የታዛቢዎችን ምርጫ ለማወክ ተንቀሳቅሳችኋል::” – ፖሊስ
ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው:- ዛሬ በየቀበሌው የሚካሄደውን የታዛቢዎች ምርጫ ተከትሎ ወደ ሚኖሩበት ጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ 3 ያመሩት የሰማያዊ አባላቶቹ ኢየሩሳሌም ተስፋው እና እመቤት ግርማ የታዛቢዎችን ምርጫ ለማወክ ተንቀሳቅሳችኋል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የምርጫ ታዛቢ መሆን የሚችሉት ገለልተኛየሆኑ እንጂ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ አይደሉም በሚል ባነሱት ክርክር ምክንያት ለማወክ እየሞከራችሁ ነው በሚል ፖሊስ ሊይዛቸው ችሏል፡፡