* “የ መዝራ መጠለያና የወተት ፋብሪካ ጥቃት ፈጻሚዎች የሁቲ አማጽያን ናቸው !” የዘመቻው ቃል አቀባይ
* በሳውዲ መራሹ ጦር የአየር ጥቃት እንደደረሰበት ሲነገር ስለነበረውና አነጋጋሪ ሆኖ ስለሰነበተው በተባበሩት መንግስታታ የስደተኞች በመዝራ መጠለያ ጥቃት ዙሪያ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ መግለጫ ሰጥተዋል ። ጀኔራሉ ከቀናት በፊት በጥቃቱ ዙሪያ ተጠይቀው በመጠለያው አካባቢ የመሸጉ የሁቲ አማጽያን ላይ ጥቃት መደረጉን አምነው ነበር ። በወቅቱ ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም ነበር ።
* ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ የዘመቻውን 7ኛ ቀን ዘመቻ መግለጫ በሰጡበት የትናንት ረቡዕ መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓም ጋዜጣዊ መግለጫቸው አነጋጋሪ ስለሆነው የንጹሃን ጥቃት መረጃ አሰምተዋል::
* ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ባሳለፍነው ሰኞ ከ40 በላይ ስለሞቱበት እና ከ200 በላይ በቆሰሉበት በአነጋጋሪው የተባበሩት መንግስታታ የስደተኞች ድርጅት UNCR በሃጃ ክልል በሚገኘው የመዝራ መጠለያ ጣቢያ ጥቃን አጣርተው እንደሚያቀርቡ በገቡት ቃል መሰረት ተጣርቷል ባሉት መረጃ ጥቃት ፈጻሚዎቹ በጥቃቱ ክፉኛ የተጎዱት ሁቲዎች መሆናቸውን አብራርተዋል ።
* ዘመቻው በተጣራ መረጃዎችን እንጅ ሰላማዊ ነዋሪዎች የሚገኙባቸው ቦታዎች ኢላማ እንደማያደርግ በማስረዳት በተለይም በተባበሩት መንግስታታ የስደተኞች ድርጅት UNCR በመዝራ መጠለያ ጣቢያን ጥቃት በሚመለከት ሲናገሩ በንጹሃን ላይ ጥቃት የተፈጸመበት ሞርታር መሳሪያ የሁቲ ሸማቂዎች ይጠቀሙበት እንደነበር መረጋገጡን በአጽንኦት አስታውቀዋል ። ከዚሁ ጋር አያይዘው ሁቲዎች በጥቃቱ ሲዳከሙ በንጹሃን እልቂት አዘኔታ ለማግኘት የረከሰ ስልት መጠቀም መጀመራቸውን አሳፈሰሪነት ” የቆሸሸ ስልት! ” ሲሉ አንቋሸውታል ! ብ.ጀኔራል አሲሪ ስለ መጠለያው ጥቃት ማብራሪያቸውን ሲያጠቃልሉ በሁቲ ሽማቂዎች የሞርታር ጥቃት የተፈጸመ እንጅ የአየር ድብደባ ጥቃት አለመሆኑ መረጋገጡን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል::
* ጥቃት የደረሰበት መጠለያ የሞቱት ዜጎች ዝርዝር መግለጫ ባይወጣም መጠላያው በየመን እርስ በርስ ጦርነት የተፈናቀሉ የመናውያንና ከምስራቅ አፍሪካ ወደ የመን የመጡ ስደተኞች መጠለያ እንደሆነ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተጠቅሷል::
* በመዝራ መጠለያ ጣቢያ በደረሰው ጥቃት የሞቱትና የቆሰሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስለመሆናቸው አለመሆናቸው ግን እስካሁን ምንም የተጨበጠ መራጃ በአረቡ አለምም ሆነ በምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን አልተጠቀሰም::
* በተመሳሳይ ሁኔታ በጠንካራው የአየር ጥቃት የተሸበሩት የሁቲ አማጽያን ንጹሃንን መሸሸጊያ የማድረግ ስልት መጠቀማቸውን የጠቆሙት ቃል አቀባዩ በአልሆዴዳ የወተት ፋብሪካው በተመሳሳይ ሁኔታ የሁቲ አማጽያን ተንኮል የተፈጸመ እንደሆነ አልደበቁም::
* የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥቃቱ አለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው በማለት ጥፋተኞች በተፈጸመው ወንጀል በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው የሚል መግለጫ ማውጣቱ አይዘነጋም …
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቡት 24 ቀን 2007 ዓም
The post (የሳዑዲ እና የመን ጉዳይ) “ወሳኙ ማዕበል” የ7ኛ ቀን መግለጫ … (ነብዩ ሲራክ) appeared first on Zehabesha Amharic.