አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሆኑት አቶ አሚን አብዱልካድርና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እስማኤል አሊስሮ በኤሊ ዳአር ወረዳ በማዳ ከተማ የሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ አደሩ።
ትናንት ማታ 10:00 ሰዓት ሲሆን በቡሬ ወደ ማንዳ የገቡት እኚህ ባለስልጣን ህዝብ እንዳያያቸው ተደበቀው እና በልዩ ኃይል ፖሊሶች ታጅበው ማለፋቸውን ምንጮችን ዘግበውልናል። እነዚህ ባለስልጣናት ወደዚህ የመጡበት ጉዳይ በውል ባይታወቅም ወደ ኤሊ ዳዓር ወረዳ የመጣነው የዓለም የባህልና የቱሪዝም ቀንን ለማክበር ነው ሲሉም ተደምጠዋል።
ከፈደራል የመጡ አንድንድ የመከለኪያ መኮነኖችም አብረዋቸው እንደነበሩም ታውቋል።
በአሁኑ ሰዓት በዛ አካባቢ የኔትዎርክ አገልግሎት ተቆርጠው ይገኛል።
በሌላ ዜና የአፋር ክልል መሪዎች በየቀኑ የኢሳት ዜና እንደሚከታተሉ አንድ ስሙን ሊነግረኝ ያልፈለገ ባለስልጣን ነግሮናል። በአሁኑ ጊዜ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገሮች ታማኝ መረጃዎች ለህዝብ እያቀረበ ያለው የኢትዮጵያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን በየቀኑ በየቤታቸው የሚከታተሉት ታማኝ መረጃ ለማግኘት መሆኑን ከእነዚህ ባለስልጣናት መረዳት ተችሏል። እንደያውም አቶ እስማዒል አሊ ሴሮን ጨምሮ ብዙዎቻቸው ዜና በሰሙት ቁጠር «እውነታቸው ነው» እያሉ ለኢሳቶች ምስክር እንደሚሆኑ ታማኝ ምንጮችን ነግረውናል። በተለይ በኦጋዴን ህዝብ ላይ የተፈፀመው ጨፍጨፋና የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚደንት የነበሩት ኡሞድ ኡባንግ ሰላደረጉት ቃለ ምልልስ አቶ እስማእል በስሜት በመሆን «የሰማሁት ሁሉም እውነት ነው» በማለት እንደመሰከሩ ሰምተናል። አብዛኛው የአፋር ክልል መሪዎች የሚችሉት የአፋርኛ እና አማርኛ ቋንቋ ብቻ ሰለሆነ ኢሳትን ለመከታተል ኢሳት የሚገኝበትን ሳተላይት በገንዘብ እንዳሰሩ ምንጮቻን ገልፀዋል።