የወይዘሮ አልጋነሽ ፎቶግራፍ እስከምናገኝ ድረስ በቀበሌ መታወቅያዋ ላይ ያለ ፎቶ እንጠቀም እስቲ። “መታወቅያዋ አልታደሰም” ተብላ የህግ ጠበቃ ተከልክላ ነበር። ማን ያሳድስላታል? መንግስትኮ የለም። በቃ ህገመንግስትና ህገመንግስታዊ ስርዓቱ በኃይል ለመናድ ሞክራለች ተብላ በሽብር የተከሰሰች የዘመኑ ጀግናችን አልጋነሽ ገብሩ ናት። ህፃን ልጆች አሏት። ትናንት ማታ ዘነበ ታደሰ የተባለ የ12 ዓመት የአልጋነሽ ልጅና ምልአት ካህሱ የተባለች የጎረቤት ልጅ በኲሓ ፖሊስ ታስረው በወረዳው የፀጥታ ሓላፊ፣ የኲሓ መርማሪ ፖሊስና ሌላ የፖሊስ አባል ተደብድበው ከእስር በዋስ ተለቀዋል። የታሰሩበት ምክንያት “ረብሸዋል” የሚል ነው። ረብሸው ምን አደረጉ? እንደ እናታቸው መንግስት አሸበሩ ወይስ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አደረጉ? ደሞ የ12 ዓመት ህፃናት ይታሰራሉ? ጥረቱ ሁሉ በአልጋነሽ ላይ ተፅዕኖ ለማሳረፍ ያለመ ነው።
↧