Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ታማኝን ጠብቁ! (ከሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 28.07.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

ታሪክ ራሱን ሲሳራ

ዘመን አፈራ

በተግባር ጎመራ!

tamagne beyene

ታማኝ በየነ

እኔ እህታችሁ ትንሽ ነገር ቆጣጥሬ ከች! እንሆ ዘንድሮም አርቲስት ታማኝ በዬነን አገኘሁት ከምል አዬሁት ልበል። አገኘሁት የምለው በሥርዓት እንደ አባት አደሩ ቁጭ ብዬ ከእሱ ጋር ወግ ቢጤ ሳደርግ ነው። ታማኝም ለእኔ እራሱን የሰጠ ነው ብዬ ነው የማስበው። ስለሆነም  ስለምን ይህን እላለሁ መሰላችሁ አሁን እኔው ሥርጉተ ከዚህች ከብዕር ቀለምና ከብራና ወጥቼ መኖር ፈጽሞ አልችልም። ሳስበው አራሱ ጭንቅላቴን መሸከም ይከብደኛል። አልገርምም ግን? ማሰቡን እንኳን አልችለውም ….

አይዋ – ጥበብ በውስጥ ሲያድር ሲውል ሲኖር መንፈስህን የመግዛት አቅሙ ከታላቅ ሐዋርያ ስብከት በላይ ነው። ፈቅደህ ወደህ ትገዛለታለህ። ቁጭ አድርጎ ጎልቶ አውሎ ያሳድርሃል። ከቤቱ ፈቀቅ ብለህ በሌሎች ነገሮች ላይ አትኩሮትህ ማዘንበሉን ሲያውቅ ጥበብ ቀናተኛ ነውና አዲስ ሃሳብ ጭሮ ሲያስጨርህ ውሎ ያድራል። ወይ ከራስህ ጋር ወይ ከዚህች ፉንጋ ዓለም ጋር ወይ ከተንጣለለው ሰማይ ላይ ወስዶ ወይ ከማራቶኑ ንፋስ ጋር ወይ ደግሞ አውሮፓና አሜሪካ ላይ ጉዝጓዝ ተጎዝጉዞ አለሜ ለምለሜ ከሚባልት እሜቴ ጠሐይ ጋር ወይ ደግሞ አራት የመብረሪያ እግረ –  ከተሰካላት ዥግራ ጋር ብቻ ከሆነ ከሚታይ ከሚጨበጥ ከማይታ በምናብ ከታላመ ልቅ ዓለም ጋር እያፈታገ ገርቶ ይደቁስህና ቅመሙ ሆነህ የዓለም መንፈስ ማጣፈጫ ያደርገኃል። ፍትልክ እላለሁ ብትል አስገብቶ ቤቱ ውስጥ ቁልፍ።

ዘበኛ ወታደሩ የአይዋ ጥበብ ማለቴ ነው፣ መዘዘዣ ጣቢያው፣ ተናጋሪው – አናጋሪው፣ አድመጩ እሱ እራሱ ሆኖ አስደግድጎ ይገዛሃል – ይነዳሃል። እንግዲህ ይህን ሰንሰለት ተጋፍቶ ጥሶ የወጣ ነው አርቲስት ታማኝ በዬነ ማለት። የጄኒራል ሥነ ጥበብ ጠቅላይ አዛዥ ከነሠራዊቱ ሽንፈት ግቶ ገዥ መሬቱን በመቆጣጠር አይዋ ሥነ – ጥበብን አፍንጫህን ላስ ያለ የነጻነት የፍቅር ሙሴ ነው ኢትዮጵያዊው ታማኝ በዬነ።

ከዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ሲወጣ ፈተናዎቹ ትሬኮለታ ናቸው። ስለምን? ጥበብ በውስጡ ካደረ ሰው ጋር ሲኖር ህይወቱ ሌላ ነው። ትገባባለህ። ትደማመጣለህ። ትተሳሰባለህ። እሰዎታ እንኳን ታላላቆቻችን የሻሩት ያልተጻፈ ህግ አካል ነው። ለቅጽበት ጥበብ ከጎበኘው መንፈስ ጋር ስትገናኙ ግንኙነቱ ረቂቅ የአንደምታ ሚስጥር ነው። የጥበብ ሰው ትርጓሜው ቅኔ ነው። እኔ እንደ ድቃቂነቴ ሲወዘርላንድ ውስጥ ከነጠሩ የጥበብ ሰዎች ጋር ተገናኝቼ መኖር የምጀምርበትን በትጋት እጸልይለት ነበር። ጸሎቴ ግን የጥበብ ሰው ሆኖ ሰነፍ ያልሆነ። ላንቁሶ ያልሆነ። በራሱ መቆም የሚችል። ከዘራ የማያስፈልገው። በመንፈሱ ውስጥ ባሉ ሴሎቹ ብቻ ለመኖር የቆረጠ። ሳንባው የሥነ ጥበባት ህገ መንግሥት የሆነ። ለሥነ ምግባሩ ስለ እውነት ለእውነት ስለ ሰብዕ ታላቅነት የማይገሰስ ተፈጥሯዊ መብተ – ውበት በውስጡ፣ በመንፈሱ ያደረበት ሰውን ፍለጋ መንፈሴ ብዙ እሩቅ ሲጓዝ ኖረ። የሥነ ጥበብ ቋንቋ አሃቲ ነው። ዓለም የምትግባባበት አንዱ ብቸኛው ቋንቋ ሥነ ጥበብ ብቻ ነው። ሥነ ጥበብ ዓለምና ውስጧን የፈጠረ የታላቁ አባት የአማኑኤል ምርቃት ነው።

አሁን ትንሽ የቀናኝ ይመስለኛል። ጥበብ በውስጡ ማደሩ ብቻ ሳይሆን ጥበቡ እሱን የሆነ ሰው አድርባይ አይሆንም – በፍጹም። ሃቅን ፈልጎ የግንባር ሥጋ ሆኖ ይማገዳል። ጥበብን ዬማድመጥ አቅሙ ብቁ እንዲሆን የሚያደርገው በእሱ ውስጥ ያደረው ጥበብ ውስጡን እሱ በእሱ የጠለፈው ከሆነ ብቻ ይሆናል። ታዲያ እንዲህ ያለ ሰው ለማግኘት ህልም ነበር። አሁን እግዚአብሄር ይመስገን ጥበብን ማደመጥ፤ ቃናውን ማጣጠም፤ ምቱን መተወን የሚችል አንድ ቀዳዳ ከተገኘ ብዙ ተግባር ይከወናል። ጥበብ እራሱ አንተን ፈጥሮ ብቃትን የመሸለም አቅሙ ቀለሙ ሰማያዊ ነውና።

ታማኝ ለጥበብ ሰው ያለው ፍቅርና አክብሮት ሃብቱ ነው። የጥበብ ሰውም ታማኝ ከሚለው ይልቅ የሥነ – ጥበብ ቋንቋ ቢለው ይቀል ይመስለኛል። ግን ለምን ይመስለኛል አልኩ? ነው! በሥነ – ጥበብ ሰው ዙሪያ ያለው ፍቅር የማያብል ነው። ከዚህ ማዕቀፍ ወጥቶ ካለ ጸጋውና መክሊቱ እራሱን ፈቅዶ በልመና ተግባር ላይ ማሠማራቱን ስታዩት ታማኝን ለነፃነት ትግሉ ራሱን ያሸነፈ የሥነጥበብ የአዲስ ዘምን ጮራ ነው!  ምዕራፍም! ታሪክ ራሱን ሲሰራ ዘመን እንዲህ አንደበቱን ከፍቶ ይናገራል! ይመሰክራል።

ክብረቶቼ ይህን ስል እራሴን በእሱ ቦታ አስቀምጬ ስመትረው፤ እራሴን በምንም ዓይነት ቀመር ከሥነ ጥበብ አውጥቼ ልኖር እንደማልችል ስለማውቀው ነው። ጥሪቴም ሃብቴም ይሄው ብቻ ስለሆነ፤ መተንፈሻ ቧንቧዋን ዘግታ መኖርን ሥርጉተ አታሰብም። ታማኝ ግን አድርጎታል። ስለዚህ ሥነ – ጥበብ የሚያውቅው ታማኝ ዛሬ ፊታውራሪ መደረክ አሱን እዬራባው ግን ቁንጥጥ አድርጎ፣ ክርኒውንም አክሎ፣ ደልቆሶ፣ አሳምሮ ቀጥቶ ለህዝብ ትንፋሽ ለሆነው ለኢሳት የጥበቡ አበወራ የመድረኩ ልዑል ከረባቱን አስሮ ይለምናል።

10.00 (10.00 CH) የሲዊዝ ፍራንክ ለታማኝ ብዙ ናት። አክብሮ ዝቅ ብሎ ይቀበላታል። በሙያው ቢሆን ደግሞ የሚሊዮን ዶላር ታማኝ በሆነ በነበረ። አንድ አጭር የእንግሊዘኛ ኮመዲ ቢሠራ የዓለም የፊልም ማዕከል ሆሊውድ እጁን ስሞ ይቀበለዋል። እሱ ግን ይሄው መተኪያ የሌለውን ጸጋውን አፍኖ፤ ከድቶ፤ ጨቁኖ ለህዝብ ዕንባ ይባትላል። ስለዚህ ታማኝ ለእኔ ለጸጋው – ለመክሊቱ  የጨቋኝ ጨቆኝ ነው። ጨቆኝነቱን ሲፈቅደው የሚበልጥበት ለምልዕት ዬዕንባ ጥሪ ለማደር መቻሉ ነው።

ታማኝ መቻል ነው። ቅርጥምጣሚ – ቅንጥብጣቢ ያላችሁ ታማኝን በሸፍጥ ታሪኩን ለማክሰል የምትሹ ታማኝ በመሆን የደመቀ ከወርቅ ገበር የተሠራ አንጡራ የህዝብ ሃብት ነው። ታማኝ መተኪያ የለውም።  ለእኔ ታማኝም እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ ሽልማቴም ጀግናዬም ነው። ይህ አገላለጼ  የማይመቻቸው የነፃነት ትግሉ ጥቂት ወገኖቼ ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን ማስተዋል እንዳለባቸው በትህትና ዝቅ ብዬ ለሳስባቸው የምሻው ብልህ ቁምነገር አለኝ። ስናጣው ሳይሆን በእጃችን ሳለ ክብሩን – ተሳትፎን – ብናከብርለት ነው የሚበጀው። በማናቸውም ሁኔታ ታማኝ ነገ ሊገጥመው ስለሚችል ማናቸውም ሁኔታ አናውቅም። ጦርነቱ የእርስ በእርስ ነው። ቢያንስ እያለ – እዬሰማን – እያዬነው ለመንፈሱ ጥንቃቄና ጥበቃ ልንደርግለት ይገባል ባይ ነኝ። አቀባባል ሲደረግ እንኳ የሚያርመጠምጣቸው እንዳሉ ሁሉ መሰናከል የሚፈጥሩ አሙካዎችም አሉ። የታማኝ ፍቅር የተገኘው ፈተናን አሸንፎ ከተፈጠረው ኢትዮጵያዊነት ወራጅ ወንዝ ሳይሆን ከምንጩ ከፏፏቴው የተቀዳ ነው።

ጠላትን ስንጠላ ጠላት የማይፈልገውን ነገር አዘውትረን ተግተን በመሥራት በባለቤትነት ስሜት በመከወን ነው። እኛ ደግሞ አብሶ ዬነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች በወያኔ ላይ ከምንሰነዝረው ጥይት ይልቅ በወገናችን ላይ የምንለቀው የቦንብ ናዳ ይልቃል። ወይ ይበልጣል። እኔን ዬሚታገለኝ ቀፎ የነፃነት ትግሉን በነቀዝ እያሳረረ የወያኔን ተክል በእንክብካቤ እንደሚያስድግ አያወቀውም።  ከእንግዲህ ግን እንዲህ እዬተላላሱ መቀጠል አይቻልም። በፍጹም። አንድ የነፃነት አርበኛ የሁለቻንም ሃብት ሆኖ ሰፊ ጥበቃ ማደረግ ስንጀምር የወያኔ ከበሮ መተንፈስ ይጀምራል። ተሰውረው ሲበሉን የነበሩ የራሳችን ተወሳኮችን በሙሉ በአደባባይ ወጥተን የምናጋልጥበት ዘመን ላይ ነን። ቀደመው እራሳቸውን ወቅሰው ከእኩይ ተግባራቸው ከተመለሱ እሰዬው ነው። በስተቀር ጉሩቧቸውን እናንቃቸዋለን። ማረገፍ ደግሞ በውጪ ላለው ኢትዮጵያዊ የተመክሮው ማሳ ፍሬ ገብ ነው።

ከረንት ቤቴ ሲዳከም እኔን ሊጎረብጠኝ ይገባል። የእኔ መጎርጥ ደግሞ በኢትዮጵያዊ ብቸኛ ተቋሜ ላይ ጥቃት በሰነዘረው ጠላቴ ላይ በእጥፍ ረመጥ ልኬ እንዲጎረብጠው – እንዲያርመጠምጠው የማደረግ አቅሜን በታታሪነት በመገንባት ነው። አቅምን ለሚሸረሽር ስንኩል ጊዜ የለንም! ትእግስትም ከተፈጥሯችን ተፍቋል! የጀግናዬ አንዳርጋቸው ጽጌን ሁለተኛውን ቪዲዮ መዳፉን ተመልከቱት በማሳተዋል ሆናችሁ። ተፈጠሯዊ ወዙ በኤሌትሪክ ተራቁቷልነጭ ሆኗል ታዲያ ከእንግዲህ በኋላ ለዬትኛውም ጥሙርሙር አቋም ነው ትእግስቱ ልክልኩ የሚኖረን?! አይታሰብም!

(No Tolranz more! )።

የማከብራችሁ ወገኖቼ የነፃነት ትግሉን ወያኔ ከወጋው – ካዳካመው በላይ በነፃነት ትግሉ ስም የተሰገሰጉ አቅመ – ቢስ ተባዮች የነፃነት ትግላችን እንደ ቅንቅን መሬት ለመሬት የበሉት በእጅጉ ይበልጣል። አንድ የነፃነት ታጋይ ከእሱ ጋር በአንድ የወያኔ ባሩድ ለሚሰዋው ወገኑ አንዲት ዘለላ መልካም ምስክርነት ቢሰጥ 100 ኪሎ ስለ አጋሩ የሚሰጠው አሉታዊ ነገር ይሆናል። ይህ ነበር ጠመዝማዛው ጉዟችን። ሥርጉተ ሥላሴ ወይንም በፓልቶክ ሥሟ ሥርጉት ለኢትዮጵያም የጥቃቱ ሰለባ ነበረች። ከእንግዲህ ማናቸውም ተቋም፣ ድርጅት፣ ግለሰብ ስለ አንድ ሰው ብቃት – ታታሪነት – ትጋትና ታሪክ ለሚበክል አቅመ ቢስ በዘመቻ ተነቅሎ እንዲወገድ ዬማድረግ ሂደቱን ሊያዘወትሩበት ይገባል። ይህን ህዝባዊ ሃላፊነት መርኃቸውና መሪያቸው ማደረግ ይኖርባቸዋል። በስተቀር ዘመቻ አንዳርጋቸው በስውር ትል ይወረራል። ይህ ነበር እዬተሰበሰበ የሚበትነን፤ እዬለቀምን ስናፈሰው፤ ከእጅ የገባውን በተመክሮ የከበረውን አፈስን ሌላ ስነለቅም የየኖርነው፤ ሁል ጊዜ ለጋ፤ ሁል ጊዜ ታቱ እንድንል ይፈለጋል። ሁለመናችን ስናባክን አቅማችን ስናሾልክ የኖርነው የድክመታችን የጨለማ ታሪክ። ስለሆነም አታዳምጧቸው የኢጎ አርበኞችን! ሰው በወደደው ይደራጅ፤ ሰው በፈለገው ይሰባሰብ አቅም በዚህ መለክ እንዲሰባሰብ ቅንነትን ልቀሙ ከፈሰሰበት – መሪዎቻችን – የነጻነት ትግሉ ማናቸው ድርጅቶች ሁሉ!

ወንድሜ ታማኝም የዚህ ዘመቻ ተጠቂ ነውና በተለይ በተለይ ውጭ ያላችሁ ወጣቶች አርበኛችሁን ጠብቁት። ስእለሱ በሚሰነዘሩ ነገሮች ሁሉ አልሰማም አላይም ብላችሁ ጆሯችሁን ቀርቅሩ። አሳፍሯቸው! እሱ በሚገኝበት መድረክ ሁሉ ከሥር ቅጥል ንድድ እርር የሚሉ ተኩላዎች አሉታዊ ነገር ይጽፋሉ። እናንተስ እጃችሁን ማን ያዘው? አስታጥቋቸው። ከሥሩ እናንተም አድናቆታችሁን አክብሮታችሁን ለግሱ። ጥበቃ ይሏችኋል ይህ ነው። መረጃ አነሰ አደገ ሳትሉ ወዲያውኑ በፌስ ቡካችሁ ላይ ልቀቁት።

ታማኝ የእኛ እኛም የታማኝ ብለን መነሳት አለብን። ታማኝ ብቻ አይደለም የሰሞናቱ የወያኔ የዜና ማሰራጫ የሚያላዝነው ዬጀግኖቻችን ዝርዝር አለ። አዎን የእኛ ጀግኖቻችን ቀንዶቻችን ዓይኖቻችን ናቸው! የምናከብራቸው የምንወዳቸው የታሪካችን ሙሴዎቻችን ናቸው! እነሱ በሚገኙበት ቦታ ሁሉ መገኘት-  በአካል። ጥበቃውን ማደረግ ከእኛ ይጠበቃል። ሳንገኝ ስንቀር ደግሞ ባለመቻል ከሆነ የተገባውን ግዴታ መወጣት። ፍቅር ፈሪ አይደለም። ኢትዮጵያ ፍቅር ናት። ልጇችም የፍቅር ልጆች ከሆኑ የፍቅርን የድፍረት ተፈጥሮ ውሰጥ ያደረጉ ናቸውና መሆን ይቻል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ባንዳ ሆና አታውቅም። ኢትዮጵያ በታሪኳ ተሸንፋ አታውቅም። ተላጣፊውን ቅብ ታሪክ የወያኔ አሽኮኮዎች ያላዝኑት። በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሰላም አግኝቶ የተውለበለበ የጠላት ሰንድቅ ዓላማ አልነበረም። ህዝቧም ባንዳ ሆኖ አያውቅም። ሆድ አደር ግለሰቦች ግን ነበሩ። ልክ እንደ አሁኖቹ አረሞች ….. የባንዳ ወያኔን አምሳያ ፍላጋ የሚፈሱት ዝብጥ ታሪኮችን አንከባሏቸው።

ለማንኛውም ባተሌው ወንድሜ ታማኝ እንዴት ሆኖ ይመጣ ይሆን ብዬ ሳዬው በተደላደለ መንፈስ፤ በተረጋጋ ህዝባዊ ፍቅር ተልዕኮውን ለማሳካት በ2013 ካዬሁት በልጦ ነው እኔ በግሌ ያገኘሁት። ሲዊዘርላንድ ትንሽዬ ሀገር ናት። ስለሆነም በ26.07.2014 ሁለት ሠርግ ነበር። ቅዱስ ገብርኤል ንግሠ – በዓልም ነበር። ዝግጅቱ ምሽቱን የሚቀጥል ስለነበረ የሮመዳን ፆሚዎችም ነበሩን። በቅርብ ሳምንታት ሁለት ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል። ግን ይገርማል ካለፈው ድንቅ የጄኔቡ ጉባኤ  በእጥፍ ታዳሚ ነበረው። መንፈሱ – ሙቀቱ – አክብሮቱ ጥረቱ መሰናዶው ሁሉም አንቱ ነበር።

በ2013 አርቲስት ታማኝ  በዬነ ቁጭ ብሎ ጨረታውን ሌሎች ወገኖቹ ነበር የመሩት። ዘንድሮ ግን እሱ እራሱ በሚፈልገው መልክ ታዳሚውን እንደ ምሽት የማህሌት ቅኝት አሳምሮ ከሸነው። ዘና ባለ በተፍታታ ገጽ ነፃ በሆነ ህሊና  ዬዕንባን ሃዲድ በመንፈስ አስተሳስሮ በውል ቋጠረው። የሚገርመው ከቤተ እግዚአብሄር ዘግይተው ለሚመጡት ሳይቀር ቦታ ተይዞ ነው የጠበቃቸው። ቀድመው ግምት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነገሮች ሁሉ በሚገባ የተደረጀ ተግባር ነበር የተከወነው። ነገም የጀግና አንዳርጋቸው መንፈስ አይተኛም አያንቀላፋም። ሲዊዘርላንድ ብዙ የተከደነ ሲሳይ ባለሃብት ናትና ተግባር ቀድሞ ሥም ዝና እንዲሁም የግል ኢጎ ተቀብሮ በሁሉም መስክ የተቀነባባረ ተግባር ይሰክንበታል። ዬእነዚህ የሲዊዝ ኢትዮጵውያን የተግባር አናባስት ተግባርም እንዲህ በአደባባይ ጎምርቶ ይከተባል። የባንዳ ዝርያ ስሌለብን አርበኝነታችን ተግባርን አስብሎ አብነቱ እንዲናገራ ይደረጋል እዚህ ሲዊዘርላድን ወስጥ!

የትናንት የሲዊዘርላንድ መሠረት ያያዘ ተግባር ዛሬም ይቀጥላል።

ሌላ አስቲ አንድ …. ግብዣው ከስክሱ። በዚህ ሊንክ ገብታችሁ። ሥርጉተ ሥላሴ ትባላላች ሰብሳቢዋ የከርንቷ ሥርጉት ለኢትዮጵያ ሌለኛ የሥጦታ ሥሟ፤ ጀግናውንም እዬዩት ሥራው ፍላጎቱን ተረካቢዎች አሉት …. ጌጥ የለም! ምቹት የለም! ዘመቻ እንዳርጋቸው ዕውን ይሆናል!  አረሞች ስሙኝ ልነገራችሁ እናንተ የምታስቡት የግንቦት 7 አባላት ተመዝግብው ወርሃዊ ክፍያ ዬሚከፍሉትን ብቻ ነው። ለእኔ ግንቦት 7 የበኸር ልጄ ነው። ግንቦት ማህደሬ ነው።  ግንቦት 7 ቁጥር ሥፍር የሌላቸው የመንፈስ ልጆች አሉት።  ይህ ደግሞ ለወያኔ ምጣና ማጥ እንደሚሆንባችሁ ነው! አትመጥኑትማ!

 

ክወና ——– እያዋት አሸባሪዋን ሥርጉተ ሥላሴን! ከጀግናዋና ከሽልማቷ ጋር!

http://www.ethiotube.net/video/3299/Andargachew-Tsige-at-Ginbot-7-Meeting-in-Germany–Part-1

http://www.ethiotube.net/video/3301/Andargachew-Tsige-at-Ginbot-7-Meeting-in-Germany–Part-2

 

የ2013  ጹሑፏን ደግሞ እንዲህ አንብቡት! አንዳርጋቸው የጭንቅላቴ ልብ ነው!

 

http://sebiawi.blogspot.ch/2013/09/blog-post_5448.html

 

ውስጤንና መንፈሴን ለነፃነት ትግሉ ቀጠይ ትግል ለልዕልት ኢትዮጵያ ሸልሜ ከመሰናበቴ በፊት አንድ ነገር ልበል ግርማዬ ለሆነው ለዘሀበሻ ዝግጅት ክፍል ዝቅ ብዬ ምስጋዬን ላቅርብ! ዘሃበሻንም እንርዳ! አብሶ ለሴቶች አብነቱ ገድል ነው!  ለነበረን ጊዜ እጅግ አመሰገንኩኝ! ውድድ! እያጣማችሁ ሽው — ለዛሬ!

 

የጀግናዬ መንፈስ ውስጤን ሰጥቼ እንድተጋ ስላደረገኝ አመስግነዋለሁ ፈጠሪዬን!

ሰማዕቱ አንዳርጋቸው ምንግዜም ህያው ነው! 

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ!

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>