(ዘ-ሐበሻ) አሁን ካሉት ወጣት ድምፃውያን መካከል የአድማጭን ጆሮ በማግኘት በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ የሆነው ድምጻዊ መስፍን በቀለ ወለላዋ ለተሰኘው ዘፈኑ አዲስ የሙዚቃ ክሊፕ ሰርቶ ለቀቀ። መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ ባደረገው ምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት አማካኝነት የቀረበውና በእውቁ ካይሮግራፈር አብዮት (ካሳነሽ) ደመቀ አማካኝነት በተዘጋጀ ውዝዋዜ አዲሱ ወለላዋ የተሰኘው ክሊፕ ታጅቧል።
በዚህ ክሊፕ ላይ እውቁን ካይሮግራፈር አብዮት ደመቀን ጨምሮ ሌሎች በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ተወዛዋዦች የተሳተፉበት ሲሆን ፊልሙ የተቀረጸውም በዛጎል ፊልምስ አማካኘት መሆኑን በክሊፑ ላይ ተገልጿል።
መስፍን በቀለ እና አብዮት ደመቀ ከ”ወለላዋ” ክሊፕ በፊት የሰሩት “እሹሩሩ” የሙዚቃ ክሊፕ ተወዳጅነትን አስገኝቶላቸው እንደነበር ይታወቃል። ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አዲሱን ወለላዋ የሙዚቃ ክሊፕ ጋብዘናል። ክሊፑን ለማየት እዚህ ይጫኑ
↧
የድምጻዊ መስፍን በቀለ “ወለላዋ”የሙዚቃ ቪድዮ ክሊፕ ተለቀቀ
↧