Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአማርኛ ሰዋስው ንፅፅራዊ ምልከታ – (ከቋንቋ መምህራን)

$
0
0

 እንደመግቢያ

ይህ ስራ ባዬ ይማም (1987/2000)ን እና ጌታሁን አማረ (1989)ን የሚመለከት ነው። ጽሁፋችን ከባዬ ስራ ይልቅ የ“ጌታሁን አማረ” ስራ ላይ ያተኮረ ነው። ባየ ይማም እና ጌታሁ አማረ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባልደረቦች ናቸው። የባዬ ስራ ሁለት ጊዜ ታትሟል። የመጀመሪያው በ1987፣ ሁለተኛው የተሻሻለው እትም ደግሞ  በ2000 ወጥቷል። በጌታሁን ስም የቀረበው እስከ 2002 አስር ጊዜ ታትሟል/ተባዝቷል። በእዝባር ተባዝቷል ያልንው የመሻሻል ህትመት (Revised edition) ስላልሆነ ነው። የባዬ የመጀመሪያ ህትመትና የጌታሁን 10ኛ እትም ዋቢ መረጃ የሚከተሉት ናቸው፤ (1) ባዬ ይማም። 1987። የአማርኛ ሰዋስው።አዲስ አበባ፤ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ማተሚያ ቤት። እና (2) ጌታሁን አማረ። 1989/2002። ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ። አዲስ አበባ፤ አልፋ አታሚዎች። (ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ መጣጥፍ መጨረሻ ላይ ዋቢጽሁፍ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ።)

Pen-4ሊነሱ ይችላሉ ብለን የምናስባቸውን ሁለት ጥያቄዎች ከመነሻው ግልፅ እናድርግ። አንደኛ፣ እነዚህ መፅሀፎች ከታተሙ በርካታ አመታትን አስቆጥረው ሳለ አሁን ላይ ማንሳቱ ለምን አስፈለገ ነው። ሁለተኛው፣ እውነት በተለይ በጌታሁን የታተመው ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በዚህ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት ለግምገማ የሚበቃ ስራ ነው ወይ የሚል ነው። ምክንያታችን ከትምህርት ጥራት ጋርና ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ ለተማሪዎች ካለው አሉታዊ ተምሳሌትነት ጋር የተያያዘ ነው።

የትምህርት ጥራት እያሽቆለቆለ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን ባሁኑ ግዜ በተማሪዎች ስራ ላይ እየታየ ያለው ግልበጣ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህ ሁኔታ ለዶክተሬት ድግሪ ማሟያ የሚቀርቡ ስራዎችንም ይመለከታል። ሁለትና ሶስት ቃላት በመለወጥ የራስ አድርጎ ማቅረቡ በጣም እየተዘወተረ ነው። እንደዚህ ሲደረግ ብዙውን ግዜ ምንጩ ቢጠቀሰም አንዳንዴ እስከጭራሹም ምንጩ የማይገለፅበት ሁኔታ አለ። አሳሳቢው ጉዳይ፣ ጥቅል ስራው ብቻ እየተጠቀሰ በራስ ስራ ላይ ማስገባቱ መለመዱ ብቻ ሳይሆን ስህተት መሆኑን በአድራጊው ያለመቀበሉ ነው። ዛሬ ተማሪዎችን ይህን ለማስተው መቸገር ብቻ ሳይሆን ድርጊቱ ትልቅ ወንጀል መሆኑን ለማሳመን ያልቻሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቋንቋ መምህራን አምርረው ይናገራሉ። ተማሪዎች አግባብ ባልሆነ መልኩ የገለበጡት ነገር ስህተት መሆኑን ላለመቀበል አብዛኛውን ጊዜ ማጣቀሻቸው በጌታሁን አማረ የታተመው ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ  ከባዬ ይማም የአማርኛ ሰዋስው ጋር ያለው መመሳሰል ነው።

መምህራኑ ከሩቅ ሳይዘሉ እዚያው በእዚያው ከመቀዳዳት አልፎ በዚህ ድርጊታቸው የማያፍሩ ከሆነ እንዴት አድርጎ ተማሪውን ከሰው መቅዳት ትክክል እንዳልሆነ ማስረዳት ይቻላል? ጉዳዩ  በርግጥ  የማሳመንና የመለወጥ ብቻ አይደለም ─ግልበጣ በየትኛውም (የትምህርት) አለም ወንጀል ነው። ወንጀልነቱ ደግሞ በእድሜ ገደብ የሚፈታ አይደለም። የዛሬ ሀያ አመትም ሆነ ሀምሳ አመት የተከናወነ ስርቆት ዛሬ ላይ ቢታወቅ ሰውዬው በአካል ካለ ከተጠያቂነት አያመልጥም።

በርግጥ የትምህርት ስርቆት ብዙውን ግዜ ፍርድቤት አስቁሞ ወህኒ አያስወርድም። ስርቆት የተረጋገጠበት ሰው ግን ከማናቸውም ትምህርት ነክ ስራዎች እንዲገለል መደረግ ብቻ ሳይሆን ስርቆት ባለበት ስራ የተገኘ ድግሪ ከሞተም በኋላም ቢሆን መነጠቅ ያስከተላል። በቅርቡ የጀርመን የመከላከያ ሚኒስትር ላይ የደረሰውን ማስታወሱ የሚበቃ ይመስለናል። የዛሬ ተማሪዎቻችን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ድግሪውን ወስደው ከአመታት ቆይታ በኋላ ቢነጠቁ ምን እንደሚሰማቸው ካሁኑ እናስበው።

ይህ ስራ በሁለቱ መጽሀፎች ላይ ጥልቅ ግምገማ አያደርግም። አላማው ችግሩን በግልፅ በማሳየት የሚመለከተው ክፍል፣ የዩንቨርሲቲው አስተዳደርም ሆነ ትምህርት ሚንስቴር፣ የራሱን ማጣራት አድርጎ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ለማሳሰብ ነው። ጽሁፉ ለሚመለከተው ክፍል እንዲደርስ ይደረጋል።

የመፅሀፎቹ መመሳሰልና መለያየት

የእነዚህ መጽሀፎች መመሳሰል ምኑ ላይ ነው የሚል ጥያቄ መነሳቱ ግድ ይላል። ይህን ጥያቄ የምናነሳው ግን መፅሀፎቹን ጨርሶ ያላየናቸው ከሆነ ብቻ ነው። መፅሀፎቹን ያየ የሚጠይቀው እነዚህ ስራዎች የሚለያያቸው ነገር ምንድነው የሚለውን ነው። በእርግጥ መፅሀፎቹን ያሳተሙት ሁለት የተለያዩ እውናዊ ሰዎች መሆኑን ያላወቀ፣ በብዕር ስም አንዱ ሰው ሌላውንም ያሳተመ ነው የሚመስለው። እስቲ የተወሰኑ ነጥቦችን እንመልከት።

ከባዬ መቅድም የሚከተለውን እናገኛለን፤

“አማርኛ በትምህርትነት መሰጠት የጀመረው ገና ዱሮ ነው። በዚያን ዘመን፣ ችግሩ የተሰማቸው እንደ ብላታ መርስዔ ሀዘን ወልደ ቂርቆስና እንደ ተክለማርያም ፋንታዬ ያሉ ሊቃውንት ካዘጋጁዋቸው ሁለት መፃህፍት ሌላ፣ ዛሬ ምንም ነገር የለም ለማለት ይቻላል። እነዚህም ቢሆኑ በይዘታቸውም ሆነ ባመለካከታቸው ለዛሬው ዘመን ትምህርት በቂ አይደሉም። ብዙ ይጎድላቸዋል። ….

“የስርዓቱ ትምህርት ካንደኛና ከሁለተኛ ደረጃ አልፎ በየኮሌጁ መሰጠት ከጀመረ በርካታ አመታትን ቢያስቆጥርም፣ በዚሁ ቁዋንቁዋ ተዘጋጅቶ የቀረበ መደበኛ ማስተማሪያም ይሁን መመሪያ ወይም ማጣቀሻ መፅሀፍ አሁንም በብቃት የለም። ባለመኖሩም ትምህርቱ የሚሰጠው የተለያዩ የስ-ነልሳን ሰዎች በልዩ ልዩ  የውጭ ቁዋንቁዋዎች ስለ ቁዋንቁዋው ከፃፉዋቸው የምርምር ስራዎች ላይ እየተቀነጨበ በሚወጣ ተበታኝ ወረቀት አማካኝነት ነው። ይህም በመሆኑ፣ መምህራን በተቀያየሩ ቁጥር የትምህርቱ ይዘትና አቀራረብ እንደመምህራኑ ዳራ እና እንደሚያጋጥማቸው የምርምር ስራ ሲቀያየር ኖሮአል። በዚህም ምክንያት የአንዱ ዘመን ተማሪ የተማረውን፣ የሌላው ዘመን ተማሪ አያገኘውም። ስለዚህም ተመጣጣኝ ችሎታና ግንዛቤ ያላቸውን ተማሪዎች ማፍራት ሲያስቸግር ቆይቶአል። ከዚህ ችግር ለመውጣት የሚቻለው፣ አንድ ወጥ የሆነ የማስተማሪያ መፅሀፍ በባዕድ ቁዋንቁዋ ሳይሆን፣ በዚሁ ቁዋንቁዋ ሲዘጋጅና ሁሉም በዚህ መነሻነት እያስተማረ ተፈላጊውን ግንዛቤና የአጠቃቀም ክህሎት ሲያዳብር ነው።

“እነሆ፣ በዚህ መፅሀፍ ለማድረግ የተሞከረውም ይኸው ነው። አንድ  ወጥና አጠቃላይ የሆነ የአማርኛ ሰዋስው ማዘጋጀት” (ባዬ 2000: xxvii)።

ከላይ ከቀረበው ከባዬ አንድምታ/ተጠየቅ ጋር ሁሉ ሰው ይስማማል ማለት አይደለም። በአማርኛ የተጻፈ የአማርኛ ሰዋስው በብዛትና በብቃት አለመኖሩ  ትክክል ቢሆንም፣ በዩንቨርሲቲው  ቋንቋውን የሚያጠኑ ተማሪዎች ተመጣጣኝ ችሎታና ግንዛቤ እንዳይኖራቸው ያደረገው በአማርኛ የተጻፈ የስዋስው መጽሀፍ በብቃት አለመኖሩ ነው የሚለው ተቀባይነት የሚኖረው አይመስለንም። “መምህራን በተቀያየሩ ቁጥር የትምህርቱ ይዘትና አቀራረብ እንደመምህራኑ ዳራ እና እንደሚያጋጥማቸው የምርምር ስራ ሲቀያየር ኖሮአል” የሚለው የባዬ አስተያየት እንደጥፋት የሚታይ ሳይሆን በዩንቨርሲቲ ደረጃ የሚጠበቅ ነው። መምህራኑ ለሚያስተምሯቸው ኮርሶች በየጊዜው ከተለያዩ የምርምር ስራዎች ሀሳብን እየጨመቁ ማስተማር ይጠበቅባቸዋል። በየጊዜው አዳዲስ ከሚወጡ የምርምር ስራዎች ጋር እራሳቸውን ማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን ኮርሶቻቸውንም ማደስ ይገባቸዋል። እንኳን በዩንቨርሲቲ ደረጃ በቅድመ-ዩንቨርሲቲ ትምህርት በአንድ ወጥ የማስተማሪያ መጽሀፍ (Textbook) የሚማሩ፣ ማስተማሪያ መጽሀፎቹ በየጊዜው ቢበዛ በአራትና በአምስት አመት መታደስ ግድ ይላቸዋል። እንደባዬ አይነት አጋዥ መጽሀፍ በዩንቨርሲቲ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የትምህርት ደረጃ መኖሩ አስፈላጊነቱ የሚያጠያይቅ ባይሆንም፣ “ተመጣጣኝ ችሎታና ግንዛቤ ያላቸውን ተማሪዎች [ለ]ማፍራት [...] አንድ ወጥ የሆነ የማስተማሪያ መፅሀፍ በባዕድ ቁዋንቁዋ ሳይሆን፣ በዚሁ ቁዋንቁዋ ሲዘጋጅና ሁሉም በዚህ መነሻነት እያስተማረ ተፈላጊውን ግንዛቤና የአጠቃቀም ክህሎት ሲያዳብር ነው” የሚለው የባዬ አስተያየት ተቀባይነት አይኖረውም። የዩንቨርሲቲ ትምህርት በዚህ፣ ባዬ ባለው መልክ የሚሄድ አይደለም። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር-ማስተማር ፍልስፍናም በአንድ ወጥ የማስተማሪያ መጽሀፍ (Textbook) ተማሩ የሚል አይደለም። እንደውም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከሁለተኛ ደረጃና ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተቋማት የትምህርት አሰጣጥ የሚለያቸው አንዱና ዋንኛው ነገር በአንድ ወጥ የማስተማሪያ መጽሀፍ የማስተማርና ያለማስተማር ጉዳይ ነው።

ከላይ የባዬን መግቢያ ቀንጭበን ሰፊ ትንታኔ የሰጠንው አስተሳሰቡ የባዬ የራሱ መሆኑን ለማሳየት ነው። ጌታሁን ይህን የባዬን ግላዊ አመለካከት እንዴት የራሱ አስመስሎ  እንዳቀረበው እንመልከት።

“የአማርኛ የሰዋስው ትምህርት ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሲሰጥ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ትምህርቱ መሰጠት የተጀመረበትን ጊዜና ለትምህርቱ የተዘጋጁትን መፃህፍት ስናነፃፅር ዝግጅቱ በየወቅቱ ከሚገኝ የሰዋስው ንድፈ ሃሳብ ጋር እየተጣጣመ ሲያድግ አልታየም። በተለይም መርስኤ ሃዘን  ወልደ ቂርቆስ (1948)ና ተክለማርያም ፋንታዬ (1964) ካዘጋጇቸው መፃህፍት በኋላ ባየ ይማም በ1987 ዘመናዊ የሰዋስው መፅሀፍ እስከታተመበት ድረስ የአማርኛን ሰዋስው ለማስተማር የተዘጋጀ የሰዋስው መፅሃፍ አልታየም። የምክነት ዘመን ነበር ማለት ይቻላል። በዚህም ምክንያት ተማሪዎቹ የቋንቋ መምህራን እራሳቸው እንደተማሩበት የዘመንና የቦታ ልዩነት የተለያየ ዳራ ይዘው ይገኛሉ። በዚህ ሁኔታ አንድ አይነት ቀርቶ የተቀራረበ ግንዛቤ ያላቸው ተማሪዎችን ማፍራት አይቻልም። ለዚህ ችግር መፍትሄ የሚሆነውና የሰዋስውን ትምህርትም ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚበጀው ከዘመናዊ የሰዋስው ንድፈ ሃሳብ በተጣጣመ ዘዴ ማስተማሪያና መርጃ መፅህፍትን (sic.) ማዘጋጀት ነው። በዚህ መፅሃፍ ዝግጅትም የተደረገው ይኸው ነው” (ጌታሁን 1989:vi)።

ከላይ በቀረቡት ጥቅሶች መሀከል ያለው መመሳሰል በሀሳብ ብቻ አይደለም። በአባባልም ነው። ለምሳሌ መዝጊያቸውን ብቻ እንመልከት፤ “በዚህ መፅሀፍ ለማድረግ የተሞከረውም ይኸው ነው” (ባዬ)፣ “በዚህ መፅሃፍ ዝግጅትም የተደረገው ይኸው ነው” (ጌታሁን)። በርግጥ በጥቅሶቹ መሀከል ልዩነትም አለ። በጌታሁን የቀረበው አጠር ያለ ከመሆኑም በላይ በአንዳንድ ቃል ከባዬ ተለይቷል። አሳጥሮና ቦታ ቀይሮ ማቅረብ በጌታሁን በታተመው በዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ በሁሉም ምዕራፎችና ንኡሳን ክፍሎች የሚታይ ነው። መስረቅ የለመደ … ካልሆነ በስተቀር እንዴት ሰው መግቢያ ሳይቀር ከሌላ ይገለብጣል?

ከመግቢያው ዘለል ብለን የባዬን “ምዕራፍ አንድ ስነድምፅ”፣ ገጽ 1 እንመልከት፤  “ማንኛውም ቁዋንቁዋ መሰረቱ ድምጽ ነው” (ባዬ 2000:1)። ማንኛውም ቋንቋ መሰረቱ ድምጽ አይደለም። መስማት የተሳናቸውና መናገር የተሳናቸው የሚጠቀሙባቸው በርካታ የምልክት ቋንቋዎች በአለማችን አሉ። ድምጽን አእምሯዊ ካላደረግንው በስተቀር እነዚህ ቋንቋዎች ድምጽ የላቸውም። እንደማንኛውም ቋንቋ ግን ስርእት አላቸው። ይህን የባዬን ብያኔ ጌታሁን፣ እሱም በመጀመሪያ ገጹ በ“ምእራፍ አንድ ስነድምፅ” ላይ እንደሚከተለው ያቀርበዋል፤ “ቋንቋ መልዕክት ማስተላለፊያ መሳሪያ ነው። … ለመልእክት ማስተላለፊያው ቋንቋ መሰረቱ ድምጽ ነው ለማለት ይቻላል” (ጌታሁን 1989:1)። ጌታሁን የባዬን ሀሳብ የራስ ለማስመሰል ባደረገው ለውጥ የበለጠ  ስህተት ውስጥ መውደቁን ልብ ይሏል።

ባለቤቱ ይደርስብኛል ብሎ ተጣድፎ የሚጠቅመውን የማይጠቅመውንም አግበስብሶ እንደሚዘርፍ ሌባ፣ በባዬ ላይ የታዩ ጉልህ ስህተቶች (ሳይቀሩ) የበለጠ “ጣፍጠው”ና የራስ መስለው በጌታሁን በታተመው ስራ ላይ ይገኛሉ። መጽሀፎቹ  ከይዘታቸው መመሳሰል በላይ ጭንቅላት በማይጠይቀው በምሳሌ እንኳ አይለያዩም። ገና ከመነሻው ከምዕራፍ አንድ የመጀመሪያ ገጽ ሳናልፍ ይህን ያህል መመሳሰል ካገኘን ውስጡ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ከዚህ በላይ እያንዳንዱን ነጥብ ማንሳቱ አንባቢን ማሰልቸት ብቻ ሳይሆን መቆምያው በእነደዚህ አይነት አጭር መጣጥፍ አይሆንም። ተጨማሪ ዝርዝር የሚመለከተው ክፍል ከፈለገ በራሱ የባለሙያ ኮሚቴ አቋቁሞ ማስገምገም ያስፈልገዋል። ሌላው አንባቢ ከዚህ ባለፈ በዝርዝር ማወቅ ከፈለገ መጽሀፎቹን ተመልክቶ የራሱን ግንዛቤ እንዲወስድ መተዉ ይሻላል።

የአማርኛ ሰዋስውና ባዬ

በላይኛው ክፍል ከባዬ ስራ ጋር የማንስማማባቸውን አንዳንድ ነጠቦች አንስተናል። ስህተት የመሰሉንን ብቻ ሳይሆን በእርግጠኝነት ስህተት ናቸው ብለን ልናወጣ የምንችላቸው ሌሎች ነጥቦችም አሉ። ለምሳሌ ጉልህ ስህተት ከምናገኝባቸው ውስጥ ቁጥርና የጊዜ ስርዓትን መጥቀስ ይቻላል። ከአንድ ስራ የማይስማሙበትን ነጥብ ማግኝትና ስህተት መልቀም ከባድ አይደለም። ቁምነገሩ ስህተት የሆነው ነገር የሚታረምበትን መንገድ በጨዋ ደንብ መጠቆምና ቢቻል ደግሞ አለኝ የሚባለውን ማሻሻያ ራሱን በቻለ ስራ ማቅረብ ነው።

እስካሁን በሚታወቀው፣ የአማርኛን ሰዋስው ጉዳዬ ብለው ከተሰሩት ውስጥ ቀደምቱ የእዮብ ሉዶልፍ/Hiob Ludolf (1698) ስራ ነው። ከዚህ በማስከተል በጥራትም ሆነ ሰፊ ጉዳይ ዳስሰው በጥልቀት ከተሰሩት ውስጥ የ19ኛው ክፍለዘመን  የፕሬቶሪየስ/Praetorius (1879) እና የቅርብ ጊዜው የዎልፍ ሌስላው/Wolf Leslau (1995) የአማርኛ  ሰዋስው መጽሀፎች ግንባር ቀደሙን ስፍራ የሚይዙ ይመስለናል።

የባዬ ስራ በበኩሉ በአማርኛ ደረጃ የራሱ የሆነ ትልቅ ታሪካዊ ቦታ አለው። እያንዳንዱ አረፍተ ነገር በጥንቃቄ መታየት የሚገባው የፀሀፊው ብስለት የታየበት ስራ ነው። ባዬ በአማርኛ እንግዳ የሆነ ፅንሰ ሀሳብን እንኳ ሲገልፅ፣ አንድ ቦታም አንባቢን የሚያደናቅፈው ነገር አይገኝም። በትንታኔውም እያንዳንዱን በራሱና በገባው መንገድ ለመስጠት ሞከረ እንጅ ልጥፍ ነገር አላመጣም። ካለማጋነን፣ ምናልባትም፣ የባዬን የአማርኛ ሰዋስው  ያህል በሌሎች የሀገራችን የቋንቋ ምሁራን ላይ ተፅእኖ ያሳደረ ስራ ያለ አይመስለንም።  ባሁኑ ግዜ በሀገራችን ልጆች ከድግሪ መመረቂያ ጽሁፎች ጀምሮ እስከ መጻህፍት ድረስ ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የባዬን መንገድ ተከትለው የተሰሩ ስራዎችን ማግኘት አይከብድም። ለምሳሌ የአንበሳ ተፈራን/Anbessa Teferra (2000) የሲዳምኛ ሰዋስው እና የተስፋዬ ተወልደን/Tesfaye Tewolde (2002) የትግርኛ ሰዋስው መጥቀሱ በቂ ይመስለናል።

የባዬ ሰዋስው በአማርኛ መቅረቡ የራሱ የሆነ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። እስከምናውቀው ድረስ፣ በአማርኛም ሆነ በማናቸውም የሀገራችን ቋንቋ (ግዕዝን ጨምሮ) የባዬን ያህል ጥልቅ የሰዋስው ትንታኔ በማቅረብ የተዘጋጀ ስራ እስካሁን ድረስ የለም። በዚህ ብቻ ለትምህርት ትኩረት የሚሰጥ አካል፣  ለባዬ ትልቅ ሽልማት ሊሰጠው በተገባ ነበር። ይህ ስለመደረጉ የምናውቀው ነገር የለም። በሀገራችን እንደዚህ የሚያደርግ የመንግስት አካልም ሆነ በጎ አድራጊ ድርጅት ጨርሶ ስለመኖሩም  የምናውቀው የለም። ችግሩ ሀገራችን ያለችበት የኢኮኖሚ ደረጃ ነውና ለምን ይህ አልተደረገም ብለን ወቀሳ የምናቀርብበት ጉዳይ አይደለም። ሽልማቱ ቢቀርበት፣ ከስርቆት ግን ልንጠብቀው ይገባል። የባዬ ስራ ተገቢውን ስፍራ ይዞ መቆየት እንዲገባው የሁሉም ስራ መሆን አለበት።

መደምደሚያ

በጌታሁን የታተመውን ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ ተማሪዎች  “ባዬ በቀላል አቀራረብ” ይሉታል። ይህ ቅፅል የወጣለት ገና መፅሀፉ እንደወጣ አካባቢ ቢሆንም እስካሁን ስሙ እንዳለ ነው። ገና የመጀመሪያ ድግሪ ያልያዘ ተማሪ የመፅሀፉን መመሳሰል በቀላሉ የለየበት ሁኔታ እያለ ሌላው ምሁር እንዴት ዝም አለ የሚለው በጣም የሚገርም ይሆናል። የሁሉንም ልብ መርምሮ ምክንያቱን ማወቅ ባይቻልም፤ ልንገምት የምንችለው ነገር ግን አለ።

አንድም በሌባና በተሰራቂው መሀከል ያለው ግንኙነት ነው። በጌታሁን በታተመው ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ  የጀርባ ሽፋን ላይ አስተያየት ሰጪው ባዬ ይማም ነው፤ “ከመምህሩ ደቀ መዝመሩ እንዲሉ፣ እኔ በቀላሉ ልገልፃቸው ያልኳቸውን ፅንሰ ሀሳቦች አቶ ጌታሁን በሚገባ ሊገልፃቸው ችሏል” (ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ  ከጀርባ ሽፋን ላይ የተወሰደ)። የሰዉ ዝምታ፣ “የተሰረቀው ሰው አቤት ማለት ቢቀርበት ለድርጊቱ ቡራኬ ከሰጠ እኔ ምን አገባኝ” በሚል ስሜት ሊሆንም ይችላል።

ሁለትም፣ ኢትዮጵያዊው ይሉኝታ ነው ─“አብሮ  በሚሰራ ሰው ላይ እንዴት እንደዚህ ይፃፋል” በሚል ይሉኝታ። በጌታሁን በታተመው በዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ ጀርባ ላይ የባዬም የሙገሳ አስተያየት መስጠት ከዚሁ ከይሉኝታ የመነጨ ይመስለናል። ገንዘብ የተበደረው ደረቱን ነፍቶ ሲሄድ አበዳሪው የሚያፍርበት ባህል ነው ያለን።

እንደባዬ አይነት እንደ እንቁ ልንጠብቀው የሚገባንን ምሁር የዋህ ይሉኝታውን ተጠቅመው ሲዘርፉት ዝም ማለት ከማናችንም የሚጠበቅ አይመስለንም። ጉዳዩ፣ አንድ ሌባ መስረቁ ሳያንሰው ተበዳዩን በይሉኝታ አጥሮ ቡራኬ እንዲሰጠው ከማድረጉ ወይም ከኢኮኖሚ ጥቅም ጋር ብቻ የሚታይ አይደለም። የትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት እናድርግ ሲባል ለትኩረቱ በመጀመሪያ ቅድሚያ የሚሰጠው ሌብነትን ማስወገድ ነው። ሌብነት በትምህርት አለም ትልቁ ወንጀል ነው። ባለቤቱ ስላላመለከተ ወይም ስላልተቃወመ ተብሎ የሚተው ጉዳይ አይደለም። የትምህርት ጉዳይ የሚመለከተው ክፍል ሁሌም እርምጃ መውሰድ አለበት። ያ ካልሆነ፣ በሀገር ደረጃ ሳይቀር ይህ ድርጊት መጥፎ ስም የሚያሰጥ ነው የሚሆነው።

ዋቢ ጽሁፎች

ባዬ ይማም። 1987 ዓም። የአማርኛ ሰዋስው።አዲስ አበባ፤ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ማተሚያ ቤት።

ባዬ ይማም። 2000 ዓም። የአማርኛ ሰዋስው(የተሻሻለ2 እትም). አዲስ አበባ፤ ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት።

ጌታሁን አማረ። 1989/2002 (10ኛ እትም)። ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ። አዲስ አበባ፤ አልፋ አታሚዎች።

Anbessa Teferra, 2000. A Grammar of Sidaama. PhD Dissertation: Jerusalem; Hebrew University.

Leslau, Wolf. 1995. Reference Grammar of Amharic. Wiesbaden: Harrassowitz Verlag.

Ludolf, Hiob. 1698. Grammaticæ Linguæ Amharicæ. Francofurti ad moenum/ Frankfurt am Main: J. D. Zunnerum.

Praetorius, Franz. 1879. Die amharische Sprache. Halle.

Tesfaye Tewolde. 2002. A Modern Grammar of Tigrinya. Rome: U. Detti.

 


Health: ከሰውነትዎ ውስጥ ስብን የሚያቀልጡልዎ 10 የምግብ ዓይነቶች

$
0
0

1. አጃ ጥሩ ጣዕም ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ ከተመገቡት በኋላ የረሀብ ስሜት  እንዳይሰማዎት ያደርጋል፤ በፋይበር የበለጸገ  በመሆኑምየኮልስትሮል መጠንን ያስተካክላል፡፡

2. እንቁላል እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ሆኖ  የካሎሪ መጠኑ ግን አነስተኛ የሆነ ነው፡፡ እንቁላል ጡንቻዎችንና ጥሩውን የኮልስትሮል  ዓይነት ለመገንባት ይረዳል፡:

color-133-Tomato-2
3. አፕል በአንቲኦክሲዳንቶችና በሌሎችም  የበለጸገው አፕል በተለይም በውስጡ የሚገኘው  ፔክቲን የስብ መጠንን ይቀንሳል፡፡
4. አረንጓዴ ቃሪያ በአረንጓዴ ቃሪያ ውስጥ  የሚገኘው ካፕሴሲን የአካላችን የእድገት  ህዋሳት እንዲዳብሩ በመርዳት ስብ በፍጥነት  እንዲቃጠል ይረዳል፡፡

5. ነጭ ሽንኩርት በነጭ ሽንኩርት ውስጥ  የሚገኘው አሊሲን የጸረ-ባክቴሪያ ባህሪአለው፣  ይህም ስብ እንዲቀንስና በደም ውስጥ  የሚገኘው መጥፎው ኮልስትሮል እንዲወገ  ድያደርጋል፡፡

6. ማር ስብን ለማቃጠል ማር ዋንኛውተመራጭ  ነው፡፡ ለዚህም ማርን በሙቅ ውሃበጥብጦ ጠዋት  ጠዋት መጠጣት ተገቢ ነው፡፡

7. አረንጓዴ ሻይ አረንጓዴ ሻይ ውስጥ  የሚገኘው አንቲኦክሲዳንት የሰውነትን ክብደት  ለማስተካከል ተመራጭ ነው፡፡ ለዚህም በየቀኑ  ሁለት ብርጭቆ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት  ይመከራል፡፡

8. ህዊት ግራስ (Wheat grass) የተሰኘው ተክል ስብ እንዲቃጠል ይረዳል፡፡

9. ቲማቲም ስብን በፍጥነት የማቃጠልብቃት ስላለው በምግባችን ውስጥ ብናካትተውተመራጭ ነው፡፡
10. ጥቁር ቸኮሌት በውስጡ የሚገኘው ፍላቮኖይድስ በደም ውስጥ የሚገኘውን  ኮልስትሮል ለመቀነስ ይረዳል፡፡

“እህቴ በባለቤቷ እሳት መለብለቧ ሳያንስ ድርብ በደል ደርሶባታል”

$
0
0

ደምሰው በንቲ
ለፖሊስ እና እርምጃው ጋዜጣ እንደጻፈው

ዕድሜዋ በ3ዐዎቹ ውስጥ እንደሚሆን ለመገመት አያዳግትም፡፡ ይህች ግለሰብ ግን ስለ ጉዳዩ ማብራራት ከመጀመሯ እንባዎቿ በሁለቱ ዓይኖቿ ጫፍና ጫፍ ቦይ እየሰሩ ይወርዱ ጀመር፡፡ ተረጋግታ የመጣችበትን ጉዳይ ታስረዳ ዘንድ ብንማፀናትም በቀላሉ የምትመለስ አልሆነችም፡፡ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ አፍንጫዋን በሶፍት እያባበሰች አሁንም ልውረድ አልውረድ እያለ ከሚታገላት እንባ ጋር በሚቆራረጥ ድምፅ “እህቴን —- ” ስትል ጀመረች፡፡ ቦርሣዋን ከፈታተሸች በኋላም የተወሰኑ ፎቶዎችን አውጥታ ከጠረጴዛው ላይ በተነቻቸው፡፡ በዓይናችን ያየነውን ነገር ለማመን ተስኖን ነበር፡፡ “እህቴ—” ስትል የገለፀቻት ግለሰብ ደረቷና ከደረቷ በላይ እስከ ፊት ገጽታዋ ድረስ በእሳት ተለብልቦ የከፋ ጉዳት አስተናግዷል፡፡
Tsige and her sister
አዲስ አበባ እንዲህ የመሰለውን አደጋ ከዚህ በፊት በከፋ ሁናቴ ሁለት ጊዜ ያህል አስተናግዳ የነበረ በመሆኑ መሰል ጥቃት ታስተናግዳለች ብሎ የሚያስብና የሚያምን ማን ይኖር ይሆን? ግን ሆኗልና የሆነውን ትገልጽልን ዘንድ ዳግም ጋበዝናት፡፡ በሀዘን በተሰበረ ድምፀት ቀጠለች፡፡ ጽጌ ገ/ኪዳን የተባለችው ይህቺው የተጎጂዋ እህት ፋንታዬ ገ/ኪዳን የተባለችው ተጎጂ እህቴ ከተጠርጣሪው ጋር ተጋብተው ሲኖሩ ዓመታትን አስቆጥረዋል ትላለች፡፡ እኒህ ጥንዶች ከባል ቤተሰብ የመኖሪያ ቤት አጠገብ ባገኙት ባዶ ቦታም በህገ-ወጥ መንገድ ጊዜያዊ ማረፊያ እንደሰሩ ትገልፃለች፡፡ “ይሁንና ከጊዜ በኋላ” ትላለች መውለድ ስላልቻለች ይሆናል የሚል ግምት የያዘችው ቅሬታ አቅራቢዋ የተበዳይ እህት ባለቤቷና ቤተሰቦቹ ጥላቻ ማዳበር ጀመሩ፡፡

ቤቱን ለቅቃ ትወጣ ዘንድም ከትንኮሳ እስከ ክስ ያመራ እርምጃ ወስደው ፍርድ ቤቱ ቤቱን በይገባኛል ያነሱት የባለቤቷ እናት እንደማይገባቸው ፈርዶባቸው መኖር እንደጀመረችም ትናገራለች፡፡ይሁን እንጂ በባለቤቷና በእርሷ መካከል የተፈጠረው መካረር ግን ሊበርድ አልቻለም ነበር የምትለው ጽጌ
ከመኖር ውጪ ሌላ አማራጭ ያልነበራት እህቴ የተለያዩ ተጽዕኖዎችን ተቋቁማ መኖር ጀመረች ትለናለች፡፡በዚህም ሳታበቃ ቦሌ አካባቢ ከሚገኝ አንድ ቦታ በጽዳት ሠራተኛነት ተቀጥራ ከምታገኘው ገንዘብ አጠራቅማ ኑሮዋንና ቤቷን ለማሸነፍ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማሟላት “አንድ ቀን ልቡ ይመለሳል” በሚል ተስፋ መኖር ጀመረች ስትልም ትገልፃለች፡፡ ተጠርጣሪው ግለሰብ ወይም የተጎጂ ባለቤት ግን ጥላቻው ከቀን ቀን እየበረታና እየጨመረ ሄደ የምትለው ጽጌ የፋሲካ ዕለት ምሽት ግን ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ ትላለች፡፡ በዚህ ዕለት እህቴ እናቷ ቤት ቆይታ ከምሽቱ 2፡ዐዐ አካባቢ ወደ ቤቷ ስታመራ ቤቷ ያለ ወትሮው ክፍት ሆኖ አገኘችው፡፡ በመደናገጥም ቤቱን ከፍታ ስትገባ ቤቱ በጭለማ ተውጦ እንደነበር ተጎጂ እህቷ የነገረቻትን ዋቢ አድርጋ ታስረዳለች፡፡ ከትንሿ ቤት አልጋ ላይ አረፍ ያለውን ሰው ጥላ እንደተመለከተችም ማነህ ስትል እንደጠየቀች ትናገራለች፡፡ “እኔ ነኝ” ሲል የመለሰው ተጠርጣሪ ግለሰብም “ዛሬ የመጣሁት ለነገር ነው”ብሎ እንደመለሰላት እህቷ የነገረቻትን ዋቢ አድርጋ ታስረዳለች፡፡አርፋ እንድትተኛ ካስፈራራት በኋላ ስትተኛም ጋዝ እንዳርከፈከፈባትና ሰውነቷ ላይ እሳት ሲለኩስባትም “እባክህ አድነኝ” ስትል እራሱን ስትማፀነውም ቁጭ ብሎ ሲጋራውን እያጨሰ ያያት እንደነበረ እህቷ የተናገረችውን ጠቅሳ ትገልፃለች፡፡

ወጥታ መሬት ላይ በመንከባለልና በቅርበት ወዳለው ወደ እናቷ ቤት ያመራችው ፋንታዬ ገ/ኪዳን የእናቷ ጎረቤት የሆኑት ሻምበልና አዛውንቷ እናቷ ደርሰው ባይረዷት ኖሮ በህይወት ባልተረፈች ነበርም ትላለች ጽጌ፡፡ አደጋው በደረሰ ዕለት በነጋታው እዚያው ቤት እንደተኛ የተያዘው ተጠርጣሪ ለጊዜው በፖሊስ ጣቢያ እንዲታሰር ሆኖ ነበርም ትላለች፡፡ እኔና አዛውንቷ እናታችን ፋንታዬን ለማዳን ከመሯሯጥ ጎን ለጎን የክሱን ሂደት እየተከታተልን ነበር በወቅቱ በአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ የአራት ኪሎ ፖሊስ የምርመራ ባለሙያ የሆነውን የፖሊስ ባልደረባ ተጎጂዋን እንድናመጣለት ክስ በመሰረትንበት ወቅት ገልፆልን ነበር፡፡ አምጡ ባለን ዕለት ጠዋት ደውዬለት “ላምጣትወይ?” ስል ጠይቄው “አታምጪያት” ሲል ፎቶዋ የጉዳቱዋን መጠን ስለሚገልጽ እንዳንጨነቅ ነገረን ትላለች፡፡ እህቴ የውስጥ ሱሪ እንኳ አልነበራትምና ቁልፉን ሰጥተውን ልብሷን እንድናወጣላት ፖሊስን ብንጠይቅ እርሱ ፈቃደኛ እስካልሆነ አንሰጥም ብለው ቁልፍ ከልክለውን ሆስፒታል ቦታ ጠፍቶ ቤቷ እንኳን ተኝታ ህክምና መከታተል እንዳትችል ተደርጎ እናታችን ማድቤት ውስጥ ለመተኛት ተገዳለች ብላለች፡፡

እኛ ትኩረታችንን ማረፊያዋ ላይ አድርገን ከቀበሌው ፍርድ ቤት ከሴቶች ጉዳይ ጋር እና ከፖሊስ ጋር እየተሯሯጥን መፍትሄ በማፈላለግ ላይ ሣለንም ተጠርጣሪው በ2 ሺህ ብር ዋስ እንደተለቀቀ ፖሊስ አረዳን ስትልም ዳግም ልትመልሰው ያልቻለችውን እንባ እየዘራች “በእኛ የደረሰ በማንም አይድረስ” ትላለች፡፡ እንዴት ሊለቀቅ እንደቻለ የምታውቀው እንዳለ ጠይቀናትም የአራት ኪሎ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ የሆኑትን ኮማንደር አነጋግሬ ጉዳዩን የያዘው መርማሪ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ባደረጉበት ወቅት መረጃ በሚገባ ባለማደራጀቱ እና የእህቴን የጉዳት መጠን በሚገልጽ ሁኔታ ለፍርድ ቤቱ ባለማቅረቡ ፍርድ ቤቱ ሊይዘው የሚገባውን ነጥብ ባለማስያዙ የዋስትና መብት እንደተፈቀደለት ትናገራለች፡፡ እንደ አጠቃላይ በምርመራ ሂደቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳላት የምትገልፀው ይህቺው ቅሬታ አቅራቢ አሁንም ማረፊያ ባጣችው እህቴ ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ በተመለከተ ዋስትና የሌለን ከመሆኑም በላይ ከብዙ ትግል በኋላ ልብሷን እንድናወጣ የተደረገ ይሁን እንጂ አሁንም በገዛ ቤቷ እንዳታርፍ እጥፍ ድርብ በደል በእህቴ ላይ ደርሶባታል ትላለች፡፡

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድንት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

$
0
0

የውህደት እንቅስቃሴአችን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል!!

ለውህደቱ መሳካት ጥረት እና ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን  ምስጋና እናቀርባለን

እንደሚታወቀው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡

ይሄው ውህደት አመቻች ኮሚቴ በስምምነት ሰነዱ በተቀመጠው መሰረት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት እየሰራ ሲሆን የሁለቱ አንጋፋ ፓርቲዎች ውህደት የተሳካ እንዲሆን ትንሽ ግዜ መጨመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በተለይም ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት ሰነዱ የተቀመጠው የውህደት ግዜ ላይ ሁለት ሳምንት መጨመር እንደሚያስፈልግ ታምኖበታል፡፡

ስለዚህ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴው ባደረገው ግምገማ የሁለቱ ፓርቲዎች የውህደት ግዜ ሓምሌ 19 እና 20 እንዲሆን ተስማምቷል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የሁለቱ ፓርቲዎች ረቂቅ ደምብና ፕሮግራም ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀቀ ሲሆን የጉባኤ ተሳታፊዎች የውህደቱን ግዜ በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡ በመጨረሻም ሁለቱ ፓርቲዎች ተዋህደውና ሌሎች ፓቲዎች ወደ መሰባሰብ መጥተው የተጠናከረ የተቃውሞ ሃይል እንዲፈጠር ብርቱ ድጋፍ ላደረጉ ኢትዮጵያውያንና የውህደት አመቻች ኮሚቴው ስራ የተቀላጠፈ እንዲሆን ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡

በመቀጠልም እስከ ውህደቱ ፍፃሜ ድረስ በሀገር ውስጥና በውጭ አገር እየተደረገ ያለው ድጋፍ እንደሚቀጥል በመተማመን ለውህደቱ ድጋፍ የምታደርጉ ኢትዮጵያውያን፡-

üመኢአድ፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ቦሌ ቅርንጫፍ፤  የባንክአካውንትቁጥር፡- AEUP – SP 235 

ü  አንድነት፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ጠመንጃያዥቅርንጫፍ የባንክአካውንት፡-  UDJ –  A/C 47

በኩል እንድታስገቡ የውህደት አመቻች ኮሚቴው አገራዊ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ስንተባባር እናሸንፈላን!!

                                     ሐምሌ 9 ቀን 2006 ዓ.ም

                                             አዲስ አበባ

udJ&AEUP

በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ዓመፅ ተጀመረ…!!!

$
0
0

mqdefaultየሃረማያ ዩኒቨርሲት የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመመረቅያ ፅሑፍ ክፍያ ከዕጥፍ በላይ በመጨመሩ ዓመፅ ኣስነስተዋል።

ተማሪዎቹ ከትናንት በስትያ ሰኞ ሓምሌ 7 /2006 ዓ/ ም ክፍያው 3000ብር እንደሆነ ከዩኒቨርስቲው ሬጅስትራር የተፃፈ ደብዳቤ የተሰጣቸው ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው ሃሳቡ በመቀየር ክፍያው ወደ 8700 ብር ከፍ በማድረግ በቦርድ ለጥፎዋል።

ተማሪዎቹ ተሰባስበው ወደ ዩኒቨርሲቲው ሃላፊዎች የሄዱ ሲሆኑ ክፍያው ከዕጥፍ በላይ እንዲሆን የተደረገበት ወሳኔ ኣግባብነት እንደሌለውና ወደ ቀድመው መጠን ካልተስተካከለ እንደማይመዘገቡ ኣሳውቀዋል።

እንደምጫችን ኣገላለፅ ከሆነ ክፍያው ባንዴ ከእጥፍ በላይ እንዲሆን የትደረገው የመንግስት ሰራተኞች ደምወዝ ጭማሪ ተደርገዋል የሚል እንደሆነ ኣረጋግጠዋ።

የሁኒቨርስቲ ኣስተዳደር በጉዳዩ ኣስቸኳይ ስብሰባ እያካሄደ እንደሆነም ለማወቅ ተችለዋል።

ሃረማያ ዩኒቨርስቲ ልማታዊ መንግስታችን ስግብግብ ዩኒቨርሲት ብሎ ታፔላ እንደሚለጥፍለት ይጠበቃል።

“ስግብግብ ነጋደዎች” ነው…! ያለው በኢቲቪ እየተናገረ የሰማሁት ኣንዱ ቱባ ባለስልጣን።

ዓመፁ በኣግባቡ ይፈታ ይሆን? ወይስ እንደ ተለመደው መቺ ሃይል ይላካል…?

 

Source- freedom4ethiopian.wordpress

ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የምርመራ መዝገቡ መዘጋቱ ሕገወጥ አካሄድ መሆኑ ተገለጸ

$
0
0

-‹‹አሁን ታስረው የሚገኙበት ሁኔታ ሕገወጥና አደገኛ ነው›› የተጠርጣሪዎች ጠበቃ

zone 9999በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በክስ ላይ የሚገኙት ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማርያን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ፖሊስ ‹‹ምርመራዬን ስለጨረስኩ መዝገቡ ይዘጋልኝ›› በማለት መዝገቡ እንዲዘጋ ማድረጉ ሕጉን ያልተከተለና አደገኛ መሆኑን ጠበቃቸው አስታወቁ፡፡

ተጠርጣሪ ጋዜጠኞች ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪያንና የሕግ መምህር ዘለዓለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃኔ ሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የሚቀርቡበት ዕለት ነበር፡፡ እንደወትሮው ሁሉ የተጠርጣሪዎች ቤተሰቦች፣ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኞች፣ ጓደኞቻቸውና የተለያዩ የችሎት ታዳሚዎች በጠዋት ማልደው በፍርድ ቤት ግቢ የተገኙ ቢሆንም፣ እስከ ቀኑ 5፡30 ሰዓት ድረስ ፖሊስም ሆነ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ችሎቱ አልመጡም፡፡ ከ5፡30 ሰዓት በኋላ ሌሎች ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ተጠርጣሪዎቹና ፖሊስ ችሎት ቆይተው ሲወጡ፣ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን፣ ደንበኞቻቸው ፍርድ ቤት መቅረብ አለመቅረባቸውን ለማጣራት የዕለቱን ተረኛ ዳኛ ለማነጋገር ገቡ፡፡ ጠበቃው ስለደንበኞቻቸው ፍርድ ቤቱን ሲጠይቁ፣ ፖሊስ ምርመራውን መጨረሱን በማሳወቅ መዝገቡ እንዲዘጋለት ጠይቆ መዘጋቱን ሲያስረዳቸው፣ ‹‹እንዴትና በምን ሁኔታ?›› የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ከመዘጋቱ ውጪ ምንም ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

እስረኛ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ የምርመራ መዝገቡ ሊዘጋ እንደማይችል የሚናገሩት ጠበቃ አመሐ፣ ተጠርጣሪዎቹ ከሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ መሆናቸው፣ በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት ምንም ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ በመሆኑ ድርጊቱ ሕገወጥና አደገኛ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ ምርመራውን ካጠናቀቀ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ይዞ በመቅረብ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳትና ክስ እስከሚመሠረትባቸው ድረስ በዋስ እንዲቆዩ ወይም የሕግ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት ስለሚቆዩበት ሁኔታ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መስጠት እንደነበረበት አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ባልሰጠበት ሁኔታ ተጠርጣሪዎቹ ባሁኑ ወቅት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የሚናገሩት ጠበቃው፣ በወንጀል ሕጉና በሕገ መንግሥቱ በተጠሰው አካልን ነፃ የማውጣት መብት (ሐቢየስ ኮርፐስ) ክስ ሊመሠርቱ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በሌላ የምርመራ መዝገብ የተካተቱት ጦማሪያን ማህሌት ፋንታሁን፣ አቤል ዋበላና በፈቃዱ ኃይሉ ደግሞ ፍርድ ቤት መቅረብ የነበረባቸው ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረ ቢሆንም፣ ተጠርጣሪዎቹም ሆኑ መርማሪ ፖሊስ ሳይቀርቡ መቅረታቸውን ጠበቃው ጠቁመዋል፡፡

ዘጠኙም ተጠርጣሪዎች ‹‹የመብት ተሟጋች ነን›› ከሚሉ የውጭ ኃይሎች ጋር በሙሉ ሐሳብና ገንዘብ በመስማማት ሕዝብን የማተራመስ፣ አገርንና መንግሥትን የማፍረስ ዘገባ በኢንተርኔትና በተለያዩ ድረ ገጾች ያልሆነ መረጃ ሲያስተላልፉ ተገኝተዋል በሚል ፖሊስ ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለሁለት ጊዜ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ከተፈቀደለት በኋላ፣ በሦስተኛው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ ውስብስብና ድርጊቱም የሽብርተኝነት ድርጊት መሆኑን በመጥቀስ፣ ለተጨማሪ ምርመራ 28 ቀን እንዲፈቀድለት የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉን በመጥቀስ ተፈቅዶለት መመርመር ላይ መሆኑን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ 78 ቀናት ሞልቷቸዋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

በአንድነት ፓርቲ ክስ የቀረበበት የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል መልስ ሰጠ

$
0
0

-ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት አቅርቤያለሁ ብሏል

‹‹ግብረ ኃይሉ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ስለማቅረቡ ማስረጃ አላቀረበም›› የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ

UDJየተጠረጠሩበት ወንጀል ግልጽ ሳይደረግላቸው ከመታሰራቸው በተጨማሪ በሕገ መንግሥቱ ‹‹ዜጎች ተጠርጥረው በታሰሩ 48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለባቸው የሚገልጸውን ድንጋጌ ተላልፏል››

በሚል በአንድነት ፓርቲ ክስ የተመሠረተበት፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ኃይል፣ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርቦ ምላሽ ሰጠ፡፡

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው ምክር ቤት አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና (ትግራይ) ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታና የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት በፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውና በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ተገልጾ ክስ መመሥረቱ ይታወሳል፡፡ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ሐምሌ 4 ቀን 2006 ዓ.ም. የተመሠረተበትን ክስ በሚመለከት፣ ግብረ ኃይሉ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ተገኝቶ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ማቅረቡን አስረድቷል፡፡

ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ዝም ብሎ ሳይሆን ከፍርድ ቤት ማዘዥያ አውጥቶ መሆኑን የፀረ ግብረ ኃይሉ ተወካይ ፖሊስ አስረድቶ፣ የተመሠረተበት የሐቢየስ ኮርፐስ (አካልን ነፃ ማውጣት) ክስ ተገቢ አለመሆኑን ገልጿል፡፡

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ እንደተናገሩት፣ ፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት አቅርቤያለሁ ባለበት ቀን እስከ ምሽት 11፡30 ሰዓት ድረስ ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ ሲጠብቁ ቢቆዩም ሊቀርቡ አልቻሉም፡፡

የሕግ አማካሪ ሊያገኙ ሲገባ መቼና በስንት ሰዓት እንደቀረቡ ሳይታወቅ ‹‹ቀርበዋል›› መባሉ ተገቢ ባይሆንም፣ ስለመቅረባቸውም ቢሆን ፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበለት ማስረጃ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ አንድ ሳምንት ያለፋቸው ቢሆንም፣ የሕግ አማካሪም ሆነ ቤተሰቦቻቸው እስካሁን እንዳላገኟቸው አቶ ተማም አስረድተዋል፡፡ ጠበቃ በእስር ላይ የሚገኙ ተጠርጣሪ ደንበኞቹን ማግኘት የሚችለው በሳምንት ሁለት ቀናት ብቻ እንደሆነ በማዕከላዊ እስር ቤት መወሰኑ አግባብ አለመሆኑንም አቶ ተማም ተቃውመዋል፡፡

በተፈቀደው ቀን ጠበቃ ማዕከላዊ እስር ቤት ሄዶ ደንበኛውን ሊያስጠራ ወደ ፖሊሶች ጠጋ ሲል ‹‹ማንን ነው የፈለጉት?›› የሚል ጥያቄ በፖሊሶች መቅረቡ ጥሩ ቢሆንም፣ ጠበቃው የደንበኛውን ስም ሲናገር ‹‹እሱን ለማግኘት አልተፈቀደም›› የሚል ምላሽ በመስጠት ጠበቃው ከደንበኛው ጋር ሳይገናኝ እንዲመለስ መደረጉን ተቃውመዋል፡፡

‹‹በሌላ በኩል ሌሎች ተጠርጣሪዎች ከጠበቆቻቸው ጋር ሲነጋገሩ በተመሳሳይ ቦታ ላይ ይታያሉ፡፡ ጠበቃን ማነጋገር መብት ከመሆኑ አንፃር እየለዩ አልተፈቀደምና ተፈቅዷል›› ማለቱ በሰዎች መካከል ልዩነትን ስለሚፈጥር ጥሩ አይደለም፤›› በማለትም አቶ ተማም አክለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ ፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉ ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው ማስረጃ እንዲያቀርብ በመንገር፣ ውሳኔ ለመስጠት ለሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ማቅረቡን የገለጸ ቢሆንም፣ ከአረና (ትግራይ) አመራር አብርሃ ደስታ በስተቀር የቀረበ ስለመኖሩ እንዳልሰሙና ማስረጃም አለመቅረቡን አቶ ተማም አስረድተዋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

በደቡብ ክልል በሸካና ሸኮ ጎሳዎች ግጭት ከ130 በላይ ቤቶች መቃጠላቸው ተሰማ

$
0
0

-ቁጥራቸው ያልተገለጸ ሰዎችም መሞታቸው ተጠቁሟል

-ለግጭቱ ምክንያት ናቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች መታሰራቸው ተሰምቷል

newsበደቡብ ክልል በሸካ ዞን ውስጥ በሚገኙት ሸካና ሸኮ ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት ከ130 በላይ ቤቶች መቃጠላቸውንና ከሁለቱም ወገኖች ነዋሪዎች ወደ ቴፒ ከተማ በመሸሽ ላይ መሆናቸው ተሰማ፡፡

በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ግጭቱ ሊፈጠር የቻለው በጋምቤላ አዋሳኝ ድንበር አካባቢ፣ ጉስታ ቀበሌ ውስጥ በሚገኝ የማዕድን ሥፍራ ምክንያት መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የሁለቱ ጎሳዎች ግጭት በ1985 ዓ.ም. የተጀመረ ሆኖ በ1994 ዓ.ም. ከረር ያለ ግጭት ውስጥ ገብተው እንደነበር ያስታወሱት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ልዩ የፖሊስ አባላትና የፌዴራል ፖሊሶች መሀል ገብተው ግጭቱን ያስቆሙት ቢሆንም፣ ውስጥ ለውስጥ መተነኳኮሱ ቀጥሎ፣ በተለይ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ የከረረ ግጭት በመጀመራቸው በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውንና የሰዎች ሕይወትም እንዳለፈ ይናገራሉ፡፡

የማዕድን ቦታውን ለማልማት ከሸካ ዞን ፈቃድ የጠየቁት ሸኮዎች ፈቃድ በመከልከላቸው፣ መዠንገር ዞን ሄደው ፈቃድ ማግኘታቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

የሸካ ዞን የማዕድን ቦታውን ለሌላ አልሚ ሰጥቶ ስለነበር፣ ሸኮዎቹን ሲከለክሏቸው በተፈጠረ ግጭት ለኢንቨስተር የተፈቀደውን ቦታ ይጠብቅ የነበረ የጥበቃ ሠራተኛ በመገደሉ፣ ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉንና የሸኮ ጎሳዎች ሸካዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እያደረጉ በመሆናቸው ንብረት እየወደመና ሕይወት እያለፈ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በጎሳዎቹ መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማስቆም ከተሰማሩት ልዩ ኃይሎች ውስጥ አንድ የፖሊስ ባልደረባ መገደላቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፣ የችግሩ አሳሳቢነት የተመለከተው የክልሉ መንግሥት የፌዴራል ፖሊስ እንዲገባ በማድረጉ ግጭቱ መብረዱን አስረድተዋል፡፡ የተወሰኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በሥፍራው እንዲቆዩ ተደርጎ ፌዴራል ፖሊስ መመለሱንም አክለዋል፡፡ የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥትም ግጭቱን ለማብረድ መተባበሩን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

በሁለቱ ጎሳዎች ግጭት እጃቸው አለበት የተባሉ ነጋዴዎችና ግለሰቦች ታስረው ጊዜ ቀጠሮ እየተጠየቀባቸው ፍርድ ቤት እየተመላለሱ መሆኑንም ነዋሪዎች ጠቁመዋል፡፡ በሁለቱ ጎሳዎች ግጭት ምክንያት ቤታቸው የተቃጠለባቸው በርካታ ነዋሪዎች ቀዬቸውን ለቀው ቴፒ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙም ነዋሪዎቹ አክለዋል፡፡ የፌዴራል መንግሥና የክልሉ መንግሥት በጋራ ጉዳዩን እልባት ካልሰጡት ወደማያባራ ግጭት ሊያመራ ስለሚችል ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ስለተፈጠረው ግጭት ማብራሪያ ለማግኘት ለሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በተደጋጋሚ የተደረገው ሙከራ ባይሳካም፣ የቴፒ ከተማ አስተዳደር ዓቃቤ ሕግ አቶ አሰፋ ደምሴ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አቶ አሰፋ እንደገለጹት፣ ግጭቱ ያለው ከቴፒ ከተማ በ60 እና 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ያኮ ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡ ወደ ቴፒ ከተማ ሸሽተው የመጡ ነዋሪዎች መኖራቸውንና እስካሁን ድረስ በተሰባሰበው መረጃ 129 ቤቶች መቃጠላቸውን አስረድተዋል፡፡ ቦታው ሩቅና ገጠር በመሆኑ መረጃ ለማግኘት እንደማይቻል የገለጹት አቶ አሰፋ፣ ቤት የተቃጠለባቸው ነዋሪዎች በቴፒ ከተማ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በአካባቢው አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን ጠቁመው፣ ግጭቱ አሁን ስላለበት ሁኔታ ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter


ሰማያዊ ፓርቲ ‹የዜጎች ቃል ኪዳን ሰነድ›ን ለውይይት ሊያቀርብ ነው

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) አዲስ አበባ፡- ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) እሁድ ሰኔ 29/2006 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ የብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ በኮሚቴ ውይይት ሲደረግበት የነበረውን የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለምክር ቤቱ በማቅረብ በሰነዱ ይዘትና አፈጻጸም ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ስምምነት ላይ መድረሱን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ethiopia-blue-party-300x164
ሰነዱ ለውይይት በሚበቃ መልኩና ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በሚያስማማ መልኩ በኮሚቴ ታይቶ ስምምነት የተደረሰበት መሆኑን የገለጹት የህዝብ ግንኙነቱ በቅርብ ቀን ህዝብ፣ ምሁራን፣ የህግ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ ተወያይተው በህገ-መሰረት እንዲጠቀሙበት እንዲያስችል እቅድ መያዙን ገልጸዋል፡፡ አቶ ዮናታን ‹‹የቃል ኪዳን መሰረቱ የተዘጋጀበት ዋናው ምክንያት ባለፉት 50ና 60 አመታት ህገ-መንግስት ተረቀቀ ቢባልም የህዝብ ሀሳብ ያልተካተተበትና የህዝብን ጥቅም መሰረት አድርገው ያልወጡ መሆናቸውን ተከትሎ ይህን ክፍተት ለመሙላት ነው፡፡›› ሲሉ የሰነዱን አላማ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የቃል ኪዳን ሰነዱ በርካታ አካላት የሚወያዩበት በመሆኑ የሰማያዊ ፓርቲ ብቻ እንደማይሆን የገለጹት የህዝብ ግንኙነቱ ‹‹ማንኛውም አካል ህግ ለማውጣት መሰረት እንዲያደርገው ለውይይት የምናቀርበው ሰነድ ነው ብለዋል፡፡›› ሰማያዊ ፓርቲ ስልጣን ቢይዝ ህገ-መንግስትነት ይጠቀመዋል ወይ ብለን የጠየቅናቸው ኃላፊው ‹‹የቃል ኪዳን ሰነዱን ህገ-መንግስት አናደርገውም፡፡ ነገር ግን ህገ-መንግስቱን ጨምሮ ሁሉም ህጎች ሲሻሻሉም ሆነ ሲቀየሩ የቃል ኪዳን ሰነዱ መነሻ ይሆናል›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ

ጧፍ! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 17.07.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

 

Hailemedhin Abera

ካፒቴን አበራ ኃይለመድህን

በርቶ!
ተብራርቶ
ድርጊት ተሰማርቶ
ጀግና ተለክቶ።
ተፍታቶ
ሩቁን አስልቶ
ዛሬን ቀድሞ አይቶ
ትናንትን አውግቶ
ነገን አስተጋብቶ
ጎልቶ!
 

ዛሬ ካፒቴን አበራ ኃይለመድህን በጀግንነት ዚዊዘርላንድ ጄኔባ ላይ የወያኔን ትዕቢት ደርምሶ የገባበት መንፈቅዓዊ ዓመቱ ነው። 6ወር ተቆጠረ። ጀግና አበራ ሃይለመድህን ፍትህ ባለበት ሀገር ስላለ ከታሠረበ በኋላ በእሱ ዙሪያ የተቀነባበሩ ዜናዎች ሆኑ ዘገባዎች ምስሉንም ድምጹንም ማግኘት አልቻሉም። በወቅቱ እጅግ በጣም ብዙ የዓለም ሚዲያዎች ሳይቀሩ እንደቋመጡ ነበር የቀሩት። የሀገሬው የዜና ማሰራጫም ቢሆን ፌስ ቡክ ላይ የተገኘውን ፎቶ ዓይኑን ከተር አድርጎ ነበር ያቀረበው። በሀገረ – ሲዊዘርላንድ እናት ልጆቿን በጡቶቿ ሥር ድብቅ አድርጋ፣ ሽሽግ አድርጋ፣ ከዓይን እንዳይገቡባት እንደምታሳሳው ዓይነት ትንግርት ነው የተፈጸመው።

የወያኔ ጉርዶች – አሸከሮች ከዚህ በከረሙበትም ወቅት ዓይኑን ማግኘት አልቻሉም። ሲንደፋደፉ ባጅተው ማድጋዋ ተስብሮ ወሃ አልባ እንደምትመለስ የሀገሬ ባለጋሜ  ኩም ብለው አፋቸው ኩበት ቅሞ፣ አመድ መስለው፣ አንደበታቸው እንደ ደረቀ ነበር ዬተመለሱት። በዚህ ዙሪያ የነበረው ጫና፣ የነበረው ጉድ መድህኒዓለም ያውቀዋል። የአሸባሪ ተባባሪ እሰከመባል ያደረስ ሰፊ ዘመቻ ነበር። ነገር ግን ለጀግናዬ ለአበራ ሃይለመድህን ደግሞ የሲዊዝ መንግሥት ጥያቄውን ተቀብሎ ቀጣዩ ሂደት በጽሞና እንድንጠብቅ  አደረገ።

መንፈሳችን ረጋ፤ ሁለመናችን ተሰባሰበ፤ በእሱ ዙሪያ የለፉ – የደከሙ – ቀን ከሌት የባዘኑ ወገኖቹ ሁሉ፤ ከአሜሪካን ሀገር ድረስ መጥተው ጉዳዩን ለመከታተተል የቆረጡት የተከበሩ ዶር. ሼክስፔር ፈይሳን ጨምሮ ትንፋሽ አገኙ። አማላካችን ይመስገን። አሜን! እንዲህ ፍትህ ባለበት ሀገር የፍትህ ጥማትን ማግኘት የሰማይ ተግባር ነው።

ሽፍታው ወያኔ በሚመራው አስተዳደር ግን ያፈነውን አንበሳ የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ምስል በአያችሁት ሁኔታ በሸፍጥ ተቀባብቶ አቀረበ። ከዛ በኋላ የተፈጸመው ድርጊት ደግሞ ከአራዊት የሚጠበቀውን ማናቸውንም የጭካኔ አሰቃቂ እርምጃ በመውሰድ የበቀል የደም ጽዋውን ወያኔ ይጎነጫል።

አዎን! የነፃነት ትግሉን፤ የመንፈስ ልጆቹን፤ የአርበኝነት መንፈስ ገድለው ተስፋ ቆራጭነት አዝማች እንዲሆን ታስቦ በደመነ ነፍስ ተተልሞ የቀርበ ነበር ያ ቅጥ አንባሩ የጠፋው የቪዲዮ ቅንብር። ይህ ዓለም ዓቀፍ ወንጀል ነው። ከአፋናቸው – ከውንብድነታቸው - ከበረት ገልባጭነታቸው የዬመኑ የውንብድና ተግባር በላይ ሰሞናዊው ዓለም ጉድ ሊለው የሚገባ የሚዲያ ህግጋትን፣ የእሥረኛ መብትን ሁሉ በማናለብኝነት የዳጣ ገመናው ነው የወያኔ የአደባባይ ሲሳይ ያደረገው። በዚህ ዙሪያ ዓለም ዐቀፉ የሰብዕዊ መብት አስከባሪ ነኝ የሚለው ድርጅት ሆነ ሚዲያዎች ሁሉ ይህን የሰማይ ስጦታ የሆነውን የሰው ልጆችን መብት የረገጠ ገመና እንዴት ሊያዩት እንደሚችሉ አላውቅም። አቅሙ ያላችሁ ተግታችሁ ብትሠሩበት በዚህ ብቻ እራሱን የሚያዞረው መዘዝ ወያኔ ሊመጣበት ይችላል።

እኛ በርትተን ከሰራን ይህ አረም መጥፊያውን ጉድጓድ እራሱ እዬቆፈረ መሆኑን የሚያውጅ ስለሆነ የሂደቱን ጠረኑ ማድመጥ ያስፈልግ ይመስለኛል። ወያኔ ከሰው ውጪ የተፈጠረ እንሰሳ ስለመሆኑ የተገነዘበው ወጣት አበራ ሀይለመድህን ከሀገርም ሲዊዝን መርጠ። ጥቃቱን በጀግንነት አዋራረደ። ለአረሙ ወያኔ የሚፈልገውን ኮሶ አስጎነጨ። ወጣቱ ዬወያኔን ህግ ጣሽነት፤ ጠንቅቆ ምርምሮ የደረሰበት በመሆኑ የዝምታ የበቃኝ ሰላማዊ እርምጃው ፍትህን እንደሚያገኝ አስቀድሞ ተልሞ ነው ነበር የተነሳው።

ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሐገር የማይፈጸሙ ህግጋት አይረቁም። አይጸድቁም። አስፈጻሚ አካላቱም ዕውቅና ያለው ተግባር አላቸው። ክንውንና ሚዛን የሚለካከቡት። የቢሮ መኖርም ትርጉም ጠገብ በመሆኑ የተረታው እንኳን የፍርድ ሂደቱን ውሳኔ በጸጋ ደስ ብሎት ይቀባላል። እንዲያውም የተፈረደበት ሰው ውሳኔውን ልክ እንደ ቤተሰቡ አቅርቦና አስጠግቶ ተግባራዊ ለማድረግ ይማስናል። ቅጣቱንም በፍሰኃ ያስተናግዳል። ይቅርታም በመጸጸት ይጠይቃል። የፍትህ አካላቱም ቢያንስ ለህሊናቸውን ለሙያቸው ሥነ ምግባር በመገዛታቸው፤ በመታዘዛቸው ማሃያቸውን ሲጠቀሙበት አይጎርብጣቸውም። ይስማማቸዋል።

በወያኔ ሰፈር ደግሞ የተገለበጠ ውርዴ ነው። እኛም እንዳሻው የምንታረድ፤ እንዳሻው የምንዘለዘለ፤ እንዳሻው የሚከትፈን እርዶች ሆንለታል። የደለብን ሰንጋዎች። ያልገባን ሚስጥር ይህ ነው። ሀገራችን የሚመራት የሚያስተዳድራት ናዚ ስለመሆኑ ፈጽሞ ጭራሽኑ አልገባንም። አልተረዳንም። አጋጣሚና ሁኔታ ካገኜ ለማንምና ለምንም የማይራራ ህጻነትትን ሳይቀር የሚያርድ ጭራቅ መሆኑን አሁንም አልተገለጠልንም። ሆድ አደሩም ሆነ ቀለብ የሚሰፈርለት እሳቱ እስኪደርሰው ድረስ ሽፋን በመስጠት ይቀልዳል። ጥግና ከላላ ሆኖም አብሮ ይዳክራል። በበቀል በጨቀዬ ሥራዓት አብሮ ያረገርጋል። ቀኑ ሲደርስ ግን እዬነጠለ ይለቅመዋል። ጅብ ዘመድ የለውም። ሆዱ ነው ዘመዱ። በቀሉ ነው እስትነፋሱ።

እውነትን መድፈር የተሳነው ደመነፍሱ የወያኔ አስተዳደር አሁንም በፍትህ ፈላጊያት ላይ የአራዊት ዘመቻውን ተያይዞታል።

ከአንድነት ፓርቲ በተረኝነት እኔ በግሌ እጠብቃቸው የነበሩት ሁለቱ  አቶ ሃብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤልን ሺበሺን ከሰማያዊ ፓርቲ የሺዋስ አሰፋ እንዲሁም ያ የአጭር ግልጽና ጭብጥ አዘል መረጃ ዘጋቢ፤ ንቁው መምህርና ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ከመቀሌም ባለተራ ሆነዋል። ያው የጭካኔ ቤተ ሙከራነታቸው በተለመደው ሁኔታ ሥጋቸው እዬተቦጨቀ ደም ያዘንባል። ይህ ሥር የሰደደ የፋሽስት የቋሳ ሥርዓት እስካልተወገደ ድረስ አፋናው ይቀጥላል።

ተሰደን እንኳን ሰላም ነሳን፤ ተሰደን እንኳን መቀመጫ ነሳን። ተሰደን እንኳን እረፍት ነሳን። በስደት ሀገር ለመንቀሳቀስ እንኳን ማዕቀብ ተጣለ። ይህ እንግዲህ እኛ የፈቀድንለት አስመችተን የምናሽሞነሙነው ውርዴታችን ነው።

ፍቅር የነጠፈበት ሽፍታ ካፒቴን አበራን አግኝቶ ቢሆን ምን ሊያደርግ ይችል እንደ ነበረ እሰቡት። አስሉት። ስጋው በቁሙ ይቀቀል ነበር። መንፈሱ በኤሌትሪክ ይደነዝዝ ነበር። አካሉ በእሳት ይቃጠል ነበር። አውሮፕላኑን ጣሊያን አሳርፎ ስለምን ሌላ ስደት አልጠዬቀም? የሚሉት ግብዝ ሆድ አደሮች – ተለጣፊ መዥገሮች ጥበቃ አልባ እንዲህ ካንፕ ውስጥ እያለ በጋንግስተር ተጠልፎ አሳሩን ሲይ አብረው ለመደለቅ አስበው ነበር። ግን ወንድና አንበሳነት – ጀግንነትና አድዋ ውል ተዋውለው በድል ላይ ሰላምን አገኙ። አሁንም እንደ ተከደነ ነው። ዘው ተብሎ የሚዛቅ ምንም ብጣቂ ነገር ማግኘት አይቻልም።  በዚህም እንዲቀጥል ምኞቴ ነው።

ጭምቷ ሲዊዝ ለአዲሱ  ለትወልዱ ታላቅ የባለውለታነት ስጦታ ነው ያበረከተችው። የፈጸመችው። ህሊና ያለው ትውልድ ይህን ሊዘክረው ይገባል። ሲዊዝ ታሪካችን ጠብቃልንአለች። አዬነው እኮ የመንን – አዬን እኮ ታላቋ ብርታንያንን – መሪያችን አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፈው ሲሰጡ ለጭራቅ። አሁንም የሚዘገዩበት ምክንያት ተጨማሪው በደል የመንፈሱን ዲታነት እንድናጣ ለወንበዴ ጊዜ ለመስጠት ነው። ሊፈጥኑ  አልቻሉም። ቀኑ በረዘመ ቁጥር መከራውም ያን ያህል መራራ ኮሶ ይሆናል።

በዛ ድልዝ ቪዲዮቸው ክብራችን ከነመንፈሱ እንደሆን አይተናል። ነገ ግን ሌላ መርዶ ይኖራል። ይህ ያመረቀዘ የቋሳ ተግባር ከማናቸውም የወያኔ ቅንጥብጣቢ ቅርጥምጣሚ ንክኪዎች ጋር ቆርጠን እንደናቆም የሚያደርግ የበደል ነጋሪት ይመስለኛል። ለዬቶ መታገል። ነጥሮ መውጣት የወቅቱ ግዴታ ነው።

በጨረፍታ ያዳመጥኩት ነገርም አለ። ይህን አቅፈን – ይህን ተቃቅፈን እንድንቀጥል ደግሞ እንሰበካለን። የሚየሳዝነው ደም የሚያስነባው ይሄው ነው። አሁንም „ስክነት“ እያለ የሆዱ ዘመዴ ቱልቱላ በመድረካችን ሲያንባርቅ እንሰማለን። እናዳምጣለን። የነጻነት ትግሉ አቅምን ከማን እግር ሥር ነው ወድቆ ዬሚለምነው? „ከልደቱ?“ „አለም ከተጸዬፋቸው የወያኔ ጋሼ ጃግሬዎች ተላላኪዎች?!“ እንዳልሰማ!

ለረዳት አውሮፕላን አብራሪ አበራ ሃይለመድህን በአካል ለሚያገኙት ቤተሰቦች።

ወገኖቼ የጀግና ቤተሰቦች ዛሬ የሚታመን የለም። ቅይጥ የጎሸ ነገር ይሸተኛል። ጠረኑ በፍጹም አላማረኝም። ጦርነቱ የእርስ በእርስ ነው።  በሁለም ዘርፍ ጥንቃቄ ማድረጉ እጅግ አስፈላጊ ነው። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። የሲዊዝ መንግሥት ክድን አድርጎ የያዛቸውን ማናቸውም መረጃዎችን ነፃነታቸውን አደራ ጠብቁላቸው።

የእኔ ክብሮች ልጨርስ። ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ለምትታደሙት ወገኖቼ ሁሉ ፍቅሬን – ናፍቆቴን – ውስጤንም ሳልሳሳ አክዬ ሸልምኳችሁ። በጀግኖቻችን ዙሪያ ዘሃብሻ ላይ የከተብኳቸውን ሌሎችም ታክለው በድምጽ ዛሬ ዕለተ ሃሙስ ከ15 እስከ 16 አዬር ላይ አዬር ላይ እንገናኝ። እርግጥ እንደ እናትነቴ- እንደ አዛኝነቴ – እንደ እርግቡ አንጀቴ አጥንቴን የሰነጠቀው ጥቃትና ውርዴት ምን ያህል አቅም ኑሮኝ ዛሬን እንደማሳካ እርግጠኛ ባልሆንም። ካልቻላችሁ ደግሞ በማግሥቱ አርኬቡ ላይ ፍቀዱና እንገናኝ። የበጋ እረፍት ራዲዮ ፕሮግራሙ ስላለው ደግመን የምንገናኘው ከወር በኋላ ይሆናል በ28.08.2014 ነው። የዛሬው የ17.07.2014 ግን በRadio Tsgaye Aktuell Sendung ወይንም  www.tsegaye.ethio.info ወይንም www.lora.ch.tsegaye በዚህ እንገናኝና መንፈሳችን በናፍቆት እናሟሸው።

 

መፍቻ

* ጎልቶ ላልቶ ነው የሚነበበው። ትርጉሙ አዎንታዊ ነው። ደምቆ፤ ቀለሙ አብርቶ፤ እንደ ጸኃይ አምሮበት ለማለት።

 

ትግል ለነጻነት መስዋዕተነቱም ህይወቱ ነው!

ትግል ለነጻነት መከራው የጽድቅ መንገዱ ነው!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

”’የሽንፈት ሰላም ግን ከሽብር ይከፋል።” ማሪቱ ለገሰ ”እንድያው ዘራፈዋ!” (ያድምጧት)

በእነ ሀብታሙ አያሌው የክስ መዝገብ አንድነት ፓርቲ ያቀረበው ክስ ውድቅ ተደረገ

$
0
0

Habtamu abrhayeshiwas daniel

በዛሬው ዕለት በአራዳ ምድብ ፍታብሔር ችሎት ሀምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የፀረ ሽብር ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ መብራህቱ የእስር ትዕዛዙንና የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀበትን ሰነድና ታሳሪዎቹን ይዘው እንዲቀርቡ ቢያዝም ኃላፊው ታሳሪዎቹን ሳይዙ ቀረቡ፡፡
ችሎቱ በ4፡30 ተሰይሞ ዳኛው ከሳሽና ተከሳሽ መቅረባቸውን ካረጋገጡ በኋላ እስረኞቹ መቅረባቸውን ዳኛው ጠየቁ፤ ተከሳሽ እስረኞቹን አለማቅረባቸውንና የሰነድ ማስረጃዎቹን ስላቀረብኩ እስረኞቹን እንዳቀርብ አይጠበቅብኝም በማለት ለፍ/ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ዳኛው የእስር ማዘዣና የፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ሰነዶች ተከሳሽ ማቅረባቸውን ከገለጹ በኋላ ከሳሾች ያቀረቡት ክስ ውድቅ ሆኗል በማለትይህንን አቤቱታ ለማየት ስልጣን እንደሌለውና ለተከሰሱበት ችሎት አቤቱታችሁን ማቅረብ ነው ያለባችሁ በማለት ክሱ መዘጋቱን ገልጸዋል፡፡
ከአራዳ ፍረድ ቤት 6 የአንድነት አባላት ታፍነው ተወሰዱ
በዛሬው እለት በነሀብታሙ አያሌው የክስ መዝገብ አንድነት ፓርቲ ላቀረበው አቤቱታ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለማድመጥ በችሎት ተገኝተው የነበሩ 6 የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት
1ኛ.ደንኤል ፈይሳ
2ኛ.አብነት ረጋሳ
3ኛ.ጥላዬ ታረቀኝ
4ኛ.ፋሲካ አዱኛ
5ኛ.ብርሀኑ ይግለጡ እና
6ኛ.መሰለ አድማሴ በደህነቶች ታፍነው በቶዮታ ደብል ጋቢና ኮድ 3-50559 መኪና ወደ ማዕከላዊ መወሰዳቸውን የፍኖተ ነፃነት የማዕከላዊ ምንጮች ገልጸዋል።

Source- Finote nestanet

በአውሮፓ በድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ላይ ቦይኮት ተጠራ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሕወሓት አስተዳደር ስር የሚመራው ሜጋ አምፊ ትያትር ስር በአባልነት ሲያገለግል የቆየውና በጀርመን ሃገር ለ12ኛ ጊዜ በሚደረገው የስፖርት ዝግጅት ላይ የሙዚቃ ሥራዎቹን ለማቀረብ የሚያቀናው ማዲንጎ አፈወርቅ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ገጠመው፤ የሙዚቃ ኮንሰርቱ እንዳይደረግ ከፍተኛ ጥረት እናደርገጋለን ብለዋል።
madingo
በተለይ ከገዢው ፓርቲ ጋር ለመስራት ፍላጎት የሌላቸውን አርቲስቶች ለመንግስት ሃይሎች በመሰለል ይታወቃል የተባለው ማዲንጎ በተለይ በቅርቡ አማሮች ከደቡብ ክልል ሲባረሩ የመንግስት እርምጃ ትክክል ነው በሚል በግልጽ ተናግሯል በሚል ማህበራዊ ድረገጾች ወቀሳ ሲሰነዘርበት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

በአላሙዲ/ወያኔ ኮንሰርቶች ጋር በመሳተፍ ብዙሃኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ አስቀይሟል፤ የወያኔ ሰላይ ነው፤ በሚል ተቃውሞ የገጠመው ማዲንጎ የፊታችን ኦገስት መጀመሪያ በጀርመን የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚያቀርብ ከተሰማ ወዲህ በዛው አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአርቲስቱ ስም ላይ ቀይ መስመር በማስመርና የወያኔን ባንዲራ በማልበስ ሕዝብ እርሱ በሚገኝባቸው ኮንሰርቶች ላይ እንዳይታደም ጥሪ ተደርጓል።

በዚህ ዙሪያ ዘ-ሐበሻ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅን ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
boycott madingo

የጁሙዓ መርሃ ግብር! –ከድምፃችን ይሰማ የተላለፈ ጥሪ

$
0
0

muslim1
ረቡእ ሐምሌ 9/2006

የፊታችን ጁሙዓ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከባድ ተቃውሞ ይደረጋል፡፡ ይህ ደግሞ ተምሳሌታዊ አብሮነታችንን በሃገራችን በሁሉም አቅጣጫ ከወትሮው በተለየ መልኩ የምናሳይበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው፡፡ የፊታችን ጁሙዓ ህዝባዊነታችን ጎልቶ የሚታይበት፣ ለፍትህ፣ ለሰላም እና ለእምነት ነፃነታችን መከበር ያለንን ቁርጠኝነት እና ፅናት ደግመን ደጋግመን ለዓለም የምናሳይበት ታላቅ ተቃውሞ ነው፡፡ ተምሳሌታዊ አብሮነታችን በአገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም የሚገለጽ ነው፡፡ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን በሳምንቱ ውስጥም የሚፈጸሙ እንቅስቃሴዎችን አዘጋጅተዋል፡፡

በሃገር ቤት የሚኖረን በሰላማዊ ትግላችን ውስጥ ዋና የሚባሉ አጀንዳዎቻችንን በሙሉ ያካተተ ብርቱና የተቀናጀ ሃገር አቀፍ ተቃውሞ ነው፡፡ ከሃገር ውጭ ደግሞ ጁሙዓን ጨምሮ በቀሪዎቹ ቀናት የተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማካሄድ ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውናል፡፡
ይህ አገር አቀፍ ተቃውሞ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጂድ ይካሄዳል፡፡ (የሚከተለው መርሃ ግብር የአዲስ አበባ ሲሆን ክልሎችም ካሉበት ሁኔታ ጋር አዛምደው ከወትሮው የተለየ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው፡፡)
በነገው ጁመዓ ከሚከተሉት 5 መፈክሮች መካከል የገራልንን መፈክር በወረቀት ላይ አስፍረን ይዘን በመምጣት በተቃውሞው ላይ ከፍ አድርገን እናሳያለን፡-
‹‹የአገር መሰረት የሆነውን ህዝብ መናቅ ይቁም!!››
‹‹የህዝብ ድምፅ ይደመጥ!!››
‹‹የሙስሊም ተማሪዎች በነፃነት የመማር መብት ይከበር!!››
‹‹ከትምህርታችን ወይ ከሃይማኖታችን አታስመርጡን!!››
‹‹የሃይማኖት ነፃነትን ማክበር ግዴታ እንጂ ምርጫ አይደለም!!››
> የጁሙዓ ሰላት እንደተጠናቀቀ እጅ ለእጅ ተያይዘን ባለንበት ቦታ በመቆምና በፅሁፍ ይዘን የምንመጣቸውን መፈክሮች ከፍ አድርገን በማሳየት የሚከተሉትን መፈክሮች በድምጽ እናሰማለን፡፡
1. ‹‹አላሁ አክበር!›› ለ 2 ደቂቃ
2. ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› ለ 2 ደቂቃ
3. ‹‹ሕገ መንግስቱ ይከበር!›› ለ 2 ደቂቃ
4. ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!›› ለ 2 ደቂቃ
5. ‹‹የታሰሩት ይፈቱ!›› ለ 2 ደቂቃ፤ በየክልልሉና በየማረሚያ ቤቱ ታጉረው የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ፍትህ ብትረሳቸውም ህዝበ ሙስሊሙ እንዳልረሳቸው ለማሳየት፡፡
6. ‹‹ጣልቃ ገብነት ይቁም!›› ለ 2 ደቂቃ
7. ‹‹ኢማሞቻችን ይመለሱ!›› ለ 2 ደቂቃ
8. ‹‹የመንግስት ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ!›› ለ 2 ደቂቃ
9. ‹‹መማር መብታችን ነው!›› ለ 2 ደቂቃ፤ ህዝበ ሙስሊሙ የመማር መብቱ ህገ መንግስታዊ እና ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ያፀደቁት ሰብዓዊ መብታችን መሆኑን ለማሳየት፡፡
በመጨረሻም ካለንበት ቦታ ሳንንቀሳቀስ እጆቻችንን ወደ አላህ በመዘርጋት ዱዓ በማድረግ ወደየመጣንበት እንመለሳለን – ኢንሻ አላህ!
ትግላችን እስከ ድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

የ‹‹ተምሳሌታዊ አብሮነት›› ሳምንትን ስኬታማ ለማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ዝግጅቶች ተሟሙቀው ቀጥለዋል፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል ሆነው ከስራ እና ከሰዓት እጥረት ጋር እየታገሉ በአገር ቤት ወንድሞቻቸውን ለማገዝ ሰንፈው የማያውቁት የዳያስፖራው ማህበረሰብ እህትና ወንድሞቻችን ዛሬም እንደተለመደው ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ እስካሁን ድረስ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በዳላስ፣ በሲያትልና በቺካጎ ለፊታችን ቅዳሜ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ማወቅ የተቻለ ሲሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባት ሳዑዲ ዓረቢያም እንዳለፉት ሁለት ሳምንታት ሁሉ በሶስተኛው ሳምንትም የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ ታውቋል፡፡

በሌሎች ሃገራት የሚገኙ የዳያስፖራ ማህበረሰቦችም በቀሪዎቹ ጊዜያት የጁሙዓውን ዓለም አቀፍ መርሃ ግብር እና ካሉበት ሁኔታ ጋር የሚጣጣሙ ሌሎች ፕሮግራሞችን ለመተግበር አስፈላጊውን ዝግጅት እንዳገባደዱ ተስፋ እያደረግን በዓለም አቀፍ ደረጃ ድምጻችን ጎልቶ እንዲሰማ ለማድረግ ሲያደርጉት የቆዩትን፣ አሁንም እያደረጉ ያሉትን ጥረት አላህ ይቀበላቸው ዘንድ ምኞታችን ነው! እኒህን መሰል ዓለም አቀፍ መርሃ ግብሮችና ዝግጅቶች ሰላማዊ ትግላችንን የበለጠ ዓለምአቀፋዊነት በማላበስ ድምጻችን የበለጠ ጎልቶ እንዲሰማ ያደርጋሉ፡፡ ‹‹ተምሳሌታዊ አብሮነት›› ሊገለጽበት የሚችልበት ሌላ የተሻለ መንገድ ከቶስ ይኖር ይሆን?
ጥቆማዎች

በውጭ ለምትኖሩ ሙስሊሞች ተግባራቱን ማዕከላዊ በሆነ መልኩ ማቀድ ካላችሁበት ሁኔታ ጋር ላይዛመድ ስለሚችል ዋና ዋና ዓላማዎችን እና በሃገር ቤት ያለን ሙስሊሞች በይበልጥ እናንተ ብትሳተፉበት ብለን የምንመኛቸውን አንኳር ተግባራትን ለመጠቆም እንሞክር፡-
1. አለምዐቀፍ መርሃ ግብሮች ሰላማዊ ትግላችን አሁንም በጥንካሬ የመቀጠሉና የሁሉም የህብረተሰብ አንገብጋቢ ጉዳይ የመሆኑ ትልቅ ማሳያዎች ናቸው፡፡ እንቅስቃሴውም የሚፈጥረው ጫና እና የሚያስተላልፈው መልእክት በራሱ በትልቅ ዓላማነት የሚያዝ ነው፡፡ በመሆኑም በሰፊም ሆነ በአነስተኛ መርሃ ግብር በዚህ ሳምንት ቢያንስ አንድ ተግባር አቅዳችሁ ትተገብራላችሁ ብለን እንጠብቃለን፡፡
2. የዲያስፖራው ማህበረሰብ ዋና ትኩረት እንዲሆን የምንሻው የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት የሚስቡ እና የሚዲያ አጀንዳ የሚፈጥሩ ለየት ያሉ ተግባራት ላይ ትኩረት እንድታደርጉ ነው፡፡

3. ባላችሁበት አካባቢ ለሚኖሩ ማህበረሰቦች እና ተቋማት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ኢፍትሃዊ ተግባራትን እንድታጋልጡ እና የተቻለውን ያክል ለማስቆም ጫና የሚያሳድሩ እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ከእናንተ በዋናነት ይጠበቃሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን ከመታሰሩ ጥቂት ደቂቃዎች አስቀድሞ ከቢቢኤን ሬዲዮ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ የዲያስፖራው ማህበረሰብ ዋነኛ ሚና ምን ሊሆን እንደሚገባ የጠቆመውን በማስታወስ የበኩላችሁን እንድትወጡ ይጠበቃል፡፡
4. ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር መልካም ግንኙነት እና በቀጣይ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት የሚያስችሉ ጤናማ ግንኙነቶችን መፍጠር ይጠበቅባችኋል፡፡

በመሆኑም ከላይ የተቀመጡትን አራት ዋና ዋና ከእናንተ የምንጠብቃቸውን ዓላማዎች ታሳቢ በማድረግ በረመዳን ሶስተኛ ሳምንት ውስጥ በንቃት እና በጠንካራ የአጋርነት ወኔ ወደተግባር የሚያስገባ እቅድ እንድታዘጋጁ እና ወደተግባር እድትገቡ እንጠቁማለን፡፡ እንደመነሻ መሆን የሚችሉ ተግባራት እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡-
• ኮንፈረንስ ብታዘጋጁ እና የተለያዩ ተቋማትን፣ በተለይም የሚዲያ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ስለትግሉ፣ በይበልጥም ስለቀጣዩ የትግል አቅጣጫ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ብትሰሩ፤
• በመካከላችሁ አንድነትን የሚያጠናክሩ እና ተባብሮ ቁም ነገር ያለው የሚታይ ስራ ለመስራት የሚያስችሉ የአንድነት የኢፍጣር ፕሮግራሞች ብታዘጋጁ፤
• የጎዳና ላይ ሰልፍ (አመቺ ከሆነ) እና ለየት ያሉ በግል እና በቡድን ሊሰሩ የሚችሉ ትኩረት ሳቢ የጎዳና ላይ ትዕይንቶች እና በእናንተ ተጨባጭ አመቺ የሆኑ መርሃ ግብሮችን በመቅረፅ የታሰበው እንዲሳካ ሰፊ ርብርብ እንድታደርጉ እንጠይቃለን፤
ለምታደርጓቸው እቅስቃሴዎች ስኬት በቂ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ በልዩ ትኩረት እንድትሰሩ እየጠቆምን ወደእኛ የምትልኳቸውን ዜናዎች በተሻለ መጠን ሽፋን እንዲያገኙ ለማድረግ የምንጥር መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በደማቅ ተምሳሌታዊ አብሮነት ድምጻችንን በዓለምአቀፍ ደረጃ ለማጉላት እንረባረብ!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

አገራዊ ጥሪ ለመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት

$
0
0

ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላትን ከአለቆቻቸው ለይቶ ይመለከታል።

G7የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ከፍተኛ ሹማምንት ከህወሓት የተቀዱ፣ ለህወሓት ሥልጣን የቆሙ፣ ዘረኞች፣ ፋሽስቶችና ሙሰኖች መሆናቸው በገሃድ የሚታወቅና በተደጋጋሚ ጥናቶችም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። በዘመነ ወያኔ የሠራዊት አዛዥነት ሹመት መሥፈርቶች ዘር፣ የፓለቲካ አመለካከትና ለህወሓት ያላቸው ታማኝነት ነው። በዚህም ምክንያት ሁሉም ቁልፍ የአዛዥነት ቦታዎች የተያዙት ሙሉ በሙሉ የህወሓት አባላት በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ነው። እነዚህ የጦርና የፓሊስ ሹማምንት ኢትዮጵያን ወረው እንደያዙት አገር ሲዘርፉ፣ ሕዝቧንም ሲገሉና ሲገርፉ እንሆ 23 ዓመታት አልፈዋል።

በእነዚህ 23 ዓመታት ትግራይን ጨምሮ በደል ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ግዛት እና የኅብረተሰብ ክፍል የለም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእነዚህ ፋሽስቶች ተረግጧል፣ ተዋርዷል፣ ተግዟል። የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በእነዚህ እኩይ የሠራዊቱና የፓሊስ አዛዦች ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው። የወያኔ የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች አገራችን እያደሙ፤ ሕዝባችንን እያስለቀሱ ነው። በወያኔ ፋሽስት የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች ጥምረት ሰቆቃ የሚፈፀምበት የኅብረተሰብ ክፍል በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል። የወያኔ ማሰቃያዎችን የሞሉት የፓለቲካና የሀይማኖት መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች መሆናቸው ለዚህ አንድ ማሳያ ነው።

የሠራዊቱ የበታች ሹማምንትና ተራ አባላት ጥንቅር ግን ከአዛዦቹ ፈጽም የተለየ ነው። የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ከመላው የኢትዮጵያ ግዛቶች የተውጣጡ፤ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በነፃነት እጦት፣ በመብቶች መገፈፍ እና በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩ ዜጎች ናቸው። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዦቹ እየታዘዘ ወገኑን የሚበድል ቢሆንም ራሱ ከመበደል ግን አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዡ ታዞ ሌላኛውን ወገኑን ቢያስርም ሹሙ ፊቱን ባዞረበት ጊዜ እራሱ ደግሞ ከመታሰር አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር ወያኔ አዞት ምስኪኖችን ይደበድባል፤ ራሱ ደግሞ በወያኔ ይደበደባል። የኢትዮጵያ ፓሊስ በወያኔ ትዕዛዝ ንጹሀን ዜጎችን ያስራል፣ ያሰቃያል፤ እራሱ ደግሞ በወያኔ ይታሰራል፣ ይሰቃያል። ይህ ምን የሚሉት ባርነት ነው? የወያኔ ሹማምንቶች በሚመሩት የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በህወሓት የሚደርስባቸው በደል ሌላው ኢትዮጵያዊ ከሚደርስበት ይብስ እንደሆን እንጂ የሚያንስ አይደለም።

ግፍ መብቃት አለበት። በጥቂት የህወሓት ሹመኖች ትዕዛዝ በኢትዮጵያዊው ወታደር ላይ የሚደርሰው ውርደት ማብቃት አለበት። ሠራዊቱ የኢትዮጵያ እንጂ የህወሓት ሠራዊት አይደለም፤ ሊሆንም አይገባውም። ሠራዊቱ ለራሱ ነፃነት ብቻ ሳይሆን ለአገርና ለሕዝብ ደህንነት ዘብ የመቆም ኃላፊነት አለበት። የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት የባንዳ ሠራዊት ሆኖ ሕዝብን በማሰቃየትና ሀገርን በመበደል ተግባር ላይ ተሠማርቶ ማየት አንሻም። ይህንን ለራሱ ክብር ያለው፤ አገሩንና ሕዝቡን የሚወድ የሠራዊቱ አባልም የሚፈቅደው ጉዳይ አይደለም።

ስለሆነም ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚከተለው ሀገራዊ ጥሪ ለመላው የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ያቀርባል።

ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያ ወይም የፓሊስ ሠራዊት አባል! በጥቂት የህወሓት ፋሽስቶች መዳፍ ውስጥ ሆነህ የገዛ ራስህን፣ የቤተሰቦችህን፣ የወገንህን እና የአገርህን ስቃይ ማራዘምህን አቁም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታ እንጂ የጥቂት ጎጠኞች ሎሌ ልትሆን አይገባም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ መከታ እንጂ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ስጋት መሆን የለብህም። አንተ የመጪው ትውልድ አርዐያ እንጂ ሕፃናትንና ወጣቶችን ማስፈራሪያ መሆን የለብህም።

የኢትዮጵያ ወታደር ሆይ! ራስህን ተመልከት! ራስህን ታዘብ! ዛሬ ያለህበት ሁኔታ አሳፋሪ ነው። አዛዦችህ አገርን፣ ትውልድንና ታሪክን ለማጥፋት የተነሱ ናቸው። አንተን ተጠቅመው ነው ይህንን ዓላማቸውን የሚያስፈጽሙት። ይህ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለልጅ ልጆችህ ውርደት ነው። ከወያኔ ባርነት ራስህን ነፃ አውጣና የነፃነት ታጋዮችን ተቀላቀል። ወያኔ መጥፋቱ አይቀርም። ወያኔ የቀድሞውን ጦር እንደበተነው አንተን ለመበተን የሚሻ የለም። አንተ ዛሬ ከወገን ጋር ወገንተኛነትህን ካሳየህ ከአገዛዙ ጋር እጠፋለሁ ብለህ አትስጋ። ለዚህም ነው አንተ ዛሬ በግልም ሆነ በቡድን የምትወስደው እርምጃ የአገራችንን ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱን እጣ ፈንታ ይወስናል ብለን ወገናዊ ጥሪ የምናቀርብልህ።

ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ወገናችን!ከበዳዮች ጎን ሳይሆን ከተበዳዮች ጎን ቁም። ከገራፊዎችና ገዳዮች ጎን ሳይሆን ከነፃነት ታጋዮች ጎን ሁን። ዛሬውኑ ወስን። አሁን የነፃነት ታጋዮችን መቀላቀል ቀላል ሆኗል። ያሉበትን ታውቃለህ፤ ተቀላቀል። አልያም የጠመንጃህን አፈሙዝ በፋሽስት አለቆችህ ላይ አዙር። ይህንን እርምጃ በመውሰድ ከታሪክ ተወቃሽነት እራስህን በመታደግ ለአገርህና ለወገንህ አለኝታህን አረጋግጥ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!


የፖለቲከኞቹ እስር እና ያስከተለው ሕገመንግሥታዊ ጥያቄ

$
0
0

በመልካሙ አበበ

ሰንደቅ

Wektawi62ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቃለምልልስ የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን ወደኢትዮጵያ ተላልፈው የመሰጠታቸው ጉዳይ በማንሳት “የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሽፋንአድርጎ የሚመጣአሸባሪነትንአይታገስም”ማለታቸውን ዘግቧል።

     የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መያዝ ተከትሎ በሀገር ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ከሆኑት መካከል አቶ ሐብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከአንድነት፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ ከሰማያዊ ፓርቲ፣ አቶ አብርሃ ደስታ ከአረና ትግራይ (ዘግይቶም ቢሆን ፍ/ቤት ቀርቧል)፣ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። የጸረ ሽብር ግብረሃይል የግንቦት 7 ልሳን ከሆነው ኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ግንኙነት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በቁጥጥር ስር ማድረጉን በደፈናው በዕለቱ የገለጸ ሲሆን የተያዙት የአንድነት፣ የሰማያዊና የአረና አመራሮች መሆናቸው ሲታይ መግለጫው እነሱን በቀጥታ የሚመለከት ስለመሆኑ የብዙዎች ግምት ሆኗል።

እስሩ እና የፓርቲዎች ምላሽ

     አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲዎች በተናጠል ሰሞኑን ባወጡት መግለጫ እስሩን ከመጪው ዓመት ምርጫ ጋር በቀጥታ አስተሳስረውታል። አንድነት በመግለጫው ኢህአዴግ የአንድነትን ከፍተኛ አመራሮች በማሰር የምርጫ ዘመቻውን ይፋ አድርጓል ብሏል። ሰማያዊ ፓርቲም በበኩሉ እስሩ ኢህአዴግ ቀጣዩን ምርጫ ያለተቀናቃኝ ለማለፍ የሚያደርገው ሕገወጥ እንቅስቃሴ አካል ነው ሲል ነቀፌታውን ሰንዝሯል።

   ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ለቢቢሲ በሰጡት መግለጫ ላይ በሕጋዊ መንገድ በፖለቲካ ፓርቲ በመደራጀት እናሽፋን በማድረግህገወጥ እንቅስቃሴን በማካሄድ መንግስትን በኃይል ለመለወጥ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ግለሰቦች አሁንም ከተጠያቂነት አያመልጡም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ሕግ አስከባሪው፤ ሕግ ያለማክበር ጥያቄ ሲነሳበት፣

     የሕጎች ሁሉ የበላይ ሕግ የሆነው ኢትዮጵያ ህገመንግስት አንድ ሰው በሕግ ጥላ ስር ከዋለ በኋላ ቢበዛ በ48 ሰዓታት ፍርድቤት መቅረብ እንዳለበት ይደነግጋል። በተለይ የአንድነት እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ማክሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ፍ/ቤት ሳይቀርቡ ሰባት ቀናት ተቆጥረዋል። ይህም ብቻ አይደለም፤ በመረጡት ጠበቃ የመወከል መብታቸውንም ተጠቅመው ከጠበቆቻቸው ጋር የመገናኘት ዕድል መነፈጋቸውን ከፓርቲዎቹ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። አንድነት ይህን ድርጊት ሕገወጥ በማለት አካልን ነጻ የማውጣት ክስ በፍርድ ቤት መመስረቱን አስታውቋል። ይህም ሆኖ እስከትላንት(ማክሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2006) ማምሻውን ድረስ ተጠርጣሪዎቹ ፍ/ቤት ስለመቅረባቸው የታወቀ ነገር የለም።

አንድ የህግ ባለሙያ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት አስተያየት “የሕግ የበላይነት በሚከበርበት ሀገር መንግሥት መረጃ አለኝ እስካለ ድረስ በሽብር ተግባር የተጠረጠሩ ሰዎችን ይዞ ማሰሩ አዲስ ነገር አይደለም። ነገር ግን ህግና ስርዓት እንዲከበር እተጋለሁ የሚል መንግሥት ራሱ ያወጣውን ሕገመንግስትን ጥሶ ያሰራቸውን ተጠርጣሪዎች በወቅቱ ወደፍርድ ቤት ማቅረብ ሳይችል ሲቀር የሕግ በላይነት የሚባለው ጉዳይ ያበቃለታል። በዚህ ምክንያት ዜጎች በመንግሥትና በሕግ ላይ ያላቸው አመኔታ የሚያጡ ሲሆን በቀጣይ ሕግና ስርዓትን አስከብራለሁ ብሎ የሚሞክራቸው ወይንም የሚናገራቸው ነገሮች ሁሉ በሕዝብ ዘንድ ተአማኒነትን ስለማይኖራቸው ትልቅ ችግር ይገጥመዋል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

በሰሞኑ ክስተት፤ የኢዴፓ አቋም

የኢትዮጽያዊያን ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) “በሽብርተኛነት ስም የሚወሰደው እርምጃ ግልጽነት ይኑረው” በሚል ርዕስ ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ የመንግሥት እርምጃ እንዳሳሰበው ጠቁሟል። መግለጫው እንዲህ እያለ ይቀጥላል «በሀገር ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም መንግሥት በሽብር ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ማዋሉ በሚዲዎች ተገልጿል። እነዚህ አመራሮች ከ48 ሰዓታት በላይ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አለማቅረባቸው አመራሮቹ የታሰሩት በሚያራምዱት የፖለቲካ አቋም እንዳይሆን ፓርቲያችን ሥጋት አድሮበታል።

የኢዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮምቴ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተለውን አቋም ወስዷል።

  1. 1. መንግሥት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የተያዙበትን ምክንያት ለህብረተሰቡ በዝርዝር እና ግልጽ መረጃ እንዲሰጥ፣
  2. 2. የታሰሩት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በሕገመንግስቱ አንቀጽ 21 መሠረት ለዜጎች የተሰጠው መብት እንዲከበርላቸው፣
  3. 3. በአስቸኳይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ፣ የፍርድ ሒደታቸውም ተአማኒ፣ ግልጽ እና ፈጣን በሆነ መንገድ እንዲታይ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን አገሪቱ ሕግ አክብረን በሰላማዊ ትግል ከምንቀሳቀስ ፓርቲዎች ይልቅ በተቃራኒ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች የሚያጠናክር፣ ክርክራቸውንም ምክንያታዊ የሚያደርግ እና የዴሞክራሲ ግንባታውን ወደኋላ የሚመልስ በመሆኑ ጉዳዩ በእጅጉ እንደሚያሳስበን እንገልጻለን። ስለዚህም መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት ተገንዝቦ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ኢዴፓ ያሳስባል።”

የፍረጃ ፖለቲካ

    የደርግ መንግሥትን በኃይል ለመጣል በተደረገው የትጥቅ ትግል ወቅት ደርግ ታጋዮችን “ገንጣይ፣ አስገንጣይ፣ የእናት ጡት ነካሽ ወንበዴ….” እያለ የህዝብ ድጋፍ እንዳያገኙ ሌተቀን የመንግስት መገናኛ ብዙሃንን መሣሪያ በማድረግ ያወግዝ እንደነበረው ሁሉ አሁንም በተመሳሳይ ሁኔታ ኢህአዴግ ተቀናቃኞቹን በተደጋጋሚ በጠላትነት ሲፈርጅ፣ ሲያጥላላ ይታያል። በተቃዋሚ ፓርቲዎችም በኩል ተመሳሳይ ዝንባሌዎች የሚታዩ መሆኑ መቻቻልና በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንኳን አብሮ የመሥራት ባህል እንዳያድግ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።

    በዚህ ምክንያት ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ እና ብዙዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግንኙነታቸው በጠላትነት መንፈስ ላይ የተመሰረተና መተማመን የሌለበት፣ ጥላቻ የነገሰበት ሆኖ እስከአሁን ዘልቋል። ኢህአዴግ በ2002 ምርጫ ከ99 በመቶ በላይ ወንበሮችን ካሸነፈ በኋላ ለንባብ የበቃው “አዲስ ራዕይ” መጽሔት በሐምሌ-ነሐሴ ወር 2002 ዓ.ም ዕትሙ ስለተቃዋሚዎች እንዲህ ይላል። “…አንዳንዶቹ ተቃዋሚዎች የተለመደውን የቀለም አብዮተኞች ስልት በመጠቀም የምርጫ ሕጎችን ሆን ብለው በመጣስ በሕጉ መሰረት እርምጃ ሲወሰድባቸው በነጻ መወዳደር አልቻልንም ብለው ኡኡ እንደሚሉ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነበር። እናም ስትራቴጂያችን እንደነዚህ ዓይነት ድርጊት ሲፈጸም መዋቅራችን የተሟላ መረጃ በቪዲዮ ጭምር እንዲይዝ፣ ይህንኑ መሠረት አድርጎ ድርጊቱን በሕዝብ ፊት እንዲያጋልጥና ሆን ተብሎ ምርጫውን ለማበላሸትና ብጥብጥ ለመፍጠር የተደረገ ተግባር መሆኑን እንዲያስረዳ፣ ሕጉ የተፈቀደለትን እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥቦ ነገሩን ለበላይ አካል ሪፖርት እንዲያደርግ ነበር የሚያስቀምጠው። በዚሁ መሠረት የተቃዋሚዎች ሕገወጥ ድርጊት በየአካባቢው እንደነገሩ ሁኔታ በአገር አቀፍ ደረጃ በሰፊው የሚጋለጥበት ሁኔታ ተፈጠረ” ሲል የመተጋገሉን ደረጃ ያሳያል።

    እንዲህ ዓይነት አንዱ አጋላጭ ሌላው ተጋላጭ፣ አንዱ ሕግና ስርዓትን አክባሪ፣ ሌላው ጸረ ሕገመንግሥት፣ አንዱ ሽብርተኛ ሌላው የሠላም አቀንቃኝ አድርጎ የመሳሉ ጉዳይ ሞቅ በረድ እያለ አሁን ድረስ መቀጠሉ በሁለቱ ኃይሎች መካከል ያለው የፖለቲካ ልዩነት ወደአላስፈላጊ ጠርዝ የሚገፋ ሆኖ ይታያል።

    ከምንም በላይ ደግሞ መንግሥት በወንጀል ጠርጥሮ የያዛቸውን ሰዎች በወቅቱ ፍርድ ቤት ከማቅረብ መቆጠቡ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን አክብሮ የማስከበር ኃላፊነቱን አለመወጣቱን ያሳያል። ሕግና ሥርዓትን የማክበር ጉዳይ ደግሞ በምንም ዓይነት ምክንያት ሊስተባበል የማይችል መሆኑንም መንግሥት ይስተዋል ተብሎ ስለማይገመት ስህተቱን በፍጥነት ሊያርም ይገባል።

ከእስሩም በላይ –“ሽብርተኝነት” –እስረኞቹ በሽብር መከሰሳቸውን አያውቁም

$
0
0

ጽዮን ግርማ
tsiongir@gmail.com

አንድ ዓመት ከአንድ ወር ኾኖታል፡፡ እስክንድር ነጋ ከታሰረ ከዐስራ ስምንት ወራት በኋላ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በሰኔ የመጀመሪያ ወር ላይ በ2005 ዓ.ም እንደተፈቀደለት ነው፡፡ በወቅቱም እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ወደሚገኘው እስር ቤት አምርቼ ነበር፡፡
zone 9
ተገናኝተን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላም እንዲህ አለኝ፤‹‹ሽብርተኛ አይደለኹም፤ሀገሬ በማንም እንድትሸበር አልፈልግም አልፈቅድምም እኔ የምፈልገው የሀገሬ ሕዝቦች በነጻነት የሚያስቡባትና የሚንቀሳቀሱባት ሰላማዊ ሀገር እንድትኾን ነው››፤እስክንድር ‹‹ሽብርተኛ›› አይደለምና ከእስሩም በላይ ያንገበገበው ‹‹አሸባሪ›› መባሉ ነበር፡፡

እስክንድር ‹‹ጋዜጠኛ›› ነው፡፡ እስክንድር ሲጽፍ ሀገሪቱ ላወጣችው ሕግ ራሱን አስገዝቶ፣በሀገሪቱ ሕግ ማዕቀፍ ሥር ራሱን ገድቦ ነው፡፡ ይህም ኾኖ ግን ሲጽፍ ሕግ ተጥሶ አደጋ ሊደርስበት እንደሚችል፣ሲጽፍ ሕግ ተጥሶ ሊታሰር እንደሚችል ያውቃል፡፡ ግን ደግሞ ቢታሰር በቀጫጭን መስመርም ቢኾን በሀገሪቱ ሕግ ተዳኝቶ ከእስር ሊለቀቅ እንደሚችል ያምን ነበር፡፡በዚህ እምነቱም የመጣበትን ለመቀበል ተዘጋጅቶ ሀገሩ ላይ ቁጭ ብሎ ይጽፋል፡፡
ከመጻፍ እና ሐሳቡን በአደባባይ ከመግለጽ ውጭ ያሉት መንገዶች እስክንድርን አይመቹትም፡፡ እስክንድር ሐቀኛና ቀጥተኛ የኾነ አስተሳሰብ ያለው ላመነበት ነገር የታመነ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ምናልባት ይህን ‹‹እስክንድርን›› ለመረዳት እስክንድርን ማወቅ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ እስክንድርን ያኔ ቃሊቲ ሳገኘው ሽብርተኛ አለመኾኑን ደጋግሞ ነገረኝ፡፡ ‹‹እስክንድር ለማነው የምትነግረው ሽብርተኛ አለመኾንህን ከቀረበብህ ክስ ጋር አንዳችም ግንኙነት እንደሌለህ እኮ ዓለም ያውቃል፤አሳሪዎችህም ይህን ጠንቅቀው ያውቃሉ›› አልኩት፡፡ እርሱን ግን ያበሳጨው ከታሰረውም፣ከተንገላታውና ከተፈረደበትም በላይ በውሸት የተወነጀለበት “ሽብርተኝነት’’ ነበር፡፡

አሁንም ሽብርተኝነት

አሁን እስክንድር ከታሰረ ሁለት ዓመት ከሰባት ወር ኾኖታል በእርሱ የተጀመረው ጋዜጠኛን፣ጸሐፊዎችንና መብቱን በአደባባይ የሚጠይቀውን ሁሉ ሰብስቦ ‹‹ሽብርተኛ›› ብሎ መክሰስ ዕለት በዕለት እየጨመረ የታሳሪዎቹን ቁጥር አበራክቷል፡፡ ላለፉት ሰማንያ ሦስት ቀናት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታስረው የሚገኙትና በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ በቀጠሮ ሲመላለሱ የቆዩት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና፣ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ የሕግ መምሕርና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘለዓለም ክብረት፣ የዞን ጦማሪዎቹ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃኑ ለቅዳሜ ሐምሌ 5 ቀን የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎቹ ማኅሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ኃይሉና አቤል ዋበላ በዚሁ በፈረደበት ‹‹ሽብር›› ተጠርጥረው የታሰሩ ናቸው፡፡
የምርመራ መዝገቡ በሌሉበት መዝገቡ ተዘግቶ ከሕግ ውጪ በእስር የከረሙት እነዚህ እስረኞች ግንቦት ዘጠኝ በነበረው ቀጠሮ ቀን ፖሊስ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተጠርጣሪዎችን በሽብር መጠርጠሩን ሲናገር ወጣቶቹ በድንጋጤ አንገታቸውን ሲሰብሩ ታይተው ነበር፡፡ የሚያስደነግጠው እስሩ አይደለም ሕግን አስከብራለሁ የሚል አንድ ተቋም ወጣቶችን ሰብስቦ አስሮ ባልዋሉበት የሚያውል የፈጠራ ክስ ሲጭን መስማቱ ነው፡፡ማንነቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው እንዲህ ያለ የውሸት ክስ ሲቀርብበት የሚሰማውን ስሜት ለመገመት ያስቸግራል፡፡ እናም ወጣቶቹ በሽብር ተግባር አለመሳተፋቸውን ያውቃሉና የቱንም ያህል ኢሕአዴግን ባህሪ ጠንቅቀው ቢያውቁት ‹‹በሽብር እንከሰሳለን›› የሚል ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ምናባት የመጨረሻውን ጣሪያ ቢገምቱ እነርሱን አስሮ ሌሎች ጸሐፊዎችን ለማስፈራራት የተነደፈ ስልት ይኾናል ከሚል ግምታዊ መላምት ‹‹ምርጫው እስኪያልፍ ታስረን እንቆያለን›› የሚለውን ነው፡፡
ዛሬ ጠዋት ልደታ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ሲቀርቡም ከዚሁ ሐሳብ ሊኖራቸው እንደማይችል እገምታለሁ፡፡ ወጣቶቹ ከታሰሩ ጀምሮ ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ጠበቃ፣ቤተሰብና ሌሎች ሰዎች ከትናንት ጀምሮ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ይችላሉ በሚል ይቀርቡበታል በተባለው ፍርድ ቤት ግቢ ክትትል ሲያደርጉ ቢቆዩም ዛሬ ጠዋት ማንም ሰው ባልተገኘበት ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ከፍቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን የክስ ቻርጁ እንዲሰጣቸውና መቃወሚያ ካላቸው እንዲናገሩ ተጠይቀው ዘጠኙም እስረኞች ጠበቆቻቸው ባልተገኙበት ክሱ እንዲነበብላቸው እንደማይፈልጉ ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነትን አግኝቶ ጠበቆቻቸው በተገኙበት ነገ ጠዋት እንዲቀርቡ ታዟል፡፡

በሌላም በኩል ዛሬ ጠዋት እስረኞቹን ለመጠየቅ ማዕከላዊ ሄደው የነበሩ ቤተሰቦችና ጠያቂ ወዳጆች መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው ተመልሰው ነበር፡፡ ከሰዓት በኋላም ሊጠይቋቸው በሄዱ ጊዜ ስለተከሰሱት ክስ የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ አብዛኞቹም (አብዛኞቹ ስል ስለ አስተያየታቸው መረጃ ያገኘኹት ማለቴ ነው) በሽብርተኝነት እንከሰሳለን የሚል እምነት አልነበራቸውም፡፡ነገ የሚኾነውን ለማየት በይደር አቆይተው ቤተሰቦቻቸውን ተሰናብተው ወደ ማደሪያቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል፡፡

የሽብርተኝነት ክሱ

የሪፖርትር ጋዜጣ ዘጋቢ ታምሩ ጽጌ ደግሞ ሰበር ዜና በሚል በጋዜጣው ድረ ገጽ ላይ፤ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ፣ እንዲሁም ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ላይ ዐቃቤ ሕግ በሽብርተንነት ክስ መመስረቱን አስነብቦናል፡፡

ዜናው እንደሚለው፤ ተጠርጣሪዎቹ በሕቡዕ በመደራጀት፣ የአጭርና የቅርብ ጊዜ ግብ በማቀድና በመንደፍ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በፓርላማ ሽብርተኛ ተብለው ከተሰየሙት የግንቦት 7 እና የኦነግ ድርጅቶች መመርያና ሐሳብ ሲቀበሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡
ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ የሆነችው ሶሊያና ሽመልስ የቡድኑ መሥራችና አስተባባሪ በመሆን ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. መቆየቷና ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በውጭ አገር አስተባባሪና የውጭ ግንኙነት ሆና ከመሥራቷም በተጨማሪ፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በማደራጀትና በመመልመል ስትሠራ መቆየቷን ክሱ ያስረዳል፡፡የህቡዕ ቡድኑ ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. ‹‹ሴኩሪቲ ኢን ቦክስ›› የተባለ ሥልጠና እንዲሠለጥንና እንዲደራጅ ስትመራ መቆየቷም በክሱ ተካቷል፡፡
ሌላኛው ተጠርጣሪ በፍቃዱ ኃይሉ የአገር ውስጥ የሽብር ቡድንን በመምራትና የሥራ ክፍፍል በማድረግ፣ እንዲሁም ግብ በማስቀመጥና ስትራቴጂ በመንደፍ ከሽብርተኛ ኃይሎች ጋር ግንኙነት ሲፈጥር መቆየቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡
የዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ ተጠርጣሪ ናትናኤል ፈለቀ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የህቡዕ ድርጅቱ የአገር ውስጥ አስተባባሪ በመሆን በሥሩ ላሉት አባላት የሥራ ክፍፍል መመርያ በመስጠት፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት በመፍጠር መመርያ ከመቀበሉ በተጨማሪ፣ ለአመፅ ተግባር የሚውል የተላከለትን 48,000 ብር ማከፋፈሉንም ክሱ ያብራራል፡፡

ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች በህቡዕ ድርጅቱ ውስጥ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ መሥራችና አባል በመሆን የግንቦት 7 እና የኦነግን ስትራቴጂና ዕቅድ በመቀበል በውጭና በአገር ውስጥ ባሉ የቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በውጭና በአገር ውስጥ ሥልጠና በመውሰድ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማቀድ፣ በመዘጋጀት፣ በማሰርና በማነሳሳት ወንጀል መከሰሳቸውን ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡

በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ሁለተኛ ክስ እንደሚያስረዳው ተጠርጣሪዎቹ በወንጀሉና በሚያስገኘው ውጤት ተስማምተው በሕገ መንግሥት ሥርዓት የተቋቋመን መንግሥት በአመፅ፣ በሁከትና በብጥብጥ ለመለወጥ በማሰብ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. እስከተያዙበት ዕለት ድረስ በህቡዕ ተደራጅተው፣ የሥራ ክፍፍል በመፍጠር፣ ሥልጠናዎችን በመውሰድ፣ አመፅ የሚቀሰቅሱ ጽሑፎችን በመበተን፣ የአመፅ ቡድኖችን በማደራጀት ሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመፅና በሁከት ለመለወጥ በመሞከር ወንጀል መከሰሳቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

በመጨረሻ

ይህን ክስ የሰማ ማንም ሰው እነዚህ ወጣቶች ሽብርተኛ አለመኾናቸውን እንደሚረዳው ኹሉ ከሳሻቸው ዐቃቤ ሕግም የውሸት ክስ እንደመሰረተባቸው ልቦናው ያውቀዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ወጣቶቹን በቅርበት ለሚያውቃቸው ሰው በእነሱ ላይ እንዲህ ያለ ክስ ሲመሰረትባቸው ምን ዐይነት ስሜት እንደሚፈጥር ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡ጠንካራና ሀገር ወዳድ ወጣቶች በሽብርተኝነት ሲከሰሱ መስማት የሚፈጥረውን ቁጭት ከቃላትም በላይ ነው፡፡ይህ ስሜት እነርሱ ላይ ሲደርስ ምን ሊኾን እንደሚችልም መገመት ያስቸግራል፡፡ እስክንድርን ከመታሰሩም በላይ ያስከፋው እንኳን ክፉ ሊያደርስባት ክፉ እንዳይነካት ቀን ከሌሊት የሚጸልይላትን የሚወዳትን ሀገሩን ገንዘብ ተቀብለህ ልትበጠብጣት ነው መባሉ ነበር፡፡
‹‹ዴሞክራሲያዊነቷ›› የታወጀላት ታሀገር ስትበደል ሕግ በሚፈቅድላቸው መሰረት ተቃውሟቸውን በጹሑፍ ያሰሙ፣ለሀገሪቱ ሕግ ራሳቸውን አስገዝተው የጋዜጠኝነት ሥራን የሠሩ በሽብርተኞች እጅ የወደቁ እንጂ ‹‹ሽብርተኛ›› ያልኾኑት ወጣቶች ነገ ጠዋት በሽብርተኝነት መከሰሳቸውን ሲሰሙ ምን ይሉ ይኾን

(ሰበር ዜና) በአንዋር መስጊድ ፖሊስ እና ሕዝበ ሙስሊሙ ተጋጩ፤ በአካባቢው ውጥረት ነግሷል

$
0
0

demtschin yesema 2(ዘ-ሐበሻ) የእለተ አርብ ጸሎት ለማድረስ አንዋር መስጊድ የከተመው ሕዝበ ሙስሊም እና የፌድራል ፖሊስ ግጭት መፍጠራቸው ተሰማ። ፖሊስ ትንኮሳ በመፍጠር በተለይ በኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት አካባቢ ሰላማዊውን ሕዝብ መደብደብና በፖሊስ መኪና መጫን ሲጀምር ሕዝቡ ቁጣውን በመግለጽ በፖሊስ ላይ ድንጋይ መወርወሩን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

የፌደራል ፖሊስ ለአርብ ጸሎት በመስጊድ የተገኘው ሕዝን በመክበብ ከመስጊድ እንዳይወጣ ለማገድ ሙከራ ሲያደርግ ነበር ያሉት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በራሱ የመንግስት ካድሬዎች አማካኝነት ብጥብጥ በማስነሳት ጉዳዩን ከሙስሊሞቹ ጋር ለማያያዝ ሙከራ ማድረጉን ጠቅሰዋል። በፖሊስ ላይ ድንጋይ መወረወር የጀመሩት መንግስት ያዘጋጃቸው ካድሬዎች ናቸው የሚሉት ዘጋቢዎቻችን ፖሊስ ይህን ተከትሎ በርካታ ሙስሊሞችን ማሰሩን እና አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

ፖሊስ በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ ድብደባ እየፈጸመ እንደሚገኝ የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አካባቢው በጥይት እሩምታ እየታመሰ እንደሚገኝና ውጥረቱም እንዳየለ አስታውቀዋል።

 



ፌደራል ፖሊስ ሕዝቡን ሲቀጠቅጥ፣ ሲያሸብር፣ አንዋር መስጊድን ሲከብና ሙስሊሙን ሲያስር የሚያሳዩ ፎቶዎች

$
0
0

ከድምጻችን ይሰማ

ሰላማዊው ሙስሊም እረፍት የነሳቸው የመንግስት ሃይሎች ዛሬም የጎዳና ላይ ነውጥ ፈጥረው እየደበደቡ እና ያለምንም ልዩነት መንገድ ላይ ያገኙትን ሁሉ እያሰሩ ነው፡፡ ፖሊሶች ከተክለሃይማኖት ጀምሮ አንዋር መስጂድ ድረስ መንገድ ዘግተው ቆይተዋል፡፡ አደባባይ ላይም ያገኙትን እያሰሩ ነው፡፡ አንድ ፖሊስ በተፈጠረው ግርግር በራሳቸው በፖሊስ መኪና ተገጭቶ ከፍተኛ አደጋ ደርሶበታል። መንግስታዊ ሽብር ዜጎች ሰላም እንዳይሆኑ የሚያደርግ ፀረ ህዝብ አቋም ነው! ህዝበ ሙስሊሙ ዛሬም በቀደሙት መንግስታት ይደርስበት እንደነበረው በእምነቱ እየተጨቆነ በአምልኮ ቤቱ እርምጃ እየተወሰደበት ነው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ዲኑን እስከዛሬ ያቆየው በመስዋእትነት ነው! ለዚህ ድንቅ ትውልድ ምስጋና ቢያንሰው እንጂ አይበዛበትም!

demtschin yesema 1

demtschin yesema 2

demtschin yesema 3

demtschin yesema 4

demtschin yesema 5

demtschin yesema 6

demtschin yesema 7

Health: ያልተመለሱ ወሲብ ነክ ጥያቄዎቻችሁ እና አዳዲስ የሕክምናው ሳይንስ ምላሾች

$
0
0


የ‹‹ጂስፖት›› አገር ከወዴት ነው?
ወሲብ በብርሃን ወይስ በጨለማ?

sex-good-for-healthበሴቶች በኩል የሚደፈር ርዕሰ ጉዳይ አይሁን እንጂ በርካታ ወንዶች በጋራ ሲሰበሰቡም ሆነ አንድ ለአንድ ሲያወሩ ወሲብ ነክ ጉዳዮችን አንዴ ወይም ሌላ ጊዜ ማንሳታቸው አይቀርም፡፡ በሴቶቹ ክብ ውስጥ ተገኝቼ ውይይታቸውን ባላዳምጥም እነርሱም ቢሆኑ ከጓደኞቻቸው ጋር ይህን ስሱ ርዕስ ሲያነሱና ሲጥሉ እንደሚቆዩ እገምታለሁ፡፡ በኛ አገር በወሲብ ነክ ጤና ጉዳዮች ላይ የህክምናው ሳይንስ ሰዎችም ይሁኑ ሚዲያው በግልፅ የመነጋገር እና ችግሮችን የማቅለል ልምዱ አነስተኛ በመሆኑ ወደ ጤና ተቋማት ለመሄድ እና የባለሞያን ሀሳብ ለማግኘት ተነሳሽነቱ ባይኖር ብዙ አይገርምም፡፡ ‹‹ቄሱም ዝም፣ መፅሐፉም ዝም›› በሆነበት የወሲብ ጤና ጉዳይ በውጪው ዓለም ለቁጥር የሚያታክቱ አማካሪ ባለሞያዎችና የፃፏቸው መፅሐፍት ለሰዎች የእለት ተዕለት ጭንቀቶች መፍትሄን ቢሰጡም እኛ አገር ገና ብዙ የሚቀረን እርምጃ አለ፡፡ ይህንን መነሻ አድርገን የተለያዩ ሴክስ ኤክስፐርቶች የፃፏቸውን መፅሐፍትና መጣጥፎች በማጣቀሻነት በመጠቀም በተለያየ ጊዜ የሚገጥመው ወሲብ ነክ ችግሮች እና ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በመመለስ ግንዛቤን የሚያሲዝ አጭር ምልከታ ልናደርግ ወደናል፡፡

ምን ያህል ወሲብ? በየስንት ጊዜው?
በዚህ ለኑሮ መሮጥ የሁሉም ሰው ዕለታዊ የቤት ስራ በሆነበት ጊዜ በፍቅርም ይሁን ትዳር ውስጥ ያሉ ጥንዶች እርስ በእርሳቸው ፍቅራቸውን ለመግለፅ እና ወሲብ ለመፈፀም በቂ ጊዜ ላያገኙ ይችላሉ፡፡ ወሲብ መፈፀም አካላዊ ግንኙነት ብቻ ባለመሆኑ ሁለቱም ተጣማጆች አእምሮአቸው አሪፍ እና ዘና ብሎ ቅርርቡንም ፈልጎ ወደ ወሲብ ሲያመራ በእርካታ የሚያጥለቀልቅ እና አዝናኝ ጥምረትን ይፈጥራሉ፡፡ አንዳንድ ጥንዶች ግንኙነት ከፈፀሙ ረጅም ጊዜ ሆኗቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ሌሎች ጥንዶች በሳምንት አሊያም በወር ምን ያህል ጊዜ ይሆን ወሲብ የሚፈፅሙት? ሲሉ በውስጣቸውም ይጠይቃሉ፡፡ በሳምንት፣ በወር ይህን ያህል ጊዜ ወሲብ ሊፈፅም ይገባል የሚል ምትሃታዊ ቁጥር የለም፡፡ የህክምና ሳይንስ ባለሞያዎችም ቁርጥ ያለ መልስ አይሰጡም፡፡ ‹‹ይህ በግንኙነቱ ጤናማነት ደረጃ እና በጥንዶች ቅርርቦሽ የሚወሰን ነው›› ባይ ናቸው፡፡
ሆኖም ግን ጤናማ ግንኙነት ውስጥ ያሉ ጥንዶች ወሳኝ ጉዳዮች መካከል ፍቅር መስራት ዋነኛው እንደመሆኑ በግንኙነት ቆይተው ለበርካታ ወራት ወሲብ ካልፈፀሙ ጥያቄ ማንሳቱ ጤናማ ነው፡፡ ለምን ያህል ድግግሞሽ እና መቼ የሚለውን ለማጥናት ሙከራ ያደረጉ ተመራማሪዎች ያሳተሙት ውጤት መነሻ ሀሳብን ሊሰጥ ይችላል፡፡ ዱሬክስ ኩባንያ 2006 ላይ ያወጣው ዓለም አቀፍ ሴክስ ሰርቬይ ላይ ዝቅተኛ ወሲብ ይፈፅማሉ የተባሉት የሲንጋፖር ሰዎች ሲሆኑ በወር 6 ጊዜ ነው ወሲብ የሚፈፅሙት፡፡ ባለሞያዎች በመጨረሻ የሚያጠቃልሉት ወሲብ የሚፈፀምበት ድግግሞሽ በሁለቱ ጥንዶች ስምምነት ያለው ከሆነ በፍቅር ግንኙነቱ አለዚያም ትዳሩ ላይ የሚፈጠር ችግር የለም፡፡ ይሁንና ከሁለቱ አንዱ ወሲብ እየፈለጉ ሌላኛው ወገን የሚያዘገየው ከሆነ በጉዳዩ ላይ በግልፅ ተወያይተው ሁለቱንም የሚያስማማ የጊዜ ርቀት እንዲያስቀምጡ እና ስሜታቸውን ተረድተው ቢዝናኑበት መልካም ነው ይላሉ፡፡

በወሲብ ስንት ደቂቃ ይቆያሉ? ቀድሞ የመጨረስ ጣጣ
በርካታ ወንዶች ወሲብ እየፈፀሙ በርካታ ደቂቃዎችን መቆየትን በፍቅር እና ትዳር አጋራቸው ዘንድ ነጥብ ያስቆጥርልናል ብለው ያስባሉ፡፡ አሳዛኙ ነገር ግን በዚህ መነሻነት በሚፈጠር መጨናነቅና የስነ ልቦና ውጥረት ገና እንደደረሱ ጨርሰው ለማቆም የሚገደዱት ናቸው የሚበረክቱት፡፡
በወሲብ የመቆየት ጊዜ ምን ያህል መሆን አለበት ለሚለው የተለያዩ የህክምና ሳይንቲስቶችና መፃህፍት የተለያዩ ምላሾችን ይሰጣሉ፡፡ በህክምናው ቋንቋ Intravaginal Ejaculatiry Latency Time (IELT) የሚባለው የቆይታ ጊዜ የሚቆጠረው ወንዱ በሴቷ ብልት ውስጥ ብልቱን ከከተተበት ደቂቃ ረጭቶ እስከሚወጣበት ድረስ ያለው ነው፡፡ ‹‹ይህ ጊዜ ልክ አንድ ደቂቃም ይሁን አንድ ሰዓት ወሳኝ ሊሆን የሚገባው በዚህ ጊዜ ሁለቱም ተጣማጆች እኩል እርካታን ከወሲብ ተጎናፅፈዋል ወይ የሚለው ነው›› ይላሉ ዶ/ር ሄለን ኦኮኔል የተባሉት የኒውሮሎጂ ባለሞያና የወሲብ ጉዳዮች አማካሪ፡፡ በደቂቃ ልኬን ማወቅ አለብኝ ለሚሉ ወንዶች መልስ ቢሆን ብለው በአማካይ አንድ ወንድ በወሲብ መቆየት ያለበትን የደቂቃ ርዝመት ያጠኑ ባለሞያዎች እ.ኤ.አ 2005 ላይ ጆርናል ኦፍ ሴክሹዋል ሜዲስን በተሰኘ የምርምር መፅሔት እንደፃፉት በአማካይ አንድ ወንድ ወሲብ እያደረገ ሊቆይ የሚችለው ለአምስት ደቂቃ ከ30 ሰከንድ ያህል ነው፡፡ ይህ ቆይታ ታዲያ ቅድመ ዝግጅቱን መተሻሸቱን እና መሳሳሙን አይጨምርም፡፡ ብልቱ ከሴቷ ብልት ገብቶ ስፐርሙን እስካፈሰሰበት ቅፅበት ያለውን ብቻ ይመለከታል፡፡ የጥናቱ አድራጊዎች ገና እንደገቡ የሚያፈሱ ሰዎችን አስመልክተው ሲፅፉ ‹‹ወሲብ መዝናኛ ነው፣ ዘና ብለው ከሴቷ ብልት መቆየታቸውን እንደ ደስታ እያሰቡ ሳይጣደፉ የሴቷ ደግሞ ስሜት እያደመጣ ወሲብ ማድረግን ይልመዱ›› ሲሉ መክረዋል፡፡ ከፍርሃት፣ ከጭንቀት እና መጠራጠር የፀዳ ንፁህ ግንኙነት ውስጥ ያሉ ጥንዶች የሚቆዩበትን ጊዜ እንዳሻቸው ሊለጥጡት ይችላሉ፡፡ ‹‹ወሳኙ የስነ ልቦናዊ ጥምረታቸው ልክ ነው›› ይላሉ የጥናቱ መሪ አያን ኬርነር፡፡ አካላዊ እና ከብልት ጡንቻዎች ጋር የተያያዘ ችግር ካለ ይህን በህክምና ማስታገስ እንደሚቻልም ያክላሉ፡፡

በወር አበባ ጊዜ ሴክስ ይፈቀዳል?
ሴቶች የወር አበባ ላይ በሚሆኑበት ወቅት አንዳንድ ጊዜ ተጣማጆቻቸውን ሴክስ ይከለክላሉ፡፡ ‹‹አሞኛል›› ይላሉ፡፡ እውን በወር አበባ ጊዜ ወሲብ መፈፀም ህመም ይሆናል? የጎንዮሽ ጉዳትስ ይኖረው ይሆን? የሚል ጥያቄ የሚያነሱ ወንዶችም ሴቶችም መልስ እንዲሆን ታዋቂዋ የሴክስ ኤክስፐርት እና የጉድቫይብስ መፅሔት ፀሐፊ ካሎል ኩዊን ያቀረቡት ፅሑፍ የሚለውን እንመልከት፡፡ ኤክስፐርቷ እንደሚሉት በወር አበባ ጊዜ ወሲብ መፈፀም ችግር የለውም፡፡ ይሁንና በአንዳንድ ሀይማኖታዊ ምክንያቶች የተነሳ ብዙ ሴቶች ከወሲብ ሲታቀቡ እንዳስተዋሉ ተናግረዋል፡፡ በሳይንሱ ግን አይከለከልም፡፡ እንዲያውም በወር አበባ ወቅት ከሚከሰተው ህመም የሚገላግልና የመዝናናት ስሜትን የሚፈጥሩት ኢንደርፊን የተባሉት ሆርሞኖች ሴክስ በሚፈፅሙ ወቅት በሰውነታቸው ስለሚለቀቅ ራስ ምታት፣ ድብርት እና ቀርጠት የመሳሰሉት የወር አበባ ህመሞችን ማስታገስ እንደሚችሉ ባለሞያዋ ያብራራሉ፡፡ ይሁንና የወር አበባ ወቅት የማህፀን ጫፍ ደሙን ለማስወጣት ከፈት የሚልበት በመሆኑ እንዲሁም የብልታቸው አካባቢ ከወትሮው በተለየ አሲዳማነቱ የሚቀንስ በመሆኑ ለተለያዩ ኢንፌክሽኖች እና አባላዘር በሽታዎች የሚጋለጡበትም ወቅት ስለሚሆን ሁልጊዜም ኮንዶም መጠቀምን አይርሱ ሲሉ ሀሳባቸውን ያጠቃልላሉ፡፡

ወሲብ በጠዋት የጤና ነው?
የባለቤቷ የወሲብ ፍላጎት ጉዳይ ያሳሰባት ሴት ባቀረበችው ጥያቄ እርሱ ወደ ቤት ማታ ሲመጣ ደካክሞ ይመጣና ይተኛል፡፡ ጠዋት ላይ ግን አፈፍ ያደርገኝና ወሲብ መፈፀም እንጀምራለን፡፡ ይሄ የሌሎች ወንዶች ተፈጥሮ ይሆን ወይ? የጤናስ ነው? ስትል ትጠይቃለች፡፡ ለእርሷና ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄ ለሚኖራቸው ሰዎች ኤክስፐርቶቹ የሚሉት አላቸው፡፡ በእርግጥም የወንዶች ተፈጥሯዊ የሆርሞን ስርዓት የሚፈጥረው ፍላጎት አለ፡፡ የወንዶች የወንዴ ሆርሞን ቴስቴስትሮን መጠን በቀን ውስጥ ከፍ እና ዝቅታ ይገጥመዋል፡፡ በተለይ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት መጠኑ ከፍ ብሎ የሚገኝበት በመሆኑ ወሲብ ቢጠይቅ አትፍረጂበት ይላሉ ዩሮሎጂስት ሐኪሟ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ያደረ ሽንት በሽንት ከረጢት ስለሚጠራቀም ግፊቱ ደም ወደ ብልቱ በብዛት እንዲደርስና ብልቱ እንዲወጠር ያደርጋል፡፡ እነዚህ የሆርሞኖችና በደም ፍሰቱ የብልት መወጠር ምክንያቶች በጠዋት ለወሲብ መነቃቃቱ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ የጠዋት ጉልበትና ብርታቱም ሳይነዘጋ፡፡

የ‹‹ጂስፖት›› አገር ከወዴት ነው?
ሴቶችን የማርካት ፈተና
ሴቶች በወሲብ መርካታቸው ጉዳይ እንደ ሁለተኛ ነገር ሲወሰድ የነበረበት ዘመን አብቅቶ ዛሬ ዛሬ አብዛኛዋ ሴት ከፍቅር እና ትዳር ግንኙነቷ ከወንድ እኩል የወሲብ እርካታን ትፈልጋለች፡፡ የሴክስ ኤክስፐርቶች ይህን የእርሷን እርካታ ለማረጋገጥ የሚሻ ወንድ ሰውነቷን፣ ስሜቷ የሚቀሰቀስበትና ከእርካታም የሚያደርሷትን ቦታዎች ልቅም አድርጎ ማወቅ ይገባዋል ይላሉ፡፡ ሴቷን ብልት ቁልፍ የእርካታ ስፍራ ‹‹ጂስፖት› ማወቅ የሁሉም ወንድ የቤት ስራ መሆን አለበትም ይላሉ፡፡ ትክክለኛ ቦታውን በመጠቆም በኩል እንዲሁም ከነጭራሹ ስለመኖሩ የሚጠራጠሩ ባለሞያዎች ቢኖሩም በአመዛኙ ግን ጂ ስፖት ቁልፍ የሴቷ የእርካታ ማዕከል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ይህ ስፍራ ጥንት በህንድና ቻይና ፅሑፎች በግምት ሲገለፅ የኖረ ቢሆንም በዘመናዊ የህክምና ሳይንስ የታወቀው በጀርመናዊው የማህፀን ስፔሻሊስት ዶ/ር ኸርነስት ግራፊንበርግ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በእርሱ በመታወቁም ይህ የሴቶች የእርካታ ማዕከል በአባቱ ስም የእንግሊዝኛ ፊደል ‹ጂ› በመውሰድ ‹ጂ ስፖት› ተባለ፡፡ እርሱ እንደሚገልፀው ጂስፖት የሚገኘው በሴት ብልት ፊት ግድግዳ በብልቷ የላይኛው ጫፍ እና በብልቷ ስንጥቅ መካከል ነው፡፡ ይህ ስፍራ በጣትም ሆነ በወንድ ብልት በሚነካካበት ወቅት በሚፈጠር የነርቮች መነቃቃት ወደ እርካታ ጫፍ ትስፈነጠራለች፡፡ የወንዱ ብልት ሲገባና ሲወጣም ይህን ስፍራ እንዲነካካ ካልሆነለትም በጣቱ ጭምር እንዲያነቃቃው የሴክስ ኤክስፐርቶቹ ይመክራሉ፡፡

ወሲብ በብርሃን ወይስ በጨለማ?
በርካቶች ወሲብ ሲፈፅሙ መብራት ያጠፋሉ፡፡ ከፊሎች ደግሞ መብራት በርቶ እርስ በእርስ እየተያዩ ሁለ ነገራቸውን እያደነቁ መፈፀሙ የተሻለ እርካታ ይሰጣቸዋል፡፡ በወሲብ ጉዳዮች የሜንስ ሄልዝ መፅሔትን የሚያማክሩት ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት እንደሚሉት በብርሃን ወይም በመብራት ወሲብ መፈፀም ዝግጁ የሆኑ ጥንዶች በግንኙነታቸው ጥልቀትና ግልፅነት የሚተማመኑ፣ ተጣማጃቸውን የሚያፈቅሩ፣ የወሲብ አካላቶቻቸውን ብቻ ሳይሆን መላ አካላትና መንፈሳቸውም ጥምረት እንዲፈጠር የሚፈልጉና የሚፈቅዱ በመሆናቸው ሊደሰቱ ይገባል፡፡ ግን ደግሞ ጭለማው እና መብራቱ መጥፋቱም በመጥፎ ምልክትነት ሊወሰድ አይገባም፡፡ አንዳንድ ተፈጥሮ ይህን አይፈቅድም፡፡ ሁለታችሁ ብቻ ባላችሁበት ክፍል ሁልጊዜ መብራት እንዲጠፋ የምትፈልጉ ከሆነ ግን እስቲ አብርታችሁ ሞክሩት፡፡ ስለግንኙነታችሁ አንዳንድ ነገር ሊገልጥላችሁ ይችላል፤ ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን ከወሲብ ህይወት ጋር ተያይዘው ሊነሱ እንደሚገባቸውና ምላሽ እንደሚፈልጉ እንረዳለን፡፡ በሌላ ጊዜ ርዕሰ ጉዳዩን ልናነሳው ቀጠሮ ይዘን የዛሬን እናብቃ፣ ሰላም!

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live