Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የአዲስ አበባ ግድግዳዎች በተቃውሞ ጽሑፍ አሸብርቀው አደሩ

$
0
0

addis ababa
ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው:-

ቅዳሜ ጥር 9/2007አዲስ አበባ ዛሬ ሌሊት በትግሉ መፈክሮች አሸብርቃ አደረች! ተቃውሞውን እና ለትግሉ ያለውን ቁርጠኝነት በተለያዩ መንገዶች ሲገልፅ የቆየው ሙስሊሙ ማህበረሰብ አሁንም በተለያዩ መንገዶች ተቃውሞውን እየገለፀ ይገኛል።

የግራፊቲ መፈክሮቹ በቦሌ፣ በጀርመን አደባባይ፣ በመካኒሳ፣ በቺቺኒያ፣ በአየር ጤና፣ በጦር ሀይሎች በሚገኘው መጅሊስ ቢሮ አካባቢ፣ በላንቻና በጎተራ፣ እንዲሁም በሌሎች ሰፈሮች ተፅፈው ያደሩ ሲሆን የአካባቢው ጸጥታ ኃይሎችም በሁኔታው መደናገጣቸውን ማወቅ ተችሏል።

በግራፊቲው ከተፃፉት መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:–

«የጨለማ ፈራጆች!»
«ኮሚቴው የህዝብ ነው!»
«ሂጃብ መለያችን!»
«ትግሉ ይቀጥላል!»
«ፍትህ ለኮሚቴው!»

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post የአዲስ አበባ ግድግዳዎች በተቃውሞ ጽሑፍ አሸብርቀው አደሩ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>