Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የሳኦል ፍሬዎች ፊልም ተመረቀ  

$
0
0

seol2በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ‘የሳኦል ፍሬዎች’ በሚል ርዕስ በበርገን ቅርጫፍ የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ አስተባባሪነት የተዘጋጀው ፊልም በርካታ እንግዶች በተገኙበት በማርች 28 ቀን 2015 ዓ.ም በኖርዌይ በርገን ከተማ በቢከስ  አዳራሽ ተመረቀ።

ይህ ፊልም በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰባዊ መብት ጥሰት ፣የአካዳሚ ነፃነት ማጣት፣የፍትህ መጓዋደል እና በስደት አለም ውስጥ ዜጎች የሚገጥሙዋቸውን የህይወት ውጣውረዶች ከፍቅር ጋር በማስተሳሰር ይዳስሳል::

በእለቱ ዝግጅቱን የመሩት በበርገን ቅርጫፍ የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ህዝብ ግንኙነት አቶ ዳዊት እያዩ የፊልም ምርቃት ዝግጅት መጀመሩን ያበሰሩ ሲሆን  በበርገን ቅርጫፍ  የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ሊቀመንብር አቶ ሰለሞን አሸናፊ  እና ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን   በአዳራሹ ውስጥ ለተገኙት እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡  ይህ በውጪው አለም  ብዙም ያልተሞከረው በሀገራችን እና በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል ኪነጥበብን በመጠቀም መረጃወን ለህዝብ የማዲረስ ዘዴ  “ በሳኦል ፍሬዎች ”  ፊልም  ፈር ቀዳጂነት ለተመልካች ቀርቧል ፡

ከዚህ በመቀጠል የሳኦል ፍሬዎች ፊልሙ ላይ ወደ በርገን አመጣጡን ፣ የተዋንያኑን መረጣ ፣ ከጥናቱ ጀምሮ  እሰከ ፊልም ቀረጻው ስላከናወናቸው ውጣ ውረዶች ቀረጻው የፈጀውን የግዜ ርዝመት ፣ የሰው ሃይል ብዛት እና ፊልሙን እስኪጠናቀቅ ድረስ የነበረውን ውጣ ውረድ ጠቅለል አድርገው ገለጻ ያደረጉት የበርገን ቅርጫፍ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አሸናፊ ሲሆኑ በቀጣይ በፊልሙ ላይ ተዋናይ እና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ እና ተዋንያን ገሊላ መኮንን የፊልም ፅሁፉን በድጋሚ በማስተካከል (script rewrite) በማድረግ ለፊልሙ ሙያዊ እገዛ በመስጠት ፊልሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ በመቆጣጠር፡አሰልቺውን እና አድካሚውን የኤዲቲንግ ስራ ከባለሙያቹ ጎን ሳትለይ  በመከታተል እና ለመጀመሪያ ግዜ ፊልሙ መመረቅ ያለበት በተሰራበት ቦታ በኖርዌይ በርገን ከተማ ነው በማለት ይህን እድል በማመቻቸት የነበራት ድርሻ ጉልህ ነው : ይህ ድርሻዋም ከአንዳርጋቸው ጽጌ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ከሌሎቹም ጀግኖቹ ጀርባ ላሉት ሴቶች እህቶቼ መታሰቢያ ይሁንልኝ በማለት ፊልሙ ስላሳለፈው ሁኔታ ገለጻ አድርጋለች ፡፡

ለሳኦል ፍሬዎች ደራሲና ተዋንያን አይንሸት ገበየሁ ካሳ ምንም እንኳ  በእለቱ በዝግጅቱ ላይ ባይገኝም  ፊልሙን የተመለከቱት እንግዶች ለደራሲና ተዋንያን አይንሸት ገበየሁ  ወቅታዊ ሁኔታን የሚያሳውቅ፣ አርዓያና ምሳሌ  የሚሆን  ፊልም ነው በማለት  በመደነቅ ሞቅ ያለ አድናቆታቸውን  በጭብጨባ ገልፀውለታል ፡፡

የበርገን ቅርጫፍ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ከዛሬ 4 ወር በፊት ባሳወቀው ኢሳት ይቀጥላል መርህ መሰረት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ከሚያደርጉት ድጋፍ ጎን ለጎን እኛም የአቅማችንን ለመወጣት በተሰራው በዚህ በሳኦል ፍሬዎች ፊልም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መተንበታል ብለዋል  ፡፡

  1. ይህ ፊልም ከምረቃው በሃላ ኢሳት በሚደርስባቸው ቦታዎች ሁሉ ፣ በአውሮፓ እንዲሁም በአሜሪካ በሁሉም የኢሳት ቤተሰቦች ባሉበት ቦታ ሁሉ በሚያዝለት የግዜ ሰሌዳ መሰረት ለእይታ ይቀርባል ከዚህ ከሚያገኘው ገቢ በሃገራችን ላይ በመረጃ እጥረት በወያኔ የሃሰት ማታለያ እየተጨብረበረ ላለው ወገናችን ኢሳት የህዝባችን አይንና ጆሮ ሆኖ እንዲቀጥል የኢኮኖሚ ድጋፍ በመሆን ያገለግላል እንዲሁም በኢሳት ቴሌዚዠን ይተላለፋል በተጨማሪም ከእይታ ሲወርድ በቪሲዲና በዲቪዲ ተባዝቶ ለህዝቡ ለሽያጭ ይቀርባል ፡፡
  2. በወያኔ እየደረሰብን የሚገኘውን አፈና ግድያ ስደት የህዝባችንን በደል በተወሰነ መልኩ አሳይተንበታል ይህ ፊልም የመጀመሪው በመሆን ብዙ የተደበቁ እውነተኛ ታሪኮችን መሰረት ያደረጉ ሌሎች ፊልሞችም እንዲሰሩ መነሻ ይሆናል ፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ደረጃውን ጠብቆ በተሰራው ፊልም ላይ ለተሳተፉ የውዲቷ ሃገራችን  ልጆች ከኢሳት ማኔጅመንት እና ከበርገን ቅርጫፍ የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ የተዘጋጀላቸውን አበባ እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ፡ አዘጋጁ ኮሚቴ በ 3 ክፍል ከፍሎ አበርክቶላቸዋል ፡፡

በምረቃው ላይ ከተገኙ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መካከል  ለ3ቱ ስጦታውን የሰጡልን በበርገን ቅርጫፍ  የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አሸናፊ ሲሆኑ
በአንደኛ መደብ ተሸላሚ ደራሲና ተዋንያን የፊልሙ መሰረት መነሻ የሆነው  ወጣት ደራሲ አቶ አይንሸት ገበየሁ ካሳ          / ተፈሪን ሆኖ የተወነው / ሲሆን ምንም እንኳ በእለቱ  ባይገኝም በተወካይ በኩል ስጦታው ተሰጥቶታል ፡፡ ሁለተኛዋ  ተሻላሚ ፊልሙ ደረጃውን ጠብቆ እንዲሰራ ፣ የፊልሙን ድርሰት ሪ ራይት እና ዳይሬክት በማድረግ ሙያዊ እገዛ ስታደርግ  የነበረችው ሪ ራይተር እና ተዋንያን ገሊላ መኮንን ነበረች ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ተሸላሚ የነበረው ይህ ፊልም  ለታሪክ እንዲተላልፍ ከንብረቱ ከሙያው በተጨማሪ ከሳኦል ፍሬዎች ደራሲ ጋር በመነጋገር ለኮሚቴው ሃሳቡን ይዞት የመጣው እንዲሁም በተዋንያን መረጣ ሰፊውን ድርሻ ወስዶ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የቀረጻውን ስራ ሲያከናውን የነበረው ካሜራ ማን አቶ ቶማስ አለባቸው ነበሩ  ፡፡

በሁለተኛ መደብ ተሸላሚ የነበሩት መሪ ተዋንያኑ  ሲሆን ስጦታውን የሰጡልን በበርገን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀ መንበር አቶ ተስፋዬ ኮርፊል ነበሩ ፡ የመጀመሪያው ተሸላሚ በፊልሙ ላይ ዋናውን ገጸ ባህርይ ወክሎ የተወነው ወጣት መክብብ ሙሉጌታ ( ሃይሉን ሆኖ የተወነው) ሲሆን  ሁለተኛው ተሸላሚ ለፊልሙ ማማር የራሱን ድርሻ በሚገባ የተወነው አቶ ሳሙኤል ተወልደ ( መሃሪ) በሶስተኛ ተሸላሚ አቶ አንተነህ አማረ (ወዲ ጠቆ) በአራተኛ ተሸላሚ የሴቶችን ተሳትፎ በማሰደግ ላይ የምትገኘው ወ/ሪት ሜሮን አድማሱ (ማስተዋል) በመሆን ስጦታቸውን ተቀብለዋል ፡፡

በሦስተኛ መደብ ተሸላሚ የነበሩትን ተዋንያን ስጦታው የሰጡልን በበርገን ነዋሪ የሆኑት በሃገራዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሁሌም ከወገናቸው ጎን በመቆም የሚታወቁት ወ/ሮ ምስራቅ ነበሩ ፡፡ የመጀመሪያው ተሸላሚ አቶ ብሩክ ጌታነህ (ዋሴን ሆኖ የተወነው ) ሁለተኛው ተሸላሚ አቶ ሰለሞን አሸናፊ (ቦጋለን ሆኖ የተወነው) ሦስተኛዋ ተሸላሚ ከነቤተሰብዋ ወ/ሮ ሰላም በጋሻው (የመሰረት ጓደኛ ሆኖ የተወነችው) አራተኛ ተሸላሚ አቶ ዳዊት እያዩ ( ደህንነት ) አምስተኛ ተሸላሚ አቶ ማንደፍሮ መንግስቱ (የደህንነት ሹፌር) ስድሰተኛ ተሸላሚ አቶ ሺበሺ ጌታቸው (ፖስተር ዲዛይነር) ሰባተኛ ተሸላሚ አቶ ዮናስ በመሆን ስጦታቸውን ተቀብለዋል ፡፡ በመቀጠልም በምረቃው ላይ ከተገኙ እንግዶች አርቲስቶች አንዲሁም ከተሣታፊዎች መካከል በፈልሙ ዙሪያ ወይይት ተደርጓል።

በፊልሙ ምርቃት ላይ ከአመስተርዳም ጋዜጠኛ እና አርቲስት ገሊላ መኮንን ፣ በበርገን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ተስፋዬ ኮርፊል፣ ጥሪ የተደረገላቸው የኢትዮጵያ ወዳጆች  እንዲሁም የበርገን ነዋሪዎች እና በፊልሙ የተሳተፉና ተጋባዥ አርቲስቶች ተገኝተዋል።
በመጨረሻም የበርገን ቅርጫፍ የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ፊልሙ እንዲሰራ በማስተባብር ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ልምድና ትምህርት አግኝቶበታል በቀጣይም ከዚህ የተሻለ ስራ ይዞ ለመቅረብ በእቅዱ ውስጥ አስገብቶ እየሰራበት ይገኛል ፡፡ የሳኦል ፍሬዎች ፊልም መነሻነት፡ ደፍረው ያልተነገሩ የወያኔ የአደባባይ ሚስጢሮች በሰፊው ለህዝብ ቀርበው ህዝቡ ፍርድ እንዲሰጥበት ማድረግ የአገዛዙን ድብቅነትና ውሸት ማጋለጥ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው ፡፡ ይህ ፊልም የፍርሃታችንን ድባብ አስወግዶ በሌላም ቦታ እንደዚህ የመሰሉ ስራዎች እንዲሰሩ ፈር ቀዳጅ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ፡፡ የሳኦል ፍሬዎች ቧልትና ቀልድ በበዛበት ዘመን ደፍሮ የተሰራ ኮስተር ያለ ፊልም ነው ፡፡ የማይነካውን ነክቶ ያሳየ መንገዱን ያመላከተ ፊልም ነው እኛ የምንችለውን አድርገናል ከዚህ በላይ የተሻሉ ስራዎች እንደሚሰሩ ተሰፋ እናደርጋለን ፡፡

የበርገን ቅርጫፍ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ህዝብ ግኑኘነት

አቶ ዳዊት እያዩ

The post የሳኦል ፍሬዎች ፊልም ተመረቀ   appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>