Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሰላማዊ ትግል የህዝብ ድምፅ የሚረጋገጠው በምርጫ ነው ብለን እናምናለን –የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር

$
0
0

1186718_600650739977528_2059123344_nአቶ ስለሺ ፈይሳ የሰያማወኢ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ናቸው። በድርጅቱ ደንብ መሰረት፣  የምርጫ ጉዳይ ሃላፊ ናቸው። በመጪው ምርጫ ዙሪያ ከሚሊዮኖች ድምጽ ጋዜጣ ጋር ቃለ መልልስ አድርገዋል። የሚሊዮኖች ድምጽ ጋዜጣ በአንድነት ፓርቲ ኤዲቶሪያል ቦርድ ታትማ ከሕዝብ የምትሰራጭ ጋዜጣ ናት። ይች ጋዜጣ ከፍኖተ ለነጻነት ጋዜጣ በተጨማሪ ሁለተኛ ጋዜጣ መሆኗ ነው)

 

ሚሊዮሞች ድምጽ – የ2007 ምርጫን እንዴት እየጠበቃችሁት ትገኛላችሁ?

 

አቶ ሰለሺ – ምልክታችንን አሳውቀናል፤ ሰሞኑን እናረጋግጣለን፡፡ በፓርቲያችን ውስጥ ሰፊ ሥራ እየሠራን ነው፡፡ በምርጫ ጉዳይ ላይ የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባላቱን አደራጅቶ የአባላቱን ጉልበት፣ ሀብትና ዕውቀትን በመጠቀም ዓመቱን ሙሉ ሰፊ

ሥራዎችን እየሠራን ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲን ለየት የሚያደርገው፣ የምርጫ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን በምክትል ፕሬዚዳንቱ እንዲመራ በፓርቲው ደንብ ማስቀመጡ ነው፡፡በደንብ እየሰራን ነው፡፡ ንዑሳን ኮሚቴዎችን

 

ምርጫው ቦርድ በጊዜ ሰሌዳው መሠረት እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ነገር ግን፣ ከምርጫው በፊት ብዙ መሠራት ያለባቸው ጉዳዮች እና መስተካከል ያለባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ከጊዜ ሰሌዳው መፅደቅ በፊት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመነጋገር ቦርዱ ነገሮችን ማመቻቸት እንዳለበት ገልጾን ነበር፡፡ ነገር ግን ፍቃደኞች አልነበሩም፡፡ በጊዎን ሆቴል ይሄን ተቃውሞ አሰምተን፣ ስብሰባውን ረግጠን ወጥተናል፡፡ ይሄም ሆኖ የምርጫ ምልክት አስገብተናል፡፡ የምርጫ ፓርቲ ነን፡፡

 

በሰላማዊ ትግል የህዝብ ድምፅ የሚረጋገጠው በምርጫ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ለኢትዮጵያ የሚጠቅመው እና ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ የምርጫ ሳጥን ወሳኝ ነው ብለን እናምናለን፡አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ ሲታይ፣ የምርጫ አስፈፃሚው አካልና መንግሥት ሌሎች አማራጮች ለሚያሳዩ ወገኖች በሩን የዘጉ እና ያደፈኑት ይመስላል፡፡

 

በፓርቲያችን አመራሮች እና አባላት ላይ በቅርቡ እንኳን የደረሰውን ድብደባ እና እስር ማየት በቂ ነው፡፡ በምርጫ ወቅት ሰዎች ድምፃቸውንና ተቃውሟቸውን ማሰማት አልቻሉም፡፡ ይሄን ይሄን ስትመለከት፣ ምን ያህል ፍትሃዊ ተዓማኒና ነፃ ምርጫ ይካሄዳል የሚለው በጣም ያሰጋናል፡፡

 

ምርጫ አስፈፃሚው፣ ምርጫ ቦርድ ከላይ እስከታች ድረስ ወገንተኛ የመሆኑ ጉዳይን ሙሉ በሙሉ እናምናለን፡፡ ማስረጃዎችም አሉ፡ ለህዝቡም ገልፀናል፡፡ ‹‹ምርጫ አለ፣ የለም›› የሚለው ያሰጋናል፡፡ የተሻለ የምርጫ ምህዳር የሚከፈት ከሆነ፣ በአዎንታዊ መንገድ ወስደን እንወዳደራለን፡፡ለዚህ ደግሞ በፓርቲው የምርጫ ግብረ ሀይል በኩል እየሠራን እንገኛለን፡፡

 

ሚሊዮኖች ድምጽ – ለምርጫው ምን ዓይነት ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛላችሁ?

 

አቶ ስለሺ – ምልክታችንን አሳውቀናል፤ ሰሞኑን እናረጋግጣለን፡፡ በፓርቲያችን ውስጥ ሰፊ ሥራ እየሠራን ነው፡፡ በምርጫ ጉዳይ ላይ የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባላቱን አደራጅቶ የአባላቱን ጉልበት፣ ሀብትና ዕውቀትን በመጠቀም ዓመቱን ሙሉ ሰፊ ሥራዎችን እየሠራን ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲን ለየት የሚያደርገው፣ የምርጫ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን በምክትል ፕሬዚዳንቱ እንዲመራ በፓርቲው ደንብ ማስቀመጡ ነው፡፡በደንብ እየሰራን ነው፡፡ ንዑሳን ኮሚቴዎችን አቋቁመናል፡፡ በምርጫ ስንገባ የመጀመሪያችን ሊሆን ስለሚችል የሚያስፈልጉንን የምርጫ ሰነዶች እያዘጋጀን እንገኛለን፡፡

 

ለምሳሌ፣ የፓርቲው ዕጩ የመመልመያ ሰነድ፣ የፓርቲውን የሥነ-ምግባር መመሪያ እንዲሁም የፓርቲውን የታዛቢዎች መመልመያ መመሪያ እና የፓርቲው የምርጫ ወቅት የቅስቀሳ መመሪያ ሰነዶችን እየሠራን ነው፡፡ ትልቁ ሰነዳችን ደግሞ የምርጫ ማኒፌስቶ እያዘጋጀን ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ‹‹በምርጫው ምን ማግኘት አለብን?››፣ ‹‹የቱ ጋር ደካማ ነን?››፣ ‹‹የቱ ጋር ጠንካራ ነን?››፣ ‹‹የድጋፍ ቦታዎቻችንን (ደካማ እና ጠንካራ) ለመለየት ዳሰሳዊ ጥናት አድርገናል፡፡

 

በዚህ መሠረት በሀገሪቱ 10 የምርጫ ዞኖች በመክፈል እነዚህን የሚያስተባብሩ አምስት አምስት ሰዎች በአጠቃላይ 50 ሰው ያለበት አንድ የምርጫ ግብረ ሀይል በሀገር አቀፍ ደረጃ አቋቁመናል፡፡ ሰሞኑን በተፈጠረው ሁኔታ ነገሮች ስለተበላሻሹብን መጓተት ተፈጠረ እንጂ በቀጣይ እነዚህን የምርጫ ግብረ ሀይላት ከአዲስ አበባ እና ከክልል አምጥተን ለአንድ ሳምንት ያህል ከጥናትና ሥትራቴጂው ጋር ሴሚናር እንሰጣለን፡፡

 

የሚሊዮኖች ድምጽ – ህብረት ወይም ቅንጅት ሳትፈጥሩ፣ በተናጥል ተጉዛችሁ ለመንግስትነት የሚያበቃ ውጤት ማምጣት እና በሰላማዊ መንገድ ከኢህአዴግ ሥልጣን መውሰድ ትችላላችሁ?

 

አቶ ስለሺ –  ምርጫውን ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ከስምንት ፓርቲዎች ጋር ትብብርን መመስረት ተችሏል፡፡ ከእነሱ ጋር እየሠራን ነው፡፡ ሌሎችም በዚህ ትብብር ውስጥ የየራሳቸው ተሳትፎ ነበራቸው፡፡ ዋና ዋናዎቹ መኢአድ እና አንድነት በራሳቸው ምክንያት ከትብብሩ ርቀዋል ብለን እናምናለን፡፡አሁንም ጥሪ እያደረግን ነው፡፡ በጋራ የህዝብ ድምፁን ለማግኘት አብረን መስራት አለብን፤ እንሰራለንም፡፡ የምርጫ ቦታን የመሻማትና ያለመሻማት ነገር ሊኖር ይችላል፤ እንደ ችግርም ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ ይሄ ችግር እንዲፈታ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡

 

ጊዜው ሲደርስ ‹‹ማን የቱ ጋር ጠንካራ ነው?፣ የቱ ጋርስ ደካማ ነው››፣ ‹‹የተሻለ ድጋፍ የቱ ጋር ማን አለው?›› የሚለውን እያየን በትብብርና በቅንጅት ስትራቴጂ ነድፈን ለመስራት ፈቃደኞች ነን፡፡ ሁሉን ነገር በእኛ ብቻ ይሸፈናል ብለን አናምንም፡፡

 

መታወቅ ያለበት፣ 2002 ምርጫን አስመልክቶ ስታትስቲክስ ያወጣው መረጃ፣ መምረጥ ከሚችለውና ከተመዘገበው ህዝብ ኢህአዴግ ያገኘው 33 በመቶ ነበር፡፡ በወቅቱ የተወዳደሩ ተቃዋሚዎች ደግሞ 14 በመቶ፡፡ በድምሩ 48 በመቶውን በጋራ ይዘዋል፡፡ መምረጥ የሚችለው 52 በመቶ ሕዝብ ግን ለኢህአዴግም ሆነ ለተቃዋሚዎች ድምጽ አልሰጠም፡፡ በማንም ላይ ተስፋ እና ዕምነት አልነበረውም፡፡ በዚህ ምክንያት ራሱን ከምርጫው አግልሏል፡፡

 

ተቃዋሚዎች በሰፊው ከሰራን ሰፊው 52 በመቶ ዋነኛ አቅማችን ይሆናል፡፡ በሀገሪቱ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በሌሎችም ዘርፎች የዛሬ አምስት ዓመት ከነበረበት የባሰበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሥርዓቱ እየተጠላ፣ ፖሊሲዎቹ እየተዳከሙ፣ ለኢህአዴግ ድምፅ የሰጠ ሁሉ ከእሱ እየራቀ ሊመጣ ይችላል፡፡ ሰፊ ድጋፍ የሚያደርግ ያልተነካ የመራጭ ሀይል ስላለ፣ እሱ ላይ አትኩረን እንሠራለን፡፡ በመገፋፋት እና በመበላላት ድምፅ እናጣለን ብለን አናስብም፡፡

 

ቢሆን እንኳ አንዱ በአንድ ቦታ ጠንካራ የድጋፍ መሠረት ካለው፣ ለእሱ እንተወዋለን እንጂ የግድ ሰማያዊ ካላመጣው ብለን አንልም፡ ይሄ ጊዜው ሲደርስ አስፈላጊ መዋቅራዊ ሁኔታዎችን በማድረግ ወይም ሥትራቴጂ በመንደፍ በዋናነት የህዝብን ድምጽ እናስጠብቃለን፡፡ ህዝብ ድምጹን እንዲሰጥና እንዲከበርለት በዋነኝነት እንሰራለን፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>