ኢትዮጵያዊዉ በየበረሃው ይጮሃል፣በሲና በረሃ ሆዱ እየተቀደደ ሆድ ዕቃው እየወጣበት ይጮሃል፥ ወደስደት ሲነጉድ በየመንገዱ በአውሬ እየተበላ ይጮሃል፥የሚጓዝባት ጀልባ እየሰጠመች በሞት ጥላ መካከል ሆኖ ኢትዮጵያውያዊው ወገኔ ይጮሃል፣በተለያዩ ሃገራት እስር ቤቶች የታጎሩ ሴትና ወንድ ኢትዮጵያውያዊያን ይጮሃሉ።የወያኔ ግፍ ያንገፈገፋቸው ኢትዮጵያውያን ይጮሃሉ፥ኦሮሞው ይጮሃል፣ አማራው ይጮሃል፣ ጉራጌው፣ከመሀል እስከ ጥግ ኢትዮጵያዊው ወገኔ ይጮሃል። ሴቱ ይጮሃል፣ወንዱ ይጮሃል ሙስሊሙ ይጮሃል፣ክርስቲያኑ ይጮሃል…. ኧረ የማይጮህ የለም ሁሉም ሰው ይጮሃል።
በየአረብ አገራት ለዘመናዊ ባርነት ተሽጠው ከአሰሪዎቻቸው ግፍ የተነሳ በፈላ ዘይት እየተቃጠሉ ይጮሃሉ፣በአለንጋ እየተገረፉ ይጮሃሉ፣ ከፎቅ ላይ እየተወረወሩ ይጮሃሉ፣ የጉልበት ዋጋቸውን ተነጥቀው ይጮሃሉ፣ በወሮበሎች እየተደፈሩ ይጮሃሉ ሌሎቹም ህጋዊ ፈቃድ የላችሁም ተብለው እየተሳደዱ ይጮሃሉ፣
በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማጥፉት ሰለባ የሆነው የአኙዋክ ወገኖቻችን ይጮሃሉ፣ አማራ ነህና በዚህ አትፈለግም ተብሎ በግፍ ከየስፍራው እየተሰደደ ያለው ወገኔ በየእስር ቤቱ የተጋዘው ኦሮሞ ወገኖቼ ይጮሃሉ፣ እውነትን በመጻፉቸውና በመናገራቸው ብቻ እስከሞት ድረስ የተፈረደባቸው ወገኖቼ ይጮሃሉ፣ በዋልድባ እየተገረፉና እየተሰደዱ ያሉ መነኮሳት ይጮሃሉ፣አብርሃና አቶ አስገደ ከትግራይ ይጮሃሉ ኧረ ዛሬማ የሚገርም ነገር ሰማሁ አባመላ የተባለ በዳያስፓራ ቀንደኛ የወያኔ ሰው ይጮሃል ሲባል።አሁንማ ማን የማይጮህ አለ? ሁሉንም የሚያስጮኸው ግን አንድ ነገር ነው፣የወያኔ ግፍ።
ክርስትያኑ |
ይጮሃል |
ሙስሊሙም |
ይጮሃል |
የመንግስትሰራተኛ |
ይጮሃል |
የግልተቀጣሪ |
ይጮሃል |
ቀጣሪው |
ይጮሃል |
ስራ እጡ |
ይጮሃል |
ነጋዴው |
ይጮሃል |
ሸማቹ |
ይጮሃል |
ሰራዊቱ |
ይጮሃል |
ጋዜጠኛው |
ይጮሃል |
እምነት የሌለው |
ይጮሃል |
የጠገበው |
ይጮሃል |
የራበው |
ይጮሃል |
ይጮሃል |
ይጮሃል |
ፖለቲከኛው |
ይጮሃል |
ፍትህ ያጣው |
ይጮሃል |
እስረኛው |
ይጮሃል |
ታሪክ |
ይጮሃል |
ሰሚአልባ |
ይጮሃል |
ጩኸት |
ይጮሃል |
እሪ |
በከንቱ |
ኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ የበላይነት አለ ብለው ያስባሉ??????
የኢትዮጵያዊያን መከራ በወያኔ ገዢዎቻቸው-ወያኔዎችም የኢትዮጵያን ልጆች በመከራ ገዙአቸው። በጽኑ ዘረኝነት፥ በስደት፥ ከስፍራ በማፈናቀል ሁሉ፥ በእስር ቤት ሁሉ ያሉ ይጮሃል፥የእስራኤላዊያንን ነፃነት የሰጠ እግዚአብሄር ለኢትዮጵያዊያንም ነፃነታችንን እንድንጎናፀፍ ይረዳናል። እኔ ለኢትዮጵያ የጉብኝት ዘመን እንደደረሰ አምናለሁ፥እስከዛው በአንድነታችን ፀንተን ጬኸታችንን ወደ ነፃነት እንቀይረዋለን።
ስቃይ |
ይበቃል! |
እስራት |
ይበቃል! |
ስልጣን |
ይበቃል! |
ስደት |
ይበቃል! |
የጎሳ ግጭት |
ይበቃል! |
የህዝብን ድምፅ መስረቅ |
ይበቃል! |
ማፈናቀል |
ይበቃል! |
ማስፈራራት |
ይበቃል! |
ህዝብን መናቅ |
ይበቃል! |
ዛቻ |
ይበቃል! |
አገርን መከፋፈል |
ይበቃል! |
ድብደባና አፈና |
ይበቃል! |
የወያኔ ስልጣን |
ይበቃል! |
ወያኔን ይበቃል ልንለው ግድ ይላል !!!
ከወያኔ/ሕወሃት ደርዝ የሳቱ ቃሎች ይልቅ ሀገራችን ብዙ አንገብጋቢና ያገጠጡ ችግሮች አሏት። ሕዝባችን ነጻ አልወጣም በጎጠኝነት የአገዛዝ ቀንበር ስር ይማቅቃል። በየዓመቱ ባስር ሽዎች የሚቆጠሩ ዘለው ያልተገቡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሕወሃት የተምታታ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምክንያት ተስፋ አጥተው በስደት ዓለም እየተንከራተቱ ይገኛሉ። በሕወሃት ውስጠ ተንኮል የተነሳም የሀገር ውስጥ ስደተኛው የትየለሌ ሆኗል። ወደድንም ጠላንም ዛሬ በዓለም ፊት ከውርደት በታች ተዋርደን የዓለም መሳቂያዎች ሆነናል። ሕወሃት ግን በኛ ኪሳራ የንግድ ኢምፓሩን በአፍሪካና በዓለም ደረጃ እያስፋፋ ቀጥሏል። ይህ የሀገራችን ቀውጢ ወቅት እኛን ካላስነሳን፤ ይህ የሕዝባችን ችግር እኛን ካላነቃን፤ ምን በጽናት ሊያቆመንና ሊያስተባብረን ይችላል? ይጠቅማል ባልነው መንገድና ወቅት ሁሉ የሕወሃትን ጎጠኛ አገዛዝ የሚያዳክም የሀገራችንን ሰላምና ጸጥታ የሚያስጠብቅና የሕዝባችንን ጥንካሬና ስነ ልቦና የሚያጠናክሩ እርምጃዎችን እንውሰድ። የኢትዮጵያዊነታችን ክብርና ኩራቱ ሀገራችን ከሕዝባችን ጋር በሰላም ተጠብቃ አስከኖረች ድረስ ብቻ ነውና።
እውነታው ግን የአባይን መገደብ የሚቃወም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የለም ። ነገር ግን አባይ የሚገደበው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀም ከሆነ ፤ ህዝብ ይከበር ነው የምንለው ። ከአባይ በፊት፦
ዘረኝነት ይገደብ !
ህዝብን ማፈናቀል ይቁም !
ሰብአዊነት ይቅደም !
በሃገራችን የአፓርታይድ ስርዐት ይወገድ !
የሃይማኖት ነጻነት ይከበር !
አባይን ለርካሽ ፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ ይቁም !
በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች ይፈቱ !
የሙስሊም ድምጽ ይሰማ !
ታሪካዊ ገዳማችን ዋልድባ ይከበር !
በህዝብ የተመረተ መንግስት ይምራን !
የህዝብ ድምጽ ይሰማ !
ነብሰ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ !
እና ሌሎችን ተያያዥነት ያላቸውን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ነው የተጠየቀው ።
ከቀረን ነገር በላይ ያጣነው ነገር ይበልጣል !
በተለያ ሀገር የምትገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሀገር ውስጥ ለሚፈጸመው የሰብአዊና የዴሞክራሲ ጥሰቶች ከሌላው ጊዜ በተለየ እና እጅግ በጣም በሚማርክ ፍጹም ጨዋነት በታየበት በስልጣን ላይ ያለው የወያኔን መንግስት እግር በእግር እየተከታተላችሁ የምታሰሙት ተቃውሞ በሀገር ውስጥ ላለን ለሀገዛዙ ቀጥተኛ ተጋላጭ ለሆነው ተስፋ እና ጉልበት እንደሚሆነን ምስክርነቴን ለመስጠት እወዳለው፤ለዚህም ተግባራችሁ ምስጋና ይገባችኃል፡፡
ይህ በእንዲ እንዳለ በሀገር ውስጥ የምንኖር ተገፍተናል፣ ተበድለናል፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን ተነጥቀናል የምንል ከቀረን ነገር በላይ ያጣነው ነገር ይበልጣል እና የሚቀርብን ነገር የለም፡፡ በመሆኑም ከገባንበት የፍርዓት ቆፈን ማንም ሳይሆን የራሳችን ችግር አፈትልኮ ሊያወጣን ይገባል አለበለዚያ ስቃዩ የእድሜ ልካችን ይሆናል እናም በቤታችን ፣በሰፈራችን ፣በመስሪያቤታችን ፣በመንቀሳቀስበት ስፍራ ሁሉ ስለ ነፃነት እንዘምር እንጩኹ !!!
ወያኔዎች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፈራረሱና ትውልድን የማጥፋቱ እኩይ ምግባር ሙሉ በሙሉ አለመሳካቱን ከቀንደኛ መሪያቸው ሞት በኋላ እንኳ’ ለራሳቸው ሲሉ ካለፈው ለመማርም ሆነ ለመጸጸት አለማሰባቸው ፕሮፌሰር እንደሚሉት ”ያሳዝናል” ተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን፤ ሀገራችን ለማጥፋትና ለማውደም፤ አስፈላጊ ከሆነም ህዝብን ከመጨረስ በምንም አይነት መንገድ ወደ ኋላ እንደማይሉ ነው ደጋግመው እየነገሩንና እያሰረዱን ያሉት። ይሁን እንጅ ትላንት ዛሬ አይደልም፤ ዛሬም ነገ አይደለም።
…….ይዘገያል እንጅ ታሪክ ውል አይስትም በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም።……
ከእንግዲ የዉሸት ፋብሪካ የሆነው ኢቲቪ ነጠላ ዜማውን ሲለቅ መስማቱ ፋይዳ የለውም።
እንደተለመደው “ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት ሃይሎች ” እያለ በቱልቱላ ጋዜጠኞቹ የህዝብን ጆሮ ሲያደማ እንሰማም ። በአንድነታችን ፀንተን ጬኸታችንን ወደ ነፃነት እንቀይረዋለን።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከዘካሪያስ አሳዬ( edenasaye@yahoo.com)