Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ውጥረት በአንዋር መስጅድ –ቢቢኤን በሰበር ዜናው ዘገባ ሊንኩን ዳውንሎድ በማድረግ ያድምጡ

$
0
0

ውጥረት በአንዋር መስጅድ

እዚህ ይጫኑ ለማዳመጥ

 

 

በአንዋር መስጊድ ሰጋጆች ላይ ፖሊስ የማሽበር ተግባር እየፈጸመ ነዉ ሲሉ ምእምናንን ገለጹ ድምጻችን የሰማ ያወጣዉን ሰላማዊ የተቃዉሞ መርሃ ግብር ተከትሎ ዛሬ ጁመዓ ለመስገድ ወደ መስጊድ በሚያመሩ ሰጋጆች ላይ ፖሊስና ደህንነቶች በመቀናጀት ጸብ አጫሪ ተግባራትን መፈጽማቸዉን እማኞች ያስረዳሉ። በሴቶች በኩል ባደረጉትም መተናኮስ ግጭት አስነስተዉ በሴት ምእምናን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ መፈጸማቸዉን የጥቃቱ ሰላባ የሆኑ ወገኖች ገልጸዉልናል። ባሁን ሰዓት ፖሊሶች የ አንዋር መስጊድን በሮች በመዝጋት ምእምናንን ያገቱ ሲሆን በመስጊዱም ዙሪያ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች እየተርመሰመሱ መሆኑ ታዉቋል።

 

በመስጊዱ ዙሪያ የጭነት መኪናዎች የተደረደሩ ሲሆን፤ አፈሳ ለማድረግ አስበዉ ነዉ የሚል ግምት አለ። በመስጊዱ ቅጥር ግቢ የድምጽ ተቃዉሞ መደረጉን የገለጹልን ተሳታፊዎች ከመስጊዱ ዉጪ ስላለዉ እንቅስቃሴ እንደማያዉቁም ገልጸዉልናል። አንዋር ዉስጥ ያለዉ ምእምንም ተረጋግቶ ዱዓ (ጸሎት) እያደረገ መሆኑን ለማወቅ የቻልን ሲሆን ቀጣዩ የፖሊስ እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም። እኛ በ አካል ተገኝተን በደልና ጭቆናን ለመጋፈጥ ባድረግነዉ ጥረት እየተደበደብን እየታሰርን ነዉ፤ ብዚህ በተቀደሰዉ የረመዳን ወር በመላዉ አለም ያለዉ ወገናችን በዱዓ ይተባበረን ሲሉ በአንዋር መስጊድ በፖሊስ የታገቱት ምእምናን መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል።

http://goo.gl/PVz4wa

http://goo.gl/PVz4wa

 

i2 i4 i3 demtschin yesema 3 demtschin yesema 3

↧

↧

የፕሬስ አፈናው በ”ሎሚ” መጽሔት ተጀመረ

$
0
0

ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም ከመንግስት በተላኩ ኃይሎች የ‹‹ሎሚ›› መጽሔት ቢሮ ‹‹ያለ ንግድ ፍቃድ›› በሚል ሠበብ ታሸገ፡፡ እነዚህ ከየትኛው ወገን እንደተላኩ ያልታወቁት ኃይሎች በቢሮ ውስጥ የነበሩትን የሂሳብ ሠነዶች ‹‹ይዘን እንሄዳለን፣ አትሄዱም›› በሚል በተፈጠረው እሰጥ አገባ ምክንያት ስልክ ደውለው ቁጥራቸው ከ20 ያላነሱ የታጠቁ የፌደራል ኃይሎችን በመጥራት እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙትን ንብረቶችና ወረቀቶችን ጨምሮ እንዳናወጣ በመከልከልና በማስፈራራት አስቀድመው ታዘው ይዘውት የመጡት ወረቀት “ያልታሰደ ንግድ ፍቃድ” የሚል ቢሆንም፣ ንግድ ፍቃዱ የታደሰበትን ማጋገጫ ሲመለከቱ ደግሞ ፊት ለፊታችን ወረቀቱን በመሠረዝ “ያለ ንግድ ፍቃድ” በሚል ጽፈው አሽገውታል፡፡ በወቅቱ ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም ለንባብ የምትበቃው ‹‹ሎሚ›› መጽሔት ወደ ማተሚያ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳለች ይህ ችግር መፈጠሩ በሎሚ አባላቶች ላይ ግሬታን ቢፈጥርም፣ በተወሰደው ሕገ-ወጥ እርምጃ ሳንደናገጥ ከምንገባበት አንድ ቀን ዘግይተንም ቢሆን በተከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ማተሚያ ቤት ልናስገባ ችለናል፡፡ በወቅቱም ቢሮአችን እንደሚታሸግ ለምን አስቀድማችሁ በደብዳቤም ሆነ በስልክ አላሳወቃችሁንም ቢባሉም ‹‹የእናንተ ስፔሻል ኬዝ ነው፤ እኛ ከላይ ታዘን ነው›› የሚል ምላሽ ሠጥተዋል፡፡
lomi megazine
ከዚህም በተጨማሪ የሎሚ መጽሔት አጋር ሆና በሣምንት ሁለቴ ለንባብ የምትበቃው ‹‹አፍሮ ታይምስ›› ጋዜጣም ከወዲሁ ልትዘጋ እንደምትችል አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የዞን 9 አባሎች ያውቁ እንደነበር መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛሉ፡፡ ይኸውም እነዚሁ ኃይሎች ከመጀመሪያው ቀን በተለየ ሁኔታ በበነጋታው ተደራጅተው በመምጣት “ሠነዶችን እንፈልጋለን” በሚል ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፌደራል ኃይሎች የታገዘ የ5 ሠዓታት ፍተሻ (ከብርበራ አይተናነስም) ከአካሄዱ በኋላ በቢሮ ውስጥ የሚገኙትን የሂሳብ ሠነዶች በሙሉ ሰብስበው ወስደዋል፡፡ ሆኖም ግን የምንፈልገው የሂሳብ ሠነዶችን ይበሉ እንጂ፣ በቢሮው ውስጥ የሚገኙትን በተለያዩ ጊዜ የታተሙ የሎሚ መጽሔቶች፣ የአፍሮ ታይምስ ጋዜጦችና በእጅ ጽሁፍ የተተየቡ ወረቀቶችን አንድ በአንድ ሲፈትሹ ተስተውሏል፡፡ ይሄ ሕገ-ወጥ እርምጃ የእኛ የፕሬስ ውጤቶች በሆኑት ሎሚ መጽሔትና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ሆነ ተብሎ ለማጥቃት የታለመ መሆኑን የሚያመለክተው እነዚሁ ያልታወቁት ኃይሎች አስቀድመው ከመምጣታቸው በፊት ‹‹የአፍሮ ታይምስ ቢሮን ለማሸግ እየመጣን ነው›› በማለት የደወሉ ቢሆንም፣ ቢሮ ድረስ መጥተው የነበሩትን ሠነዶች ከወሰዱ በኋላም ከአለቆቻቸው ጋር በስልክ በመነጋገር ሊያሽጉበት ይዘውት መጥተው የነበረውን የማሸጊያ ወረቀት ሳያሽጉበት ተመልሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአንድ ወር በፊት ገዢው መንግስት ነፃውን ፕሬስ ጥላሸት በመቀባትና እርምጃ እንደሚወስድ (ሎሚ መጽሔትን ጨምሮ) በፈበረካቸው የተለያዩ ዶክመንተሪዎቹ ሲዝት የቆየ ሲሆን፣ አሁን አፈናውን በሎሚ መጽሔት ‹‹አሃዱ›› ብሎ ጀምሯል፡፡ ሎሚ መጽሔትም ሆነ አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ እራሱ ገዢው መንግስት ባወጣው የፕሬስ አዋጅ መሠረት ሕግና ደንቡን ተከትለን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ድምጽ በመሆን ተገቢውን መረጃ በወቅቱ እያደረስን ቢሆንም፣ ይህንን ያልወደደው ገዢው መንግስት ነፃ ፕሬሱን ከነአካቴው ለማጥፋት የተለያዩ ወጥመዶችን እያዘጋጀ መሆኑን አንባቢያን እንድታውቁልን እንፈልጋለን፡፡ ውድ አንባቢዎቻችንም ይሄንን ተገንዝባችሁ እስከመጨረሻው ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመቀበል ከጎናችን እንድትቆሙ እናሳስባለን፡፡

↧

በብጥብጥ የተቋጨው የጁምዓ ስግደት በአንዋር መስጊድ

$
0
0

ከኤልያስ ገብሩ (አዲስ አበባ)

መጽሐፍ ሳነብ ስለነበር በጣም አምሽቼ የተኛሁት፡፡ ጠዋት አረፍጄ ተነሳሁ፡፡ ቁርሴንም ሳልበላ ወደ አንዋር መስኪድ አመራሁ፡፡ ከፒያሣ ጀምሮ መንገድ የተዘጋጋ ስለነበረ፤ ከሦስት ሙስሊም ወንድሞቼ ጋር አንድ ላዳ ታክሲ ኮንትራት ይዘን አቆራረጥን ታላቁ አንዋር መስኪድ ደረስን፡፡ አካባቢው በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተሞልቷል፡፡ አብዛኛው ምንጣፍ እና ካኪ ወረቀት አንጥፈው ለጁምዓ ጸሎት እና ለስግደት ተቀምጠዋል – አስፋልቱን ጭምር ተጠቅመውበታል፡፡ ለመቀመጫ ቦታ ያላገኙት ቆመው ከመስኪዱ በአረብኛ ቋንቋ የሚነገረውን ምስጋና (ትምህርት) በጥሞና እየተለታተሉ ነው፡፡
በርከት ያሉ ፖሊሶች በመስኪዱ አቅርቢያ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ቆመዋል – ረዥም ሽመል ይዘዋል! እኔም እንደ ጋዜጠኛ የሙስሊሞቹን ሰላማዊ ተቃውሞ ለመከታታል በማሰብ ነው አንዋር መስኪድ የተገኘሁት፡፡ ከመስኪዱ ራቅ ብዬ በመቆም ሁኔታውን መከታተል ጀመርኩ፡፡ ነገሮች ሰላማዊ ነበሩ፡፡ ከሥፍራው ከተገኘሁ ከአሥራ አምስት ደቂቃ በኋላ በመስኪዱ ዋና በር አካባቢ ወረቀቶች ወደ ላይ ይበተኑ ጀመር፡፡ ሦስት፣ አራት ቦታም ተመሳሳይ ወረቆች መበተናቸውን ቀጠሉ፡፡
demtschin yesema 2
ወዲያው፣ ከርቀት ከመስኪዱ በስተቀኝ በኩል ረብሻ ነገር ተመለከትኩ፡፡ ድንጋይ ሲወረውር እና ፖሊሶች ዱላ እንደያዙ ሲሯራጡም ማየት ችያለሁ፡፡

አፍታም ሳይቆይ አካባቢው በሰዎች ሩጫ፣ በረብሻና በፖሊሶች ማሳደድ ትርምስምሱ ወጣ፡፡ ብዙ ሰው በአካባቢው ወደሚገኙ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች እየዘለለ መግባት ጀመረ፡፡ ነገሮች ለአፍታ ጋብ ያሉ ቢመስሉም ሁኔታው በድጋሚ ተቀሰቀሰ፡፡ በርካታ ፖሊሶች ወደ መኖሪያ ሰፈሮች እና ግቢዎች ውስጥ ዱላቸውን ይዘው በመግባት ሰዎች ማባረር፣ ማሳደድና በዱላ መማታት ጀመሩ፡፡

እኔም ከሦስት ፖሊሶች ጋር ከአንድ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ተፋጥቼ ነበር፡፡ አንድ ዱላ ሲሰነዘርብኝ በእጄ ተንቀሳቃሽ ኮምፕዩተር (ላፕቶፕ) ይዤ ስለነበረ እሱ ከፍ በማድረግ ዱላው የላፕቶፕ ቦርሳዬ ላይ አረፈ፡፡ የቀኝ እጄ ጠቋሚ ጣት ግን ከበትሩ ማምለጥ ሳይቻለው ቀረ፡፡
… ከበሩ ፊት ለፊት የነበሩት ፖሊሶች ጥለውን ሄዱ፡፡ ወደ አሜሪካን ግቢ በጉራንጉር ውስጥ አልፌ ብሄድም ድብደባው እና ወከባው በዚህ አለ፡፡ ብዙ ወጣቶች ተደብድበው፣ ጭንቅላታቸው ተበረቃቅሶ ደም በደም ሆነው ተመልክቻለሁ፡፡
በዛሬው ዕለት ምስቅልቅሏ የወጣውን መርካቶ በቻልኩት አቅም ለማየት ችያለሁ፡፡ ሱቆች ተዘጋግተዋል፡፡ አንዋር መስኪድ በፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦች እና መኪኖች ተከብቦ ነበር፡፡ አድማ በታኝ ፖሊሶችም በምዕራብ ሆቴል ቁልቁል በሰልፍ ሲያዘግሙ እና ሰፊዋ መርካቶ በፌዴራል ፖሊሶች ተወርራ ነበር፡፡
በጥቅሉ በዛሬው የአንዋር መስኪድ የጁምዓን ጸሎት ተከትሎ የተፈጠረው ሁኔታ አሳዛኝ እና ዘግናኝ ሆኖብኛል፡፡

↧

ሽንፍላ –ተንሳፎ የሚፈላ! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ –  ሲዊዘርላንድ ዙሪክ

2

እያዘንኩ ብዕሬን አነሳሁ። የእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን በፆማቸው እንኳን እንዲህ ሰላም ማጣታቸው የኢትዮጵያን መከራ ሃሞት ያደርገዋል። ፆም ላይ አኮ ምዕመኑ ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙበት የአደብ፤ የተደሞ፤ የጭምትነት ጊዜያቸው ነበር። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያን አጋድሞ እያረዳት ያለው ወያኔ ሽንፍላ በመሆኑ አቅል አልፈጠረለትም። ኑሮትም አያውቅም። ወያኔ በሁሉም መሰፈርት ከላይ ተነሳፎ የሚፈላ ሽንፍላ ነው። እርምጃው ሸውሻዋ፤ ትንፋሹ ከልካላ። አቅሙ ጭድ – ራዕዩ ንፋስ – አካሉ ብክነት – ህሊናው አሲድ ነው። ከንቱ!

የወገኖቻችን ዬአካሎቻችን ናፍቀውና ጓጉተው በምልዕት በሚታደሙት ፆመ – ሮመዳን የዛሬ ዓመት አሳርን አብዝተው የተቀበሉበት ወቅት ነበር። ዓውዳመታቸውም በደም ነበር የተወራረደው። በዐለም ላይ ያሉ ህዝበ እስልምና እምነት ተከታይ ሁሉ በሰላም ፍስካቸውን ሲከውኑ፤ ደስ ብሏቸው የተሰጣቸውን ጸጋ ለነድያን ሲራሩ፤ ኢትዮጵያ ላይ ግን በአደባባይ ዬዕምነቱ አዛውንታት የተደበደቡበት፤ ህፃናት ሳይቀሩ የተገደሉበት የመከራ ድቅድቅ የጨለማ ቀን ነበር።  ቀንበር! የኢትዮጵያ እስልማ እምነት ተከታዮች ከሌሎች ሀገር ሙስሊሞች በፍጹም ሁኔታ የተለዬ ሥነ ምግባርና ጨዋነት ያላቸው ሲሆኑ፤ በፋሽስቱ ወያኔ ግን በጠላትነት ተፈርጀው፤ መተንፈሻ ቧንቧቸውን ዘግቶና አስሮ አሳራቸውን – ፍዳቸውን እንሆ ቀን እዬቆጠረ ያበላቸዋል። ዬኢትዮጵያ የእስልማ ዕምነት ተከታዮች ሀገራችን ኢትዮጵያ በጠራቻቸው ማናቸውም ጊዜያት ሁሉ በግንባር ቀደምትነት እናታቸው ከእነሱ የምትጠብቀውን ግዴታ ሲወጡ ኖረዋል። ታሪካችን- ነፃነታችን፣ የጥቁር ገድላችን ሁሉ በዚህ ቅመም የተቀመመ ነው። በጠቀራው በወያኔ ዘመን ደግሞ የኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መብታቸው እንዲህ ተረገጦ፤ እንዲህ ተቀጥቅጦ በሰላምና በሥርዓት ሊፈታ የሚገባው ጥያቄዎቻቸው እንዲህ ባላፈለጉትና ባላሰቡት መልክ አቅጣጫውን እንዲቀይር ረብሻ የፈጠረው ፋሽስቱ ወያኔ እንጂ እነሱ በፍጹም ሊሆኑ አይችሉም። ይህ የፋሽስቱ ባህሬ መገለጫ በመሆኑ ደም መዲናዋ ላይ ስለጠማው ለዚሁ አቅዶ የተነሳበት እንጂ እነሱ ለምዕተ ዓመቱ የሰላማዊ ትግል ሐዋርያ ናቸው። ሰላማዊ ትግል ስልቱና አፈጻጸሙ፤ የሰላማዊ ትግል መሪና ተመሪ፤ የሰላማዊ ትግል ትሩፋትና ፋይዳ በስክነት አምሮበት የተከወነው ታሪክ አንድ የገደል መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን ተቋምም ነው። መጸሐፍ ተጽፎበት በት/ቤት ደረጃ ተማሪዎች ሊማሩት የሚገባ። ዜግነትንት አከበረ – ኢትዮጵያዊነትን ከበከበ – አብሮነት በተግባር ኳለ። አዎን! የፋሽስቱ ወያኔ መሰረታዊ የግለት መንገዱ  እንዲህ እሰኪ ላብራራው። ምሳሌ። ሀ/// ለ//// ሐ/// መ//// ሠ/// ቢኖሩ። የመጀመሪያ የጥቃቱ ሰለባ ሀ/// ከሆነ ወያኔ ለ – ለ/// ለ –  ሐ///  ለ – መ//// ለ – ሠ/// የተለዬ እንክብካቤና ግልብ ፍቅር ይለግሳል። ለ/// ሐ/// መ/// ሠ/// እውነት ይመስላቸውና በሀ/// ላይ ክንዳቸውን – ኃይላቸውን  - አቅማቸውን ከወያኔ ጋር አዳምረው ሀን//// ይከተክታሉ። ጦሩ ወደ እነሱ መዝመቱን ነገን ፈጽሞ አያቅዱትም። የወያኔ ዘመን ጠገብ እኩይ ረቂቅ መሰሪ ተግባሩ አንዱን ለማጥቃት ሌለውን በማስተባበር በሚያጠቃው ላይ ማናቸውንም ዬግለት ዘመቻ በመፈጸም ነው። ሽፍታው ወያኔ – ሀ/// ጥሩ ሁኖ መድቀቁን – ዳግም አገግሞ ሊነሳ አለመቻሉን ስያረጋግጥ ቀጣዩን  ዒላማ ለስለስ ብሎ እዬሰረሰረ ይጀምራል። በፋረሰው ሀ ላይ ሌላ ሸንኮፍ ሀን ይለብጣን ተለጣፊ ይፈጥራል። ይህም ቢሆን እዬተመነጠረ የሚወገድበት ቀን የሚጠብቅ የደለበ ሰንጋ ነው። የሆነ ሆኖ መተንፈሻ ቧንቧውን ከፍት አድርጎ እንዲያንቧርቅ ይፈቅድለታል – ለተለጣፊው። ከዚህ በኋላ ደግሞ ወደ ሌላው ጉልበታም የማንነት ተቋም ከዘራውን ይዞ ይዘምታል – አረሙ ወያኔ። ወደ ለ//// ይሄዳል። መጀመሪያ ለን/// ተርተር እያረገ አቅሙን ይሸረሽራል፤ እንደ ሥጋ ቀረምት በተመቸው መልክ ትናንሽ መደብ – ይሠራል። መደቡ በአፈር ሆነ በአሸዋ ይሆናል።። ከዛ በኋላ የለ/// አቅም መከፋፈሉን ሲያረጋግጥ ተለጣፊውን ሀን///  ከነተፈጥሯቸው ያሉትን  ሐ//// መ//// ሠ/// ያሰልፍና በእውነተኛው  ለ ላይ ጦር ያውጃል። ሐ// መ/// ሠ/// ወደ እንሱ የሚመጣ ስለማይመስላቸው ጋሻ ጀግሬ ሆነው ጎሽ በርታ! እያሉ ሽፍታውን ይከብክቡና ዕውነተኛውን ለን//// በጠላትነት ፈርጀው አብረው ከጠላታቸው ጋር ይከተክቱታል። ለ/// የሚባል ነገር ድብዛው መጥፋቱን ሲያረጋግጥ ወያኔ ሌላ ተለጣፊ ለን/// ሞሽሮ የክህደት ካባ አለብሶ፤ ትንሽ እንደ ከብት አሞሌ መላሾ ሰጥቶ፤ ቀባብቶ ይጠፈጥፍና ያስጨፍረዋል። ለተወሰነች ጊዜ ያስዳንሰዋል። እሱ እራሱ ወያኔ እኮ  ቀፎውን አራት ኪሎ ልቡን ታላቋ ትግራይ ዶክተሪን ላይ አስቀምጦ በጅል አጃቢዎቹ ሸምቆ በቆረቆንዳ ተከታዮቹ ከትክት ብሎ ይስቃል። በዚህ መልክ አቅም ያለው ማናቸውም የማንነት ማማሳከሪያ ሰነድ ሆነ ውስጠት ሁሉ በዬተራ ደመራ የዶግ አመድ ይሆናል። ቲያትሩ ይህ ነው። ወያኔ አንድም የሚምረው ኢትዮጵያዊ ዘለላ አይኖርም ቁርጣችሁን እወቁ። የሚቀር የለም። ሆድ አደሩም ነገ ስሎ ወይንም ሰልቶ ወይንም ተስሎ በቀል ይጠብቀዋል። ልብሰህን እያወለቀ እርቃንህን ሲዘለዝልህ እያንዳንድህ ነገ ታገኘዋለህ። ብጣቂ ብናኝ እፍረት – ይሉኝታ ያልሰራለት የዘመኑ የአራዊት ተሰምሳሌት ቢኖር ወያኔ ብቻ ነው። የወያኔ ልብ በድንጋይ የተሰራ የበቀል ማሰሮ ነው። በዬትኛውም ዘመንን ትውልድ፤ በዬትኛውም ሁኔታ በህልም እንኳን የማይታሰብ ረግረግ ገደል ጉድጓድ ነው ወያኔ ማለት። የሚያረቃቸው አናቂ እሾኃማ ህግጋቶቹ የሚሞሽሩት ቋሳን ብቻ ነው። ነገር ግን በዚህ የቋሳ – ዝልል ጠማቂውም ጠጩም የነገ ተረኛ ተጠቂ መሆኑ ነው ሊመረምር የሚገባው ቁም ነገር። ሊፈተሽ የሚገባው እውነት። ሊታሰብበት የሚገባው አምክንዮ። ግን ህሊና ልብ ተግባራቸውን እንዲከውኑ ስንፈቅድ ብቻ። እማዝነው ለአፋሽ አጎንባሾች አሁንም ለወያኔ አንጣፊዎች ሆድ አደሮች ነው። ጅብ ዘመድ የለውም። እያንዳንዱ የወያኔ አባል ለህልውናው ተግቶ በተከታታይነት ይሠራል። በትጋት ሰይፉን በማናቸውም የወያኔ መንፈስን በሚጻረሩ ኃይሎች ላይ ይሰነዝራል። ትንሿን ነገር አይንቁም። የተሰባሰበ ፍላጎት ነው ያላቸው። ለማፍረስ ተልዕኮቻው ቃል ጠባቂዊች ናቸው። አጃቢው ደግሞ በማለቅለቅ ሸር ጉድ ይላል። ይህ ነው መፈታት ያለበት እንቆቅልሽ። የሰው ልጅ የቆመበትን መሬት ከመራመዱ በፊት አስተውሎ ሊያው ይገባል። መሬቱ ገደል ወይንስ ለጥ ያለ ሜዳ ስለመሆኑ? የወያኔ ማናቸውም እርምጃ በድልድይ ላይ ሳይሆን በገደል ላይ ነው። ድልድይ የሆኑት ደግሞ ከሌላ ብሄረሰብ የተወለዱ የባንዳ አበልጆች ናቸው። አሁን ደመ ነፍሱ  ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደስ አለኝ አንዱ አሻንጉሊት ናቸው። ቀን ወያኔ የሚጠብቅላቸው። ነገ ወያኔ ያሾልካቸዋል። አዋርዶና ጎራርዶ። አሁንም የተሰበረ ቅል ታውቃላችሁን ወገኖቼ? አዎን ለወያኔ ሃርነት ትግራይ አቶ ሃይለማርያም ማለት የተሰበረ ቅል ማለት ናቸው። ነገ ከጉብራቸው ላይ ሆኖ ወያኔ ያስተንፍሳቸዋል። ደመንፈስነታቸውን በሚገባ የተገነዘበው ወያኔ ዕቃ – ዕቃ እዬተጫወተባቸው ነው። ዝልብ! በተከበሩ የጀግና ጽላት አቶ አንዳርጋቸው እስር ላይ አቶ ሃይለማርያም እኮ ድርጊቱን ወያኔ ከፈጸመው በኋላ እኛ እንደሰማነው ነው የሚሰሙት። አሁንም ያሉበትን አያውቁም። የአቶ አንዳርጋቸውን ማናቸውንም የተከደኑ የበቀል እርምጃዎች ሲፈጸሙ ከጠባቂዎቻቸው ጀምሮ ከትግራይ ልጅ ውጪ ፈጽሞ ሊሆን እንዳማይችል በጣም በእርግጠኝነት መናገር እችላላሁ። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የታማኝነት መለኪያው ዘር ነው። ትግራዊነት። ከዚህ ያመለጡት እንደ ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ያሉት ደግሞ በእጥፍ የወያኔ ጭካኔ የሚጨቀጭቃቸው ለወያኔ የበቀሉ ቁርሾ ተጠቂዎች ናቸው። ስለምን? የወያኔን የናዚ መንገድ የተጸዬፉ ጀግኖቻችን ለእኛ  ስለሆኑ። በዚህ የባንዳ ዘመን የአሉላ ማሾ ስለሆኑ! ከመከራችን – ከችግሮቻችን – ከእንባችን ጋር ቤተኛ ስለሆኑ። የበቀልን የደም ጽዋ በአረመኔነት የሚያስፈጽሙ ባላሟሎች የፊት ለፊት ረድፈኞች የወያኔ ሃርነት አባላት ጭምር ናቸው። ነገም ለእያንዳንዱ የሚደርሰው የፈተና ጅረት ከዚህ አንጻር መፈተሽ አለበት።  ይህንን ያመረቀዘ – እጅግ የረቀቀ  - እጅግም በበቀል የበሰለ፤ እጅግም በበቀለ የተጠና፤ እጅግም በሳጥናኤላዊነት ግብር የተበከለ፤ የመርዝ ዘመን ከልብ ሆኖ መርምሮ፤ ቢያንስ አሁን ከ40 ዓመት ጥቃት በኋላ የጠላትን ጉርቦ አንቆ ደም ለማስተፋት መቁረጥ ያስፈልጋል። ቢያንስ ሥር ሰደዱ በቀል መነሻውና መድረሻውን በማስተዋል ማገናዘብ ያስፈልጋል። ንክኪ – ይሉኝታ – ዝምድና – ጋብቻ ይበቃ! ጥርት ብሎ የወጣው ጠላት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማኒፌስቶና አራማጁ ፖሊሲ ነው። ሌላው ጭራሮ ነው። አሁንም የወያኔ ገበርዲን ለባሽ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች የዛሬ የአካላችሁ ጥቃት ምንጩን ዕወቁት። ተራችሁ እስኪደርስ ከመጠበቅ አሁኑኑ ወያኔን አራግፋችሁ ከተጎዱ – ከተጎሳቆሉ – ከግፉዕን ጋር ሁኑ! ሌሎቻችሁም ብትሆን ተረኝነታችሁ የጊዜ ጉዳይ ነው። ከዛ በፊት መስመርን አስተካካሎ በጠላት ላይ አቅምን መሰንዘር ይገባል እላለሁ። የወያኔ ሃርነት ትግራይ አባላት እኮ በጣም ነው የሌላውን ዝርያ የሚጸዬፉት። ምርጥ ዘሮች ናቸው። ደማቸው ተልይቶ የተፈጠረ¡ ማስጠጋትም አይፈልጉም። ከደማቸው ጋር እንዲቀራረብ አይሹም። እዬተጠላ የሚያጎነብስ – የሚያረብርብ ግልብ እንደ ሰው ለማዬት ይቀፋል። የሚያናድደኝ እኔ በግሌ ስጠላው የሚወደኝ ነው። አዎን የሌላ ዘር አባላትን የወያኔ አሽቃባጮችን የወያኔ ሃርነት ትግራይ አባላት እንዴት እንደሚጠሏችሁ ማን በነገራችሁ?! አስተውሉ! ፉከራ አይደለም ከልባችሁ ሁኑ ለማላት ነው። አረም እያለ በወገኑ የሚስነቀለው ወገን ጠላቱ ወያኔ ነገ የነቀላው ተባባሪ የሆነውን አረም ብሎ መነቀሉን ፈጽሞ አስቦት አያውቅም። ትዝም አይለውም። እያንዳንዱ የወያኔ ጋሻ ጀግሬ የታላቋ ትግራይ ራዕይ አስፈጻሚ ስለመሆኑ ምን አልባት ከእንቅልፉ ሲነቃ – ሀገር አልባ ሆኖ አፈር ለማኝ ሲሆን – ይገባው ይሆናል። እስካ ዛ ድረስ ግን የወያኔ አሲድ አዚም ተጠቂ ነው …. እራስን ማቃጠል ….. ማንደድ ….. ለትምህክት ሰለባነት፤ ዘር ለማጥፋት ተልዕኮ አባሪና ተባባሪ መሆን። ነገም በተረኝነት እራስን እረስቶ ወይ ፍቆ መጠበቅ። ሃፍረት! ይቋጭ። እጅግ የማከብራችሁ የሀገሬ ኢትዮጵያ ልጆች የእስልምና ዕምነት ወገኖቼ ሀዘኔ ከልብ፤ ዕንባዬም ከውስጥ ነው። እግዚአብሄር አምላክ ብርታትና ጥንካሬውን ይላክላችሁ። አሜን!   Radio Tasegaye or www.tsegaye.ethio.info aktuell sendung www.lora.ch.tsegaye   መራራውን ዘመን ጣፋጭ ለማደረግ ሁሉም በጠላቱ ላይ ይቁረጥ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

↧

“የእናቶች ምርቃት ለእኔ ህይወት ሆኖኛል”–ጆሲ ኢን ዘ ሃውስ (ቃለምልልስ)

$
0
0

jossy gebre
በራሱ የሙዚቃ ስልት በመጫወት ተወዳጅነት ለማትረፍ የቻለ ድምፃዊ ነው፡፡ እስከዛሬም በተለያዩ አገራት እየዞረ የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ አድናቂዎቹን በማዝናናት ላይ ይገኛል፡፡ ከድምፃዊነቱ በተጨማሪ ከአንድ ዓመት በፊት ‹‹ጆሲ ኢን ዚ ሃውስ›› (Jossy in the house) የሚል የራሱን ቶክ ሾው የኢቢኤስ የቲቪ ጣቢያ ማቅረብ ከጀመረ በኋላ የፕሮግራሙ ይዘት የብዙ የኢቢኤስ ተመልካቾችን አይን ሊስብ የበቃ ባለሙያ ለመሆን ችሏል፡፡

በተለይ በዚህ ዓመት በትንሣኤ በዓል ላይ አቅርቦት በነበረው ፕሮግራሙ ላይ የቀድሞዋን ተወዳጅ ድምፃዊ ማንአልሞሽ ዲቦ ልጆች ገጥሟቸው በነበረው የህይወት ፈተና ዙሪያ በሰራው ዘጋቢ ፊልም ምክንያት ልቡ ያልተሰበረ የፕሮግራ ተከታታይ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡

ዛሬ መተሳሰብና መረዳዳት እንደሰማይ በራቀበት ዘመን ዮሴፍ (ጆሲ) በፕሮግራሙ ላይ እንዲህ የተረሱና የወገን ድጋፍ የሚያሻቸው ወገኖችን ከህዝቡ ጋር በማገናኘት ህይወታቸው እንዲለወጥ ያደረገው አስተዋፅኦ የተከታተሉ ተመልካቾች እደግ፣ ተመንደግ፣ ተባረክ በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ዙሪያ ከድምፃዊና የቶክ ሾው አዘጋ ዮሴፍ ገብሬ ጋርየተደረገው ቆይታን እንሆ።

ጥያቄ፡- አዲሱ አልበምህ ከምን ደረሰ?

ዮሴፍ፡- አልበሙ ከሞላ ጎደል አልቋል፡፡ ለፋሲካ ይደርሳል የሚል ሃሳብ ነበረን፡፡ አንዳንድ የስፖንሰር ሺፕና ሌሎች ጉዳዮች ነበሩን፡፡ እነዚያን ጉዳዮች ፋሲካ ከመድረሱ በፊት ነበር የጨረስነው፤ ከዚያ በኋላ ያሉት ነገሮች ለማስተካከል እየሞከርን ነው ያለነው፡፡ የጆሴ ሾው ምዕራፍ 3 ልጀምር ስለሆነና ትንሽ ለየት ባለ መልክ ይዘን ለመውጣት ስለፈለግን ትንሽን ድካሞች ነበሩበት፡፡ ያንን አስተካክለን አልበሙ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለ1 ወር ከ15 ቀን ውስጥ ለአድማጭ ወደ መልቀቁ እንሄዳለን፡፡

ጥያቄ፡- አልበሙን ዜማ፣ ግጥምና ቅንብር ከእነማን ጋር ነበር የሰራኸው?

ዮሴፍ፡- በርካታ ሰዎች አሉበት፡፡ ይልማ ገ/አብ፣ ጌትሽ ማሞ፣ መለሰ ጌታሁንና ሙያው ላይ ይሰራሉ የሚባሉ የተለያዩ ሰዎች ጋር ነው የሰራሁት፡፡ ዜማውና በቅንብርም ሁሉም ጋር ነው የተሰራው ማለት ይቻላል፡፡

ጥያቄ፡- በዚህ አልበም ላይ የበፊቱን ስታይል ይዘህ ነው የመጣኸው ወይስ የተለየ?

ዮሴፍ፡- የበፊቱ እስታይል 6 ወይም 7 ዓመት በፊት ነው ይዤ የወጣሁት፡፡ ያኔ ደግሞ ወታት ነበርኩ፣ አሁን ወደ መብሰሉ ስለሆንኩ በዚያው ልክ በሰል ያሉ ዜማዎች ናቸው፡፡ ለበፊቱ አድናቂዎችም የሚሆኑና እንዲሁም አገራዊ ፋይዳ ያላቸው መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉ፣ ሀገርኛ ባህልን የሚያስተዋውቁ ሆነው የዕድሜዬን ያህል አልበሙም አድጎ ይወጣል፡፡

ጥያቄ፡- የአልበሙ ርዕስ ታውቋል?

ዮሴፍ፡- የተመረጡ ርዕሶች አሉት፡፡ ግን ሊወጣ ሲል ነው አንዱ ርዕስ የሚመረጠው፡፡

ጥያቄ፡- አልበሙን የገዛው ወይም የሚያከፋፍለው ማነው?

ዮሴፍ፡- ያንን ለጊዜው ምስጢር ላድርገውና ስፖንሰርሽፕ ከአንድ ካምፓኒ ጋር ጨርሰናል፡፡ ከዚ ባለፈ ግን የማከፋፈል ስራው እንዴት እንደሚሆን እያሰብንበት ስለሆነ ለጊዜው ይፋ አልሆነም፡፡

ጥያቄ፡- በአንተ እይታ አሁን እንደሚታወቀው የሙዚቃው ኢንዱስትሪ የገጠሙት ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው?

ዮሴፍ፡- ምክንያቶቹ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ሁልጊዜ እንደሚባለው የኮፒራይት ያለመከበር ችግር ዋነኛው ነው፡፡ ነገር ግን የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ሙሉ ለሙሉ እንዳልተቀዛቀዘ የሚያመላክቱ እንደ ብዙአየሁ አይነት ስራዎች አሉ፡፡ የብዙአየሁ አልበም በደንብ ተሰምቶ ነበር፡፡ አልፎ አልፎም ቢሆን ተሰርተው መቅረብ የሚችሉ አልበሞች አሉና ከእነኛ አንዱ የመሆን ዕድል አልመህ ያለውን ስራ በደንብ አጠንክረህ ሰርተህ ማቅረብ እንጂ ከሙያው ጨርሶ መራቅ አያስፈልግም፡፡ ምናልባት ከሚሰሙ ስራዎች መካከል አንዱ ትሆናለህ፡፡ አለበለዚያም ሪስኩን ወስደህ የሚመጣውን መቀበል ነው፡፡

ሌላው ግን ሁሉ ነገር ጨምሯል፣ ዛሬ አንድ ማኪያቶ አንዳንድ ቦታ 13 ብር ገብቷል፡፡ ከጓደኛህ ጋር ሆነህ ሁለት ማኪያቶ ከጠጣህ 26 ብር ነው፡፡ የእኛን ሲዲ በ25 ብር ለመግዛት እንደ ከባድ ይቆጠራል፡፡ አብዛኛው ሰው ለሙያው የሚሰጠው ቦታ ከደብል ማኪያቶ በታች ሆኗል፡፡ ለሙያው ክብር ብንሰጥ መልካም ነው፡፡ ድሮ እኛ ልጅ እያለን አዲስ ዘፈን ሲወጣ በየሙዚቃ ቤቱ ደጃፍ እንሰባሰብ ነበር፡፡ ሌላው ችግር ብዙ በመፅሔትና ጋዜጦች ላይ አላግባብ የአርቲስቱ ይሰጥ የነበረው ያልሆኑ ስም ማጥፋቶች ይወጡ ነበር፡፡

ወደ መፍትሄው ስንሄድ ያንን ገፅታ ለመቀየር አርቲስቱ ዝም ብሎ ከመዝፈን ባለፈ በማህበራዊ ስራዎች ውስጥ ራሱን ማሳተፍ አለበት፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እኔም የጀመርኩት ነገር አለ፡፡ እኔ ብቻም ሳልሆን የሙያ ባልደረቦቼም በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፈው ያ ገፅታ ከተቀየረ በኋላ ህዝቡ ውስጥ የእኔነት ስሜት ፈጥሮ ገበያውን የመመለስ ነገር ይኖራል ብዬ አስባለሁ፡፡

ጥያቄ፡- አንተስ ለአዲሱ አልበም ከአድማጮችህ ምን ትጠብቃለህ?

ዮሴፍ፡- መልካም ነገሮችን እጠብቃለሁ፤ ጥሩ ነገሮች ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ ጥሩ ነገር ሰርቻለሁ፡፡ በተለያዩ ባለሙያዎች አሰምቼ በጣም ቀና የሆነ ምላሽ ነው ያገኘሁት፡፡ አድማጩ ሰምቶት ደግሞ የሚሰጠውን ምላሽ አብረን እናየዋለን፡፡

ጥያቄ፡- ‹‹ጆሊ ቶክ ሾው››ን እንዴት ጀመርከው?

ዮሴፍ፡- ት/ቤት ውስጥ እያለሁ ሚኒ ሚዲያ ውስጥ እሰራ ነበር፡፡ ከ9-12ተኛ ክፍል ስማር በጣም ታታሪ ጋዜጠኛ ስለነበርኩ ይመስለናል የሚኒ ሚዲያው ኃላፊ ጭምር ነበርኩኝ፡፡ 10ኛ ክፍል ላይ የህዝብ ግንኙነትና የተማሪዎች ተወካይ ተብዬ ከ3 መምህራን ጋር የሹመት ደብዳቤ ደርሶኛል፡፡

ጥያቄ፡- የት ነበር የምትማረው?

ዮሴፍ፡- ናዝሬት አዳማ አጠቃላይ 2ተኛ ደረጃ ነበር የምማረው፡፡ እዚያ ነበር የጋዜጠንነት ህይወት የጀመርኩት፡፡ በየእረፍቱ እየገባሁ አምስቱን ቀናት ሙዚቃ ማሰማት፣ ስነ ፅሑፍ ማቅረብና ፕሮግራም መምራት የመሳሰሉትን እሰራ ነበር፡፡

መርካቶ ከወንድሜ ጋር ቢዝነስ እየሰራሁ ኢትዮ-ኒውስ፣ ዘ ፕሬስ፣ አዲስ አድማስ ላይ ከ60 በላይ አርቲክሎችን ጽፌያለሁ፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኝነት ከዚያ ጀምሮ ያደገ ሙያ ነው፡፡

ወደ ቶክሾው ስንመጣ ለምሳሌ ክዊን ላቲቫ ዘፋኝ ናት፡፡ የራሷ ቶክሾውም አላት፡፡ ሌሎችም እንደዚያው፡፡ እኔም የራሴ ቢኖረኝ ብዬ አልም ነበር፡፡ ኢቢኤስ ቲቪ ሲመጣ ፕሮግራሞች ይፈልግ ነበርር፡ ከባለቤቶቹ ጋር ተገናኝተን ለመጀመር አሰብኩኝ፡፡ በወቅቱ አልበሙ ትንሽ ያዝ ስላደረገና ልጀምር አልቻልኩም ነበር፡፡ ከቆይታዎች በኋላ ጀመርኩኝ፡፡

ጥያቄ፡- የፕሮግራሙ ፎርማት ምንድነው?

ዮሴፍ፡- ሲጀመር የታዋቂ ሰዎች የህይወት ሂደት ምን ይመስላል፣ አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ ታዋቂ አይሆንም፡፡ እነዚያ ታዋቂ ሰዎች እዚያ እውቅና ላይ የደረሱበት መንገድ እንዴት ነው? የሄዱበት መንገድ ለሌሎች መማሪያ መሆን በሚቻልበት መልኩ ማቅረብ ነው፡፡

ስለ አርቲስቶቹ የነበረን ገፅታ ጥሩ ስለነበር አርቲስት ከተጠቀምንበት በጣም ብዙ ነገር የማድረግ አቅም አለው፡፡ ብዙ ነገር ማድረግ ይችላል፡፡ የአርቲስቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያልታዩ ማንነቶችን እያሳዩ ያለውን መንፈስ ሊቀየር የሚችል መንፈስ ይዞ ነበር የተነሳው፡፡ ያንንም ስናደርግ የታመሙት፣ የተጎዱ፣ የተረሱትን፣ የትኛቸው ያሉት ብለን የመጠየቅ መንፈስ ይዘን መጣን፡፡ ከዚያም የበዓለት ዘመድ ጥየቃ የሚል ፕሮግራ ጀመርን፡፡ እያልን አሁን ያሉት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ፕሮግራ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተላበሰ፣ ከቋንቋ አጠቃቀም ጀምሮ፣ ከአቀማመጥ፣ በእያንዳንዱ ነገር ከልጅ እስከ አዋቂ የሚከተለው የቤተሰብ ፕሮግራም እንደሆነ ነው እየሰራን ያለነው፡፡

ጥያቄ፡- ምን ያህል ፕሮግራሞች ሰራችሁ?

ዮሴፍ፡- እስካሁን ዓመቱን ሙሉ ስንሰራ ነበር፡፡ ሶስት ልዩ የበዓል ፕሮግራሞች ሰርተናል፡፡ ለአዲስ ዓመት፣ ለገና እና ለፋሲካ፣ ከእነሱ ሌላ በእርግጠኝነት ከ3-4 ፕሮግራሞች ካልሆነ በስተቀር ዓመቱን ሙሉ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ነበር ስናቀርብ የነበረው፡፡ ስኬታማ ያደረገንም ፕሮግራም ያለመድገማችን ነው፡፡ ዓመቱን ሙሉ አዲስ ነገር እያሳየን ነው እዚህ የደረስነው፡፡

ጥያቄ፡- ሰዎችን መርዳት እና ማገዝ የፕሮራሙ አካል እንዴት ልታደርገው ቻልክ?

ዮሴፍ፡- ሰዎችን የማገዝና የመርዳት ነገር አሪፍ ፕሮግራም አዘጋጅ ስለሆንክ ወይም እውቀት ስላለህ ስለዚህ ብቻ ሳይሆን ልብ ይፈልጋል፡፡ አንተ ትንሽ በመስጠት የምትደሰት ከሆንክ ያንን ትሰራለህ፣ ለምሳሌ 5 ብር ኖሮህ 1 ብር በመስጠት የምትደሰት ከሆንክ እንደዚህ አይነት ፕሮግራም ትሰራለህ፡፡ እንደዚህ አይነት ልብ ከሌለህ የፈለገው ጎበዝ ጋዜጠኛ ብትሆን አትሰራውም፡፡ ይሄ የልብ ነገር ነው፡፡

ጥያቄ፡- የማንአልሞሽ ቤተሰቦች ህይወትን በፕሮግራም ላይ ለማቅረብ ምን አነሳሳህ?

ዮሴፍ፡- የእኔ ታላላቆች ወይም በዘመዶቼና ቤተሰቦቼ በተለይ በዳግማይ ትንሣኤ ወቅት ‹‹አክፋይ›› በሚባለው ስነ ስርዓት ውስኪ እና በግ ይዘው ይጠይቃሉ፡፡ ይሄ የክብር መገለጫ ነውና ያንን ሃሳብ ይዤ ነው ወደዚህ ያመጣሁት፡፡

ፕሮግራሙ ላይ በዓል ከተለመደው ፕሮግራም ውጭ የተለየ ነገር መሰራት አለበት አልኩኝ፡፡ ትዝ የሚልህ ከሆነ ለ2006 አዲስ ዓመት እነ ማንአልሞሽ ቤተሰቦች ቤት ሄጄ ነበር፡፡ በሁኔታው እኔ ብቻ ሳልሆን ተመልካቾችም በጣም ነበር ያዘኑት፡፡ ከዚያ በኋላ የአባባ ተስፋዬም የአርቲስት ዘሪቱ (እንቁጣጣሽ) ጉዳይም ነበር፡፡ ስለዚህ የማንአልሞሽ ልጆች ጥሩ ኑሮ የሚኖሩ፣ አሪፍ ት/ቤት ይማሩ የነበሩ፣ የአንዲት ታዋቂ ዘፋኝ ልጆች ነበሩ፡፡ አሁን ያሉበት ህይወታቸው ሲታይ በጣም ያሳዝናል፡፡ ቤታቸው በጣም ሩቅ ነው፣ በተለይ የማንአልሞሽ ዲቢ ሁለተኛ ልጅ ምስጢረ የተናገረችው ንግግር በጣም ልብ ይሰብር ነበር፡፡ እንደማንኛውም ሰው እኔም ልብ ተነክቶ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የምችለውን ነገር ሁሉ አድርጌ ህይወታቸው የሚስተካከልበት ነገር ልፈልግ በማለት ተነሳሁ፡፡

ጥያቄ፡- ልጆቹ የት ነበሩ አሁን የት ደረሱ?

ዮሴፍ፡- የሚኖሩበት አካባቢ በጣም ሩቅ ነበር፡፡ የት/ቤት እና የመኖሪያ ቤት ችግር ነበረባቸው፡፡ አንደኛዋ ልጅ የጤና ችግር ነበረባት፡፡ ወንድየው ት/ቤት ቢገባም የመማሪያ ቁሳቁስ ችግር ነበረበት፡፡ ከዚህ አንፃር በቂ ነው ባይባልም ዛሬ ሩቅ ከሚባል ሰፈር ወጥተው እዘህ ግሎባል ሆቴል አካባቢ ከዋናው አስፋልት 150 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኝ ንፁህ ቤት ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ቤቱ አንዳንድ ነገሮች ቢቀሩትም እየተስተካከለ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎችም እያገዙን ነው፡፡ አሁን ህይወታቸውን ከሞላ ጎደል በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ተቀይሯል፡፡ እነሱም ህይወታችን እንደ አዲስ ጀመረ ብለው ነው ደስታቸውን የገለፁት፡፡

ጥያቄ፡- ፕሮግራሙ ከተላለፈ በኋላ ምን ምላሽ አገኘህ?

ዮሴፍ፡- ከፕሮግራሙ በኋላ ያለው ነገር ማመን ያቅትሃል፡፡ ፕሮግራ የተላለፈ ቀን ባህሬን ዝግጅት ነበረኝ፡፡ ሰው ሾውን ካየ በኋላ ነው ማታ ወደ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለመከታተል የመጣው፡፡ የነበረው ምላሽ በታም የሚገርም ነበር፡፡ በነጋታው ሰኞ ፌስ ቡክ ስከፍት ከነበረው የፌስ ቡክ ፋን ከነበረው 94 ሺ ገደማ በአንድ ቀን ልዩነት ወደ 106 ሺ ከዚያም በተከታታይ ቀናት ከ120 ሺ በላይ ሆነ፡፡

እዚህም ስመጣ በየመንገዱ የሚያልፈኝ ሰው አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር ይክበር ነው ያልኩት፡፡ ይሄ ብርታት ሆኖኝ እኔ ላይ የነበሩ ፕሮግራሞች የበለጠ እንድገፋበት ጉልበት ሆነኝ፣ የእናቶች ምርቃት ለእኔ ህይወት ሆኖኛል፣ ምርቃት በጣም ነው የምወደው፣ ያደኩበት ቤተሰብ እንደዚ ስላሳደገኝ ምርቃት በጣም ነው የምወደው፡፡ ከገንዘብ በላይ ምርቃት ደስ ይለኛል፡፡

አንዳንድ ሰዎች በቃል መግለፅ የማይችሉት ፍቅር አሳይተውኛል፡፡ የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ፍቅሩን በፍቅር ይመልስልኝ ነው የምለው፡፤ መልካም ነገር ስሰራ ለራሴ ብዬ ነው ያደረግኩት፡፡ እንደ ፕሮግራምም ስታየው ጥሩ ነገር እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ግን እንደዚህ ህይወትህ ግልብጥ ብሎ እስኪቄር ድረስ ይሆናል ብዬ በፍፁም አልጠበቅኩም ነበር፡፡ ይህን ክብር መልሼ ለእግዚአብሔር ነው የምሰጠው፡፡

ጥያቄ፡- ከዚህ በኋላ እኛም አግዘንህ እንርዳ ያሉ በጎ አድራጊዎች የሰጡ ካሉ?

ዮሴፍ፡- በቂ ነው ባይባልም የመጡ ሰዎች አሉ፡፡ የመጡትን እናመሰግናለን፡፡ አሁንም እጄ ላይ ያሉ ጥቂትም ቢሆኑ መታገዝ የሚገባቸው ሰዎች በእነዚህ ፕሮግራሞች ለመርዳት እንሞክራለን፡፡ እኔም አቅሜ በሚችለው ሁሉ ከማገኘው ነገር ላይ ለማገዝ እሞክራለሁ፡፡

ጥያቄ፡- የወደፊት እቅድህስ ምንድን ነው?

ዮሴፍ፡- ምዕራፍ 3 ባይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በተለያየ መልኩ የማህበረሰቡ ችግሮችን የሚቀርፉ ምክሮች ወይም ትምህርቶች፣ ምሳሌ መሆን የሚችሉ ፋይዳዎችን የፕሮግራማችን አካል ለማድረግና የበለጠ የፕሮግራሙን ይዘት አሳድጎ የማህበረሰቡ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ነገሮች እንዲሆኑ አቅደናል፡፡

እስካሁን የሠራናቸውን ፕሮግራሞች በተመለከተ ተመልካች አስተያየት እንዲሰጡን እናደርጋለን፡፡ የምዕራፍ 3 ፕሮራሞች በአዲስ አቀራረብ፣ በጥራት ሰርተን ለእይታ እናበቃለን፡፡

ጥያቄ፡- የማን አልሞሽ ልጆች የወደፊት ህይወት የት ሊሆን እንደሚችል ይታወቃል?

ዮሴፍ፡- ልጆቹ ጎበዝ ተማሪዎች ናቸው፡፡ በትምህርታቸው ታታሪ ናቸው፡፡ አንደኛው ልጅ የትምህርት መሳሪያ ያስፈልጉት ነበር፡፡ ላፕቶፕ በስጦታ አግኝተንለታል፡፡ ከዚያ ውጭ ደግሞ በትምህርቱ ሂደት ውስጥ የሚያስፈልጉት ነገሮች እንደ ወንድም አግዘዋለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ምስጢረም ትምህርቷን እስክትጨርስ የስኮላርሺፕ እድል አግኝታለች፡፡ ፍቅርተም (የማንአልሞሽ ወንድም ልጅ) ጤናዋ ተስተካክሎ ወደ ትምህርቷ የምትመለስበት ሁኔታ ተመቻችቶላታል፡፡ ቲጂም (የማንአልሞሽ እህት) ያቋረጠችው የዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን ትቀጥላለች፡፡ መሰረታዊው ነገር እራሳቸውን ችለው ጥረው ነገ ለሰው የሚተርፉበት ህይወት ላይ ያቆምናቸው ይመስለኛል፡፡ ቀሪው ነገር የራሳቸው ጥረት ይሆናል ማለት ነው፡፡

ጥያቄ፡- ስኬታማ ነህ?

ዮሴፍ፡- እንደ ጀማሪ ጥሩ ነው፡፡ ግን የስኬት መጨረሻ ይሄ አይደለም፡፡ ገና ብዙ ይቀረኛል፡፡ እዚያ ደረጃ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር እንደምደርስ እምነት አለኝ፡፡

ጥያቄ፡- ደስተኛ ነህ?

ዮሴፍ፡- የምፈልገውን ነገር ስለምሰራ፣ የምፈልገውን ስላደርግ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በህይወት ውስጥ ስትመላለስ ማድረግ የምፈልጋቸው ነገሮች አሉ፡፡ እኔ የምሰራው የህዝብ ስራ ነው፡፡ ከማህበረሰቡ የምታገኘው ምላሽ ደግሞ ጥሩ እየሆነ ሲመጣ ከዚህ በላይ ደስተኛነት የለም፡፡ ከራስህም አልፈህ በሰዎች ህይወት ውስጥ ምክንያት መሆንህ በራሱ ከማንም በላይ ደስተኛ ያደርግሃል፡፡

ጥያቄ፡- የምትጨምረው ነገር ካለ?

ዮሴፍ፡- በመጀመሪያ አክብራችሁ ስለጋበዛችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡ በአዲስ አልበም፣ በአዲስ የቲቪ ሾው ሲዝን ጥሩ ነገሮችን ይዘን ራሳችንን አሻሽለን የምናርመውን አርመን፣ የምናዳብረውን አዳብረን ለማህበረሰቡ ይጠቅማል በምንለውና ባደገ የስራ አካሄድ ወደ ህዝቡ እንመጣለን የሚል እምነት አለኝ፡፡

 

 

↧
↧

የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራር በዞኑ አቃቤ ህግ ይግባኝ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

$
0
0
10329778_አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በደቡብ ክልል የወላይታ ዞን የፓርቲው አመራር የሆኑት ወ/ሪት ሀዲያ መሀመድ ዓሊ አንድነት ፓርቲ በወላይታ ለሚያደርገው ሕዝባዊ ስብሰባ በፓርቲው የተዘጋጀ ፍላየር ከፓርቲው አባሎች ጋር በመሆን ሲያሰራጩ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው የሚታወስ ሲሆን ጥር 8 ቀን 2006 ዓ.ም በወላይታ ዞን ፍ/ቤት ቀርበው በ1000. 00 /አንድ ሺህ ብር/ ዋስትና መለቀቃቸውን ፍኖተ ነፃነት መዘገቧ ይታወሳል፡፡

በወላይታ ዞን ከ/ዐ/ህግ ይግባኝ ባይነት ጥር 8 ቀን የተሰጠው ውሳኔ ተከሳሿ ጥፋተኛ የተባሉበት ወንጀል በዓለም አቀፍ ሽብርተኞች አስተሳሰብ ሲቀሰቅሱ የነበሩትን እንዳለ በመውሰድ ከአስተሳሰብ ባለፈ መልኩ በተግባር በአገራችን ውስጥ ተቻችሎ የመኖር ሁኔታ የሚያቃውስና ወደ ጦርነት የሚያመራ ጽሑፍ በርካታ ገፆች ይዛ የተገኙትን ግለሰብ በጥፋታቸው ልክ መቅጣት ሲገባ በጣም ዝቅተኛና ተመጣጣኝ ያልሆነ ቅጣት በመሰጠቱ ቅር ብሎኛል በማለት የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማሻሻል ከጥፋታቸው ጋር የሚመጣጠን ቅጣት እንዲሰጣቸው በማለት በወላይታ ከተማ ለሚያስችለው መደበኛ ተዘዋዋሪ ችሎት እንዲቀርቡ አዟል፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የተቃዋሚ ፓርቲ አባሎችን በማስፈራራት፣ በመደብደብና በማሰር ሀሰተኛ ምስክር አዘጋጅቶ ክስ መመስረት ለማሸማቀቅ የሚደረገው ሙከራ አባላትን እያጠናከረ እንጂ እነሱ እንደሚያስቡት እንዳልሆነ ለፍኖተ ነፃነት የገለጹት የፓርቲው አባላት ወደፊትም ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
10347545_

10408794_6

10505522_66

↧

እስረኞቹ በሽብር መከሰሳቸውን አያውቁም (ጽዮን ግርማ)

$
0
0

Stion Girmaአንድ ዓመት ከአንድ ወር ኾኖታል። እስክንድር ነጋ ከታሰረ ከዐስራ ስምንት ወራት በኋላ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በሰኔ የመጀመሪያ ወር ላይ በ2005 ዓ.ም. እንደተፈቀደለት፤ እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ወደሚገኘው እስር ቤት አምርቼ ነበር።

ተገናኝተን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላም እንዲህ አለኝ፤ ”ሽብርተኛ አይደለኹም፤ ሀገሬ በማንም እንድትሸበር አልፈልግም አልፈቅድምም እኔ የምፈልገው የሀገሬ ሕዝቦች በነጻነት የሚያስቡባትና የሚንቀሳቀሱባት ሰላማዊ ሀገር እንድትኾን ነው”፤ እስክንድር ”ሽብርተኛ” አይደለምና ከእስሩም በላይ ያንገበገበው ”አሸባሪ” መባሉ ነበር።

እስክንድር ”ጋዜጠኛ” ነው። እስክንድር ሲጽፍ ሀገሪቱ ላወጣችው ሕግ ራሱን አስገዝቶ፣ በሀገሪቱ ሕግ ማዕቀፍ ሥር ራሱን ገድቦ ነው። ይህም ኾኖ ግን ሲጽፍ ሕግ ተጥሶ አደጋ ሊደርስበት እንደሚችል፣ ሲጽፍ ሕግ ተጥሶ ሊታሰር እንደሚችል ያውቃል። ግን ደግሞ ቢታሰር በቀጫጭን መስመርም ቢኾን በሀገሪቱ ሕግ ተዳኝቶ ከእስር ሊለቀቅ እንደሚችል ያምን ነበር። በዚህ እምነቱም የመጣበትን ለመቀበል ተዘጋጅቶ ሀገሩ ላይ ቁጭ ብሎ ይጽፋል።
zone 9

ከመጻፍ እና ሐሳቡን በአደባባይ ከመግለጽ ውጭ ያሉት መንገዶች እስክንድርን አይመቹትም። እስክንድር ሐቀኛና ቀጥተኛ የኾነ አስተሳሰብ ያለው፤ ላመነበት ነገር የታመነ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ነው። ምናልባት ይህን ”እስክንድርን” ለመረዳት እስክንድርን ማወቅ ሊጠይቅ ይችላል። እስክንድርን ያኔ ቃሊቲ ሳገኘው ሽብርተኛ አለመኾኑን ደጋግሞ ነገረኝ። ”እስክንድር ለማነው የምትነግረው ሽብርተኛ አለመኾንህን ከቀረበብህ ክስ ጋር አንዳችም ግንኙነት እንደሌለህ እኮ ዓለም ያውቃል፤ አሳሪዎችህም ይህን ጠንቅቀው ያውቃሉ” አልኩት። እርሱን ግን ያበሳጨው ከታሰረውም፣ ከተንገላታውና ከተፈረደበትም በላይ በውሸት የተወነጀለበት “ሽብርተኝነት’’ ነበር።

አሁንም ሽብርተኝነት

አሁን እስክንድር ከታሰረ ሁለት ዓመት ከሰባት ወር ኾኖታል በእርሱ የተጀመረው ጋዜጠኛን፣ ጸሐፊዎችንና መብቱን በአደባባይ የሚጠይቀውን ሁሉ ሰብስቦ ”ሽብርተኛ” ብሎ መክሰስ ዕለት በዕለት እየጨመረ የታሳሪዎቹን ቁጥር አበራክቷል። ላለፉት ሰማንያ ሦስት ቀናት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታስረው የሚገኙትና በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ በቀጠሮ ሲመላለሱ የቆዩት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና፣ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ የሕግ መምሕርና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘለዓለም ክብረት፣ የዞን ጦማሪዎቹ ናትናኤል ፈለቀ እና አጥናፉ ብርሃኑ ለቅዳሜ ሐምሌ 5 ቀን የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎቹ ማኅሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ኃይሉ እና አቤል ዋበላ በዚሁ በፈረደበት ”ሽብር” ተጠርጥረው የታሰሩ ናቸው።

የምርመራ መዝገቡ በሌሉበት መዝገቡ ተዘግቶ ከሕግ ውጪ በእስር የከረሙት እነዚህ እስረኞች ግንቦት ዘጠኝ በነበረው ቀጠሮ ቀን ፖሊስ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተጠርጣሪዎችን በሽብር መጠርጠሩን ሲናገር ወጣቶቹ በድንጋጤ አንገታቸውን ሲሰብሩ ታይተው ነበር። የሚያስደነግጠው እስሩ አይደለም፤ ሕግን አስከብራለሁ የሚል አንድ ተቋም ወጣቶችን ሰብስቦ አስሮ ባልዋሉበት የሚያውል የፈጠራ ክስ ሲጭን መስማቱ ነው። ማንነቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው እንዲህ ያለ የውሸት ክስ ሲቀርብበት የሚሰማውን ስሜት ለመገመት ያስቸግራል። እናም ወጣቶቹ በሽብር ተግባር አለመሳተፋቸውን ያውቃሉና የቱንም ያህል የኢሕአዴግን ባህሪ ጠንቅቀው ቢያውቁት ”በሽብር እንከሰሳለን” የሚል ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ ሊኖራቸው አይችልም። ምናባት የመጨረሻውን ጣሪያ ቢገምቱ እነርሱን አስሮ ሌሎች ጸሐፊዎችን ለማስፈራራት የተነደፈ ስልት ይኾናል ከሚል ግምታዊ መላምት ”ምርጫው እስኪያልፍ ታስረን እንቆያለን” የሚለውን ነው።

ዛሬ ጠዋት ልደታ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ሲቀርቡም፤ ከዚሁ ሐሳብ ሊኖራቸው እንደማይችል እገምታለሁ። ወጣቶቹ ከታሰሩ ጀምሮ ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ጠበቃ፣ ቤተሰብና ሌሎች ሰዎች ከትናንት ጀምሮ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ይችላሉ በሚል ይቀርቡበታል በተባለው ፍርድ ቤት ግቢ ክትትል ሲያደርጉ ቢቆዩም ዛሬ ጠዋት ማንም ሰው ባልተገኘበት ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ከፍቶባቸዋል። ነገር ግን የክስ ቻርጁ እንዲሰጣቸውና መቃወሚያ ካላቸው እንዲናገሩ ተጠይቀው ዘጠኙም እስረኞች ጠበቆቻቸው ባልተገኙበት ክሱ እንዲነበብላቸው እንደማይፈልጉ ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነትን አግኝቶ ጠበቆቻቸው በተገኙበት ነገ ጠዋት እንዲቀርቡ ታዟል።

በሌላም በኩል ዛሬ ጠዋት እስረኞቹን ለመጠየቅ ማዕከላዊ ሄደው የነበሩ ቤተሰቦችና ጠያቂ ወዳጆች መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው ተመልሰው ነበር። ከሰዓት በኋላም ሊጠይቋቸው በሄዱ ጊዜ ስለተከሰሱት ክስ የሚያውቁት ነገር አልነበረም። አብዛኞቹም (አብዛኞቹ ስል ስለ አስተያየታቸው መረጃ ያገኘኹት ማለቴ ነው) በሽብርተኝነት እንከሰሳለን የሚል እምነት አልነበራቸውም። ነገ የሚኾነውን ለማየት በይደር አቆይተው ቤተሰቦቻቸውን ተሰናብተው ወደ ማደሪያቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል።

የሽብርተኝነት ክሱ

የሪፖርትር ጋዜጣ ዘጋቢ ታምሩ ጽጌ ደግሞ ሰበር ዜና በሚል በጋዜጣው ድረ ገጽ ላይ፤ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ፣ እንዲሁም ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ላይ ዐቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ክስ መመስረቱን አስነብቦናል።

ዜናው እንደሚለው፤ ተጠርጣሪዎቹ በሕቡዕ በመደራጀት፣ የአጭርና የቅርብ ጊዜ ግብ በማቀድና በመንደፍ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በፓርላማ ሽብርተኛ ተብለው ከተሰየሙት የግንቦት 7 እና የኦነግ ድርጅቶች መመርያና ሐሳብ ሲቀበሉ መቆየታቸው ተገልጿል።

ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ የሆነችው ሶሊያና ሽመልስ የቡድኑ መሥራችና አስተባባሪ በመሆን ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. መቆየቷና ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በውጭ አገር አስተባባሪና የውጭ ግንኙነት ሆና ከመሥራቷም በተጨማሪ፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በማደራጀትና በመመልመል ስትሠራ መቆየቷን ክሱ ያስረዳል። የህቡዕ ቡድኑ ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. ”ሴኩሪቲ ኢን ቦክስ” የተባለ ሥልጠና እንዲሠለጥንና እንዲደራጅ ስትመራ መቆየቷም በክሱ ተካቷል።

ሌላኛው ተጠርጣሪ በፍቃዱ ኃይሉ የአገር ውስጥ የሽብር ቡድንን በመምራትና የሥራ ክፍፍል በማድረግ፣ እንዲሁም ግብ በማስቀመጥና ስትራቴጂ በመንደፍ ከሽብርተኛ ኃይሎች ጋር ግንኙነት ሲፈጥር መቆየቱ በክሱ ተጠቅሷል።

የዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ ተጠርጣሪ ናትናኤል ፈለቀ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የህቡዕ ድርጅቱ የአገር ውስጥ አስተባባሪ በመሆን በሥሩ ላሉት አባላት የሥራ ክፍፍል መመርያ በመስጠት፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት በመፍጠር መመርያ ከመቀበሉ በተጨማሪ፣ ለአመፅ ተግባር የሚውል የተላከለትን 48,000 ብር ማከፋፈሉንም ክሱ ያብራራል።

ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች በህቡዕ ድርጅቱ ውስጥ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ መሥራችና አባል በመሆን የግንቦት 7 እና የኦነግን ስትራቴጂና ዕቅድ በመቀበል በውጭና በአገር ውስጥ ባሉ የቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በውጭና በአገር ውስጥ ሥልጠና በመውሰድ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማቀድ፣ በመዘጋጀት፣ በማሰርና በማነሳሳት ወንጀል መከሰሳቸውን ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ ያስረዳል።

በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ሁለተኛ ክስ እንደሚያስረዳው ተጠርጣሪዎቹ በወንጀሉና በሚያስገኘው ውጤት ተስማምተው በሕገ መንግሥት ሥርዓት የተቋቋመን መንግሥት በአመፅ፣ በሁከትና በብጥብጥ ለመለወጥ በማሰብ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. እስከተያዙበት ዕለት ድረስ በህቡዕ ተደራጅተው፣ የሥራ ክፍፍል በመፍጠር፣ ሥልጠናዎችን በመውሰድ፣ አመፅ የሚቀሰቅሱ ጽሑፎችን በመበተን፣ የአመፅ ቡድኖችን በማደራጀት ሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመፅና በሁከት ለመለወጥ በመሞከር ወንጀል መከሰሳቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል።

በመጨረሻ

ይህን ክስ የሰማ ማንም ሰው እነዚህ ወጣቶች ሽብርተኛ አለመኾናቸውን እንደሚረዳው ኹሉ፤ ከሳሻቸው ዐቃቤ ሕግም የውሸት ክስ እንደመሰረተባቸው ልቦናው ያውቀዋል። በተለይ ደግሞ ወጣቶቹን በቅርበት ለሚያውቃቸው ሰው በእነሱ ላይ እንዲህ ያለ ክስ ሲመሰረትባቸው ምን ዐይነት ስሜት እንደሚፈጥር ለመግለጽ ያስቸግራል። ጠንካራና ሀገር ወዳድ ወጣቶች በሽብርተኝነት ሲከሰሱ መስማት የሚፈጥረውን ቁጭት ከቃላትም በላይ ነው። ይህ ስሜት እነርሱ ላይ ሲደርስ ምን ሊኾን እንደሚችልም መገመት ያስቸግራል። እስክንድርን ከመታሰሩም በላይ ያስከፋው እንኳን ክፉ ሊያደርስባት ክፉ እንዳይነካት ቀን ከሌሊት የሚጸልይላትን የሚወዳትን ሀገሩን ገንዘብ ተቀብለህ ልትበጠብጣት ነው መባሉ ነበር።

”ዴሞክራሲያዊነቷ” የታወጀላት ሀገር ስትበደል ሕግ በሚፈቅድላቸው መሰረት ተቃውሟቸውን በጹሑፍ ያሰሙ፣ ለሀገሪቱ ሕግ ራሳቸውን አስገዝተው የጋዜጠኝነት ሥራን የሠሩ በሽብርተኞች እጅ የወደቁ እንጂ ”ሽብርተኛ” ያልኾኑት ወጣቶች ነገ ጠዋት በሽብርተኝነት መከሰሳቸውን ሲሰሙ ምን ይሉ ይኾን?

↧

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት በ24 ሰአታት አገር ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ

$
0
0

ethsatየአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት በ24 ሰአታት አገር ለቀው እንዲወጡ ታዘዙለሰአታት በቁም እስር ላይ የነበሩት የታዋቂው ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ታጋይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ የወንድማቸውን ጉዳይ ለመከታተል በሚል ከ10 ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ቢያመሩም፣ ከትናንት በስቲያ ደህንነት ጽ/ቤት ከተጠሩ በሁዋላ አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። በታዘዙበት ሰአት ለመመለስ እንደሚቸገሩ የተናገሩት ወ/ሮ ብዙአየሁ፣ የ 24 ሰአት ጊዜ የጊዜ ገደብ ከተሰጣቸው በሁዋላ ዛሬ ወደ አሜሪካ ተመልሰዋል። ወ/ሮ ብዙአየሁ የአቶ አንዳርጋቸውን ቤተሰቦች በመወከል ጉዳዩን ለመከታተል በሚል መሄዳቸውን ከቤተሰቦች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። 


ኢህአዴግ የአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ የእግር እሳት እንደሆነበት የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። አቶ አንዳርጋቸው የህዝቡ የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆናቸውና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የግንቦት7 ዝናም ከምንጊዘውም በላይ በመጨመሩ የገዢውን ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን እያበሳጨ ነው። 


ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ በአገር ውስጥም በውጭም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አሁንም በተከታታይ ስልኮችን እየደወሉ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው። (ድምጽ ) በፐርዝ አውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ከእንግሊዝ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ኢትዮጵያውያኑ ለቆንስላው ላቀረቡት ጥያቄ የፐርዝ የእንግሊዝ የቆንስላ ሃላፊ፣ አገራቸው የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየተከታተለችው ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል። 


በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት በላኩት ደብዳቤ የአቶ አንዳርጋቸው መታፈን ” ወያኔ ፍጹም አወሪነቱን ያሳየበት እና ዘላአለም የነጻነት ታጋዮችን ለማስፈራራት እና ከትግሎ ሜዳ ለማስውጣት የተጠቀመበት የትእቤት ስራ ነው። ” መሆኑን ያሳያል ካሉ በሁዋላ፣ የተወሰደው እርምጃ ህዝቡን ለትግል እንደሚያነሳሰው ገልጸዋል። 


በሌላ ዜና ደግሞ በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው ማእከላዊ እስር ቤት እንዲታሰሩ የተደረጉት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የድርጅቱ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል የምክር ቤት ሰብሳቤ አቶ የሽዋስ አሰፋ እንዲሁም አረና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚና ታዋቂ ጸሃፊ መምህር አብርሃ ደስታ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። አንድነት ፓርቲ የተያዙት ሰዎች በ48 ሰአታት ውስጥ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን በመግለጽ ክስ መስርቶ ነበር። ይሁን እንጅ ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርጎታል።

 

↧

የሰማያዊ ፓርቲዋ ወጣት ወይንሸት ሞላ ተፈንክታ፣ እጆቿ በፋሻ ጠቅልሎ፣ ሰውነቷ ዝሎ ፍርድ ቤት ቀረበች

$
0
0
(ፎቶው የተገኘው ከሰማያዊ ፓርቲ ነው)

(ፎቶው የተገኘው ከሰማያዊ ፓርቲ ነው)

(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው እለት የአንዋር መስጊድ አካባቢ የሕወሓት አስተዳደር በንጹሃን የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ አሰቃቂ እርምጃ እየወሰደ በሚገኝበት ወቅት መርካቶ አካባቢ ለሥራ ጉዳይ ሄዳ የነበረችው የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤትና የሴቶች ጉዳይ አባል ወጣት ወይንሸት ሞላ በደህነንቶች ታፍና ከተወሰደች በኋላ ከፍተኛ ድብደባ ሲፈጸምባት ቆይቶ በዝግ ችሎት ቀርባ 14 ቀን የምርመራ ቀጠሮ ተጠየቀባት።

የነፃ አሳቢ ዜጎች መሰቃያ በሆነውና ከማዕከላዊ አጠገብ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ውስጥ የምትገኘው ወጣት ወይንሸት ማንም ሰው እንዳይጠይቃት በፖሊሶቹ መከለከሉ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ዛሬ ረፋዱ ላይ ሜክሲኮ አካባቢ ያለ ፍርድ ቤት የቀረብቸው ወጣት ወይንሸት ምንም እንኳ ችሎቱ በዝግ ቢደረግም ጭንቅላቷ ተፈንክቶ፣ ቀኝ እጇ በፋሻ ተጠቅልሎና አንገቷ ታስሮ የተመለከቷት ሲሆን የህግ አማካሪ እንዳታገኝም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ መከልከሉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አረጋግጠዋል።

↧
↧

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መግለጫ –ክፍል 1&&2 (ሐምሌ 11/2006 ዓ.ም)

↧

ቋሚ ሲኖዶስ ለፓትርያርኩ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

$
0
0
  • አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለመጥራት ታቅዶ ነበር፡፡
  • ፓትርያርኩ በአ/አበባ የአድባራት አለቆች ዝውውት ስሕተት መፈጸማቸውን አምነዋል፡፡
  • ‹‹የቤተክርስቲያንን ሼል ይጎዳል በሚል እንጂ ተመራጩ ነገር ከእሳቸው ጋር(ፓትርያርኩ) ጋር መሥራት ማቆም ነበር፡፡›› የቋሚ ሲኖዶስ አባል የተናገሩት

1af06-patriarch-ab-mathias

  • ፓትርያርኩ ከአሁኑ መንገዳቸው ካልተጠቆማቸው ፤ ስህተታቸው ካልተነገራቸው ቤተክርስቲያኒቱን አደጋ ላይ ሊጥሏት ይችላሉ፡፡

አንድ አድርገን ሐምሌ 12 2006 ዓ.ም፡- 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕግን የመተርጎምና የማስፈጸም መብት ያለው ቋሚ ሲኖዶስ ፤ ውሳኔዬን አክብረው አላስከበሩኝም ፤ ጠብቀው አላስጠበቁኝም ላላቸው ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገለጸ፡፡

ቋሚ ሲኖዶሱ ፓትርያርኩን ያስጠነቀቀው ፤ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ባካሔደው ሳምንታዊ ስብሰባ ወቅት ነው፡፡ የቤተክህነቱ የፋክት ምንጮች  እንደተናገሩት  የማስጠንቀቂያው መንስኤ ፤ አቡነ ማትያስ ምክራቸውን ለስልጣነ ፕትርክናቸው አይመጥኑም ከተባሉ ግለሰቦችና የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ክብርና ነጻነት በመጋፋት ከሚወቀሱ አካላት ጋር ግንባር በመፍጠራቸው ፤ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔንና ልዕልና የሚጻረር ተግባር በየጊዜው በመፈጸማቸውና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላቱን ክፉኛ በማሳሰቡ ነው፡፡

ከፍተኛ ገቢና አገልግሎት አቅም ባላቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመዋጋት የተመሰገኑ አለቆችን ከሓላፊነት በማንሳት በተመለከተ አገልጋዩና ምዕመኑ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ባልሰጡበት ኹኔታ ፤ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ በመጻረር በአቡነ ማትያስ ትእዛዝ የተፈጸሙ ዝውውሮች ፤ ቋሚ ሲኖዶሱ ሳይወስንና የሚመለከታቸው አካላት ሳያውቁ ልዩ ጸሐፊያቸውን በማንሳት በሌላ መተካታቸውና የመሳሰሉት ጉዳዮች የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ከፓትርያርኩ ጋር በከፍተኛ ደረጃ የተጠየቁባቸው ዐበይት ነጥቦች እንደነበሩ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በስብሰባው ላይ ለፓትርያርኩ ጥያቄ ያቀረቡት የቋሚ ሲኖዶስ አባላቱ ፤ ሳይገባቸውና ደረጃቸውን ሳይጠብቁ ‹ፓትርያርኩን ያማክራሉ› ያሏቸውን ግለሰቦች ስም በመጥቀስ ‹ከማን ጋር ነው የሚሰሩት? ማንን ነው  የሚሰሙት ? ከእኛ ጋር ይሰራሉ ወይስ አይሠሩም ?  › በሚል ጠንክረው እንደጠየቋቸው በምንጮቹ መረጃ ተመልቷል፡፡

አቡነ ማትያስ ስማቸው በሊቃነ ጳጳሳቱ ከተጠቀሱት ሰዎች ጋር የሚመክሩትና የሚሠሩት ‹አላማዬን ስለሚያስፈጽሙልኝ ነው›› በማለት አቋማቸውን ለመከላከል ቢሞክሩም ‹‹ አገልጋዩና ምዕመኑ የሚዘረፍበትና የሚሰቃይበት ዓላማ ሊኖርዎት አይችልም›› በሚል ጠንካራ ምላሽ እንደተሰጣቸውና በኹኔታውም መደንገጣቸው ተሰምቷል፡፡

st-urael-parish-head-row02‹‹የቤተ ክርስቲያንን ሥራ ይጎዳል በሚል እንጂ ተመራጩ ነገር ከእሳቸው ጋር(ፓትርያርኩ) ጋር መሥራት ማቆም ነበር፡፡›› ማለታቸውን የተጠቀሰላቸው አንድ የቋሚ ሲኖዶስ አባል ፤ ቋሚ ሲኖዶሱ ፓትርያርኩ በአጋጣሚው በብጹአን አባቶችና በወዳጆቻቸው ጭምር ቢመከሩም ሊያርሙት ስላፈቀዱትና ከሚገኙበት አሳሳቢ የአሰራር ኹኔታ አንጻር የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይና ድንገተኛ ጉባኤ ስብሰባ ለመጥራት የሚገደዱበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር ማለታቸው ተነግሯል፡፡

አቡነ ማትያስ በቋሚ ሲኖዶስ አባላቱ በተጠየቁባቸው ጉዳዮች ስሕተት  መፈጸማቸውን አምነው መቀበላቸውና  ‹‹ከእኛ ጋር ይሰራሉ ወይስ አይሰሩም›› በሚል በቁርጥ ተጠይቀውበታል ለተባለው አዎንታዊ መልስ መስጠታቸው ፤ በቃለ ጉባኤውን የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ ለጊዜው እንደገታው ጠቁመዋል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ የቅዱስ ሲኖዶሱን ልዕልናና የቤተ ክርስቲያኒቱን መብትና ጥቅሞች ከመሰል ተግዳሮቶች የማስጠበቅ ርምጃውን በተተኪ ተለዋጭ አባላቱ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበትም አስታውቀዋል፡፡

በተያያዘ ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ በመጋፋት ስሕተት መፈጸማቸውን አምነው ከተቀበሏቸው ርምጃዎቻቸው መካከል ፤ ብልሹ አሰራርንና ሙስናን በመዋጋት የአገልጋዩና ምእመኑ ከፍተኛ ተቀባይነት ማትረፋቸው የሚነገርላቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደ/ጽጌ ቅ/ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ዝውውር ዋንኛው ነው ተብሏል፡፡

Source- andadirgen.blogspot.com

↧

‹‹የአንዳርጋቸው ጽጌን የሞት ቅጣት ሊያፀኑ የሚችሉት ፕሬዚዳንቱ ናቸው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

$
0
0

ባለፈው ዓርብ በጽሕፈት ቤታቸው ከጋዜጠኞች ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሞት ቅጣት ሊፀና የሚችለው በፕሬዚዳንቱ ይሁኝታ ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ላይ ያላት የመሪነት ሚና እንዳልቀነሰ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥታቸው የአገር ውስጥ የግል ዘርፉን ለማበረታታት እየሠራ እንደሆነና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን እያሰረ ያለው በፖለቲካ አቋማቸው የተነሳ እንዳልሆነም ገልጸዋል፡፡ የደመወዝ ጭማሪውን መጠንም ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ከ9፡00 ጀምሮ ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀው ጋዜጣዊ መግለጫቸው ከጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎችን ያስተናገዱ ሲሆን፣ ከእነዚህም አንዱ ሪፖርተር የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በድጋሚ የማይታይ ከሆነ የሞት ፍርዱ ተፈጻሚ ይሆናል ወይ? ሲል የጠየቃቸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሞት ፍርድ ተፈጻሚ የሚሆነው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ካፀደቁት በኋላ እንደሆነ አስታውሰው፣ ይኼን ጥያቄ መመለስ የሚችሉት ፕሬዚዳንቱ ብቻ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የነበራት ተሰሚነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ስለመቀነሱ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በደፈናው የኢትዮጵያ ተቀባይነት ቀንሷል ከማለት ይልቅ በየትኛው ዘርፍ እንደሆነ ተለይቶ ጥያቄው ቢቀርብ የተሻለ እንደሚሆን ካስረዱ በኋላ፣ በእሳቸው እምነት የኢትዮጵያ የመሪነት ሚና አሁንም እየቀጠለ ለመሆኑ ማሳያ የሚሏቸውን ጉዳዮች ጠቅሰዋል፡፡ የመጀመርያው ጉዳይ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላይ የአፍሪካውያንን ድምፅ ማሰማት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ተፅዕኖ አሁንም ጉልህ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ እንደ ምሳሌም በዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር በሚመራው የአረንጓዴ ዕድገት ፎረም ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ አማካይነት የቦርድ አባል ሆና መመረጧን ጠቅሰዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2015 የሚጠናቀቀው የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ከተጠናቀቀ በኋላ ስለሚቀጥለው ሁኔታ አፍሪካ ያላትን ድምፅ ለማሰማት ከተወከሉት አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ እንደሆነችም አመላክተዋል፡፡ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) አፍሪካ ላይ በተለየ ሁኔታ ትኩረት አድርጎ መሥራቱን ለመቃወም የተደረገውን ትግል በስኬት ለመደምደም፣ በተለይ የኬንያ ፕሬዚዳንት ክስ በሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ እንዳይነሳ ለማድረግ የኢትዮጵያ መሪነት ሚና ጉልህ እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡ ይኼን ስኬት የጠቀሱት ባለሥልጣናት ከተጠያቂነት ቢያመልጡ ደስተኛ ስለሆኑ ሳይሆን፣ የአገሮች ሉዓላዊነትና የሕዝቦች ምርጫ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ስለሆነ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እስርም የተለየ ፖለቲካ ስለሚያራምዱ የተወሰነ ውሳኔ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያንና አካባቢውን በሽብርተኝነት ለማናጋት በተቀናጀ ሁኔታ ከሚሠራው የሽብር መረብ ጋር ግንኙነት ፈጥረው በመገኘታቸው እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ የጦማርያኑና የጋዜጠኞቹ ጉዳይም ከተመሳሳይ መረብ ጋር የተገናኘ እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥታቸው የዜጎችን ሰላማዊ ኑሮ ለማረጋገጥ የሽብርተኝነት መረቡን ለመበጣጠስ የጀመረውን ስኬታማ ሥራ አጠናከሮ እንደሚቀጥልም ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ሥር ተወሽቀው የሽብር ተግባር ላይ ተሳታፊ የነበሩ ጥቂት ግለሰቦች ታሰሩ ማለት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ታሰሩ ማለት እንዳልሆነም በመጠቆም፣ ለምርጫ 2007 ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እያደረጉት ያለው ዝግጅት ሊስተጓጎል እንደማይችልም አመላክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸውና ግንቦት 7 ብቻቸውን ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከባድ እንደማይሆን ቢገባውም፣ እነዚህ የሽብር ቡድኖች የተደገፏቸውና የሚተማመኑባቸው አገሮች ጋር ከሠሩ ጉዳቱ ከባድና አካባቢያዊ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ግን አስረድተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቁጥጥር ሥር መዋል በሽብርተኞቹ ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ከባድ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከአስመራ ወደ ደቡብ ሱዳን ለመዘርጋት የተሞከረው መረብ እየተበጣጠሰ ለመምጣቱ የአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ማሳያ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡ በቅርብ ጊዜያት የጋምቤላ ንቅናቄና የኦብነግ አባላት በቁጥር ሥር መዋላቸውም የሽብር ቡድኑ አባላት የሌላ አገር ዜግነት ቢኖራቸውም፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እስከነኩና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው የሽብር ወንጀል እስከተካፈሉ ድረስ ዕርምጃ ከመውሰድ ኢትዮጵያን የሚያቆማት አካል እንደሌለም አስታውቀዋል፡፡ በተለያዩ ሙያዎች ውስጥና በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በመጠለል የሽብር ወንጀል ላይ ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የውጭ ኃይሎችን በተለይም ኤምባሲዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን መንግሥት ለመጠምዘዝ ሙከራዎች እየተደረጉ እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት በማክበር ሕጋዊ ዕርምጃ ከመውሰድ የሚያግዳቸው ኃይል እንደሌለ አመልክተዋል፡፡

በተደጋጋሚ የፋይናንስ ችግር የለም በሚል መንግሥታቸው ቢገልጽም፣ በዚህ ችግር በተለይ የአገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ እየተጠቃ ስለመሆኑ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥት ለብድር ያስቀመጠውን ገንዘብ አሟጦ ጥቅም ላይ የሚያውል አካል ባልመጣበት ሁኔታ የገንዘብ ችግር አለ ማለት ተገቢ እንደማይመስላቸው ገልጸዋል፡፡ 70 በመቶ የባንክ ብድር ለማግኘት 30 በመቶ የፕሮጀክት ወጪ ማሳየት የሚጠይቅ ሕግ ያለ ሲሆን፣ የውጭ ባለሀብቶች ይህን 30 በመቶ ማሽንን በኮላተራልነት እያቀረቡ እያለ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች መከልከሉ አግባብነት ያለው ስለመሆኑ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የውጭ ባለሀብቶች ፋብሪካ በመንቀል ሲመጡ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስለሚያመጣ የተፈቀደ ቢሆንም ይህን የማድረግ አቅም ያለው የአገር ውስጥ ባለሀብት እስከመጣ ድረስ መንግሥት ለአገር ውስጥ ባለሀብቱ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚያጤነውም ቃል ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ መንግሥታቸው ይፋ ባደረገው የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ መጠን ላይ የተጠየቁ ሲሆን፣ በሐምሌ ወር መጨረሻ እስኪገለጽ ድረስ የመንግሥት ሠራተኞች በትዕግሥት እንዲጠባበቁ ጠይቀው፣ ገና የደመወዝ ጭማሪው መጠን ሳይታወቅ በአንዳንድ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱ አሳሳቢ መሆኑን ግን ተቀብለዋል፡፡ መንግሥት የደመወዝ ጭማሪ ያደረገው ባለፉት ሁለት ዓመታት በገንዘብና በፊሲካል ፖሊሲው እንዲሁም በአስተዳደራዊ ዕርምጃዎች አማካይነት የዋጋ ግሽበቱን ኢኮኖሚያዊ ጤንነት ጋር በተጣጣመ መልኩ በአንድ አኃዝ እንዲገደብ ካደረገ በኋላ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ የዋጋ ግሽበቱ የመንግሥት ሠራተኛውን ብቻ ሳይሆን በዝቅተኛ ደመወዝ ኑሯቸውን የሚገፉ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ እንደሚጎዳ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ የዋጋ ግሽበትን ጉዳት በሚፈለገው መጠን መቀነስ ባይቻልም አነስተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ገቢያቸው እንዲጨምርና የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ለማድረግ መንግሥታቸው የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የደመወዝ ማስተካከያው የሚደረገው የመንግሥት ሠራተኞችን ኑሮ ለማሻሻል ቢሆንም፣ ስግብግብ ነጋዴዎች የሚያደርጉት የዋጋ ጭማሪ ችግር እንዳይፈጥር መንግሥት ቁጥጥር እንደሚያደርግና አደብ እንዲገዙ ለማድረግ ዕርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ጊዜ መንግሥት ነጋዴዎቹን የማሳመንና የማስረዳት ሥራ እየሠራ መሆኑን በመጠቆም፣ ከሕጋዊ ዕርምጃ ባለፈ ማግባባት መምረጡን አስረድተዋል፡፡ ሕጋዊ ዕርምጃ የሚወሰደው ስግብግብ ነጋዴዎች ካስገደዱ ብቻ እንደሚሆንም አመላክተዋል፡፡

 

Source: Ethiopian Reporter

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መግለጫ – ክፍል 1& &2  (ሐምሌ 11/2006 ዓ.ም)

↧

የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ታሰሩ

$
0
0

–ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተጠቁሟል

newsየፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ምክትል ዋና ቃዲ (ምክትል ፕሬዚዳንት) ሼክ አማን ሽፋው ዓለሙ ጉቦ በመቀበል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ 50,000 ብር ጉቦ ጠይቀው 10,000 ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

እንደ ኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ምክትል ዋና ቃዲው፣ በሥራ ኃላፊነታቸውና ግዴታቸው ማድረግ የሚገባቸውን አላደረጉም፡፡ በመሆኑም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት አስበው የግል ተበዳይ ናቸው የተባሉት ወ/ሮ ሮዛ መሐመድ ጁሃር፣ የጋብቻ ሰነዳቸው የሸሪዓ ስለመሆኑ ተመስክሮ እንዲሰጣቸው ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ማመልከታቸው በክሱ ተጠቅሷል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ማስረጃውን ሊሰጣቸው ባለመቻሉ ግለሰቧ አቤቱታቸውን ለጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቅረባቸውም በክሱ ተገልጿል፡፡ ምክትል ዋና ቃዲው ጉዳዩን ለመጨረስ 50,000 ብር ጠይቀው፣ ከግለሰቧ ጋር ከተስማሙ በኋላ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት፣ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ልዩ ቦታው አስኮ ነዳጅ ማደያ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ፣ ከግለሰቧ 10,000 ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ክሱ በዝርዝር ያስረዳል፡፡

ተጠርጣሪው ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው የዋስትና መብታቸው ታልፎ፣ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩና ሐምሌ 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

በክሱ ላይ የተጠቀሰው የወንጀል ሕግ ቁጥር 408(2) ከሰባት እስከ 15 ዓመታት በእስራት ሊያስቀጣ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

↧
↧

ለአዳማ ከተማ አዲስ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው

$
0
0

-የ20/80 እና የ40/60 ኮንደሚኒየም ቤቶች ግንባታ ይጀመራል

daየአዳማ ከተማ አስተዳደር አዲስ ማስተር ፕላን በማዘጋጀት ላይ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የአዳማ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ የሱፍ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት፣ መስተዳደሩ የከተማዋን ዕድገት ያገናዘበ አዲስ

ማስተር ፕላን በማዘጋጀት ላይ ነው፡፡ አዲሱ ማስተር ፕላን የመኖሪያ ክልሎች፣ የንግድ ማዕከላትና የኢንዱስትሪ ዞኖችን ያካተተ እንደሆነ የገለጹት አቶ አህመድ፣ የኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግና የዓለም ባንክ ደግሞ ለፕሮጀክቱ ወጪ የሚውል ገንዘብ እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የአዳማ ከተማና የአሜሪካ ዴንቨር ከተማ በተለያዩ ዘርፎች ለመተባበር የሚያስችላቸውን የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ለመፈራረም በሒደት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ አዲሱ የከተማ ማስተር ፕላን አዳማን ከዓለም አቀፍ ከተሞች ጋር የሚያስተካክላት እንደሆነ አክለው ገልጸዋል፡፡

የአዳማ ከተማ የኢትዮ፣ ጂቡቲ የባቡር መስመር ግንባታ ተከትሎ በ1908 ዓ.ም. የተቆረቆረች ነች፡፡ ‹‹የስምጥ ሸለቆዋ እንቁ›› የሚል መጠሪያ የወጣላት አዳማ ከተማ 133.6 ካሬ ኪሎ ሜትር ሥፋት ሲኖራት፣ የሕዝብ ብዛቷ 300,000 ያህል ይገመታል፡፡

የከተማዋ መስተዳደር አዳዲስ የአስፓልትና የኮብልስቶን መንገዶች በመገንባት ላይ እንደሚገኝ፣ በከተማዋ ዙሪያ የአሥር ኪሎ ሜትር የቀለበት መንገድ በመገንባት ላይ እንዳለ፣ የጎርፍ መከላከል ሥራዎችና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ግንባታ እየተካሄደ እንደሆነ፣ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ እንደሆነ፣ የአዳማ ከተማ የቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት ተወካይ አቶ ለሜሳ ቱራ ለሪፖርተር የገለጹ ሲሆን፣ ጽሕፈት ቤቱ የ20/80 እና የ40/60 የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ መስተዳደር የጀመረውን የ20/80 እና የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እንደ ሞዴል በመውሰድ በአዳማ፣ በሻሸመኔና በሌሎች 38 የኦሮሚያ ከተሞች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ በጨፌ ኦሮሚያ (የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት) መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በአዳማ ከተማ የቦታ መረጣ ሥራ እንደተካሄደ እንደሆነ የገለጹት አቶ ለሜሳ፣ ምን ያህል ቤቶች እንደሚገነቡና የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጪ ጥናት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡ የቤቶቹ ግንባታ በ2007 ዓ.ም. እንደሚጀመር አክለው ገልጸዋል፡፡ ቀደም ሲል መስተዳደሩ 2,769 ኮንደሚኒየም ቤቶች መገንባቱንና በ2004 ዓ.ም. ባካሄደው የቤት ፈላጊዎች ምዝገባ 16,000 ነዋሪዎች እንደተመዘገቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

- See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=1296#sthash.oTXKS2hD.dpuf

↧

የአፍሪካ ነገር – የኢትዮጵያ ነገር

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም

የካቲት 2006

Prof. Mesfin

መስፍን ወልደ ማርያም

በሃያኛው ምዕተ-ዓመት ላይ የታወቀ የፈረንሳይ ፈላስፋ ነበረ፤ እሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ከእሱ ጋር በዩኒቨርሲቲ ሁለት አፍሪካውያን አብረውት ይማሩ እንደነበሩ ይናገራል፤ እነዚህ አፍሪካውያን የፈረንሳይኛ ቋንቋን ልክ አንደፈረንሳዮች እየተናገሩ፣ እንደፈረንሳዮች እያሰቡ ከፈረንሳዮቹ ተማሪዎች ጋር እኩል በትምህርት እየጎለበቱ ነበር፤ በኋላ እነዚህ አፍሪካውያን ወደአገራቸው ተመልሰው ሥልጣን ላይ ሲወጡ ሰፊ አገራቸው ለሁለቱ የተማሩ አፍሪካውያን የማይበቃ ሆነባቸው፤ ስለዚህም አንደኛው የአገር መሪ ሆነና ሌላውን ገደለው፤ የፈረንሳዩ ፈላስፋን ያሳዘነው ትዝብት ነው።

በአለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ በአፍሪካ የታየው የሥልጣን ሽኩቻ ለብዙ የአፍሪካ አገሮች የእድገት ማነቆ ሆኖ ቆየ፤ ከአውሮፓውያን ቄሣራዊ ኃይሎች ቅኝ አገዛዝ ነጻ ሲወጡ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸው አገሮች ዛሬ ቆመው ቀርተዋል፤ በሰሜን አፍሪካ አልጂርያና ቱኒስያ እንደፈረንሳይ የሚቆጠሩ ናቸው ይባል ነበር፤ እነዚህ ትልልቅ አገሮች ለሁለት ለሁለት ሰዎች የማይበቁ ሆነው የመከራ አገሮች ሆነዋል፤ ከፈረንሳይ ጋር በአደረጉት መራራ ትግል ሕዝቦቹ የከፈሉትን መስዋእትነትና ትግላቸው አሳድሮባቸው የነበረውን የላቀ ተስፋ መሪዎቹ ዋጋ አልሰጡትም፤ (ተመስገን ደሳለኝ በፋክት ቁጥር 33 ‹‹የሕወሓት ሰማዕታት አጭር ማስታወሻ፣) በዚህም ምክንያት እነሱ ለአንድ ወንበር ሲፎካከሩና ተወዳዳሪዎቻቸውን አስረውም ሆነ ገድለው ወንበሩን ለብቻቸው ሲይዙት ቆይተዋል።

በአንድ በኩል ከወንበሩ በሚመነጨው ኃይልና ሀብት መከታን የሚያገኙ መስሏቸው በነበራቸው ተስፋ፣ በሌላ በኩል በምዕራባውያን ኃይሎች ላይ ተማምነው ሕዝባቸውን በመናቃቸው በአረብ አገሮች መሪዎች ላይ በቅርቡ በተከሰተው ወረርሺኝ ብዙዎች ከወንበራቸው ተደፍተዋል፤ የሁሉም አወዳደቅ የከፋ ውርደትን የለበሰ ቢሆንም አንደጋዳፊ ያለ አልነበረም፤ እኛስ ብንሆን በዓለም በሙሉ የተከበሩትን ንጉሠ ነገሥት እንዴት አዋርድናቸው! ያወረዷቸውስ ሰዎች በተራቸው እንዴት ተዋረዱ! ያዋረዱ ሁሉ ይዋረዳሉ፤ ሕዝብን ያዋረዱ ይዋረዳሉ፤ አገርን ያዋረዱ ይዋረዳሉ፤ የሰው ልጅን ያወረዱ ሁሉ ይዋረዳሉ።

ለጭቆናና ለክፋት ሰብአዊ መብቶችን እንደልብ እየጣሱ በጉልበተኛነት መታወቅ የራስን ታሪክ ራስን ዋቢ አድርጎ መጻፍ ነው፤ ያለፉት ባንዶች ተመችቷቸው ስለነበረ ወደፊትም የባንዶች ዕጣ-ፋንታ እንደበፊቱ ይሆናል ማለት ልበ-ደንዳናነት ብቻ ሳይሆን፣ በጥላሸት የጨለመ አእምሮ ብቻ ሳይሆን፣ በዛር ፈረስ ላይ ወጥቶ ወደገደል መጋለብ ነው፤ ከአሁን ወዲያ አገዛዙ ሲከሽፍ ሕዝቡ አብሮ ከከሸፈ በአገዛዙ ማመካኘት አይጠቅምም፤ ሕዝብ ኃላፊነትን መውሰድ አለበት፤ አገር በጥቂት ሰዎች አይገነባም፤ እያንዳንዱ ሰው የድርሻውን ኃላፊነት መቀበል አለበት፤ የእየአንዳንዱ ሰው አስተዋጽኦ አሰፈላጊ ነው።

የእያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት ከየት የመጣ ነው? አንደኛ አያት ቅም-አያቶቻችን ይችን አገር ለመገንባትና በነጻነት ለመጠበቅ በሕይወታቸው ሳይቀር የከፈሉት ከባድ መስዋዕት እየቆረቆረን ኃላፊነትን ይጭንብናል፤ በሞታቸው ያስተላለፉልንን ኩራትና ክብር ብናጣ የምናዋርደው እነሱን ብቻ ሳይሆን ራሳችንንም ነው፤ የኃላፊነታችን አንዱ ምንጭ ይህ ነው።

ሁለተኛው የኃላፊነታችን ምንጭ ልጆቻችን ወይም የሚቀጥለው ትውልድ ነው፤ እኛ ከአባቶቻችን የወረስነውን ኩራትና ክብር መጠበቅ አቅቶን ለልጆቻችን ውርደትን እንዳናወርስ ኃላፊነት አለብን፤ ሲሆን የወረስነውን ኩራትና ክብር አዳብረንና አጠንክረን ማቆየትና ለልጆቻችን ማውረስ፣ ቢያንስ ግን የተረከብነውን ማስረከብ ግዴታችን ይሆናል፤ አለዚያ መክሸፍ ይሆናል፤ ኢትዮጵያዊነት ማንነት አይደለም ከተባለ፣ ከኋላችን በሕይወት መስዋእትነት የተረከብነውን ክደናል፤ ከፊታችንም ለልጆቻችን የምናስረክበው የጋራ እሴት የለንም፤ በወጥመድ ውስጥ እንዳለች አይጥ መንፈራፈር ብቻ ነው።

በአገርና በአገዛዝ ሥርዓት መሀከል ያለውን ገደል ማየት የማይችሉ ሰዎች የወጣቱን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ሲያላሉት፣ የወያኔ ካድሬዎች እየተቀባበሉ ሲያራግቡት ውርደታችን የለበስነውን ክብራችንን እየገለጠ ገብቶ ራቁታችንን እያስቀረን ነው፤ ኢትዮጵያም እንደኮንጎ፣ ኢትዮጵያም እንደኒጄር፣ ኢትዮጵያም እንደመሀከለኛው አፍሪካ፣ ኢትዮጵያም እንደሩዋንዳ፣ ኢትዮጵያም እንደሱዳን፣ ኢትዮጵያም እንደሶማልያ ወደትርምስ እየዘቀጠች መሆኑን ምስክሮች ሆነን እያየን ነው፤ ምዕራባውያን ኃይሎች ለውርደታችን እንጂ ለክብራችን እንደማይጠቅሙ በኢራቅ፣በአፍጋኒሰታን፣ በፓኪስታን ለሆነው ሁሉ ምስክሮች ሆነን እያየን ነው።

ከሃምሳ ዓመታት ያህል በፊት በማናቸውም ነገር የአፍሪካ መሪዎች ሆነን የጀመርነው ሰዎች ዛሬ በዚህ ትልቅ የአፍሪካ አህጉር ኔልሰን ማንዴላ ከሚባል ትልቅ ሰው በቀር ስሙ በዓለም የሚጠራ አለመኖሩ የውርደታችንን ጥልቀት ያመለክታል፤ በኔልሰን ማንዴላ ትልቅነት ላይ ብቻ ሳይሆን በኔልሰን ማንዴላ ህልውና ላይም ኢትዮጵያ ማኅተምዋን በጉታ ዲንቃ ሃይማኖት አማካይነት ማሳረፍዋን አልዘመርንበትም፤ በአብዲሳ አጋ የአውሮፓ አርበኝነት አልዘመርንበትም፤ በዘርዓይ ደረስ የአውሮፓ አርበኝነት አልዘመርንበትም፤ በአበበ አረጋይ አርበኝነት አልዘመርንበትም፤ በበላይ ዘለቀ ስቅለት እንጂ በአርበኝነቱ አልዘመርንለትም፤ ኢትዮጵያን የጠበቋትን ልጆቿን፣ ኢትዮጵያን ያስከበሯትን ልጆቿን ታሪክ ረግጦና ችላ ብሎ ለባንዶችና ለባንዶች ልጆች ውዳሴ ከርስ የሚዘምር ትውልድ ውርደትን ይለብሳል፤ በኀልዮም ሆነ በነቢብ፣ ወይም በገቢር፣ አውቆም ይሆን ሳያውቅ አገሩንና ወገኑን ያዋረደን ማንም አያከብረውም፤ በሆዳሞች የተገነባውና የሚገነባው ሁሉ ከርሰ-መቃብር ውስጥ ይፈራርሳል።

የዛሬ ሁለት መቶ ዓመታት ግድም አንድ የአንግሊዝ ፈላስፋ ሕዝብን ስለማዶልዶም የሚከተለውን ብሎ ነበር፤ ዛሬ ለኛ የሚናገር ይመስላል፡–

ለጥሩ ዓላማም ቢሆን እንደፈለገ የሚያገላብጣቸው የተገሩ ለዘብተኛ መሣሪያዎች እንዲሆኑለት የራሱን ሕዝብ የሚያቀጭጭ ሀገረ-መንግሥት በትንንሽ ሰዎች ምንም ትልቅ ነገር ማከናወን አንደማይቻል ይገነዘባል፤ መሣሪያው በቀላሉ እንዲሠራለት ሁሉንም ነገር መስዋእት በማድረግ መሣሪያውን ፍጹም አድርጎ ሲስል  ያወደመው የሕይወት ኃይል በመጨረሻ ላይ  ለምንም ነገር አይጠቅመውም፡፡  

በእንግሊዝኛው  … a state which dwarfs its men, in order that they may be more docile instruments in its hands even for beneficial purposes, will find that with small men no great thing can really be accomplished; and the perfection of the machinery to which it has sacrificed everything will in the end avail it nothing, for want of the vital power which, in order that the machine might work more smoothly, it has preferred to banish.

በሃያ አንደኛው ምዕተ ዓመትም ኢትዮጵያ በረጅም ታሪክዋ ሲከሽፍባት የቆየውን ሥልጣንን የመግራት ብቃት ማግኘት አቅቷት ትናንት ከተፈጠሩ አገሮች ተርታ ተሰልፋ ትገኛለች፤ ይህ ውርደት የማይሰማው ባለሥልጣን ነኝ-ባይ ከነሎሌዎቹ በውርደት ባሕር እየሰመጠ ነው፤ የሚሰምጠው ሎሌዎቹን ብቻ ይዞ አይደለም።

↧

የኢትዮጵያው ጓንታናሞ ቤይ ‹‹ ማዕከላዊ ››

$
0
0

ዳዊት ሰለሞን

maeklawi prison

ማዕከላዊ

አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለፉት አመታት ሁሉ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያስቆጣ ባለ 70 ገጽ ሪፖርት ከሁለት ሳምንታት በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ የተቋሙን ሪፖርት ከሌላው ጊዜ የተለየ የሚያደርገው በአንድ ርዕሰ ጉዳይ በአንድ ተቋም  በማጠንጠኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የወንጀል ምርመራ ማዕከሎች መካከል በአዲስ አበባ ዕምብርት በሚገኘው ማዕከላዊ ተጠርጣሪዎች ግርፋት፣ማሰቃየትና ድብደባ እንደሚፈፀምባቸው ሪፖርቱ አትቷል፡፡

አሜሪካ በሁለቱ የኒውዮርክ መንትያ ህንጻዎቿ ላይ በአልቃይዳ የተቀነባበረ ጥቃት ከተሰነዘረባት በኋላ ‹‹ሽብርተኛ›› በማለት የሰየመችውን ቡድን አባላት ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በጆርጅ ቡሽ ፊት አውራሪነት የሽብር ቡድኑ ዋነኛ መጠለያ ያለቻችትን አፍጋኒስታንን ወረረች፡፡ በዘመቻው በቁጥጥር ስር የዋሉ የአልቃይዳ አባላትና ተጠርጣሪዎች በጄኔቭ ስምምነት መሠረት በህግ የመዳኘት መብት እንዳያገኙ ለማድረግ የቡሽ አስተዳደር ከግዛቱ ውጪ በኩባ ድንበር የሚገኘውን ጓንታናሞ ቤይን ከዛሬ አስር አመታት በፊት ከጦር ካምፕነት ወደ ማሰቃያ ማዕከልነት አሸጋገረው፡፡

‹‹በሽብርተኝነት›› ተጠርጥረው ወደ ጓንታናሞ ቤይ እንዲገቡ የተደረጉ ተጠርጣሪዎች የዜግነት ስብጥር የሚበዛበት ቢሆንም አንዳንድ መረጃዎች የሚበዙት ተጠርጣሪዎች አፍጋናዊያን፣ ኢራቃዊያን፣ የመናዊያን፣ ሊቢያዊያንና ግብጻዊያን ስለመሆናቸው ይጠቁማሉ፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል 99 ከመቶ ያህሉም የሙስሊም እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡

አሜሪካ በህገ መንግስቷ ተጠርጣሪዎች ዋስትና፣ ጠበቃ፣ ጎብኚና ነጻ የፍትህ ስርዓት  እንዲያገኙ ለማድረግ ቃል የገባች ቢሆንም በጓንታናሞ ቤይ የተጣሉ ተጠርጣሪዎች ለረዥም አመታት ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዳይታይ፣ ጎብኚዎች እንዳያገኙ፣ ግርፋትና ስነ ልቦናዊ የሆነ ቶርቸር እንዲደርስባቸው በማድረግ ከህገ መንግስቷ የተጣረሰ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ስትፈጽምባቸው ቆይታለች፡፡

እስረኞቹን አጋቾቻቸው እጅና እግሮቻቸውን ለ24 ሰዓታት በሰንሰለት በማሰር ሲያሰቃዩአቸው ቆይተዋል፣ በረመዳን የጾም ወቅት እስረኞቹ የሃይማኖታቸውን ትዕዛዝ ለመፈጸም ከምግብ ተከልክለው ወሩን ለማሳለፍ ቢዘጋጁም የማጎሪያው ሃላፊዎች ሀይልን በመጠቀም በቀን ለሁለት ጊዜያት ምግብ እንዲመገቡ በማድረግ ጥቃት ፈጽመውባቸዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት (የቡሽ አስተዳደር) ይህንን ግፍ በጓንታናሞ ቤይ ሲፈጽም የከረመው በገዛ ዜጎቹ ላይ ባይሆንም በሰብአዊ ፍጥረት ላይ የሚደርስን በደል የአገሪቱ ህዝብ በራሱ እንደደረሰ በመቁጠር የቡሽን የበቀል እርምጃ በተለያዩ መድረኮች ሲቃወም ተስተውሏል፡፡

ጥቁር አሜሪካዊው ባራክ ሁሴን ኦባማ ለፕሬዝዳንትነት ያደርጓቸው በነበሩ ቅስቀሳዎች ‹‹ጓንታናሞን›› ከተመረጡ እንደሚዘጉ መግለጻቸውም በአስገራሚ ሁኔታ የአገራቸውን ህዝብ ድጋፍ እንዲያገኙ ረድቷቸዋል፡፡ ኦባማ የማሰቃያ ማዕከሉን ለመዝጋት ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ እንቅስቃሴ ቢጀምሩም ከተፎካካሪዎቻቸው ጠንከር ያለ ተቃውሞ ማስተናገዳቸው አልቀረም፡፡ አሁን የኦባማ ምኞት እውን ሆኖ ጓንታናሞ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ተዘግቷል፡፡ ፍትህ ተነፍገው የወታደሮች መጫወቻ ሆነው የቆዩ ተጠርጣሪዎችም በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች እንዲቀርቡ ተደርገዋል፣የሚበዙትም ከአልቃይዳ ጋር ምንም አይነት የሚያገናኛቸው መስመር እንደሌለ በመረጋገጡ ከቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ተደርገዋል፡፡

 

      በኢትዮጵያው ጓንታናሞ ቤይስ?

የዛሬው የአፍሪካ ህብረት ህንጻ የቆመበት መሬት በዘመነ ደርግ ላቅ ያለ የስቃይ ምድር ነበር፡፡ ከርቸሌ ብዙ ሺህ ወጣት ኢትዮጵያዊያንን በልታለች፣ በወታደራዊው መንግስት ላይ ተቃውሞን ያሰሙ ዜጎች በከርቸሌ ፊደል የማይተርከውን ስቃይ አስተናግደዋል፡፡ በኢትዮጵያውያኑ የለቅሶና የደም መሬት ላይ የአፍሪካ መሪዎች አመታዊ ስብሰባቸውን ለማድረግ ሲመጡ በቻይና እርዳታ የተሰራላቸውን ህንጻ ውበት እንጂ በከርቸሌ የፈሰሰው ደም፣ የባከነው አእምሮና የተፈፀመው ግፍ አይታሰባቸውም፡፡ በዘመነ ደርግ ለከርቸሌ እስረኞችን ይመግብ የነበረው የምርመራ ማእከል ደግሞ ማዕከላዊ ነው፡፡

ማዕከላዊን በመገንባት የተቃዋሚዎቻቸውን በአደባባይ ለመገንፈል ያሰፈሰፈ ቁጣ መሸበብ የጀመሩት አጼ ኃይለስላሴ ናቸው፡፡ ንጉሱ ተማሪዎችን፣ አመጽ ያማራቸውን ወታደሮች፣ ስልጣኔ የሸተታቸውን ሰራተኞችና የባላባት ጭሰኛ መሆን የመረራቸውን ገበሬዎች በምስጢር ፖሊሶቻቸው አማካኝነት እያደኑ ማስፈራሪያና ግርፊያ ይፈጽሙባቸው እንደነበር ለዚህ ፊቸር ያናገርኳቸው ሰዎች እማኝነታቸውን ሰጥተውኛል፡፡ ደርግ የንጉሱን ወንበር በመገልበጥ ስጣኑን እንደተረከበ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማፈን ከሁሉም የማጎሪያ ካምፖች በተሻለ ማዕከላዊን ስለመጠቀሙ በዛ ያሉ ምስክሮችን መቁጠር ይቻላል፡፡

የኢህአፓ ወጣቶች በማዕከላዊ የሚያውቁትን ምስጢር እንዲያወጡ፣ያልተያዙ ጓደኞቻቸውን እንዲጠቁሙ በሚል በወታደሮች ተደብድበዋል፣ ሴቶቹ ተደፍረዋል፣ በኤሌከትሪክ ሽቦ ተጠብሰዋል፣ ጥፍሮቻቸው በጉጠት እንዲነቀሉ ተደርገዋል፣ ሰውነታቸው ተገልብጦ ውስጥ እግራቸው በበሬ ቆለጥ ተገርፏል፡፡ ድብደባውን መቋቋም ተስኗቸው ይህችን ጨካኝ አለም የተሰናበቱ የት የሌለ ናቸው በማዕከላዊ፡፡የወቅቱ የምርመራ ሰራተኞች ብቃት የሚለካው እየገረፉና እያሰቃዩ በሚያገኙት መረጃ እንጂ መረጃውን ለማግኘት በሚጠቀሙት ፖሊሳዊ የምርመራ ጥበብ አልነበረም፡፡ይህ ጥበብም እነሆ እስካሁን ድረስ እየተወራረሰ ይገኛል፡፡

በ1983 የሰርዓት ለውጥ ተደርጎ ራሱን ነጻ አውጪ በማድረግ የሚቆጥረው ኢህአዴግ ስልጣነ መንግስቱን ሲቆናጠጥ ማዕከላዊ ዑደቱን እንዲያቋርጥ አለመደረጉን በየጊዜው ከማዕከላዊ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡

በ1987 ዓ.ም የፀደቀው ህገ መንግስት ተጠርጣሪዎች ህገ ወጥ ለሆነ አያያዝ እንደማይደረጉ፣ ኢሰብአዊ የሆነ ጥቃት እንደማይደርስባቸው፣ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ፣ በምርመራ ወቅት የሰጡትን የእምነት ክህደት ቃል በፍርድ ቤት መለወጥ እንደሚችሉ ቢደነግግም በማዕከላዊ እነዚህ ህገ መንግስታዊ መብቶች ሆን ተብለው እንደሚጣሱ በምርመራ ጣብያው ዘግናኝና የሰቆቃ ጊዜያትን ያሳለፉ ሰዎች ይናገራሉ፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች ላወጣው ሪፖርት እማኝ እንደሆኑ የተነገረላቸው 35 በማዕከላዊ የነበሩ እስረኞችም የተናገሩት ለወራት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቆየታቸውን፣ በጨለማ ቤት መክረማቸውን፣ ከጠያቂዎች ጋር እንዳይገናኙ መደረጋቸውንና በምርመራ ወቅት ግርፋት፣ ማሰቃየትና ማስፈራራቶች ይፈፀምባቸው እንደነበር ነው፡፡

ከሪፖርቱ ውጪ ጀሚል አክበር፣ ስዬ አብርሃ፣ ደበበ እሸቱና ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል በጻፏቸው መጻህፍት በማዕከላዊ የምርመራ ማእከል ቆይታቸው ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ስቃዮችን ማለፋቸውንና መስማታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የመጻሕፍቱ መልእክት አንድና አንድ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመንግስታት ለውጥ ቢደረግም ማዕከላዊ ግን የየስርዓቱን ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞችና ተቺዎች ማሰቃ በመሆኑ ቀጥሏል፡፡

      ጣውላ፣ ጨለማ ቤትና ሸራተን በማዕከላዊ

በማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል እንዲገቡ የተፈረደባቸው ዜጎች ቆይታ ለሚያደርጉባቸው ክፍሎች ተገቢ ነው ያሏቸውን ስያሜዎች አውጥተውላቸዋል፡፡ ጨለማ ቤት እጅግ ቀዝቃዛና ዘና ብሎ ለመተኛት የማያወላዳ የተፈጥሮ አልያም የሰው ሰራሽ ብርሃን አልቦ ነው፡፡ ወደዚህ ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቀንና ሌሊት በጨለማ የሚዋጡ በመሆናቸው ሰዓት፣ ቀንና ምሽትን ለመለየት ይቸገራሉ፡፡ የቅንጅቱ ሊቀመንበር የነበሩት ኃይሉ ሻውል በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ ለ28 ቀናት ጨለማ ቤት እንዲቆዩ መደረጋቸውን በመጨረሻም መርማሪዎቹ ‹‹መብራት የሚሰራልን አጥተን ነው ይቅርታ›› በማለት አምፑል በማስገባት እንዳበሩላቸው ገልጸዋል፡፡ እንደ ሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሪፖርት ከሆነ በዚህ ጨለማ ክፍል የቆዩ ሰዎች ጊዜያቸውን በማጠናቀቅ ወደ ውጪ ሲወጡ ለከፍተኛ የአይን ህመም ይዳረጋሉ፡፡

ጣውላ ቤት የተሻለ ስፋትና አጋር እስረኛ የሚገኝበት ከመሆኑ ባለፈ በጨለማ የተዋጠ ነው፡፡ ቤቱ ከጣውላ የተሰራ በመሆኑም ድምጽ ከየትኛው ክፍል እንደሚመጣ አይታወቅም፡፡ ይህም እስረኞቹ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲያንጎረጉሩ፣ የመሰላቸውን እንዲናገሩ ይረዳቸዋል፡፡ አንደኛው እስረኛ ለመጸዳዳት ከክፍሉ ወጣ በሚልበት አጋጣሚም ከሌላው እስረኛ ጋር የሚገናኝበት፣ የሚተያይበት በመሆኑም ለታሳሪዎቹ ህይወት እንድትሸታቸው ያደርጋል፡፡ ሸራተን በማዕከላዊ የቅንጦት ክፍል ነው፡፡ የክፍሉ ስፋት በመጠኑ የሚያወላዳ ከመሆኑም በላይ የመብራት ባለቤት ነው፡፡በዛ ያሉ እስረኞች የሚገኙበት በመሆኑም በማዕከላዊ እንደ ቅንጦት ተቆጥሮ ሸራተን ለመሰኘት በቅቷል፡፡ ሸራተን የገቡ እስረኞች በአብዛኛው የምርመራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ በመሆናቸው በጨለማ ቤትና በጣውላ ቤት ያሳለፉትን መከራ እያነሱና እየጣሉ ከሌሎች ታሳሪዎች ጋር ፍርድ ቤት የሚያሳልፍባቸውን ውሳኔ ይጠባበቃሉ፡፡

 

           የመንግስት ምላሽና ሪፖርቶች

ሂዩማን ራይትስ ዎቹ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ ሲያጋልጥ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ የመንግስት ኃላፊዎችም ሪፖርቱን ከመንግስት ተቃዋሚዎች የተሰበሰበና እውነታውን የማያሳይ በማለት ከማጣጣል ተቆጥበው አያውቁም፡፡

የአሜሪካ መንግስት /ስቴት ዲፓርትመንት/ በሚያወጣቸው ሪፖርቶች የእስረኞች አያያዝ እንዳሳሰበው የገለጸባቸው አጋጣሚዎች በዛ ያሉ ናቸው፡፡ በ2007 ኤፕሪል በዊኪሊክስ አማካኝነት የወጣ መረጃም በኢትዮጵያ የሚገኙ እስረኞችን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉት የፕሪዝን ፌሎው ሺፕ መስራች ፓስታር ዳንኤል ለአሜሪካ ኤምባሲ ሰዎች መንግስት በእስረኞች ላይ ግርፋት፣ ማስፈራራትና ማሰቃየት እንደሚፈጽም መናገራቸውን አትቶ ነበር፡፡ በቅርቡ ሂዩማን ራይትስ ዎች  ላወጣው ሪፖርት የመንግስት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ሽፈራው በጽሁፍ እንዲሁም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል  ለኤኤፍፒ በሰጡት ምላሽ ክሱን አጣጥለውታል፡፡

በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ቆይታ አድርገው የነበሩት ሁለቱ ስዊዲናዊያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺብዬና ዮሃን ፒርሰን ‹‹ፖሊስ ሁሉም ነገር የሚያልቀው በፍርድ ቤት እንደሆነ ይናገራል፣ ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚሆነው በምርመራ ወቅት ነው፡፡ ፖሊስ በሀይል ተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበትን ጉዳይ መፈፀማቸውን እንዲያምኑ ያደርጋል›› ይላሉ፡፡

በሪፖርቱ ዙሪያ ለኤ.ኤፍ.ፒ በእስር ላይ ስለምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የተናገሩት ወላጅ አባቷና ጠበቃዋ አቶ አለሙ ጌቤቦ ለሦስት ወራት ያህል ልጃቸውን በማዕከላዊ ማየት እንዳልቻሉ በመጥቀስ በእነዚያ 90 ቀናት ውስጥ ከቤተሰብና ከጠበቃዋ ለይተው ምን ሲፈጽሙባት እንደቆዩ እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ ርዕዮትን ከሦስት ወራት በኋላ እንዲመለከቷት ሲፈቀድላቸው ተጎሳቁላ ማግኘታቸውንና ለዘጠኝ ቀናት ያህል ምግብ ሳትመገብ መቆየቷን መረዳታቸውን መስክረዋል፡፡

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ወደ ማዕከላዊ የገቡ ሌሎች ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ከርዕዮት ጋር የሚመሳሰል ታሪክ እንዳላቸው የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ይናገራሉ፡፡

ፓስተር ዳንኤል በእስር ቤቶች ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈጽሙ መርማሪዎች መኖራቸውን መንግስት ከደረሰበት በኋላ የሚበዙትን ከስራ እንዳባረራቸው ለአሜሪካው ዲፕሎማት መናገራቸውን ዊኪሊክስ ቢዘግብም የመረጃ መረቡ ባወጣው ሪፖርት ፓስተሩ ነገሩን ለማድበስበስ ያህል እንደተናገሩት እንደቆጠረባቸው አትቷል፡፡

በምርመራ ላይ የቆዩ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት በሚቀርቡባቸው አጋጣሚዎች በምርመራ ወቅት ድብደባ፣ ማስፈራራትና ማሰቃየት እንደደረሰባቸው የተናገሩባቸው አጋጣሚዎችም በዛ ይላሉ፡፡  ዳኞች እንዲህ አይነት የመብት ጥሰት አቤቱታ ሲቀርብላቸው ፖሊሶች ላይ ጫን ያለ እርምጃ እንዲወሰድ አለማድረጋቸው የምርመራ ውስጥ ስቃዩ እንዲቀጥል የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

 

            የእኛ ኦባማ የት ነው?

የኢትዮጵያ መንግስት ኃላፊዎች የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅቶች አልያም የአለም ባንክ ለሚያወጧቸው ሪፖርቶች የሚሰጧቸው ምላሾች አንድ ጫፍ የረገጡ ናቸው፡፡ የሪፖርቶቹን መውጣት ተከትሎ ጉዳዩን ለማጣራት ገለልተኛ ቡድን እንዲዘጋጅ የተደረገበት ጊዜ የለም፡፡ ጆርጅ ቡሽም እንዲህ ነበሩ፡፡ በጓንታናሞ ለሚፈጸም የሰብአዊ መብት ጥሰት ጆሮ አልነበራቸውም፡፡ ወታደሮቻቸው ሴት እስረኞችን እንደሚደፍሩ፣ ታሳሪዎችን በረመዳን የጾም ወቅት በኃይል እንዲመገቡ ማድረጋቸው፣ ተጠርጣሪዎች ለወራት ፍትህ ሳያገኙ መቆየታቸው ሲነገራቸው ለመስማት አልፈቀዱም፡፡ በፕሬዝዳንቱ እምነት እየተሰቃዩ የሚገኙት ሰዎች ሳይሆኑ ‹‹ሽብርተኞች›› ናቸው፡፡

ኦባማ ግን እንደ ቡሽ በጭፍን ጥላቻ የታወሩ አልነበሩም፡፡ ጓንታናሞ የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚፈፀምበትና አሜሪካ ቆሜለታለሁ ለምትለው ዲሞክራሲ ተቃራኒ መሆኑን በመረዳት ጓንታናሞን ላይከፍቱት ቆለፉት፡፡

የእኛው ማዕከላዊ በእኛው ዜጎች እኛው ላይ ኢ- ህገ መንግስታዊና ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈፀምበት ማዕከል ነው፡፡ በጓንታናሞ አሜሪካዊያኑ የገረፉት፣ ያሰቀዩት አፍጋኑን፣ ግብጻዊውን፣ ኢራቃዊውን፣ አፍሪካዊውን ነው፡፡ በማዕከላዊ መሰቃየቱንና ህገ መንግስታዊ መብቱ እንደተጣሰበት የሚናገረው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ኦባማ ጓንታናሞን ስለ አሜሪካዊያን አልዘጉትም፡፡ ስለ ፍትህ እንጂ፡፡ የእኛ ኦባማ ለጊዜው እዚህ ነኝ ባይለንም የመጣ ቀን ግን ማዕከላዊን ስለእኛ ይዘጋዋል፡፡

↧

አቶ ግርማ ሰይፉ ለአምባሳደር ጥሩነህ ዜና ደብዳቤ ጻፉ

$
0
0
(ግርማ ሰይፉ)

(ግርማ ሰይፉ)

(ዘ-ሐበሻ) በፓርላማው ውስጥ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ በጥርጣሪ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሰብዓዊ መብት አያያዝ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ደብዳቤ ጻፉ። ደብዳቤው እንደወረደ ይኸው፦

ሐምሌ 11 ቀን 2006

ለክቡር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡ በጥርጣሪ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ይመለከታል

ክቡር ኮሚሽነር ከሐምሌ አንድ ቀን ጀምሮ በ “ወንጀል” ተጠርጥረዋል በሚል የፓርቲያችን አንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ (አንድነት) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም አቶ አብርሃ ደስታ ከአረና ፓርቲ እና አቶ የሺዋስ አሰፋ ከሰማያዊ ፓርቲ በፖሊስ ቁጥጥር ስር አንደሚገኙ ሰምተዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይሁን አንጂ ይህን ማመልከቻ እሰከምፅፍበት ሰዓት ድረስ ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ታሳሪዎች ከህግ አማካሪ እና ቤተሰብ ጋር በህግ በተፈቀደው ስርዓት መሰረት ሊገናኙ አልቻሉም፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ማንም በሌለበት እና ከህግ አማካሪዎች ጋር ሳይገናኙ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸው ወደ ማእከላዊ ሄደዋል የሚል ዜና ቢወጣም አሁንም በትክክለኛ ሁኔታ ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው መረጃ የሚሰጥ አካል አላገኘንም፡፡ አንድ እድ ሰዎች ከምሸቱ በአንድ ሰዓት ፍርድ ቤት ቀርበዋል የሚሉም አሉ፡፡
በዚህ የተነሳም ተሳሪዎች በድብቅ ፍርድ ቤት ቀርበዋል የሚባልበት ሁኔታ እና ይልቁንም ከህግ አማከሪያቸው እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ የተደረገበት ሁኔታ ለከፍተኛ ጥርጣሬ የሚያሳድር ነው፡፡ የእነዚህ ታሳሪዎች በጥርጣሬ የታያዙበትን ወንጅል እንዲያምኑ በኢትዮጵያ ህገ መንግሰትም ሆነ በህገ መንግሰት ተቀባይነት ባገኙ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት ምንም ዓይነት የሀይል እርምጃ እና ህገወጥ የሆነ ምርመራ ማካሄድ አይቻለም፡፡ ሰለሆነም ክቡር ኮሚሽነር በህግ መንግሰት የተፈቀደ ሰብዓዊ መብታቸውን የተነፈጉ እነዚህ ታሳሪዎች ያሉበትን ሁኔታ መስሪያ ቤቶ ክትትል እንዲያደርግ እና ለቤተሰቦች እንዲያሳውቅ አደራ ጭምር እየጠየቅሁ፡፡ የፖሊስ አካላትም ይህን ህገወጥ ክልከላቸውን እንዲያቆሙና ለህግ ተገዢ እንዲሆን እንዲያሳሰቡልን እንጠይቃለን፡፡ በአፋጣኝ ታሳሪዎችን ሁኔታ ማወቅ በታሳሪዎች ላይ ሊደርስ ከሚችል አካላዊም ሆነ ሌላ ማንኛውም ጉዳት ለመታደግ ስለሚረዳ፣ ሀገርም ከዚህ የምትጠቀመው አንድም ነገር ስለማይኖር ክቡርነትዎ አሰፈላጊውን ትኩረት ስጥተው ኃላፊነቶን እንደሚወጡ ተሰፋ አለኝ፡፡

ከማክበር ከሠላምታ ጋር
ግርማ ሠይፉ ማሩ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል

↧
↧

አዲስጉዳይ ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም ዕትሙ (አዲስ ጉዳይ)

$
0
0

ማስታወሻ
awe

ያለፉት ሁለት ዕትሞቻችን በማተሚያ ቤት ችግር ምክንያት ቀናችንን ሳንጠብቅ እሁድ በመውጣታችን አንባቢዎቻችንን ጊዜ እንደተሻማን ቢገባንም ችግሩ የጋራችነው ብለቹ ገበያ ላይ ስንውል ለገዛቹሁንና አስተያየት ለሰጣቹን እናመሰግናለን፡፡ አዲስጉዳይ ሁልጊዜም ታማኝነቷ ለአንባቢዎቿ ነው፡፡
በሐተታ አምዳችን አገራዊ ምርጫ በተቃረበ ቁጥር በአገራችን የፖለቲካ ትኩሳቱ እየጨመረ መሄዱ የተለመደ መሆኑን የቀደሙት ምርጫዎች ምስክሮች ናቸው፡፡ ሰሞኑን የታየው የሦስት ፓርቲ አመራሮች እስር ከእዚህ ጋር ተያያዥነት እንዳለው የተለያዩ ግለሰቦችና ምሁራኖች ይናገራሉ፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ 2007 ምርጫ ከመድረሱ በፊት የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸው ጨምሮ ጋዜጠኞችን በሽብተኛ ሕግ በማሰረ ምርጫውን ጠቅልሎ ለማሸነፍ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ጨምረው ይነጋራሉ፡፡ ጉዳዩን አስመልክተን የምርጫ ዕዳዎች ምርጫ ሲቃረብ፣ውጥረቶች ሲባባሱና እስራቶች ሲበራከቱ ሲል በሽፋን ገፃችን አስፍረናል፡፡
አንድ ሀገር ተተኪ ትውልድ እንዲፈጠርባት ከተፈለገ በቤተሰብ፣በአካባቢና በትምህርት ቤት ልጆች እንዲያነቡ የሚያበረታቱ ለትውልድ ተቆርቋሪ የሆኑ ዜጎች ያስፈልጉናል፡፡ምክንያቱም ያላነበበ ትውልድ ስለራሱ፣ሰለ ሀገሩ ታሪክ የሚናገረው ያጥረዋል፡፡ በተጨማሪም የማያነብ ኀብረተሰብ እንደማይጽፍ ፣የማይጽፍ ኀብረተሰብ ደግሞ እንደማያብና ማንበብና መጻፍ፣አንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን የሚዳስስ ጹሐፍ በዐብይ ጉዳይ ገጻችን “ኢትዮጵያ ታንብብ!! የዕውቀትና ያባህል ሕዳሴ በኢትዮጵያ” በሚል ሰፊ ትንታኔ የሚሰጥ ጹሑፍ አስተናግደናል፡፡
የሰሞኑን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እስርን አስመልክቶ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት ከሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፋራው እና ከሰማዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጋር በቃለምልልስ አምዳችን ተስተናግደዋል፡፡
80 ቀን ያስቆጠረው የስድስት ጦማሪያንና የሦስት ጋዜጠኞች እስር የፍርድ ቤት ውሎና የክሳቸውን ዝርዝር የሚያመልከት በሰሞነኛ አምድ ተስተናግዷል፡፡
በአንድ ጉዳይ ገጻችን እሁድ ከምሽቱ 3፡45 እልፈቱ የተሰማው ታዋቂው የወግ ፀሐፊ፣ደራሲ፣ ጋዜጠኛና መምህር የሆኑት መስፍን ሀ/ማርያም የሕይወት ታሪካቸውን የወግ ‘አባት በወግ’ በወግ ሲሸኝ ብለን አቅርበነዋል፡፡
አምደኞቻችን፡- ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ “ግራ እግርን ፍለጋ”፣ፊልፖስ ዓይናለም “የባልና ሚስት የእኩልነት መብት”፣ዳንኤል ክብረት “እንደገና እንጋባ”፣አሌክስ አብርሃም “ዘርፌ ቡቲክ!”፣በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር “የፓርላማው ኩንግ ፉ” እና ሰሎሞን ተሰማ ጂ. “መልሳይነት”! (ትናትና እና ዛሬ) የሚሉና ሌሎች በርካታ ጹሑፎች ተስተናግደዋል፡፡ —

 

Source-  Addis Guday
↧

ከድምፃችን ይሰማ የተላለፈ ጥሪ፦ “መንግስታዊው ‘ጥቁር ሽብር’የህዝብን የድል ችቦ አያጠፋውም!”

$
0
0

ሰኞ ሐምሌ 14/2006
demtschin yesema 2
ከቀናት በፊት በእለተ ጁምአ በታላቁ አንዋር መስጂድ በመንግስት ታጣቂዎች የተወሰደው ድንበር የለሽ ጭፍጨፋ የሙስሊሙ ህብረሰተብ ሰላማዊ ትግል በታሪኩ ሌላ መጠምዘዣ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት እንዲሆን የሚያስገድድ ነው፡፡ በዚህ በመንግስት የደህንነት ኃይሎችና በፖሊስ ሀላፊዎች ከቀናት በፊት ታቅዶ በተወሰደ እርምጃ ከ6 ሺ በላይ የመንግስት ቅጥረኛ ሲቪል ለባሾች እንደተሳተፉበት መገለጹ ይታወሳል፡፡ ቅጥረኞቹ የተከበረው የረመዳን ወር የጁምአ ሰላት ከመሰገዱ በፊት በመስጊዱ ውጫዊ ሰሜናዊ አቅጣጫ ግርግር በማስነሳትና ከፖሊሶች ጋር ከሁለቱም አቅጣጫ ድንጋይ በመወራወር የታለመውን ውጤት ለማምጣት ሞክረዋል፡፡ በዚህም በአካባቢው የነበሩትን ጨምሮ በሁሉም አቅጣጫ የነበሩና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የጁምአ ሰላታቸውን እንዳይፈጽሙ እክል ከመሆናቸውም በላይ እጅግ በርካታ ጾመኛ ሙስሊሞች ላይ እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል፡፡
በእለቱ በተካሄደው ጭፍጨፋ እንደተለመደው የመንግስት የጦር ሜዳ ስልት ሙስሊሙን ከሁሉም አቅጣጫ በቆረጣ ስልት ለሰላት በተቀመጠበት በመቁረጥ በነፍስ ወከፍ በያዙዋቸው ዱላዎችና የመሣሪያ ሰደፎች ርህራሄ አልባ በሆነ ሁኔታ ደብድበውታል፤ ጭፍጨፋ አድርሰውበታል፡፡ ጭፍጨፋው እድሜ፣ ጾታ፣ አስተሳሰብና፣ የአካል ሁኔታን ሳያገናዝብ ነበር የተወሰደው፡፡

ይህን ጭፍጨፋና ክስተቱ የደረሰበትን እለት ማሰብና በሌላ የታሪክ የቀን መቁጠሪያ ውስጥ መክተቱ አስፈላጊ ከመሆኑ አንጻር ለእለቱ ልዩ ስያሜ እንዲሰጠው ታምኖበታል፡፡ በዚህም መሰረት በእለቱ የተወሰደው መንግስታዊ ሽብር ‹‹ጥቁር ሽብር›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› በሰለጠነ ውይይት ከማያምን፣ ሰላማዊነትና ዲሲፒሊን ከማይገባው መንግስት የሚፈልቅ፣ ሰዎች ሳይሆኑ ዱላ ብቻ የሚናገርበት፣ ሐሳብ የሚንሸራሸርበት ሳይሆን ነውጥና ግፍ የሚሰፍንበት ሂደት ነው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› አይናቸውን የጋረደው ጥቁር ግርዶሽ የህዝብን እውነታ እንዳይረዱ ያደረጋቸውና ብቃት የሌላቸው ኃላፊዎች የሚወስኑት፣ ሰብዓዊነት በጭካኔ ጭለማ ውስጥ የሚሰጥምበት አስከፊ ክስተት ነው፡፡ አዎን! ለሰላማዊ ሕዝብና ጥያቄ ምላሹን ዱላ ያደረገ ኃይል፣ ባልታጠቀና በእጁ ድንጋይ ባልጨበጠ ጾመኛ ሕዝብ ላይ የጥይት ቃታ የሚስብ መንግስት ከርሞም የሚነዳው በ‹‹ጥቁር ሽብር›› ብቻ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግላችንም ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሂደት የሐምሌ 11/2006ን አሰቃቂ የመንግስት ጭፍጨፋ የታሪክ ካስማ በማድረግ እለቱ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ሲባል ከዚህ በኋላ ያሉ ክስተቶችም ‹‹ከጥቁር ሽብር በኋላ›› ወይም ‹‹ከጥቁር ሽብር በፊት›› እየተባሉ የሚዘገቡ ይሆናል፡፡
‹‹ጥቁር ሽብር›› ከአወሊያ መስጂድ የውድቅት ሰዓት ቀድሞም በአሳሳ በጁሙአ ሰላት ወቅት የተፈጸመ ነው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ጨለማ ተገን ተደርጎ በአወሊያ መስጂድ ከሁለት አመታት በፊት እንደተወሰደው፣ በጠራራ ጸሐይም በሲቪል ለባሽ ካድሬዎች አሻጥር ተከልሎ ልባቸው በተንኮል በጠቆረ ኃላፊዎች ትእዛዝ፣ በታወረ ህሊና እና አይን የሚወሰድ የአላዋቂነት ድርጊት ነው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› እውቀት አይጠይቅም፤ ዱላና እርግጫ ብቻ ነው የሚጠይቀው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ህገ መንግስቱን በድቅድቅ ጨለማም ሆነ በቀትር ጸሐይ ንዶ ያሻውን የሚገድል፣ የተቀረውንም የሚያቆስል ጸያፍ ድርጊት ነው፡፡ የእለቱ ስያሜ እስከመቼውም የሚዘልቅ ሲሆን ለወደፊቱም በዚህ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› አሻጥር ውስጥ የተሳተፉ ወንጀለኞች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን እናምናለን፡፡

ይህ በእውር ድንበር የተወሰደና ማንንም ሳይለይ ድንገት እንደደራሽ ጎርፍ የደረሰ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ብዙዎችን በአካል ያቆስል ይሆናል፤ በተቃራኒው ግን ዱላውና ግድያው የሰዎችን ሞራል ከፍ ያደርጋል፡፡ በመብት ነጠቃ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› ሰለባነት ማግስት የሞራል ከፍታና የአላማ ጽናት ጎልቶ ይታያል፡፡ ባለፉት ሶስት በሚጠጉ አመታት መሰል በርካታ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› ዘመቻዎች ተፈጽውብናል፡፡ በማግስቱ ግን ሁሌም ጎልተን እንታያለን፡፡ በተደበደብን ቁጥር፣ በደሉ ባረፈብን ቁጥር ቁስላችን ከመመርቀዝ ይልቅ እየጠገገ ጥንካሬያችንን ሲያጎላው አይተናል፡፡ ሁላችንም እንደምንረዳው ኃይል የተስፋ መሟጠጥ፣ የሐሳብና ዴሞክራሲያዊነት መራቆት አይነተኛ ምክንያት ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሲናኝ ኃይል ባህሪ ይሆናል፡፡ የእኛ ትግል ግን በሰላምና ዲሲፕሊን ውስጥ እያለፈ ድልን ይቀዳጃል!
መንግሥታዊው ‹‹ጥቁር ሽብር›› የህዝብን የድል ችቦ አያጠፋውም!
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

↧

በአንዋር መስጊድ በተፈጠረ ግጭት የታሰሩ ፍርድ ቤት ቀርበው ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

$
0
0

-አንድ ጋዜጠኛና አንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባልን ጨምሮ በርካቶች መታሰራቸው ተጠቁሟል ‹‹አብዛኛዎቹ ተለቀው ለግጭቱ ምክንያት የሆኑት ብቻ ታስረዋል›› ፖሊሶች

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ለጁምዓ (እለተ ዓርብ) ፀሎት መርካቶ በሚገኘው ታላቁ የአንዋር መስጊድ ተገኝተው የነበሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ባሰሙት ጠንከር ያለ ተቃውሞ ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት

demtschin yesema 2በመፈጠሩ፣ የተጎዱ የዕምነቱ ተከታዮች፣ የተለያዩ ግለሰቦችና የፖሊስ አባላት መኖራቸው ተገለጸ፡፡ በግጭቱ ምክንያት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የዕምነቱ ተከታዮችና በአካባቢው በግርግሩ ወቅት የነበሩ ሰዎች በፖሊስ ታስረው አንድ ቀን ካደሩ በኋላ፣ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀርበው ለተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ታውቋል፡፡

ሐምሌ 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በተለይ ሴት የዕምነቱ ተከታዮች ከድምፅ ያልዘለለ ተቃውሞ ማሰማታቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ የአሁኑ ከበድ ያለ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ግጭቱ በተፈጠረበት ወቅት በቦታው የጋዜጠኝነት ሥራዋን ስትሠራ ነበረች የተባለችው የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና ለግል ጉዳይዋ መርካቶ አካባቢ እንደነበረች በፓርቲው አመራሮች የተገለጸው የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ወ/ት ወይንሸት ሞላን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ወደተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች መወሰዳቸው መገለጹ ይታወሳል፡፡

በተለይ መሀል መርካቶ በሚገኘው አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ ኮልፌ ፖሊስ ማሠልጠኛ፣ ማዕከላዊና ኢትዮጵያ ትቅደም ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በርካታ ሰዎች ታስረው እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ተጠርጣሪዎች በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች በማቅረብ ለተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ታውቋል፡፡

በወቅቱ በነበረው ግጭት የተፈነከቱ፣ የእጃቸው ጣቶች የተሰበሩ፣ የሚያነክሱና ራሳቸውን ስተው የወደቁ እንደነበሩ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸው፣ የፖሊስ ተሽከርካሪዎችና የቀይ መስቀል አምቡላንሶች ወደ ሆስፒታል ሲያመላልሱ መታየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ታሳሪዎቹ ‹‹ፍትሕ ናፈቀን፣ ፍትሕ ይከበር፣ የዕምነት ነፃነታችን ይከበር፣ የታሰሩ ይፈቱ፣ መንግሥት በዕምነታችን ጣልቃ አይግባብን፣ የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ…›› እና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት በአንዋር መስጊድ ግቢ ውስጥ በማሰማት ላይ እያሉ፣ ከማን እንደተወረወረ ባልታወቀ ድንጋይ ፖሊሶች መጎዳታቸውን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡

ለሥራ ወጥተው ምንም ሳያደርጉ ልጆቻቸው የት እንደደረሱ ማወቅ ያልቻሉ እናቶች፣ ቤተሰቦችና የሚመለከታቸው ወገኖች በየፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሲጠይቁ በቂ ምላሽ አለማግኘታቸውን የገለጹ ቢሆንም፣ አንዳንዶቹ ወላጆች ደግሞ የልጆቻቸውን ስም እየተናገሩ የታሰሩበትን ፖሊስ ጣቢያ ለማወቅ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሐምሌ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በድጋሚ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡና ምናልባትም በተለይ ሳያስቡትና በወጡበት ችግሩ የገጠማቸው በዋስትና ይለቀቃሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል፡፡

በግጭቱ ወቅት በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ሰዎች ብዛትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ እንዲሁም የግጭቱ ዋነኛ መነሻ ምን እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና የፌዴራል ፖሊስ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁ ቢሆንም፣ ማብራሪያውን ለማግኘት አልተሳካም፡፡ ነገር ግን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፖሊስ አባላት እንደገለጹት፣ በግጭቱ ወቅት ቁጥራቸው በዛ ያሉ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር፡፡ ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ከበላይ ኃላፊዎች በመጣ ትዕዛዝ ሁሉም ማለት በሚባል ደረጃ ተለቀዋል፡፡ አሁን በቁጥጥር ሥር ሆነው በምርመራ ላይ የሚገኙት ለረብሻው ምክንያት የሆኑና በተደጋጋሚ ችግር ሲፈጥሩ የተገኙ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በደንብ በመደራጀት ሕዝብ ሰላም እንዳያገኝ በተደጋጋሚ ግጭት ሲያስነሱ የተገኙ ከ14 በላይ ግለሰቦች በተፋጠነ ችሎት እየቀረቡ መሆኑንም አክለዋል፡፡

በግጭቱ ወቅት ፖሊሶች ሞተዋልና ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል ስለመባሉም ሐሰት መሆኑን ተናግረው፣ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉ ግን አልካዱም፡፡ ፖሊስ ምርመራውን ጨርሶ ለዓቃቤ ሕግ ካስረከበና የሚከሰሱ ከሆነም የፍርድ ቤት ጉዳያቸው ሲጠናቀቅ፣ የግለሰቦቹን የወንጀል ድርጊትና እንቅስቃሴ ከነማስረጃው ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live




Latest Images