Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የአንዳርጋቸውን የአርበኝነት መንፈስ በታጠቁ ቁርጠኞች ዬዓለሙ ዐጤ (UNO) መዲና ጄኔባ ቀውጤ ሁኖ ዋለ።

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 08.07.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

ምዕራፍ አንድ – የሲዊዝ ትንታግ የኢትዮጵያዊነት አርበኞች ዛሬ እለተ ማክሰኞ በ08.07.2014 በዓለሙ ንጉሥ የተባበሩት መንግሥታ ፊት ለፊት እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው የታላቁን የነጻነት አርበኛ የአቶ አንዳርገቻውን ጽጌ ቅዱስ መንፈስ ታጠቀው ጄኔባን በቁጣ ሲኑጣት ዋሉ። „እኛ አንዳርጋቸው ነን አሉ አደራን ለመረከብ በሰነቀ ቁጣ“

Andargachew2የአንዳርጋቸው የመንፈስ ልጆች ጀግናችን – አርበኛችን  -አሸባሪ ከተባልም እኛም አሸባሪ ነን ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት ጽ/ቤት ፊት ለፊት የውስጣቸውን ቋያ  በእርግጠኝነትና በድፍረት አደባባይ አውለውታል። ሰልፈኞቹ ቃላት ሊገልጸው በማይችል ቁጣ በወንበዴው – በሽፍታውና በአሸባሪው አረም የጎሳ ድርጅት፤ በወያኔ ያላቸውን ቁጣ እስከ ዬሚመካብት ትምክኽቱ ድረስ  ይቃጠላል በማለት በ በአለሙ ዐጤ ደጅ ላይ እልል እያሉ በሰደድ እሳት አቃጥለውታል።። የሉዕላዊነታቸው ጉዳይ ያርመጠማጣቸው፤ የአንድነቷ ጥቃት የበላቸው፤ የነገ የትውልዱ ተስፋ ያንገበገባቸው የጭምቷ ሲዊዝ „ዘመቻ አንዳርጋቸው ለነጻነት“ ቤተሰቦች እጅግ ልብን የሚመስጥ፤ ህሊናን የፈተሽ የተቃውሞ ሰልፍ ነበር ያካሄዱት።  ነፃነትን ፈላጊነታቸው ከመሪያቸው – ከምልክታቸው ነፃነት ጋር በትግላቸው አምጠው እንደሚውልዱት በመግለጽ አሸባሪን መደገፍ ውርደት ነው ሲሉ ዬዐጤውን የመንግሥታት ጽ/ቤት ክፉኛ ወቅሰውታል። በተጫማሪም በስውር ደባ ለወንበዴ ቡድን አሳልፎ የሸጠውን ዬዬመን መንግሥትና በቸልታ በደሉን ያዬውን የእንግሊዝ መንግሥትንም አፍርንልህ ብለውታል። ቁጣው ነዲድ ነበር። ቁጣው የጋመ ነበር። ቁጣው ይጋረፍ ነበር። ነፍስ ያለው – ነፍስን የሚታደግ ጥቃትን ያወጣ፤ ወገናዊነትን – አለኝታነትን  በማተበኝነት ያስተገባ፤ የተፈሪዎች ድባብ የረበበት ቀላማም ሰልፍ ነበር ማለት ይችላል።

በዛ በተንጣለለ የወልዮሽ የነጻነት ጥማት ልዩ የቁጣ – የብስጭት ድምጽ ቦታ ላይ የሌላ ሲዊዝን ለመጉብኝት ከተለያዬ አህጉራት የመጡ በርካቶች፤ እንዲሁም ነዋሪው በመስቀለኛው መንገድ አሽከርካሪውን ተግ አድርጎ ህሊና ያለው ሁሉ የሳበ፤ የመቅረጫቸውን ቀልብ የወደደ – ስለነበር በሁሉም አቅጣጫ የአርበኞች የሚንቀለቀል ብሄራዊ ስሜት በለስ የቀናው ነበርም ልበል።
የሰልፈኞቹ ውስጥን የፈተሸ አኃታዊ ድምጽ የቁርጥ ቀን ልጅነታቸውን ማስመስከር ብቻ ሳይሆን፤ ከመከራው ሁሉ ጋር ለመጋራት የወሰነ ልብን የነካ ህሊናን የፈተሸ ያናገረም ደፋር ነበር ማለት ይቻላል። በቁጣ የቆሰለው መንፈስ ውስጡን ገለጥለጥ አድርጎ በመንግሥታቱ ጽቤት ቢሮ ሲያስተገባ የአንዳርጋቸው አብዮት በሲዊዘርላንድ አፍቃሪዎቹ  በዛ ደማቅ የማንነታቸው መግለጫ በሆነው ቀደምት ሰንደቅዓላማቸው ሥር የአባቶቻችን ታሪክ ይደገማል በማለት የመንፈስ ኪዳን ነበረበት። ሰልፈኞቹ ወያኔ በዘውዳችን ላይ የወሰደውን የበቀል እርምጃ በእጥፍ ይምለሳዋል በማለት ያላቸውን ጉልበተኛ አቅም ለማሳዬት መቁረጣቸውን በሙሉ ልብ አትመውበታል። ዕለቱ የነጻነታችን መለያ የሆነውን የተፈሪነታችን ግርማ ዬተላበሰ፤  የአትንኩን ባይነትን አብዝቶ ሞገሱ ያደረገ፤ ነገ የጎበኘው መሆኑ ብቻ ሳይሆን የተሳታፊዎችን ውስጥ ፍንትው አድርጎ ያሳዬ ታሪካዊ ነበር።

በጥዋቱ በተደራጀ መጋጓዣ በአራቱም አቅጣጫ ወደ ጄኔባ የተመሙት ስልፈኞች የማንነታችን ወታደር በመሆን ግንባር ላይ ወጥተው፤ አንገታቸውን ቀና በማድረግ፤ አደራ አውጪነታቸውን በልበ ሙሉነት በአጽህኖት ገልጸዋል። ዛሬ ገርሞኛል። በሲዊዝ የነፃነት እንቅስቃሴ ውስጥ ፈጽሞ ታይተው የማይተወቁ፤ በቤተ እግዚአብሄር ጉዳይ ብቻ ያተኮሩ ወገኖች ቤታችን ሆነን ሃዘናችን ከማወራረድ ትግሉን እንቀላቀላለን በማለት ያሳዩት የወገናዊነት ሙቀታማ ታማኝነት፤ ስቃይን የመጋራት አብነት ብዕሬ ችላ መግለጽ አትችለውም። ያኮራሉ!

በተደራጃ መስናዶ በሁለገብ ቅድመ ዝግጀቱ፤ እንክን ባልነበረው በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ለመገኘት ጉዞውም ሆነ ጊዜው  የአንዳርጋቸውን መንፈስ ሰንደቁ ያደረገ የተዋጣለት ብሄራዊ ነበር ማለት እችላላሁ።  የነበረው የሰልፈኛው የጉዙ ሂደትም በረጅሙ ጉዞው ላይ ሆነ ሰልፉ ላይ „ለአንቺ ነው ኢትዮጵያ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል መዝሙ ዳግሚያ ትንሳኤው ወይንም ልደቱ ነበር።“ ያን ልዩ ሽልማት መድረክ ላይ ዝማሬውን በአካል ተገንቶ ሲያቀርብ የነበረውን ስሜት ዘውድ ደፋለት – እላለሁ እኔው ዘጋቢዋ። የቅኔ ማህሌት ነበር። የአርበኝነት ሽብሸባ ነበር። የአትንኩኝ ባይነት ውብ ዜማ ነበር። የማግሥት ዋዜማ – ተስፋም! ምልዕቱ እራሱ ከነመንፈሱ ነበር የታደመበት። ተሳታፊዎች ውላቸውን አደሱበት።

ድንቁ ሰላማዊ ሰልፉ የነሸጠው – ዱርና ገደሉ የናፈቀው – የቆረጠ ስለነበር ረመጡ እኩል ስሜት ነበረው። የሰላማዊ ሰልፉ አዘጋጆች ብቻ ሳይሆኑ ባለቤቱ የአርበኛው ቁጣ – ንዴት – ብስጭት – አለሁባይነት ነበር። የሁሉም ድምጽ የሁሉም ፍላጎት የሁሉም ራዕይ ሞልቶ የተረፈውን የወንበዴ በደል በቃኝን ከኢትዮጵያዊነት ጋር በሥርዓት ተለክሊል የተጋበባት ነበር ብዬ ብናጋር ማጋነን አይሆንብኝም።

 

የነጻነቱ በትረ ጀግና “ወዲ ሃሪና የጀግናችን ዬአርበኝነት ሥም ነው“ ዛሬ እለተ ማክሰኞ እ.አ.አ. 8.2014 ሰንድቅ ዓላማ – ብሄራዊ መዝሙር – የኢትዮጵያዊነት ልዩ ምልክት ሆኖ ነበር ዬዋለ። የተቃጠለ ዕንባ – በማህጸን ዕልህን ያረገዘ ብስጭት ጥንካሬን ያዘከረ ጽናትን መንገዱ በማድረግ ድልን አለሞ ሽፍታን ሊገድል ወስኖ ቃሉን ሰጥታል። እልሁ – ሲቃው የተፈሪነት – ልዕልናው ጎልቶና ደምቆ፤ እንዲሁም አብቦ የዋለበት ነበር። ወገንና ባንዳንም አበጥሮ – አንተርትሮ በመለዬት ቀጠሮውን የቋጨበትም። በዓይን ቀልድ የለም ብለዋል የሲዊዝ ሳታናዎች።

በሰልፉ በተባባሩት መንግሥታት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ላይ  የመጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ በጣም መጠነ ሰፊ ቱሪስቶችና የዜና አውታሮችም ታድመውበታል። ከተጠበቀው በላይ ሰፊ ተደማጭነትም ተገኝቶበታል። እያንዳንዱ በነፍስ ወከፍ የነፃነቱ ዘብ አደር ሆኖ የቆመበት ዕለት ዛሬ ነበር ብዬ ደፍሬ እኔም ልናገረው።

ምዕራፍ ሁለት።

ሰልፈኛው በተያዘለት መርሃ ግብር የመጀመሪያ ግበረ – ታሪካዊ ክንውኑን በተገባ አጠናቋ ያመራው ወደ ተባበሩት መንግሥታት የሰብዕዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ነበር። ደሙ የመራው ሰልፍኛ፤ ማንነቱን ያልተዋሰው ሰልፈኛ። እሱነቱን ያልተበደረው ሰልፈኛ፤ ሳያቋርጥ የነበረውን ዝናብ ሳይገድበው ረጅሙን የእግር ጉዞ ወኔውን ሰንቆ በህብረት ዘመረ። ሁለተኛው የቁጣ የብስጭት ጉዞው እራሱ  ልዩ ታሪካዊ አቅል – ሳቢም – አቅም ነበረው። የአቅም ፈተና የድል ቀን። በተለያዬ ሁኔታ እኔ ሳውቃቸው ዳማ የነበሩት ሁሉ የጥቃቱ ጭስ ዛሬ አጥቁሯቸው ነበር ያገኘኋቸው። ይህ ለወያኔ የማይመለስ ደምን የቋጠረ የነገ መከራው ነው። ወያኔ በሰብዕዊ ፍጡር ሳይቀር የሚያደርገው የውንብድና ተግባር ቅርስና ውርስ አልባ አድርጎ እኩይ ተግባሩ እራሱ እንደሚፈጨው ዛሬ ጄኔባ ላይ ሚስጥር ጉባኤ ላይ ዋለ። ወያኔ የማይነካ ፍሬ ነክቷልና -የተከለከለ መንገድ ተዳፍሯልና የአድምን መከራ  በቀጣይ ዘመኑ ለመቀበል መዘጋጀት ይኖርበታል ሲሉ በተደሞ ገለጹ – ሰልፈኞቹ። የገነት ዛፍ መርገመት በወያኔ ላይ እንደሚደገምም ዛሬ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ፏ ብሎ ይታይ ነበር። ይህ ነው ኢትዮጵያዊነት ማለት። ይህ ነው ፈተናን አሸንፎ የተመሰጠረው የማንነት አሻራ። ይህ ነው የእኛነት ገጸባህሪ። ይህ ነው የትውፊት ካባ። በሰልፉ ላይ የተገኙት የሲዊዝ አንበሶች „ግንባራችን አናጥፍም ብለዋል“

ሀገርን ትውልድን ለሚሸጥ – ለሚለውጥ እራሳቸውን ያልሸቀጡት የኢትዮጵያ ልጆች ወኔ። ጩኽቱ በእውነት ልብ ይነካ ነበር። የተዘጋን የብርት በር ይበረግድ ነበር።  ተሳትፏቸውም ጽናት ነበር።

መከራ ተችሎ በኢትዮጵያዊነት ጨዋነት በዛ መልክ የተገባውን ተግባር ለመከውን መሰናዳት ዛሬም እንደ ትናንቱ ኢትዮጵያ ዘመን ያፈራውን የባንዳ ተውሳክ ብቻ ሳይሆን ቀለብ ተሰፋሪና ሆድ አደሩ ታላቅነቷን አጋድሞ እዬከተፋት ቢሆንም ያህቺ የቃል ኪዳን ሀገር ግን እንዲህ የሚንገበገቡላት ልጆች ስላሏት መጪውን መራራ ጉዞ የፈካ ያደርገዋል ዬሚል ንጹህ ራዕይ አለኝ። እዬተንጠባጠበ የሚቀረው ይቀራል። ቆራጦች ወደ ፊት ይገሰግሳሉ። ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረውም መንፈስም አንደ አበበ ይቀጥላል።

ባጠቃላይ ሰልፉ ጀግናውን ያከበረ፤ ደምን ያንቀሳቀሰ፤ እምነት የሚጣልበት የተዋጣለት ነበር። ታምቆ የነበረው ሁሉንም ሰቀቀን አስታግሶታል። ጥሪ የሚቀበል ተረኛን በዓይን ከማዬት በላይ ምን የሚያጽናና ሰብል አለና። ነገም ይኖራል። ወያኔም ይበናል – ይተናል።

መፈከሮቹ ጥቂቶቹ በእንግሊዘኛ

Andargachew Tsega A Symbel of Freedom

Free Andargachew Tsega

The Foreign Office Too Slow to Act, Way?

British Citizenshio Without Protection?

Britain Where is Andargachew Tsige?

ከዚህም በተጨማሪ በእንግሊዘኛና በፈረንሳይኛ ቋንቋ ስለ ተከበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ክውን ያለ አጭር የፖለቲካ ህይወት ታሪክ፤ እንዲሁም የሽፍታው ቡድን ሆድ ዕቃ ክሽን ያለ አጭር በራሪ ጹሑፍ ተዘጋጅቶ ተብትኗል። የሲዊዙ ሰላማዊ ሰልፍ በተባበሩት መንግሥታት ሁለት ታላላቅ ቦታዎች መካሄዱ የልብ ትርታን – የብሄራዊ ሃላፊነትን የማካለ ከወቅቱ አጀንዳና መቸቱ ጋር የተስማማ ጉልበታም ክንውን ነበር። በማዕልቱ መወድስ ለማንዴላው ኢትዮጵያዊ ለአቶ  አአንዳርጋቸውም ቀርቧል። የሴቶች ተሳትፎ ጉልህ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የእናትነት መክሊታቸው ጣይቱን ዓውጇል። አስተማማኝ ብዛት ነበረው። በተመቸኝ ምልክ ስለቀረጽቁት እንጂ እጅግ የሚያኮራ አቅምና መጠን ነበረው።

 

የጀግናችን መንፈስ መንገዳችን ነው!

ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ማንነት – ኢትዮጵአዊነት – ሚስጥር።

z1

z2 z3 z6 z4


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>