Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ የጀመረው እስር የ2007ን ምርጫ ጠቅልሎ ለመውሰድ ያደረገው መጀመሪያው ርምጃ ነው!!! (አንድነት ፓርቲ )

$
0
0

የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እናሳስባለን!!!

ከአንድነት ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በቅርቡ ለህዝቡና ጋዜጠኞች ይፋ እንዳደረግነው ሕወሓት/ኢህአዴግ  ለአለፉት 23 ዓመታትወደርየሌለውየዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋና የሰብአዊመብትረገጣበዜጎችላይሲፈጽምመቆየቱዓለምየሚያውቀውእውነታመሆኑን፤
በአሁኑወቅትይህየሰብአዊመብትረገጣና ድፍጠጣበእጅጉተባብሶወደመንግሥታዊየውንብድናናጥቃትመቀየሩን፤ ዜጎችመንግሥትእንዳሰማራቸው የምንጠረጥራቸውየደህንነትኃይሎችያለፍርድቤትትእዛዝበጅምላመታሰራቸውን፣መደብደባቸውንናበስውርእስር ቤቶችተወርውረውደብዛቸውእንዲጠፋመደረጉን ገልፀን ነበር፡፡ እንደዚህ አይነቱ ውንብድና ደግሞ ምርጫ ሲቃረብና የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰባሰብ ብሎም መዋሃድ ሲገለፅ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነ ከዚህ በፊት በውዱ ታጋያችን አንዱአለም አራጌ እና ሌሎችም ያስተዋልነው የገዥው ፓቲ ድርጊት ነው፡፡

ለባለፉት 23 ዓመታት ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ ምርጫ ሲደርስ የሚጨነቀው ገዢ ፓርቲ አባሎቻችንን መደብደብና ማሳደዱ አልበቃ ብሎት በምርጫው ዋዜማ በተለመደውና አሰልቺ ፍረጃው ተደግፎ አመራሮቻችንን ማሰር ጀምሯል፡፡ ፓርቲያችን እንደሚረዳው ይሄው በዛሬው ዕለት እንደገና የተጀመረው የአንድነት የስራ አስፈፃሚ አባልና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ሀብታሙ አያሌውን እና የምክር ቤት አባልና የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺን በማሰር እና በርካታ አባሎቻችን ላይ አፈና በማካሄድ የምርጫ ዘመቻውን ይፋ አድርጓል፡፡ ፀረ-ውህደት አቋሙን አንፀባርቋል፡፡

ይሄው እስር እንደተለመደው የተቀነባበረ የስርዓቱ ድራማ ከመሆኑም በተጨማሪ የ2007ን ሀገራቀፍ ምርጫ በተለመደው ማሸማቀቅና ማወናበድ ለመውሰድ የተጀመረ የመጀመሪያ ርምጃ ነው ብለን እናምናለን፡፡ የተቀነባበረ ድራማም በሚቆጣጠራቸው ስማቸው የህዝብ ተግባራቸው ግን የፓርቲ መገልገያ በሆኑ ሚዲያዎች ማቅረቡንም እንደሚቀጥልም እናውቃለን፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና ድራማ የሚከናወነው ከአፍ ባለፈ መተግበር ያልቻለውን ዴሞክራሲያዊ ስርኣት ለማስመሰያነት ለመጠቀምና የቀጣዩን ዓመት ምርጫ በለመደው ሁኔታ ከቻለ አስሮና አደናግሮ ካልተጫለ ጉልበቱን ተጠቅሞ ለመጠቅለል ነው፡፡

ፓቲያችንአንድነት አባላትንና አመራሮቻችንንበማሰቃየትናበማሸማቀቅ፣በመደብደብየአካልማጉደልጉዳትበማድረስየሚያደርገውንአስነዋሪተግባርእያወገዘየፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ አቶ ዳንኤል ሺበሺና ሌሎችም በፖለቲካ አመለካከታቸውና እምነታቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ ፖለቲከኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም በተቃውሞ ጎራ የተሰለፉ ፓርቲዎችም ይህን ህገ ወጥ እስር በማውገዝ እንዲሁም ኢ-ፍትሀዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚደረገውን ሩጫ በመቃወም እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንቆም እየጠየቅን ይህንን ህገ-ወጥነት በህዝባዊ ንቅናቄ ለማሸነፍ በምናደርገው ትግል በጋራ እንድንሰራ ሀገራዊና ወቅታዊ ጥሪ እናቀርባለባለን፡፡ የሲቪክ ተቀቋማት፤ ነፃው ሚዲያና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን መንግስታዊ ግፍና በደል በዓለማቀፍ ደረጃ በማጋለጥ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ስለሰብዓዊ መብት መከበርና ዴሞክራሲ መረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ተግል በመደገፍ የአምባገነኖችን ውድቀት እንዲያፋጥን ሀገራቀፍ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

                                              ትግላችን እስከ ነፃነት ይቀጥላል!!!  

                                            አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)

                                                       ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም

                                                               አዲስ አበባ

UDJ Head

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>