Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ስበር ዜና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ህክምና ላይ የሚገኙት የአቶ በረከት ስሞኦን የጤነት ሁኔታ እያነጋገር ነው።

$
0
0

bereketእሁድ ከአዲስ አበባ አንድ የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ዶ/ር አስከትለው በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን እኩለለሊት ጅዳ ስውዲ አረቢያ ለህክምና በሚስጠር እደገቡ የሚነገርላቸው አቶ በረከት ስሞኦን በተለምዶ ብግሻን እይተባለ የሚጠራ አንድ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የልቡ ደም ቧንቧ ለማስፋት የተደረገላቸው መሆኑን ከሳውዲ አየር መንገድ ምንጮቻችን ለማረጋገጥ ተችሏል ። የመንግስት ባለስልጣኑ ጤንነት በአሁኑ ሰዓት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የሚገልጹት እንዚህ ምንጮች ዛሬ ጠዋት ከመካ የዒድ አል ፈጠር የፀሎት ስረአት ባሃላ ሼክ አላሙዲን በስልክ እንዳነጋገሯቸው ይናገራሉ። አቶ በረከት ስመኦን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ በድብቅ መምጣታቸውን የሚናገሩ እንዚህ የሳውዲ የአየር መገድ ምሲጥራዊ መረጃዎች ባለስልጣኑ በአሁኑ ሰዓት ጅዳ ሆስፒታል መተኛታቸው በተለያዩ የዜና ማስራጫዎች በመዛመቱ ህክምናቸውን በተረጋጋ ሁኔታ ሳይጨርሱ ወደ ሃገር ሊመለሱ እንድሚቸል ገልጸዋል።


እስካሁን የመንግስት መገኛኛ ብዙሃን በኚህ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ዙሪያ ምንም ያሉት ነገር አለመኖሩን የሚናገሩ አንዳንድ ወገኖች የአቶ በረከት ስሞን ተደብቆ እንድተራ ሰው ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ሆስፒታል ለህክምና መግባት ምናልባተም ለደህንነታቸው ሲባል የተወስደ እርምጃ ሳይሆን እንደማይቀር ይገምታሉ። ጅዳ ብግሻን ሪፈራል ሆስፒታል 4 ፎቅ ከበሽታቸው በማገገም ላይ እንደሚገኙ የሚነገረው አቶ በረከት ፍጹም መረጋጋት እንደማይታይባቸው የሚያመለክቱ መረጃዎች የባለስልጣኑ የደም ግፊት አለመስተካከል በልባቸው ላይ የሚያሳድረው ተጸኖ ወደፊት ለከፍተኛ የጤና መታወክ ሊዳርጋቸው እንደሚቸል ገልጸዋል ።


በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን ተደብቀው ለህክምና ትላንት ለሊት ሳውዲ ጃዳ ስለገቡት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አቶ በረከት ስሞኦን በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ሆነ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ምንም የሚያቁት ነገር እንደሌለ ለማረጋጋጥ ተችሏል። አቶ በረከት አንድ ሴት ልጃቸውን እና ሚስታቸውን አስከትለው መምጣቸውን የሚናገሩ የአየር መንገዱ ምንጮቻችን ባለስልጣኑ በተረጋጋ ህክምና ላይ አለመሆናቸውን በተጨባጭ ማረጋገጥ ተችሏል ። ይህ በዚህ እንዳለ በአሁን ሠዓት መካ ፀሎት ላይ የሚገኙት ሼክ አላሙዲን ማምሻውን እኚህን የመንግስት ባለስልጣን ይጓበኞቻዋል ተብሎ ይጠበቃል። በአቶ በረከት ዙሪያ የሚደርሱንን አዳዲስ ተጨማሪ መረጃዎች እይተከታተለን የምናቀርብ መሆኑንን እናስታውቃለን ።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>