Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሁለት የኢትዮጵያ አየር ሀይል ኤም አይ 35 ሄሊኮፕተር አብራሪዎች የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ጠፉ -\

$
0
0

ኢሳት ዜና –  ሁለት የኢትዮጵያ አየር ሀይል ኤም አይ 35 ሄሊኮፕተር አብራሪዎች የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ጠፉ።የት እንደገቡ እስካሁን አልታወቀም። ለኢሳት በደረሰው መረጃ የ ኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪዎቹ ሻምበል ሳሙ ኤል ግደይ እና መቶ አለቃ ቢልልኝ መኮንን ትናንት ጧት ለልምምድ እንደወጡ ነው ጠፍተው የቀሩት። አብራሪዎቹ ከ 30 ደቂቃ በላይ እንዲቆዩ ከማይፈቀድላቸው የበረራ ራዲየስ በመውጣት የሚያበሯቸውን ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ይዘው መጥፋታቸው ተረጋግጧል። ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀረበት ድረስ አብራሪዎች የት እንዳሉ አልታወቀም። ሁለቱ ከፍተኛ የ ኢትዮጵያ አየር ሀይል አብራሪዎች በስልጣን ላይ ያለውን ስር ዓት በመክዳት ከጎረቤት ሀገሮች በአንድኛቸው ሳያርፉ እንዳልቀረ ግምት አለ።

captured-ethiopian-mi-24-by-eritrea


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>