Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በአፋር ክልል ዱብቲ ከተማ አንድ ወጣት ባልታወቁ ኃይሎች ተገድሎ ተገኘ

$
0
0

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
afar kilil
በአፋር ክልል በዱብቲ ከተማ አንድ ወጣት ተገድሎ ተገኘ። ከሁለት ሳምንታት በፊት በዱብቲ ከተማ ሲዒድ አባተ የተባለ ወጣት ባልታወቁ ኃይሎች በከፉኛ ተደብድቦና ተገድሎ መገኘቱን ከቦታው ዘግይቶ ዛሬ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ግድያውን የፈፀሙትን አካላት እሰካሁን አልተያዙም።

ሲዒድ አባተ አፋር ባይሆንም በዱብቲ ከተማ ተወልዶ ያደገና በዱብቲ ወጣቶች ዘንድ የሚወደድ ልጅ እንደነበረ አንዳንድ የዱብቲ ነዋሪዎች የሆኑ አብሮ አደጎቹ ያስረዳሉ። የዱብቲ ከተማ ፖሊስም የዚህ ወጣት ህይወት ማትረፍ እንዳልቻሉና ወንጀለኞችን ፈልጎ ለህግ ለማቅረብ በመጠነኛ መልኩም የጣሩ ቢሆንም እሰካሁን አልተሳካም። አሁንም በከተማዋ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለህይወታቸው እንደሚሰጉ ይናገራሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ የዱብቲ ከተማ የፖሊስ ኮሚሽን ጽ/ቤት አስተያየት ለማካተት ያደረኩት ሙከራ አልተሳካም ።

ሲዒድ ላይ በተፈፀመው ግዲያ በጣም ማዘናችንን እየገለፅን ለወዳጅ ቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>