በቅርብ ጊዜያቶች ስለ ስኳር በሽታ ይቀርቡ የነበሩ መረጃዎችን አንብቤያለሁ፡፡ በአጠቃላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ በተለየ ሁኔታ ስለ ሃይፖግላይሴሚያ ማብራሪያ እፈልጋለሁ፡፡ ይኸውም በሽታው ሃይፖግላይሴሚያ፣ በደም ውስጥ የስኳር ማነስ ነውና ለምን የስኳር ምግቦችን በሽተኛው እንደሚከለከል አልገባኝም፡፡ እኔ የስኳር በሽታ ተጠቂ ብሆንም ችግሬ የሃይፖግላይሴሚያ (ተረፈ ስኳር) እንዳልሆነ ያወቁ ሰዎች ወይም የነገርኳቸው ጣፋጭ ብቀምስ ምንም እንደማልሆን ይገልፁልኛል፡፡ እንዳሉትም በመጠኑ ሳደርግ ችግሩ ይብስብኛል፡፡ ሆኖም የእግር እንቅስቃሴ ከማድረጌ በቀር የተሰጠኝ ክኒን ባለመኖሩ አላዋቂዎችን ማሳመን ከብዶኛል፡፡ ለማንኛውም ግን ሃይፖግላይሰሚያ ለሃይፐርግላይሴሚያ ቀዳሚ ምልክት ላይሆን የሚችልበት ሁኔታ ካለና ማብራሪያ ብትሰጡኝ እወዳለሁ፡፡
ውድ የአምዳችን ተከታታይ ነፃነት ጥያቄህን ግልፅ በማድረግ አንተ የስኳር ህመምተኛ መሆንህን ነገር ግን ሃይፖግላይሴሚያም (የስኳር ማነስ) ሆነ ሃይፐርግላይሴሚያ (ተረፈ ስኳር) የሌለብህ ቢሆንም ስለ ሁለቱ ማወቅ ግን ትፈልጋለህ፡፡ በአጭሩ ለመግለፅ ያክል በሰውነታችን ውስጥ ትክክለኛ የስኳር መጠን ከ70 ሚ.ግ-110 ሚ.ግ በአንድ ሚሊ ሊትር ደም ውስጥ ይገኛል፡፡
ነገር ግን የስኳሩ መጠን ከ70 ካነሰ አነሰ ስኳር (አይፖግላይሴሚያ) ከ110 ከበለጠ ደግሞ ተረፈ ስኳር (ሃይፐርግላይሴሚያ) ይባላል፡፡ ብዙውን ጊዜ ሃይፐርግላይሴሚያ የምንለው የስኳር ልክ ከሌሎች ምልክቶች ጋር ተደምሮ የስኳር በሽታ ተብሎ ይጠራል፡፡ ከዚህ በተረፈ ሃይፖግላይሴሚያ የስኳር በሽ በህክምና ጊዜ የስኳር መጠናቸውን ለመቀነስ የሚወስዱት መድሃኒት ከበዛ ወይም መድሃኒት እየወሰዱ ነገር ግን በተገቢው ሰዓት ምግብ ካልወሰዱ የደም ስኳራቸው የሚያንስበት ሁኔታ ነው እንጂ ራሱን የቻለ በሽታ አይደለም፡፡ በዚህ ወቅት ተጠቂው ሰው በድንገት ራሱን ይስታል፡፡ ይወድቃል፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ የደም የስኳር መጠኑን ከፍ ለማድረግ ስኳር ቢሰጡት ወይም በጥብጠው ቢያጡት መልካም ነው፡፡ ከዚያም ቶሎ በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል መውሰድ አስፈላጊ ቀጣይ እርምጃ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ የስኳር ህመምተኞች በሌላ ጊዜ በህክምና ላይ እያሉ ጣፋጭ ነገሮች መውሰድ የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም የህክምናው አላማ የበዛውን የደም የስኳር መጠን መቀነስ ነውና፡፡ ጣፋጭ ምግቦች ደግሞ የደም ስኳር መጠንን በኃይለኛ የመጨመር ባህሪ አላቸውና ነው፡፡ ስለዚህ ስኳር ነክ ምግቦች ላይ ጥንቃቄ ማድረጉ የተሻለ ነው፡፡ መልካም ጤንነት እንመኝልሃለን፡፡