ሪፖርተር፡- ናትናኤል ፀጋዬ
የእርስ በእርስ ግጭቱን ተከትሎ በሽታው በእጅጉ እንዳይስፋፋ አስግቷል
በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከምድረ ገጽ ጠፍቶ የነበረው ጊኒ ዎርም እንዳዲስ ማንሰራራት መጀመሩ ታውቋል፡፡ በደቡብ ሱዳን ውስጥም በሽታው በ11 ሰዎች ላይ መታየት መጀመሩን የጤና ባለሙያዎች አስታውቀዋል፡፡ ከረዥም የእርስ በእርስ ጦርነት በኋላ እ.ኤ.አ በ2011 ነፃነቷን ያገኘችው ደቡብ ሱዳን ባገኘችው የፖለቲካ መረጋጋት፤ የተስፋ ጭላንጭል እና የጤና ባለሙያዎች የጊኒ ዎርምን ከሃገሪቱ ለማጥፋት ችለው ነበር፡፡ ነገር ግን በሃገሪቷ ፕሬዘዳንትና ምክትል ፕሬዘዳንት መካከል በተነሳው አለመግባባት ምክንያት ዲንካ እና ኑር በተሰኙ ጎሳዎች መካከል ለተነሳው የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ሆኗል፡፡
በእርስ በእርስ ግጭቱ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱ ሲሆን 1.3 ሚልዮን ሰዎችም ቤትና ንብረታቸውን ትተው ሊሰደዱ ችለዋል፡፡ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት የሆነው ኦክስፋም እንደገለጠው በግጭቱ ተጨማሪ 7 ሚልዮን ሰዎች ሊጎዱ እንደሚችሉ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዝናባማው ወቅት በመግባቱ ኮሌራ የተሰኘው በሽታ መዛመት መጀመሩን ታውቋል በዚህም ምክንያት በበሽታው 892 ሰዎች ለበሽታው ተጋልጠዋል፡፡
ድህነትና የውሃ እጥረት ለበሽታው መስፋፋት ከፍተኛ ደረጃ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን በአትላንታ የሚገኝ እና የጊኒ ዎርም ለመጥፋት አበክሮ እየሰራ የሚገኝ ዓለማቀፍ ድርጅት አስታውቋል፡፡