ጥር:- 5 ቀን 2007 ዓ/ም
ለተከበራችሁ ለድርጅቱ ሥራ አመራር አባላትና በዱር በገድሉ ከጠላት ጋር ለምትዋደቁ ታጋይ ጓዶች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ፤ በማለት የአክብሮት ሰላምታችን እያቀርብን፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና በግንቦት 7 ለፍትህ ዴሞክራሲና የነጻነት ንቅናቄ መሀል የተደረገውን ውህደት በታወጀ ጊዜ
የተስማን ደስታ እጅግ የላቀ ነው::
ይህን የአንድነትና የወንድማማችነት ትስስር የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት የሚጠብቀው በመሆኑ ይህ ውህደት ለህዝባችን ታላቅ የምስራች እንደሆነ እናምናልን::
ለዚህ ታላቅ ውህደት ለወድፊቱ ለምታደጉት የስራ እንቅስቃሴ ሁሉ ከጎናቸሁ የምንቆም መሆኑን እያረጋገጥን መጪው ጊዜ ይህ ሃገር ሻጭና ዜጋን ገዳይ የሆነ ዘረኛ የወያኔ ኢሃዴግ ጎጠኛ ድርጅት ተወግዶ ሰላምና ደስታ ህይወትና ብልጽግና የሰፈነባት ዜጎችዋ ሃገሪ ብለው የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለማየት እንድንበቃ ሁለንተናዊ አንድነት እና ኅብረት ለነጻነት በር ከፋች መሆኑን አምነን በጋራ ለመቆም ቃል እንገባለን !!
አንድነት ኃይል ነው!!
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዓለም አቀፍ ኮሚቴ
The post የኢ.ሕ.አ.ግ. ዓለም አቀፍ ኮሚቴ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት appeared first on Zehabesha Amharic.