Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሚኒሶታ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው የ61 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ አባት ፍትሃት ዛሬ እሁድ ይደረጋል

$
0
0

አቶ ለሙ መሹ የተባሉ የ 61 ዓመት ኢትዮጵያዊ አዛውንት በድንገተኛ የመኪና አደጋ በሚኒሶታ ሕይወታቸው ማለፉን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: የ እኚህ ኢትዮጵያዊ አባት የፍትሃት ስነስርዓት ዛሬ እሁድ ኖቬምበር 23 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ ከቤተሰቦቻቸው አካባቢ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል::
ኢትዮጵያዊው አባት ሕይወታቸው ያለፈው አስፓልት በሚሻገሩበት ወቅት ሲሆን የገጫቸው መኪናም ሳይረዳቸው መሄዱንም በሚዲያዎች ተዘግቧል::
FullSizeRender
ከቤተሰቦቻቸው የደረሰን መል ዕክት የሚከተለው ነው:-

አቶ መሹ ቡልቶ ለሙ በ 1953 ዓመተ ምህረት ከአባታቸዉ ከአቶ ቡልቶ ለሙ እና ከናታቸዉ ከወይዘሮ ሃታቱ ጅንዶ በሽዋ ክፍለ ሃግር በግንደ በረት ወረዳ ተወልደዉ ማክሰኞ November 18, 2014 በደረሰባቸዉ ድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። አቶ መሹ ቡልቶ ከሶስት አመታት በፊት ለልጆቻቸዉ ለወደፊት የትምህርት እድል እንዲያገኙ በማሰብ ወደ አሜሪካ አገር የመጡ ሲሆን ዉድ ባለቤታቸዉን እና ልጆቻቸዉን ለማስመጣት በዝግጅት ላይ እንዳሉ በድንግተኛ አደጋ ህይወታቸዉ አለፈ፤። ቤተ ሰቦቻቸዉ እና ወዳጅ ዘመድ ሁሉ እንዲሁም በአጠቃልይ በሚኒሶታ የምንኖር ኢትዮጵያዉያን የተሰማንን መሪሪ ሃዘን እንገልጻለን፤ ለቤተሰቦቻቸዉ ም እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥልን።

የአቶ መሹ ቡልቶ ጸሎተ ፍትሃት በመጭዉ እሁድ November 30,2014 በደብረ ብርሃን ቅዱስ ኡራኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከጧቱ 10:00am ሰዓት ጀምሮ ይከናወናል። ለወንድማችን አቶ መሹ ቡልቶ ለሙ (ወልደሰንበት)
ከቅርብ ጓደኞቹ
የፍትሃተ ጸሎት የሚከናወንበት አድራሻ
አድራሻ፦ 1144 Earl Street St. Paul, MN 55106
ሰዓት 10:00am
ስልክ : 763 412 5279


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>