Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የህገ ወጡ መጅሊስ አባላት እና ሲቪል ፖሊሶች ባዩሽ መስጂድን ለመንጠቅ ሙከራ ማድረጋቸው ታወቀ!

$
0
0

bayush mosque
ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው፦

የህገ ወጡ መጅሊስ አባላት እና ሲቪል ፖሊሶች ባዩሽ መስጊድን ለመንጠቅ ሙከራ ማድረጋቸው ታወቀ::

ዛሬ ረፋዱ ላይ የህገ ወጡ መጅሊስ አባላት፣ ሲቪልና ፌደራል ፖሊሶች፣ እንዲሁም ወደሃያ የሚጠጉ በእድሜ የገፉ ሴቶች አንድ ላይ በመሆን የሴቶችን መስጂድም ጭምር በማስከፈት ወደመስጂዱ በመግባት ቦታውን የተቆጣጠሩ ሲሆን በመስጂዱ የሚገኙትን ቁርአኖችም ቆጥረው ‹‹መስጂዱን እናሽገው? አናሽገው?›› በሚል እርስ በእርስ መጨቃጨቃቸውን የዓይን ምስክሮች ገልጸዋል፡፡ በመስጂዱ የነበረው ሙስሊም በወቅቱ በዝምታ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየ ሲሆን የዝሁር ሰላት ሰዓት ሲቃረብም ያለማይክራፎን አዛን ተደርጎ ተሰግዷል፡፡

ሁኔታው በዚሁ መልኩ እስከ 9 ሰዓት ከቆየ በኋላ ሰዎቹ የላይኛውን መስጂድ አሽገው ቦታውን ለቅቀው የሄዱ ሲሆን በህገ ወጥ ተግባራቸው የተቆጣውና ዝሁር ሰላቱን ታግሶም ቢሆን የሰገደው የአካባቢው ህዝበ ሙስሊም ግን አስር ሰላት ሲደርስ ሰላት የማይቀር አምልኮ ነውና መስጂዱን ከፍቶ የተለመደ ዒባዳውን ለመቀጠል መገደዱ ታውቋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች ሲገኙ የምናሳውቅ ይሆናል::

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል::
ድምፃችን ይሰማ::


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles