Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport:ኢትዮጵያ ከወር በኃላ የሚጀመረውን የሴካፋ ዋንጫ ማዘጋጀት እንደማትችል በመጨረሻ ሰአት አሳወቀች

$
0
0

* ሴካፋ በኢትዮጵያ ውሳኔ ክፉኛ አዝኗል!

ኢትዮኪክ እንደዘገበው:-

የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ አገራት የሚሳተፉበት የሴካፋ ውድድር ከአንድ ወር በኃላ November 24 – December 10 በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ይካሄዳል ቢባልም ኢትዮጵያ ውድድሩን ማዘጋጀት እንደማትችል ለሴካፋ በመጨረሻ ሰአት አሳወቀች።
የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የሚዲያ ኃላፊ ሮጀር ሙሊንዳዋ ዛሬ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውድድሩን ማዘጋጀት እንደማችይል የውድድሩ ቀናት በተቃረበበት ሰአት ማሳወቁ መደንገጣቸውን እና ብሎም ክፉኛ ማዘናቸውን ገልፀው፤ ውድድሩን ሱዳን አልያም ታንዛንያ ማዘጋጀት የሚችሉበትን አፋጣኝ ውስኔ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል።
africa_2005-6_1128986520_addis-soccer3
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያልጠበቀ እና ድንገተኛ ውሳኔ ምክንያቱ በይፋ ባይገለፅም ፌዴሬሽኑ የገንዘብ ችግር እንደምክንያት ተቀምጧል። ኢትዮ ኪክ ጉዳዮን ለማጣራት ጥረት በዳረገበት መረጃ ምንም እንኳን ውድድሩ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ቢሆን በፌዴሬሽኑ አካባቢ በምህራብ አፍሪካ የተከሰተው የኢቦላ ቫይረስ ለውድድሩ አማካይነት ከተለያየ የአፍሪካ አገራት በሚመጡ እንግዶች ላይ የመከሰት ስጋት ሊፈጠር ይችላል በሚል እንደሆነም ተሰምቷል።

ኢትዮጵያ ቀድም ባሉት ጊዚያት ውድድሩን ስፖንሰር ባደረጉት ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስያሜ ተሰጥቶት ማዘጋጀቷ ይታወሳል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከወራቶች በፊት ለማዘጋጀት እድሉን ተቀብሎ ውድድሩ ሊጀመር አንድ ወር ሲቀረው ወገቤን ከማለቱ ይልቅ በትክክል የገንዘብ ችግር እና የማዘጋጀት አቅሙ ከሌለው ፌዴሬሽኑ ቀደም ብሎ ለሴካፋ ማሳወቅ ይጠበቅበት ነበር።

በ2013 የሴካፋ ውድድር በኬንያ ሲዘጋጅ
ጎ ቲቪ 11.25 ሚልዮን የኬንያ ሽልንግ ከፍሎ ውድድሩን ስፖንዘር አድርጎታል።
የዘንድሮ ውድድር አዘጋጅ አገር ከተገኘ በውድድሩ ኬንያ፣ታንዛኒያ፣ቡሩንዲ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ጂቡቲ፣ሶማሊያ እና ኤርትራ ተሳታፊ ይሆናሉ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>