ኢትዮጵያውያንን በመግደል፣ በማሰር ፣ ሰብአዊ መብታቸውን በመርገጥ፣ በማስረብ እንዲሁም በዘር፣ በጎሳ ፣ በእምነት ፣ በመከፋፈል በሥልጣን የሚገኘው የወያኔ መንግሥት የለመደበትን የክፍፍል ድርጊት ለመፈጸም በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ መዕካሎች ላይ ማለትም የእምነት ፣ የማሕበረሰብና የእስፖርት ቦታዎች ላይ ትኩረት በመሰጠት ሥራውን እያካሄደ ይገኛል። በዚህም ውጥኑ መሰረት በሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያውን ለ31 ዓመታት በመሰብሰብ የእግርና ፣ የቅርጫት ኳሶች ጨዋታና የባሕል ፌስቲባል የሚያካሔዱትን በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽንን ለመክፈል ለሶስት ዓመታት በተከታታይ (ከ2004-2006ዓ.ም)ጥረት ቢያደርግም በኢትዮጵያውያን ተቃውሞ የክፍፍል ሴራው ከሽፎ በሔዱበት ቦታ ሁሉ ተመልካች በሌለበት በገንዘብ የገዙ ተጫዋቾችና ዳኞች ብቻ ውርውር የሚሉበት ባዶ እስታድየም ይዘው ቀርተዋል። ለዛንድሮ ሙክራቸው ሚንሶታን ምርጫቸው አድርገው በሚኒሶታ ሕዝብ ተቃውሞ ባዶ ስታድየም ይዘው ለመቀመጥ ተገደዋል። ገንዘብ በመስጠትና በመደለል እስታደየሙ ውስጥ ሱቆች የሚከፍቱ ( Venders) ፣ ምግብ የሚሸጡ ሰዎችን ለመግኘት ቢሞክሩም አልተሰካላቸውም። ከፍ ያለ ምስጋና ለሚኒሶታ ሕዝብ እናቀርባለን።
በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚታገዘው የወያኔ መንንግሥት የፖለቲካ ተቃዋሚዎችንና ሌሎች ኢትዮጵያዉያንን ከውጭ መንግሥታት በተለይም ከሱዳን፣ ከሳውዲ-አረቢያና ከየመን ጋር በማበር ሲያስገድል ፣ ሲያስዝና ሲያሳፍን ቆይቷል። ከሰሞኑም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የግንቦት 7 ዋና ጻሐፍን የየመን መንግሥት ከስናዓ አይሮፕላን ጣቢያ ወደ ሌላ ሶስተኛ አገር ትራንዚት ከሚያደርጉበት ጓዟቸውን አሳናክሎ በጸጥታ ኃይሎቹ በመያዝና በማሳር ካጉላሏቸው በኋላ ለወያኔ መንግሥት አሰልፎ ሰጥቷቿዋል። ይህን የዓለም አቀፍ ሕግን የተላለፈ የየመን መንግሥት ሕገወጥ ድርጊት ለማውገዝና ለወደፊትም በጋራ ሆነን በዚህ ጉዳይና በአካባቢያችን የወያኔ ሰላዮችና ከፋፈዮች የሚፈጽሙትን ደባ ለመከለከልና ለመመከት ሕዝባዊ ስብሰባ የተዘገጃ ስለሆነ በስብሰባው እንዲሳተፉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።
ቦታ (Place) : 1821 University Ave 2nd floor ( Fairview & University)
Saint Paul, MN 55104
ቀን ( Date) : እሑድ ሰኔ 29, 2006 ዓ.ም ( Sunday, July 6, 2015 )
ሰዓት (Time) ፡ ከሰዓት በኋላ 9፡00 ሰዓት( 3፡00pm )
በሚኒሶታ የተቋቋመው ግብረኃይል