Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አንድነት አሁንም ቀሪ ሒሣብ አለበት!

$
0
0

ከይድነቃቸው ከበደ

“አያገባኽም፣ማን ደረሰብህ፣የራስህን ስራ ሥራ” እና የመሳሰሉ ምክሮች ከትችት ማምለጫ የሞኙ-አሞኝ ቀፋፊ አካሄድ ነው፡፡ሁሉ ነገር በእጄ ነው የሚለው ገዥው የወያኔ መንግሳት ከመተቸት እና ከማጋለጥ ከፍ ሲልም ከስልጣኑ ለማውረድ ሞራል አለኝ የሚል ሰው ፣ማንኛውንም ፓርቲ እና ግለሰብን ለመተቸት እና ለማጋለጥ የሚያፈገፍግ እንደማይሆን እርግጥ ነው፡፡

ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ


እኔም ከዚህ የተለየ እምነት የለኝም፡፡ በማልስማማበት እና ቅር በተሰኘሁበት ጉዳይ አስተያየት የመስጠት ልምዴን እያዳበርኩ የምገኝ ፣ለመተቸት እና ለመማር እራሴን የዘጋጀው ነኝ፡፡ሌላው ቀርቶ እኔ በሃላፊነት ያለሁበት ፓርቲ የተሳሳተ ሃሳብ እና አቋም የያዘ ሲመስለኝ በግሌ ትችት አዘል አስተያየት በጋዜጣ፣በመፅሔት እና በተለያዩ ዌብሳይቶች ላይ በፁሑፍ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መካክለ “ወደፊት ቆሞ ወደ ኋላ መመልከት”፣ “ጥያቄው ሃይመኖታዊ ነፃነት መብት ወይስ ፖለቲካዊ ” እና “ድንጋይ ቢቆሉት አይሆንም ቆሎ ”የመሳሰሉት የገኝበታል፡፡

ይህ በእንዲ እንዳለ አንድነት ፓርቲ “በምርጫ እሳተፈላው” በማለት ያወጣው መግለጫ ከሰሞኑ የመነጋገሪ ዕርስ እንደነሆነ ለማናችንም ግልፅ ነው፡፡ ይሄን ተከትሎ “በምርጫ ለመሳተፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ለምን ?” በማለት የግል ዕይታዬ ገልጫለው፡፡በዚህም ምንያት ትችት እና አስተማሪ የሆነ አስተያየት በፊስቡክ ገፄ እና ሣጥኔ በግል መልዕክት እንዲሁም ባመቻቸው መንገድ የሰጡኝ አስተያየት ደርሶኛል፡፡ ለዚህም አስተያየታችሁ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነውና በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡

እኔም ሆንክ ሌሎቻችን በሰጠነው ትችት እና አስተያየት አንድነት ፓርቲ ጉዳዩን ለማጥረት በዛሬው ዕለት “አንድነት የፀረ ሽብር አዋጁ ተቀብሎትም አያውቅም፤ አይቀበለውም!” በማለት ያዋጣው መግለጨ የሚበረታታ እና የሚደነቅ ነው፡፡ በፀረ ሽብር አዋጁ ላይ አንደነት የሰጠው ማብራሪያ የሚደግፍ ቢሆንም በምርጫ ላይ ያለው አቋም ግን የፀና መሆኑ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በማህበራዊ-ድረ ገፃቸው እንዲሁም በተለያየ መንገድ አረጋግጠዋል፡፡ይህን አቋማቸው እና የትግል ስልታቸውን አከብራለው ፡፡ የሚያዋጣቸውም ከሆነ ወደፊት በጋራ የምናየው ይሆናል፡፡

አሁን ላይ አስቀድሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ፣ ለዛውም አቋምን ለመግለፅ አስገዳጅ ሁኔታ ባልተፈጠረበት፣ “ምርጫ እሳተፋለው” ማለት ለቀጣይ የትግል ስልት ለፓርቲው(ለአንድነት) የስልጣን ባለቤትነት የሚያበቃው ከሆነ መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት፡፡ለመረጃ ያኸል አንድነት አወጣ የተባለው መግለጫ ሾልኮ የወጣ እንጂ የታሰበበት እንዳልነበር እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ የሚሆነው “የአንድነት የምርጫ ጉዳይ ግብረ ሃይል” በጉዳዩ ዙሪያ የሚያወቀው ነገር እንደሌለ እና በዚህም ምክንያት በአንድነት ቤት ውጥረት እንደሰፈነ፣በተጨማሪ በአቶ ግርማ ወቅታዊ አቋም ከጥርጣሬ ባለፈ “ጫጫታ” እንዳለ የአንድነት ፓርቲ ወፍ ነግራኛለች፡፡ወፏ ደግሞ ለእኔ ታማኝ ናት፡፡

ሌላው እና ዋናው ጉዳይ አቶ ግርማ በተመለከተ ነው ፡፡ አቶ ግርማ የአንድነት ፓርቲ ም/ት ሊቀመንበር መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ይሁን እንጂ እነደሳቸው አገላለፅ የግሌ ሣይሆን የፓርቲየ አቋም ነው በማላት ስለሚናገሯቸው ነገሮች እና ስለሚፁፏቸው ጹሑፍ መጠነኛ ምልከታዬን ለመግለፅ እወዳለው፡፡አንድነትም ያላወራረደው ቀሪ ሒሣብ ያለበት እዚህ ላይ ነው፡፡ እዴት ለሚለው ይህን እንመልከት፡፡

1ኛ. በድረ-ገፃቸው በ “ፀረ ሽብር ህግ” ተከሰው ቅጣት ከተጣለባቸው ውስጥ ቅጣት የሚገባቸው ተከሳሾች የሉም የሚል ጭፍን ዕየታ የለኝም፡፡ እነዚህ ሰዎች በወንጀል ህጉ ሊቀጡ የሚችሉ እንደሆነ ግን መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡”ማለታቸው ከምን የመነጨ ነው ! በ “ፀረ ሽብር ህግ” ተከሰው ቅጣት የተጣለባቸው እና ቅጣታቸውን የሚጠብቁ 1ኛ.ናትናኤል መኮንን 2ኛ.አበበ ቀስቶ 3ኛ.አንዱአለም አራጌ 4ኛ.እስክንድር ነጋ 5ኛ.ርእዮት ዓለሙ 6ኛ.በቀለ ገርባ በተጨማሪ ሌሎች ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ ጦማሪያን፣ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች፡፡ በአቶ ግርማ አገላለፅ እነዚህ ሽብርተኞች በወንጀል ህጉ ሊቀጡ የሚችሉ መሆናቸው መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
Girma  Seifu
2ኛ.ሌላው ደግሞ አቶ ግርማ በድምፅ ከተናገሩት “……ሁሉ ጊዜ ከመንግስት ጋር “እንትን” የምንለው በኢትዮጵያ ሰላም እና ፀጥታ፣ ችግር ይፈጥራሉ ብሎ የሚባል ነገር ካለ እኛም የበለጠ ያጋባንል….” ይቺ ናት ጨዋታ! የት ነበር ይሄን ዘፈን የሰማሁት ? አቶ ግርማ ስለሚናገሩት ነግር ምን ያህል እርግጠኛ ስለሞሆናቸው እጠራጠራለው፣ይሄን ንግግር የተናገሩት ከ“ፀረ ሽብር ህግ” ጋር በተያያዘ ነው፡፡መንግሰት ደግሞ እስካሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከገዥው መንግሰት የተለየ ሃሳብ ያለውን በሙሉ “የሕዝብን ሰለምና ፀጥታ፣ለማደፍረስ” በሚል የሽብር ክስ የሚመሰርተው እና የሚያስረው እንዲሁም የሚያሰቃየው ፡፡እንደ አቶ ግርማ አገላለፅ ከመንግስት እኩል ፓርቲያቸው እንደሚያስጨንቀው የገለፁት፡፡

ነገሩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ “የአ.አ አሰተዳደር ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል በሰማያዊ ፓርቲ ላይ እርምጃ እወስዳለው” ማለቱ የሚታወቅ ነው፡፡ አስተዳደሩ ይሄን ያለበት ምክንያት ደግሞ ለማንም ግልፅ ነው፡፡ በአቶ ግርማ ቀመር መሠረት ከምንግሰት እኩል ጉዳዩ አግብቷቸው እሳቸው እና ፓርቲያቸው እርምጃ ሊወስድ ነው ማለት ነው ? እንዴን ግምት አቶ ግርማ ሊያደርጉት ይችላሉ፣ፓርቲያቸው ግን ይሄን የሚያደርግ አይመስለኝም ፣ከአይመስለኝም ወደ እርግጠኝነት የሚያሸጋግረኝ፤ አንድነት ፓርቲ በዚህ ላይ ያለውን አቋም ለክ እንደ ፀረ ሽብር አዋጁ በግልፅ ካሳውቅ ነው፡፡ለዚህም ነው “አንድነት አሁንም ቀሪ ሒሣብ አለበት” !ያልኩት፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !



Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>