Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አቶ አንዳርጋቸው “ለኢትዮጵያ መንግሥት ተሰጡ” ሲል ግንቦት ሰባት አስታወቀ (VOA Amharic)

$
0
0

የየመን መንግሥት የግንቦት ሰባትን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ሰጥቷል ሲል ግንቦት ሰባት አስታውቋል፡፡

ግንቦት ሰባት በዌብ ሳይቱ ላይ ባሠፈረው መግለጫ “የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቶ መቆየቱ ማስታወቃችን ይታወሳል።” ብሏል፡፡

ግንቦት ሰባት ይቀጥልና “የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቄዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም – ይልና – የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል።” ብሏል፡፡ “በዚህም ሳቢያ – ይላል የግንቦት ሰባት መግለጫ – የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ፤ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወዳጅ ጎረቤት ትሁትና ቀና ቢሆንም ጥቃት በሚያደርስበት የቅርብም ሆነ የሩቅ ጎረቤት ላይ ግን ቁጣውን የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ያውቅበታል።”

ግንቦት ሰባት ያወጣውን ሙሉውን መግለጫ ለማየት ከሥር የተያያዘውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፡፡
DEA54BEE-2996-4145-A17A-2842A121CD0E_w640_r1_s


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>