እንዳይቀላቀሉ ይመከራሉ፡፡ በሁለቱም ወገን ያሉትን የደረት ክፍልዎ እኩል መንቀሳቀሳቸውን ፈጽመው አይዘንጉ ሚዛንዎን ያሳጣዎታል፡፡
6. የሚያነሱትን ክብደትና የጊዜ መጠን ይወስኑ፡፡ ከሳምንት ሳምንትም ከክብደት ለመሸጋገር ቢያንስ 5 ደቂቃ ይውሰዱ፡፡
7. ትከሻዎን ከጉዳት ይከላከሉ፤ ሰውነቱን በስፖርት የሚገነባ ሰው ትከሻውን ከአደጋ የመጠበቅ ያህል ወሳኝ ተግባር የለም፡፡ ለዚህ እንዲረዳም ትከሻን በምናምን መሸፈን ሁለት ጥቅም ይሰጣል፡፡ የመጀመሪያው ሰውነታችን ተረጋግቶ እንዲቆይ ማድረጉ ሲሆን፣ ሌላው ዝቅተኛ የጉዳት ተጋላጭነት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
8. በሚገባ ይመገቡ፡- እንቅስቃሴ ባደረጉበት ዕለት ብቻ ሳይሆን አምስቱን ቀናት በሙሉ፣ ከፍተኛ የፕሮቲን መጠን ያላቸውን ምግቦች መመገብ ያስፈልጋል ይላሉ ባለሙያዎቹ፡፡
9. ብዙ ውሃ መጠጣት፡- በሰውነቱ በቂ ውሃ ያለው በ19% ጥንካሬው እንደሚጨምር ታሳቢ ያድርጉ፡፡ ይሄ ጥንካሬ አለዎት ማለት ተጨማሪ ክብደቶችን በማንሳት ጡንቻዎትን የማጎልበት አቅም ይፈጥርልዎታል ማለት መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ ወደ ጂም እስኪሄዱ ውሃ ካልጠጡ፣ እርስዎ ጊዜዎን እያጠፉ ነው ተብለዋል፡፡ በስፖርት ማዕከሎች የውሃ ኮዳዎችን ተሸክመው እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ያስገርሙናል ነው የሚሉት ባለሙያዎች፡፡ በበቂ ሁኔታ ውሃ በሰውነታችን ውስጥ መኖሩን ለማረጋገጥ፣ ከ15-30 ባሉት ደቂቃዎች ሽንት መሽት ከቻሉና ንፁህ ፈሳሽ ከሰውነትዎ መውጣቱን ማጤን በቂ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ እንቅስቃሴ ከማድረግዎ በፊት በቂ ውሃ መጠጣትዎን በፍፁም አይዘንጉ፡፡
10. እንቅስቃሴዎን ይመጥኑ፡- ግዙፍ ደረትን ለመገንባት በተከታታይነት በመሬት ላይ የደረት ስፖርት ማከናወን ያስፈልጋል፡፡ ይሄ እንቅስቃሴ በቀጣይ የምናደርገውን መጠን ምን ያህል መሆን እንደሚገባው የሚወስንልን ነው፡፡
11. በቂ እንቅልፍ ያግኙ፡- አላርም የሚጠቀሙ ከሆነ በቂ እንቅልፍ እንዳላገኙ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ ከእንቅስቃሴ በኋላ በቂ እንቅልፍ ማድረግ ለውጡን ለማፋጠን ይረዳዎታል እና በተቻለ መጠን በቂ እንቅልፍ ሊያገኙ የሚችሉበትን መንገድ ይምረጡ፡፡
12. የደረት ቅርፅ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ በደረትና በደረትዎ መካከል ክፍተት መኖሩ የሚያስቡትን ግዙፍ ደረት ለመገንባት ይረዳዎታል፡፡ ይታደሉታል እንጂ እንዲሉ፣ በዚህ ረገድ በተፈጥሯዊ መንገድ ደረት የተቸራቸው ሰዎች፣ የሚያስቡትን ደረተ ሰፊነት በቀላሉ መላበስ ዕድል ይፈጥርላቸዋል፡፡
እነዚህ 12 ምክረ ሐሳቦች፣ ወንዶችን ወደ ልዩ ቀመር ሊያመጡ ከሚችሉ መንገዶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት ለሴቶች የተለዩትን ነጥቦች የምናቀርብ ይሆናል፡፡
The post Sport: ወደ ልዩ የወንድነት ቀመር የሚያመጡዎት ነጥቦች፡- ግዙፉ ደረት መገንቢያ 10 ምስጢሮች appeared first on Zehabesha Amharic.