(ሚሊየኖች ድምጽ) የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና የሚሊዮኖች ግብረ ኃይል ሰብሳቢ የነበሩት፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው በጸና መታመማቸዉንና ዛሬ በሆስፒታል መዋላቸዉን ለማረጋገጥ ችለናል።
የማእከላዊ እሥር ቤት ብዙ ቶርቸር የሚደረግበት እስር ቤት እንደሆነ ይታወቃል። አቶ ሃብታሙ አያሌው ከብሎገር አብርሃ ደሳታ፣ ዳን ኤል ሺበሺና የዚዋስ አሰፋ ጋር ሐመሌ 1 ቀን የታሰሩ ሲሆን፣ ፖሊስ «መረጃ ለማሰባሰብ ጊዜ ይሰጠኝ» በሚል አራት ጊዜ ለሃያ ስምንት ፣ ሃያ ስምንት ቀናት መጠየቁ መዘገቡ ይታወሳል። በፍርድ ቤቱ የተቀመጡ ዳኞችም፣ ፖሊሲ ምንም አይነት መረጃ ሳያቀርብ፣ የእነ ሃብታሙን የዋስትና መብት በመከልከልና በወህኒ እንዲቆዩ በመፍቀድ፣ ሕግን የሚያስፈጽሙ ሳይሆን ፣ ለሕጉ ዉጭ በቀጥታ የፖሊስን መመሪያ የሚይሳተናግዱ መሆናቸዉን አሳይተዋል።
አቶ ሃብታሙ በአገራችን ፖለቲክ ትግል በዘመናችን የተነሱ አንጋፋ ፖለቲከኛ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ገዢው ፓርቲ በርሳቸው ላይ ኢሰብአዎና ኢፍትሃዊ ግፍ መፈጸሙ በካላላቸው ላይ ጉዳይና ሕመም ቢያስከትለም፣ በመንፈሳቸው ግን ከመቼዉም ጊዜ በላይ ጠንካራ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል።
ሃብታሙ አያሌዉን በሰልፍ ላይ !