Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

4 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጠፉ

$
0
0

orgon
(ዘ-ሐበሻ) በሃይዋርድ ፊልድ ኦሪገን (አሜሪካ) የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ የመጡ አራት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መጥፈታቸውን የኦሪገን ዩኒቨርሲቲ ቃል አቀባይ ሚስ ጁሊ ብራውን አታወቁ።

ከጠፉት አራት የሚሆኑት አትሌቶች ውስጥ 3ቱ ሴቶች መሆናቸውና አንዱ የ17 ዓመት ወጣት ወንድ መሆኑን ያስታወቁት ቃል አቀባዩዋ ከቅዳሜ ጀምሮ የደረሱበት ባይታወቅም ምናልባትም ከጓደኛና ከቤተሰብ ጋር በሌላ ስቴት መኖር ሳይጀምሩ እንዳልቀሩ ያላቸውን ግምት ሰጥተው “ሆኖም ግን ይህንን ከአትሌቶቹ ማረጋገጥ አልቻልንም” ብለዋል።

ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዌብሳይት መረዳት እንደተቻለው 17 ሴቶች እና 13 ወንዶች ለዚህ ሩጫ ወደአሜሪካ የመጡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 4ቱ ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የተሰወሩ ሲሆን የፖርትላንድ ፖሊስ፣ የአሜሪካ ፌደራል ፖሊስ እና ሌሎችም በፍለጋ ላይ መሆናቸውን ዘ-ሐበሻ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

እነዚህ የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ምናልባትም የፖለቲካ ጥገኝነት ሊጠይቁ ይችላሉ የሚል ግምት እንዳለው ሪጅስተር ጋርድ የተባለው የኦሪገን ጋዜጣ የዘገበ ሲሆን ጋዜጣው ባወጣው ዘገባው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ እስር፣ ሽብርተኛ ተብሎ መንገላታትን፣ እንዲሁም ሌሎች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትኩሳቶችን ዘርዝሯል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>