Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ወደ ሰማያዊ ፓርቲ የተወረወረች ቀስት ማን ላይ ታርፋለች?

$
0
0

Politiczedበዛሬው የሰንደቅ ጋዜጣ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ እና ስለ ሊቀመንበሩ አንባገነንነት እተርካለው የሚል አቅመ ደካማ ጽሁፍ አነበብኩ፡፡ ጽሁፉን አንብቤ ስጨርስ የተሰማኝ ነገር ቢኖር ይህች ሀገር ያልታደለች መሆኗ ብቻ ነው፡፡ ምራቅና ምላስ ያለው ሁሉ ተነስቶ ማንም ላይ የሚተፋባ ሀገር እምየ ኢትዮጵያ፡፡ ኪቦርድ መደብደብ የሚችል ሁሉ ጸሃፊ ነኝ የሚልባት ሀገር ኢትዮጵያ፡፡ ይህ ጽሁፍ በጥላቻና እርስ በርሱ በሚጋጭ አረፍተ ነገር ተደልዞ እስከመጨረሻው ይንዘላዘላል፡፡ እዚህ ነህ ሲባል እዚያ ማዶ የሚረግጠው ጽሁፍ የመጨረሻ አላማው የሰማያዊ ወጣቶችን የትግል ጉዞ መግታት ይመስላል፡፡ ይህ ግን ፈጽሞ ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚህ ወጣቶች ከቤታቸው ያስወጣቸው የወገናቸው ሰቆቃ ሳይመለስ ወደ ቤታቸው የሚመለሱበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም፡፡ የሰማያዊ ፈንጅ እረጋጭ ወጣቶችም ስለ ኢህአዲግ ግዙፍነት ሳይሆን ስለ አላማቸው መሳካት ብቻ አጥብቀው ይጨነቃሉ፡፡ ምድረ ኢትዮጵያ በኢህአዲግ የአፈና ፈንጅ ታጥራለች፡፡ ይህን የአንባገነንነት ፈንጅ የምንበጣጥስበት ጊዜ ደግሞ ሩቅ አይሆንም፡፡ በነገራን ላይ ጽሁፉ የማን ሴራ እንደሆነ ጠንቅቀን እንረዳለን፡፡ ሴረኛውም በጸሃፊው ላይ አድሮ የመጨረሻ መርዙን እንደተፋ እናውቃለን፡፡ ምክንያቱም ጸሀፊው ከሰማያዊ ፓርቲ በራሱ ፈቃድ የለቀቀ በመሆኑ መረጃው እንደሌለው እራሱም ያውቀዋል፡፡ በነገራቻን ላይ ጸሀፊው በአለፈው አርብ ከሀገር ወጥቷል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው እንዲያ ነው በሚል ሰንካላ ምክንያት ውድ የትግል ጊዜያችን አናባክንም፡፡ ይህ ማለት ግን ነገሩን ግልጽ አናደርገው ማለት አይደለም፡፡ በቀጣይ የነገሩን ዝርዝሩን እስክናሳውቅ ድረስ አንባቢ እንዳይደናገር መረጃ ለመጠቆም ነው፡፡ በመጨረሻም ማወቅ መልካም ነገር ነው፡፡ ለማወቅ ካልታደልን ደግሞ አለማወቅን ማወቅ መልካም ነው፡፡
በማንም ፍረጃ የሰማያዊ ትግል አይደናቀፍም፡፡

Gashaw Mersha

\freedom4ethiopian.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>