Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

!ይቅናህ! –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

18.04.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

„ምንም፡ እንኳን፡ በለስም፡ ባታፈራ፣ በወይን፡ ሐረግ፡ ፍሬ፡ ባይገኝ፣ የወይራ፡ ሥራ፡ ቢጓደል፣ እርሾችም፡ መብልን፡ ባይሰጡ፣ በጎች፡ ከበረቱ፡ ቢጠፉ፣ ላሞችም፡ በጋጡ፡ ውስጥ፡ ባይገኙ፣ እኔ፡ ግን፡ በእግዚአብሔር፡ ደስ፡ ይለኛል፣ በመዳህኒቴ፡ አምላክ፡ ሐሤት፡ አደርጋለሁ። ጌታ፡ እግዚአብሄር፡ ሃይሌ ነው፤“

/ትንቢተ – ዕንምባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17-19/

እንዴት ሰነበታችሁልኝ የኔዎቹ – ደህና ናችሁን? ትናንት ሲፈናቀል እጅግ ይከፋኛል። ትናንትን የገነባው፤ ዛሬን ያስገኘው የነገም አስኳል ሊሆን የሚችል ዕውነት ጥግ ሲያጣ ወይንም አትኩሮት ሲነፈገው ወይንም በቅጡ ማስተዳደር ሲሳነን – ያርመጠምጠኛል። ስንት ጊዜ ይማጥ ይሆን?

በፈተና ውስጥ አብዝተው ዋጋ የሚከፍሉ የምናፍቃቸውና የምሳሳላቸው ወገኖቼ ከእነሱ በከፋ ሁኔታ ያሉም እንደሉ ልብ ሊሉት ይገባል ባይ ነኝ፤ እኔው ሥርጉተ ሥላሴ። ከሁሉም እጅግ የከፋው ጎምዛዛ ገጠመኝ በሰው እጅ ቁጥጥር ሥር መሆን ነው። በሰው ቁጥጥር ሥርነት ክስ ደግሞ በስውርም በግልጽም ሊሆን ይችላል። በስለላ ወይንም በካቴና። „ለወንጀለኝነቱም“ ሎቶ ስብኃት ስለ ቃሉ፤ ሳቢያ ይፈለግለታል። በዘመነ ናዚ፤ የናዚን ፓሊሲ የተቃወሙ፤ የስድስት ሚሊዎንን አይሁዳዊ ህይወት ቀድመው ለመታደግ፤ ሀገራዊ ታሪካቻውንም ለማዳን ይተጉ የነበሩ „አሸባሪ“ ይባሉ ነበር። ለአዶልፍ ሂትለር እነኛ የሰብዕዊነት ደቀመዝሙሮች በአደባባይ „አሸባሪ“ ተብለው ተወገዘዋል፣ ፍዳ መከራቸውን አይተዋል፤ ደማቸውንም አፍሰዋል። በዘመነ አፓርታይድም የሰላም አባት የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላም „አሸባሪ“ ይባሉ ነበር። በእኛም የሄሮድስ ራዕይ የፈበረከው ዘር የማክሰል ዘመቻዊ አፓርታይዳዊውን፤ ዘመነ ሱባኤ የተቃወሙ፣ የተሟገቱ „አሸባሪ ወንጀለኛ ናቸው“ ምንም እንኳን ለታደሉት ቀና ብሎ ለመናገር እውነት መድፈር የትውልድ ክብርና ጌጥ፤ ልዩ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ አስገኝ ኃይል፤ ልዩ አዲስ ቀለም ቢሆንም፤ ለእኛ ግን እነሱ የተከደኑ ሲሳዮቻችን፣ ታሪኮቻችን፣ ጀግኖቻችን ናቸው። የመንፈስ ሃብታት፤ ሽልማትም!

አብሶ ፋሽስት በነገሠበት ወቅት የነፃነት ቀማኛው አፈጻጸሙ ሴራማ፤ ሥሩም ትብትብ ነው። ስለዚህም በአንድም በሌላም መንገድ በፈተና አጥር ያሉ ወገኖች ከእነሱ እጅግ በባሰ ጥምዝዝ ገጠመኝ ላሉት፣ በፍም ድቅድቅ ውስጥ ለተማገዱት ደሞቻቸው ማሰብ ይገባቸዋል። ልሳናቸውን ወደ ህዝብ ሲልኩ ጥበብ ያስፈልጋቸዋል – ይመስለኛል። ለደራጎን ማመሳከሪያ – መረጋገጫ ገበር ከመሆን በእጅጉ መቆጠብ አለባቸው። እንዲሁም ቀጣይ አቅም ተስፋ አጥ እንዳይሆንም ከልባቸው ሆነው ሊመትሩት ይገባል። ተስፋ – ያውላል – ያሳድራል – ያኖራልና። ተስፋ የማይለቅበት የሩኽ ስንቅ ነው።

በሌላ በኩል ለአማንያን የመንገድ ምርጫ ጌታ መዳህኒት ፈጣሪ አምላክ ስለመሆኑም  „አለሙን፡ ሁሉን፡ ከፈጠረ፡ ከእግዚአብሄር፡ ከህጉ፡ ከሥርዓቱ፡ የወጣ፡ የለም፡ በሰማይ፡ የሚበር፡ ያሞራ፡ ፍለጋ፡ ቢሆን፡ ወደ፡ ወደደበት፡ መሄጃውን፡ እሱ፡ ያዛል።“ / መጽሐፈ መቃብያን ሣልሳ ምዕራፍ 9 ቁጥር 2/። „ … ያሞራ ፍለጋ ቢሆን ወደ ወደደበት መሄጃውን እሱ ያዛል“ ይላል አካል የሌለው የእግዚአብሄር ትጉኽ አገልጋይ ወንጌል፤ እንኳንስ የሰው ልጅ። የነፃነት ቀማኛው ቀንዶና ቁጭሎቹ እጅግ በበረከቱበት፤ ገደብ አልፎ የነፃነት ጥሰቱ አና ባለበት በዛሬው ጊዜ፤ እዳሪ ላይ በግፍ የወደቀ ነፍስ እልፍ በሆነበት ህማማተ – ዘመን፤ ባለቤት ያጣ ህዝብና አፈር – ለባዕቱ በባዕድነት የተገፋ ህሊና የሚችለውን ሁሉ፤ በቻለው መንገድ እንደምርጫው እንዲከውን የፈቀደለት አምላኩ ብቻ ነው። ስለሆነም ግፊያ አያስፈልግም።

ከእንሰሳ በታች ክብሩ ተገፎ በዬሄደበት እዬታደነ የሚቃጠለው ሥጋና ደም ጪስ እረፍት የነሳው ወገን በአሻው መንገድ የድርሻውን ሊወጣ መሰናዳቱ ሆነ፤ ውጤቱን በአግባቡ ቢተረጎም መልካም ነው። „ነፍሴን ለሀገሬና ለህዝቤ ክብር ብሎ ለመማገድ መቁረጥ“ በራሱ የድል ዋዜማ ነው። ለአንድ ነፃነትን ፈላጊ ድርጅት ወይንም ግለሰብ ወይንም ማህበር ሊሆን ይችላል፤ የነፃነት ፍቅረኛነቱን ከእሱ ለዬት ያለ የነፃነትን መገኛ አማራጭ መንፈስን ቢያንስ በህሊናው ጥበቃ የማደረግ አቅሙ ባለቤቱን ይለካዋል። ስለምንስ ምስጋናው ቀርቶበት፤ ሞትን ቆርጦ ለተሸከመ ሰላሙ ይተዋካል? ነፃነቱን ይቃማል? አይገባኝም። እንዲገባኝም – አልፈልግም።

ጤፍ እንጀራ በእርጎ እኔ መች ጠልቼ፤ ? ? ?

ሲበሉ ለማዬት – ፈቃድ ተነስቼ፤ ? ? ?

ጉሮሮ ለማርጠብ እንዲህም  – ተሟሙቼ፤ ? ? ?

በእቃ ተገምቼ – እንደ ዕቃም ታይቼ

ቢቸግረኝ እንጂ፤ —- መች ክብር ጠልቼ!

ቢከፋኝ ነው እንጂ፣ – ዱሩን ተመኝቼ

መጠለያ ከፈን አፈሩን በልቼ

ቅንቅን በቋጠሮ – ዕንባነን አውግቼ።

የነፃነት ፍለጋ መንገድ ሎተሪ አይደለም። ደግሞም ቀኑ ቢረዝምም ሀሰትን ተስፋ ያለደረገ መንፈስ መጨረሻው አሸናፊ ነው። ውዶቼ – የኔዎቹ – ይህን ግጥም ስጸፈው መንፈሴን እያመመኝ መሆኑን ጨምሬ እገልጻለሁ። ህመሙ ሥም የለሽ ነው። ምክንያቱም፤ እንዴት ያደርግሻል? ብባል መግለጽ እችል ዘንድ አልተሰናዳሁምና። ብልህነት ብልጫ ነው። ብልጫው ደግሞ ብርቅነትን – ያሰነብታል። ብርቅነትን ለማዝለቅ ለብዙኃኑ መንፈስ ፅኑ ጠባቂና ጠንቃቃ መሆንን ይጠይቃል። የመንፈስ ሃብት ዕትብታዊ ትቅቅፉ ረቂቅ ነው። አንዱን ሲነኩት ሌላው ይነቃነቃል ወይንም ይናጋል። መስተጋብራዊ ውህደቱ ሰውኛ አይደለም እና። እንደ ተለመደው ቃናው ሆነ ምቱ ሁልጊዜ በአንድ ማስኬድ አይቻልም። ድምጽ ላይ ሲወጣና በልክ ሲጓዝ ወይንም ጥልቀትን ሲመርጥ የሙዚቃ ባህሬ ብቻ ሳይሆን ዓይነቱም ሆነ መደቡ ይለወጣል። ባለሮኩ እንደ ባለሀገረሰቡ፤ ባለሀገረሰቡ እንደ ፖፑ፤ ባለፖፑም እንደ ቴክኖ ወዘተ … አያስኬዱትም። ፍቅር አብሶ የህዝብ ፍቅር ጥሩ አስተዳዳሪነትን ይሻል። በስተቀር – ይፈሳል። ለማንኛውም በዓይኔ ዞር የምትሉት እትብቶቼ ውስጤ ይሄውላችሁ –

!ይቅናህ!“

*

ከሆንልህ – እልል ልበልልህ።

ከታሳካልህ – ሆ! ብዬ ማጫ ልሁንልህ።

ግን ለባለዛገ ጆሮ አታውስኝ

አትንቀሰኝ – አትውቀሰኝ

የወጨፎ ማዕትህ እኮ – በላኝ

ተለተለኝ፤

እንደ ተመቸህ – እባክህን አትሰልቀኝ?

ይበቃኛል! የባለጊዜ፤ – የጎጠኛ አባዜ

የዘመንተኛ ጃርተ – ሟርት፤  የለዛዜ።

አንተም ባሻህ፤ እኔም ባሻኝ

የአቅሜን መሻቴን እባክህን? – አክብርልኝ።

አይዋ! የኔው በሻ – አታድርገኝ ሆደባሻ

እንደ ልቤ ሸኜኝ፤ እንደ ልብህ ልሸኝህ።

ግን! አዎን! ግን – አትውቃኝ

አትሰቅዘኝ፤

ዬአፓርታይዱ ላይበቃኝ! አንተ ተደምረህ – አታጣውረኝ፣

አታ—-ሳ—-ጣኝ። አታ —- ሥ —- ጣኝ።

አ-ት-ቀ-ረ-ጣ-ጥ-ፈ-ኝ

በመስቃ  አ-ት-ሰ-ነ-ጣ-ጥ-ቀ-ኝ

አትሰልቀኝ፣

አታዋክበኝ ——አትበጣጥሰኝ።

ህም! —- የደም አንባር አይደለሁ፤

መውጫ ባጣ አማራጩን ለተስፋችን ተመኜሁ …..

ዱር ገደሉን ለወላችን – ሞረሽ አልሁ፤

እንጅ፤ እኔማ! ቢያቀማጥሉኝ መቼ ጠላሁ?!

እኮ አንተስ!!? አንተስ፤ ብትሆን ሰኞኛ

ሰውኛ ሁነህ ብትቦጭቀኝ – አይቀርብኝ – ድርሻዬ ይቀልልኝ

ኃጢያቴ – ይሠርይልኝ፤

ብቻ አዎን ብቻ፤ ታናሼዋ – ዳኛው ህዝብ ነው ይፋረደኝ።

እኔ ከሆንኩኝ ጥፋተኛ … ?

…. የማገዶ – አስቀማኛ?

የትውልድ – ቀበኛ …..?

—- የቀንበጥ – እግረኛ?

የደም ጥማተኛ ….?

…. የበቀል – ጉሮሮኛ?

ሀገራዊ – በደለኛ …..?

~~~~~~አድሎኛ~~~~~~~?

እ! ተጠያቂ ለዛውም – ዕንቡጤን አሳልፌ አሰጪ ለዱለኛ —-?

? ? ? ? —-

ለዘር – ብለኛ?

እም! –

የራስ – ህመም -

እማዳግም?

ይሁንልህ ብቻ – አዎን! ብቻ ይፋረደኝ – ዘመን

ይዘምዝመኝ – ይፍተለኝ

እንዳሻው – ያፍተልትለኝ።

ምነው እግረ ተከሉ ታናሼ? ክንድዬ – ታሪክንም ቢሆን አሳርፈው -

አትወርፈው!

ምን ባጣፋ እንዲህ ታቁስለው?

ቁም – ተቀመጥ፤ አትበለው?

አታሳቅለው -

ይበቃዋል – የእነሱ

የነማተበቢሱ።

ለቀን ያደረሰን እሱው ነው ———–በቅኔ ቤት ለካው፤

ባለ አፈር፤ ባለ ቋንቋ፤ ባለማተብ፤ ባለመቀነት – ጥቁር ንጡር አልማዝ እሱውልህ

አስላው – በሚያበለው – ፤

ውልህ።

የአፍሪካ ሰንደቅ፣ የጥቁር ዓርማ። ባርነትን ሰንጥቅ፣ – ድንቅ – እፁብ ፍልቅ፤

እንደ እንሰሳ መሬት ላይ ያላስጎተተኝ/ተህ/

ቀና አድርጎ ያናገረኝ/ህ/ — የትናንቱ የ3000 ከዚህም በላይ ውለኛ። የእናት ያባትህ – ርስትህ – ዋጋ አስራትህ፤

የራስህ ——

ትርሲትህ፤

ቅርስህ።

አያ አንቫዬ! ይልቅ ሥራህን – ሥራ ———

ሥራህ በርቶ ዴሞክራሲን – እስኪያበራ፤ – እስኪናገር – እስኪያወራ ከታሪክ ጋራ

ድምፅ መራሽ ሸንጎ እስክታለማ ——

እስክትሁን – ጉልት ማማ።

ትእግስት ሸምት ከእዮብ ጎራ፤

ከአባ መሆን ጎመራ

ከቅድስና አውራ።

ተወኝ! አልኩኝ – ይበቃኛል የእነሱ

እባክህን! አትነስተኝ ቀልቤ ሆኗል ስሱ፤

የእናት ሀገር ፍቅር ትዝታ – ስስቱ

የአደራ ጥሪት ትሩፋቱ

ሳልመልሰው ገድላዊ ታምራቱ

አቫዝቶኛል ቀን መግፋቱ።

እኮ!

እኮ! ከእኔ ምን አለህ?! – የእናቴ ልጅ በፈቀድከው ባሰኘህ መጪ በል …..

ከሳቱ ላይ እያለህ – አንተም ተረመጥኽ

እያንገበገቡህ – እዬወቁኽ

ከ—–ዘመንተኛ ልቀህ አትዘልዝለኝ – አትዘቅዝቀኝ፤

አትጎልጉለኝ – አትፈርፍረኝ።

ቁጥሩስ ቢሆን ጋሻዬ፤  እኩል – ለእኩል

እኔም አንተም ዬባለ24 ክናድ ባለኩል

የዕንባ – ኩልል።

ልንተያዬ ቀናት ሲያፈጥ——–

ምነው እንዲህ ቸኮልክ – ለማፋጠጥ!?

ይዘኸዋል – ታዬዋለህ

ብቻ ከእኔ ወረድ በል።

አሪወሱ – ባለ ጎራዴ

ተስፋ በቀረመት ጎራርዴ

አለልህ ቋሰኛው – ሸለሸሉ ጉርዴ።

እኔን ለቀቀ! እሱን ጠበቅ!

ጉባኤውን በድል ጥልቅ!

ዳኝነቱን ለህሊና አጥልቅ።

ወልደህ እዬው እንዳልልህ …

አንተም ህዋሴ ሆንክና፤ ምርቃቴን ላኩልህ።

እኔ እንዳተ አይደለሁም። ክብሬ – መንፈሴ – ጥንዴ – አልኩህ

የእኔ ጌጤ ብዬ፤ ውስጤን መርቄ ሸለምኩህ።

ሥጦታነትህን – በውስጥነት አወጅኩልህ

መንገድህን ይቅናህ! ይቅናልኝ፤ ድል ያቅናልኝም – አልኩህ!

እደግልን – ዘለግ ይበል ድልህ

አሁንም እልሃለሁ – በአጭሩ ከደመደመክ – ይሳካልህ~!

አርጎትነው አዶናይ! … እሰይ … እሰይ … ይሁንልን – ይሁንልህ፣

የእመቤቴም ጥበቃዋ አይለይህ፤

መቋጫውን ሐሤትማ – አማንዬ ያድርግልህ

አንደ ልብህ – አንድያዋ – ያሳማማልህ።

ሥጦታ – ለቁስለኛ – ከቁስለኛ።

© Seregute Selassie ሥርጉተ ሥላሴ –  08.04.2015 ሲዊዘርላንድ – ቪንተርቱር።

የኔዎቹ መሸቢያ ሰንበት ተመኝቼ የቤት ሥራ እንሆ – ብትህትና፤ ይህቺን ድግም – ድግምግም አድርጋችሁ ብታነቧት  ትፈወሳላችሁ። „ይህቺ ሐገር ሚስጢር ናት“ ከጸሐፊ ከተማ ዋቅጅራ – እግዚአብሄር ይስጥልኝ። በህሊናችን ሰሌዳ ዓምድ የሆነ ወርቅ አገላለጽ ከጭብጥ ተነስቶ በዕውነት አምክንዮ – የሰከነ። እጅ ይባርክ! http://www.zehabesha.com/amharic/ ውድ ዘሃበሻ – ውድድድ – ኑሩልኝ!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

ኢትዮጵያ አላዛር ናት!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

The post !ይቅናህ! – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>