Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ከባለቤቱ ያላወቀ በፍቅሬ ቶለሳ ጂግሳ

↧

↧

አዬነው ጽናቱን የጴጥሮስ ህይወቱን። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ ሲዊዘርላንድ)

እንግሊዝ አደባ ቴወድሮስን ሰቶ

የቀድምት ራዕዩን ልጁን አስቀምቶ።

ምድር የተከለ የደሙ ቆይታ

በመርዝ ተጠቅልሎ —– የዘመን ስሞታ።

የታመቀ እርሙን አጥብቶ አሳድጎ

አረምን አብቅሎ አሳምሮ ጉቶ

ጽዋ ተወራርዶ ——— በቋሳ ታግቶ።

ወያኔ ደነፋ የአርሙ መንጋጋ

ጨላማም አውጇል ሊመጣ ሊነጋ።

ውሉ ተዋውሏል ተስፋ ተዚያ ማዶ

መከራን ሊቀበል———- ጀግና ጽላት ወዶ።

የለመደበትን ብረት መዝጊያነቱን

አዬነው ጽናቱን የጴጥሮስ ህይወቱን።

እኔም እለዋለሁ የአንድዬ ትውፊት

ቀራንዮ ሆኖ – ታምር ትሩፋት።

እስኪ ሆዴ ቻለው የተከዘነውን

የአባትህን ቆላ እባክህ ዝገነው።

እዩት ከዛ ማዶ የተከደነውን

እራስን በመስጠት አራሽ የሆነውን።

እልሁ መጥቶ – እኔን ሊያናግረኝ

የአንዳርጋቸው ዶግማ እኔኑ ጋገረኝ።

ጀግንነት የባቱ የዚያ የአንበሳ

ናፍቆቱን አዬነው ነፃነት ሲሳሳ።

ብቃቱ ይህ ነበር የአርበተበታቸው

የጫካን አራዊት የአንተረተራቸው።

ዘመን ይመለሳል እንደወጣ አይቀርም

ሰነብት ይቆጠራል ————————-ጠላቱን ሲቀብር።

የሀገሬ ፋፋ ዱርና ገደሉ

ደም መልሱን ላከው የአርበኛ ዝልሉ።

ይሄውልህ ተዚህ ያነ ማተበኛ

ተስፋ እንደ ጸና ሆነበት መጋኛ።

ጽጌ ትመጫለሽ — እጠብቅሻለሁ

ጉርሻሽን ለማግኘት ፍጹም —- ጓጉቻለሁ።

አታጥፊ ቃልሽን አንቺ የእኔ እመቤት

ዕንባ ተቀበይኝ የጌታዬ አንደበት።

 

ሥጦታ እራሱን ንቆ ለነፃነት ሁለመናውን ለሰጠ የጀግና ጽላት አንዳርጋቸው ጽጌ ይሁንልኝ።

ተጣፈ 11.07.2014 ሲዊዘርላንድ።

 

መፍቻ።

  • ሲሳሳ — ሲናፍቅ፣ ሲፈልግ፣ ሲመኝ፣ ሲማስን፣ ሲባትል፣ ሲደክም፣ ሲሆን፣ ሲገኝ፣ ለማለት ነው

ትርጓሜው አዎንታዊ ነው።

አራሽ —– ሰሙ ጠጋኝ፣ የተጎዳን የሚረዳ ሲሆን ወርቁ ደግሞ የነፃነት ገበሬ ለማለት ነው።

ሰሙም ሆነ ወርቁም አገባባቸው መንፈሳዊ ተዋፆን አምልካች ናቸው።

 

 

እግዚአብሄር አምላክ ዘመነ ቋሳን ከሥሩ ነቅሎ ያሰዬን! አሜን!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Comment

↧

አበራ ለማ፡ ለባሉ ግርማ፡ አስቦ ወይንስ ሌላ? (ከማተቤ መለሰ)

$
0
0

ከማተቤ መለሰ

 

bealu girma 1አቶ አበራ ለማ፡ ሰሞኑን ”የማይጮኹት ባሉ ግርማን የበሉ ጅቦች” በሚል እርዕስ የጻፈውን በኢትዮ ሚዲያ ድህረ ገጽ ላይ ሳነብ” በአቆማዳው ገመሰኝ” ቢለው ተው ወንድሜ በውስጡ ዲንጋይ ይኖርበታል አለው የሚባለው ብሂል ነው። በሃሳቤ የመጣብኝ። እውነት ከ30 አመት በፊት አድራሻው ስለጠፋው ስለ ብርቅየው የብዕር ሰውና ንጹሁ ኢትዮጵያዊ ሰለ አቶ ባሉ ግርማ ተቆርቁሮ ያነሳው ሃሳብ ቢሆን በበኩሌ እሰየው ነበር።

 

ግን በእርግጠኝነት መታከኪያ ፈልጎ እንጅ ለባሉ ግርማ ተቆርቁሮ አይደለም። አበራ ለማ በተፈጥሮው የሚጨነቀው ለጥቅሙና ለጥቅሙ ብቻ እንጅ ለሰው እንዳልሆነ አሁን የምንኖረው አብረን አንድ አገር ማለትም ኖሮዌይ ስለሆነ በቅርበት የማውቀው በቤተሰቡ ላይ ሳይቀር የፈጸመውና የሚፈጽማቸው ዲርጊቶች ማረጋገጫዎች ናቸው። በአስነዋሬ ምግባሩም መንስኤ ነው በሚኖርበት ሃገር ከማህበረ ሰቡ ተገልሎ ያለው።

 

አበራ ለማ የግል ስብናውን ለመገንባት በጣረበት፡ በዚያ ዝባዝንኬ መጣጥፉ፡ የአለቃው አለቃ የነበሩትንና እውቁን ጋዜጠኛ ዛሬም ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት በብዕራቸው በመታገል ላይ ያሉትን። አቶ ሙሉጌታ ሉሌን የሚከስበት ጭብጥ፡ ሰለ ባሉ ግርማ ፕሬዘዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም አናግረውታል የሚል ነው። አቶ ሙሉጌታ ተጠርተው ከሆነም በአንድ እርዕሰ ብሄር የነበራቸውን ክብር ማሳየቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ለአቶ ባሉ ግርማ መገደል ምክናያት ነው የሚለውን ነጥብ አላመላከተንም።

 

ከዚህም በላይ፡ አቶ ክፍሉ ታደሰ፡ ”በያ ትውልድ” መጻፋቸው እንደገለጹት አበራ ለማ ኢህአፓ ነህ በማለት የገደለውና በእነ እርገጤ መድበው የክስ መዝገብ ተራቁጥር 27 ላይ ስሙ ተጠቅሶ በሌለበት የተከሰሰበት ሟች ሰው አይደለምና ነውን? የሚለውን ጥያቄ ካነሳን፡ ዛሬ አበራ ለማ የሟች ወንድማችንን የአቶ ባሉ ግርማን አጽም መታከክ የፈለገበት ምክናያት ሰባዊነት ሳይሆን፡ ከወያኔ ጋር ያለው የጥቅም ግንኙነት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መስታዋት ነው።

 

ሌላው አበራ ለማ በጽሁፉ፡ ባሉን የበሉ ጅቦች ሲል፡ ምን ለማለት ነው የሚለው ጥያቄም መታለፍ የሌለበት ነው። በእሱ ቤት ቅኔ መሆኑ ነው፡ ድንቄም ተቀኘች? እሱ በሁለተኛ ቋንቋው ሲቀኝ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሆኑት ጎጃሞች፡ አይገባቸውም ብሎ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ምክናያቱም ሰማቸውን በመደርደር የአንድ መንደር ሰዎች እያለ በፍጹም ጭፍን ጥላቻ የሚያብጠለጥላቸው፡ ትውልደ ጎጃሞችን ነው። ከጅብ ጋር ለማዛመድ የሞከረበት አንደምታም፡ በጅምላ አንድን ህዝብ እንደህዝብ ማዋረዱ ነው፡ በእሱ ቤት። ኢትዮጵያ ውስጥ ጌቶቹ የኦህዴድ ካድሬዎች አማረኛ ተናጋሬውን እየመረጡ በመግደል፣ በማሰርና በማፈናቀል፡ ከግፎች ሁሉ የከፋ ግፍ እየፈጸሙበት ነው። ሐገር ጥለን በመሰደድ እንኳን በሰላም እንዳንኖር፡ እንደ አበራ ለማ አይነት ሰዎች፡ በእየወሩ ሃገር ቤት በመመላለስ፡ ከአለቆቻቸው መመሬያ እየተቀበሉ፡ ተሰዶ ለወገኑ ነጻነት ከምር

2

የሚታገለውን ኢትዮጵያዊ በመዝለፍና በማሸማቀቅ ስራ ላይ ተጠምደዋል፡ በአበራ ለማ ያልተገራ ስድ አንደበት የሚዘለፉ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ። ብቻ አይደሉም፡ ነጻነቴን እሻለሁ በማለት ወያኔን የሚቃወም ሁሉ እንጅ። ለዚህ ማስረጃው ኖረዌይ በሚኖሩ የነጻነት ታጋዮች ላይ በእየ ጊዜው የሚፈጽመው ድርጊት ነው።

 

ዛሬ 30 አመት በሗላ፡ በባሉ ግርማ ሰበብ፡ የተሳበው የጭዋታ ካርታም፡ ሰለ እውነት ለእሱ በመቆርቆር ሳይሆን። ወያኔ ከጀግኖች ሁሉ የላቀውን ጀግናና እውነተኛውን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን፡ በማፈኑ፡ ከሃገር ቤት ጀምሮ በመላው ዓለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያውያን  በጋራ ለመታገል ያለውን ፍላጎት ማሳየቱ ወያኔን ያልተጠበቀ የብራ መብረቅ የወረደበት ታክል ስላስደነገጠው፡ መላ እንዲፈልጉ ካድሬዎቹን በማራወጥ ላይ ሲሆን፡ አበራ ለማም በድርሻው ይህንን የትግል ግለትና የአንድነት እንቅስቃሴ አቅጣጫ ያስቀይስልኛል ሲል ያሰበውን፡ ለጌቶቹ መታያ ይሆን ዘንድ ያቀረበው መሆኑን ልብ ልንልለት ይገባል።

 

በተረፈ አገራችንን ጥለን ተሰደናል፡ በእያለንበት ደግሞ የምናገኛትን ዳቦ በሃገር ናፍቆት እንባ እያራስን እንዳንበላ፡ በእየ ሳምንቱ እየተመላለሱ ተጭነውት የሚመጡ መርዘቸውን  እየደፉበን ያሉ እንደ እነዚህ አይነት አስመሳይ ምንደኞች በእየቦታው እየፈሉ ነው፡፡ ጎበዝ ምን ይሻላል? ከዚህ በሗላ ጨረቃ ላይ አንወጣ፣ የት እንድረስ? አሞትን ኮስተር፣ ትንፋሽን ክትት አድርጎ ከምር ከመታገል በቀር።

 

ቸር እንሰንብት

 

ሃምሌ 6 ቀን 2006

 

 

 

 

 

 

 

↧

በተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ የሚደረገው ማዋከብ ይቁም፣ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ አሁኑኑ ይፈቱ

$
0
0

ማክሰኞ ኅምሌ 1፣ 2006 ( July 8፣ 2014) shengoየህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ በህጋዊነትና በሰላማዊ መንገድ  የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች አመራር አባላት ከሆኑት ውስጥ አቶ ሀብታሙ አያሌውንና አቶ ዳንኤል ሽበሽን ከአንድነት  ፓርቲ፣ አቶ የሽዋስ አሰፋን ከሰማያዊ ፓርቲ እንዲሁም አቶ አብረሀም ደስታን ከአረና ፓርቲ ማሰሩን ተረድተናል።  የተጠቀሱት ግለሰቦች በሀገራችን ውስጥ ያለው የመብት መረገጥ፣ የፍትህ መጥፋት፣ የህግ የበላይነት አለመኖር ፣ ግፍ  ስቃይና መከራ እንዲያበቃ ምሳሌ የሆነ ትግል በሰላማዊ መንገድ ሲያካሂዱ የቆዩ ለመሆናቸው እጅግ ብዙ መረጃ መጥቀስ  ይቻላል።  [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]

 

 

 

↧

ተበላ! ጀርመን በላችው! (VOA Amharic)

$
0
0

VOA Amharic ጎ…………ል! ጀርመን 1 አርጀንቲና 0 – ሃያኛው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ ተጠናቀቀ፡፡ ጀርመን አርጀንቲናን በፍፃሜ ግጥሚያ ለሁለተኛ ጊዜ ድል ነሣች፡፡

6D963441-D16E-4DE3-97F9-05306B641415_w268ጀርመን አርጀንቲናን በፍፃሜ ግጥሚያ ለሁለተኛ ጊዜ ድል ነሣች፡፡ ጨዋታው በተጨማሪ የጨዋታ ጊዜ በተቆጠረች ግብ 1 ለባዶ አለቀ፡፡

በሪዮ ዴ ጃኔይሮው ማራካና ስታዲየም የተካሄደው ጠንካራ ሊባል የሚችል ትንቅንቅ የታየበት ጨዋታ ዋናው የግጥሚያ ጊዜ /ዘጠና ደቂቃው/ የተጠናቀቀው፣ ብዙ የግብ አጋጣሚዎች ተፈጥረው የነበረ ቢሆንም፣ ያለምንም ግብ ባዶ ለባዶ በሆነ ውጤት ነበር፡፡

ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ዘልቆ በ112ኛው ደቂቃ ላይ 19 ቁጥር ለብሶ የሚጫወተው ማሪዮ ግዮትዘ በድንቅ አስተላለፍ የአርጀንቲናን በረኛ አሳልፎ መረብ ላይ ያስቀመጣት ኳስ የጨዋታውም ለብርቱው የጀርመን ቡድንም በዚህ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም ግብ ሆነች፡፡

ጎ……………………….ል! ጀርመን የዓለም ዋንጫን ለአራተኛ ጊዜ ወሰደች፡፡

በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ታሪክ ጀርመን 4 ጊዜ አሸንፋ አምስት ጊዜ ያሸነፈችውን ብራዚልን እየተከተለች ነች፡፡

በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ታሪክ ውስጥ እአአ በ1954 ዓ.ም ልክ የዛሬ ስድሣ ዓመት ስዊትዘርላንድ አዘጋጅታው በነበረው 5ኛው የዓለም ዋንጫ ላይ ጀርመን ሃንጋሪን 3 ለ 2 አሸንፋ የመጀመሪያውን ዋንጫዋን ወስዳለች፡፡

ከዚያም እአአ በ1974 ዓ.ም እራሷ /የያኔዋ ምዕራብ ጀርመን/ አዘጋጅታው በነበረው 10ኛው የዓለም ዋንጫ ላይ ለፍፃሜ ከሆላንድ ጋር ተገናኝታ 2 ለ 1 አሸነፈች፡፡

እአአ በ1990 ዓ.ም /የዛሬ 24 ዓመት/ ጣልያን ባዘጋጀችው 14ኛው የዓለም ዋንጫ ልክ እንደዛሬው ጀርመንና አርጀንቲና ተገናኝተው፤ ልክ እንደዛሬው ጀርመን አርጀንቲናን 1 ለ 0 አሸንፋ ዋንጫውን አስቀረች፡፡

ዛሬ፣ ዕሁድ – ሐምሌ 6/2006 ዓ.ም /በኢት.የዘ.አቆ/ የሪዮ ዴ ጃኔሮው ማራካና ስታዲየም ላይ ጀርመን የዛሬ ሃያ አራት ዓመቱን ታሪክ ደገመች፡፡

የማርዮ ግዮትዘን ጎል ለማየት ከታች የተቀመጠውን ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ፤ http://www.espnfc.com/video/latest-videos/600/video/1948633?&ex_cid=espnapi_affiliate_Google_World_Cup_Video

 4C51EB3A-1295-4F54-A984-6743FA99F22F_w640_sየጀርመኑ ባስቲያን ሽቫይንሽታይገር ከአርጀንቲናዎቹ ሉካስ ቢህሊያና ሊዮኔል ሜሲ ጋር የነበረው ፍጥጫ – ሪዮ ዴ ጃኔይሮ – ማራካና ስታዲየም፤ ዕሁድ – ሐምሌ – 6/2006 ዓም
↧
↧

ግልፍተኛነት

$
0
0

angerበስራም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ ህይወታችን ውስጥ ግልፍተኛ የሆኑ ሰዎች ይገጥሙናል፡፡ ምናልባትም እኛ ራሳችን በሌሎች እይታ ግልፍተኛ ልንባል እንችል ይሆናል፡፡ ግልፍተኝነት ተራ በሚባሉ ጉዳዮች ሳይቀር በቁጣ መገንፈልና ይህንንም ተከትሎ ለአላስፈላጊ ውሳኔ ወይም ድርጊት መጋበዝን ያመለክታል፡፡ በዚህ በግልፍተኝነት ምክንያትም ለዓመታት የተገነቡ ጓደኝነቶች፣ ትዳር ወይም እቅድ ሊከሽፍና ሊበላሽ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ግልፍተኝነት መቅረፍ የሚቻልባቸው እና የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት መኖር የሚያስችሉ ሳይንሳዊ ስነ ልቦናዊ መንገዶች እንዳሉ ማስታወስ ያሻል፡፡ ከግልፍተኝነት ለመላቀቅ የሚበጁ ተብለው በተለያዩ የስነ ልቦና ምሁራን ከሚጠቀሱት ምክሮች በፊት ‹ግልፍተኝነት› በምን ምክንያት ይከሰታል የሚለውን ነጥብ እንመልከት፡፡

ግልፍተኝነት እንዴት ይከሰታል?

ግልፍተኝነት ከጭንቀትና ከውጥረት ብዛት እንደሚከሰት ብዙዎች ቢስማሙበትም፣ አታካች በሆነ የህይወት ሂደት፣ በቤተሰብ፣ በከባድ ኃላፊነቶች ምክንያት ሊመነጭ ይችላል፡፡ በተደጋጋሚ ሲነገረው አልሰማም ባለ ልጅ አባት/እናት ግልፍተኛ ሊሆኑ ይችላሉ፣ የጠበቅነው ነገር ሳይሆን ሲቀር ለግልፍተኝነት ሊዳርገን ይችላል፡፡

አና የተሰኘች የ25 ዓመት ወጣት ስለ ፍቅር ጓደኛዋ እንዲህ ስትል ትናገራለች፡፡ ‹‹እኔና ጓደኛዬ ላለፉት ሁለት ዓመታት በጓደኝነት ኖረናል፡፡ ይህ ጉድኝታችን ግን በጓደኛዬ ግልፍተኛነት ምክንያት አንዴ ሲቋረጥ አንዴ ሲቀጥል ነበር የቆየው፡፡ በጣም ተራ በተባሉ ጉዳዮች ከመጠን ባለፈ የሚበሳጭ ሲሆን ሲበሳጭ ደግሞ አጠገቡ ያለውን እቃ ከመስበር አንስቶ ግድግዳ በቦክስ ሲደበድብ ሊታይ ይችላል፡፡ እንደውም በአንድ ወቅት ራሱን ለማጥፋት እስከመሞከር የደረሰበት ሁኔታ ነበር፡፡ እርሱ መናደድ በጀመረበት ወቅት ለማረጋጋት መሞከር ንዴቱን ይበልጥ ማባባስ ስለሆነ ቆሜ ከማልቀስ ውጭ ምንም ማድረግ አይቻለኝም›› ስትል ትገልፀዋለች፡፡

ይህን አስመልክቶ መልስ የሰጡ አንድ የስነ ልቦና ባለሙያ ግልፍተኛነት ማንኛውም ሰው በህይወት ዘመኑ ሊገጥመው የሚችል ስሜት ሲሆን ይህ ስሜት ግን በአንዳንድ ሰዎች ላይ በተደጋጋሚና ጠንከር ባለ ሁኔታ ሊከሰትበት የሚችል እድል እንዳለ ያስረዳሉ፡ ፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ማለትም ክብራችን ሲደፈር፣ ጥቃት ሲደርስብን ወይም አይነኬ ያልነው ድንበር ሲጣስ ግልፍተኝነት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል የሚሉት እኚህ ባለሙያ ግልፍተኝነት ጤናማ የማይሆነው የተፈጠረው ችግር ለግልፍተኛነት የማይጋብዝ ሁኔታ ላይ ሲከሰት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ከዚህ ቀደም በመልካም ባህሪያቸውና በትህትናቸው የምናውቃቸው ሰዎች ድንገት ቁጡና ግልፍተኛ ሆነው የሚገኙበት አጋጣሚም አለ፡፡ ይህ አይነቱ ግልፍተኛነት ‹secondary emotion› ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ በሚከሰቱ የስራ ወይም የሌሎች ማህበራዊ ህይወት ጫናዎች ለዚህ ባህሪ ሊዳረጉ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው፡፡ አንድ ሰው በዚህ ሁኔታ ለግልፍተኛነት ሲጋለጥ ምንም አይነት ደስታ ላይኖረው ሲችል የፍቅር ቃላትና ሰላምታ ሳይቀር ለቁጣና ለብስጭት ሊዳርገው ይችላል፡፡

ግልፍተኛነት የረጅም ጊዜ ባህሪያችንንም ሆነ የአጭር ጊዜ በተለያዩ ሳይንሳዊ መንገዶች ተጠቅመን ልናስወግደው የምንችለው ባህሪ መሆኑ ግን ሊታወቅ ይገባል፡፡ ተግባቢና ተጫዋች ሆኖ ከመገኘት የበለጠ ምን አለ? ግልፍተኛ ከሆኑ ወይም ‹ግልፍተኛ ነዎት!› የሚባል ከሆነ እስቲ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነጥቦች ለመተግበር ይሞክሩ፡፡

የግልፍተኛነት መፍትሄዎች

ቁጡነትንም ሆነ ግልፍተኛነትን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የተለያዩ ስትራቴጂዎች በተለይ በሰለጠነው ዓለም በስፋት ይገኛሉ፡፡ ጭራሹኑም በግልፍተኛነት ችግር የሚፈጥሩ ሰዎች በህግ ታዘው ከግልፍተኛነታቸው የሚገላገሉበት ስልጠና እንዲወስዱ ሲደረግም ይታያል፡ ፡ ከእነዚህ የግልፍተኛነት መቅረፊያ መንገዶች ውስጥም ለቁጣ /ለግልፍተኛነት የሚዳርጉንን ነገሮችን ለይቶ ማወቅና ከእነርሱም መራቅ፣ ለግልፍተኛነት የሚዳርጉ ስነ ልቦናዊ ችግሮች ማለትም ጭንቀትና ውጥረት ካሉብን ለእነርሱ መፍትሄ መፈለግ፣ ከአልኮልና ከሌሎች ሱስ አስያዥ ነገሮች መቆጠብ፣ የመግባቢያ /Communication/ መፃህፍትን ማንበብ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እርስዎ በቤትዎ ግን እነዚህን ምክሮች ሊተገብሩ ይችላሉ፡፡

- ከግጭቱ፣ ከተበሳጩበት ሰው ወይም ቦታ ዘወር ማለት፡- ከአንድ ሰው ጋር በአንድ ጉዳይ እየተከራከሩና በሰውዬው ንግግር /ድርጊት ብስጭት የሚሰማዎ መስሎ ከተሰማዎት ምንም መልስ ሳይሰጡ ከሰውየው ይራቁ፡፡ ብቻዎትን ይሁኑናም ‹ብቻዬን ሆኜ ራሴን ማረጋጋት እችላለሁ› ይበሉና ለራስዎት ይንገሩት፡ ፡ ወይም ክፍልዎ ይግቡና ግድግዳ ይደገፉ፡፡ ሁለት እጅዎንም ግድግዳው ላይ ይለጥፉና 5 ጊዜ በጥልቀት አየር ወደ ውስጥ እየሳቡ ይተንፍሱ፡፡ ውስጥዎ ሲረጋጋ ተሰማዎ? ‹አዎ! አሁን ተረጋግቻለሁ› ሲሉ ለራስዎ ይንገሩት፡፡

- ቁጣዎን ያስወጡት፡- በብስጭት ውስጥዎ ሲነድ ግድግዳ በጡጫ ይነርታሉ? ዕቃ ይሰብራሉ? ግድግዳውም ሆነ ዕቃው ከብስጭትዎ ጋር በምን ይገናኛሉ?

በእርግጥ ሰው ሲበሳጭ ይህን ብስጭቱን ቢያስወጣው ለመረጋጋት እንደሚያስችለው ይታመናል፡ ፡ እርስዎም ብስጭትዎን ቢያስወጡት መልካም መስሎ ከተሰማዎ ለምን እንዲህ አያደርጉም?! አንድ ሞቅ ያለ ሙዚቃ ድምፁን ከፍ አድርገው ይክፈቱና በደንብ ይደንሱ፡፡ ለዳንስዎ ህግ አያውጡ፤ እጅዎም ሆነ እግርዎ እንደፈለጉት ይንፈራገጡ፡፡ ይህችን ነገር ከ2 እስከ 3 ደቂቃ ካደረጉ ብስጭትዎን ድራሹን ለማጥፋት በቂ ነው፡፡

↧

Hiber Radio: “ጠንክረን በጋራ መታገል እንጂ ማልቀስ የሚያስፈልግበት ወቅት አይደለም”–የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እህት እስከዳር (ቃለምልልስ)

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 6 ቀን 2006 ፕሮግራም

ቃለ መጠይቅ ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እህት እስከዳር ጽጌ ጋር ስለ ወንድሟ አፈና እና ወቅታዊው በሆነው ጉዳይ አጠር ያለ ውይይት አድርገናል። >(ሙሉውን ያዳምጡት)

ሕወሃትና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኘው የማሰቃየት እርምጃዎቹ (ልዩ ዘገባ)

>

አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሀላፊ

<...> ደራሲና ፖለቲከኛ አስራት አብርሃም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ካደረግንለት ቃለ መጠይቅ የተወሰደሙሉውን ያዳምጡት)

ሕወሃት በኣለም አቀፍ የአሸባሪነት መዝገብ ያሰፈረው የአፈና ተግባሩና ከ38 ዓመት በፊት ከታፈኑት የውጭ ሰዎች የጋዤጠኛው ምስክርነት(ልዩ ጥንቅር)

የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ (ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም አሉ

ዜናዎቻችን

የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት በእንግሊዝ የስለላ ድርጅት ላይ ቅሬታቸውን ገለጹ

የህወሃት ካድሬዎች የህወሃት ባንዲራ ለተቃውሞ ሲቃጠል የትግራይ ባንዲራ ተቃጠለ ማለታቸው ተቀባይነት እንደሌለው ተገለጸ

ሰማያዊ ፓርቲ መሪዎቹ በአገዛዙ የእስር ሰለባ ቢሆኑ በተተኪ አመራር ጉዳይ እየመከረ ነው

የኦጋዴን ነጻ አውጭ የአገዛዙን ወታደራዊ አሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ የደረሰበትን የመብት ረገጣ እንዳይዘነጋ ተጠየቀ

የኢህአዴግ አገዛዝ አገሪቱን ወደ ፍጹም አምባገነን አገዛዝ እየመራት ነው ተባለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

↧

የዶ/ር ነገደ ጎበዜ አዲስ መጽሐፍ

$
0
0

dr_negede_two“…ይህንን የትግሉን ህዝባዊ ገፅታ ችላ ብለን እነዚህን ሚሊዮኖች የሚያካትት ህዝባዊ የትግል ማእበል ለመቀስቀስ፣ መቀስቀስ ብቻ ሳይሆን ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችለን የጋራ ስትራቴጂ አውጥተን ካልተንቀሳቀስን በስተቀር “በእኛና  በእነሱ” መሃከል በተወሰነ የትግል ክፈፍ ከብረት ድስትና ከሸክላ ድስት ፍልሚያ፤ ሸክላ በአሸናፊነት ይወጣል በሚል የአጉል  ህልም ዓለም ውስጥ ነን ማለት ይሆናል፡፡” ዶ/ር ነገደ ጎበዜ–-  [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—-

↧

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አደረጉ

$
0
0
Pቅዳሜ ጁለይ 12/2014 በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አዘጋጅነት ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን በሚል አላማ በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የደንነት ሀይሎች መታፈንና ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ታላልፈው መሰጠታቸውን በተመለከተ ወደ ፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከተለያዩ ከተሞች በመሰባሰብ በኖርዌ ኦስሎ ለአምስት ሰዓታት የፈጀ ውይይት ሲያደርጉ ውለዋል::
ሕዝባዊ ውይይቱ ከቀኑ 15: 00 ሰአት ላይ የተጀመረ ሲሆን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያኖች የአቶ እንዳርጋቸው ምስል ያለበትና ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን የሚል ጹሁፍ የተጻፉበትን ቲሸርት በመልበስ ለስብሰባው ድምቀት የሰጡት ሲሆን ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውንም የትግል አጋርነት አስማስክራዋል እነዚህን ቲሸርቶች የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርንጫፍ በራሳቸው አነሳሽነት የሰሩ ሲሆን የድጋፍ ድርጅታችን ወጪውን በመሸፈን ለተሰብሳቢው በነጻ ኣድሏል።
ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት አላፊ አቶ አቢ አማራ በሃያ ሶስት አመታት በወያኔ ጨካኝ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉትና በግፍ ለሚሰቃይዩ ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማስደረግ አስጀምረውታል በመቀጠልም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር በስብሰባው ላይ የተገኛውን ሕዝብ እንኮን ደህና መጣችሁ በማለትና በማመስገን ፐሮግራሙን በንግግር የከፈቱት ሲሆን አቶ ዮሀንስ በንግግራቸው የወያኔ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ባደረሰው አፈና ግንቦት 7 የክተት አዋጅ ማስተላለፉን ጠቅሰው አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በአሁን ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል እየታገሉ ባሉ ታጋዮች ላይ ሳይቀር እስር እያደረሰባቸው እንዳለ በማመልከት ሰሞንኑን እንኮን የሰመያዊ፣ የአንድነት፣ የአራና የፖለቲካ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ለስር ተዳርገዋል ብለዋል::
ስለሆነም ህዝባችንን ለእስር እያደረገ ያለውን አገዛዝ ለመቃወም ሁሉም በአንድነት መሰባሰብ እንዳለበት አጠንክረው በመናገር በአሁን ሰአት የአቶ አንዳርጋቸው በወያኔ መታፈንና መታሰር መላውን ኢትዮጵያ ዳር እስከ ዳር እያንቀሳቀሰውና ሕዝቡም እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በማለት በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጠቅሰው በአሁን ሰአት ትግሉ የግንቦት 7 ብቻ አይደለም ይህን ትግል በዚሁ አንድ ሆነን መቀጠል እለብን ብለዋል::
በመቀጠል አቶ ደባስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባል የአቶ አንዳርጋቸውን ከወጣት እድሜያቸው ጀምሮ ያለውን የፖለቲካ አካሄድ አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ማን ነው ? በሚል ርእስ የአቶ አንዳርጋቸውን የትግል ጉዞ የሚዳስስ ዘገባ ሰፋ ባለ ትንታኔ በጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በስብሰባው ላይ የኢሀፓ ፣ የአርበኞች ግንባር፣ የሸንጎ ፣የስደተኛው ማህበር ተወካዮች እና ሌሎችም ሰዎች በየተራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የየድርጅቷቹም ተወካዮች የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መታፈንና ለእስር መዳረግን በተመለከተ የድርጅታቸውን አቋም ለተሰብሳቤው ያስረዱ ሲሆን የሁሉም ፖርቲ ተወካይች በአቶ አንዳርጋቸው መታፈንና ለእስር መደረግ ማዘናቸውን ገልጸው ሁሉም በአንድነት በመተባበር በማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ የወያኔንን መንግስት ማስወገድ እንዳለባቸው አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል::
በየፕሮግራሞቹ መሀል ግጥሞችና ሌሏችም ፕሮግራሞች ቀርበው የመጀመሪያው ዞር ተጠናቋል::ከ30 ደቂቃ የእረፍት የሻይ እና የቡና ፕሮግራም በኋላ የሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ፕሮግራም በተያዘለት ጊዜ ተጀምሮ የፕሮግራሙን ተሳታፊዎች ያሰተፈ ፕሮግራም በአቶ አብዱ የሱፍ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ስታቫንገር ቅርንጫፍ ምክትል ሊቀመንበር ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና ተግባሪዊ የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪን ካብራሩ በኋላ ለተሰብሳቢው ለውይይት በማቅረብ በኖርዌ የምንኖር ኢትዮጵያኖች ይህን የትግል ጥሪ ለማስፈጸም ምን እናድርግ በማለት ለውይይት አቅርበው የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በአቶ ዮሀንስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር አወያይ አማካኝነት በስፋት ተወያይተውበታል ::
ተሰብሳቢውም በብዙ ነገሮች ከተወያዩ በኋላ ይሄ ግንቦት 7 ያወጣውን የመጀመሪያ እንከን የትግል ጥሪ ተግባራዊ በየቦታው አለም አቀፍ ታክስ ፎርሶች እየተቋቋሙ እንዳለና በኖርዌይም ይህንኑ ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቷች ያካተተ ታክስ ፎርስ እንዲቋቋም ተወስኖል:: በመቀጠልም በተሰብሰቢዎች በተመረጡ ሰዎች የተጻፋ ባለ ስድስት አሃዝ የተሰብሳቢው የአቋም መግለጫ ለጉባሄው በጹሁፍ ቀረቦል:: ተሰብሳቢው ያወጣው የአቋም መግለጫ
1. ሁላችንም አንዳርጋቸው ወይም አንድ አርጊያቸው ነን ስንል ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሐገራችን ኢትዮጵያ ለማስፈን የሚከፈለውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ማለታችን ነው።
2. የተለያዩ የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት የሚያደርጉትን መጠላለፍ እንዲቀርና በጋራ ወይም አንድ በመሆን እንዲሰሩ ግፊት እናደርጋለን።
3. ለሚቀርብልን ሐገርን የማዳን ጥሪ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።
4. የየመን መንግስት ከአለም አቀፍ ህግ ጋራ የሚፃረር ስራ በመስራት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለወያኔ አሳልፎ በመስጠት የሰራውን ወንጀል ለዓለም አቀፍ ህግ የማቅረብ ስራ በጋራ እንደምንሰራ።
5. የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ መታፈን ትግሉን የበለጠ እንደሚያጠናክረውና ወደ ውጤት እንዲያመራ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናደርጋለን።
6. ወያኔ የተለያየ ምክንያት በመፍጠር ኢትዮጵያውያንን እስርቤት ማስገባቱን እንዲቀርና የታሰሩትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ እንጠይቃለን በማለት የአቋም መግለጫ አውጥተዋል ።

በመጨረሻም አቶ ዳንሄል አበበ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ምክትል ሰብሳቢ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የአቋም መግለጫ ለተሰብሳቢው በጹሁፍ ያሰሙ ሲሆን በንግግራቸውም አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የቋሙ የነጻነት ታጋይ ናቸው እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ የምንል ሁሉ ለሃያ ሶስት አመታት ህዝብን በዘረኝነት የከፋፈለውን ወያኔን በቃ ልንለው ይገባል ካሉ በኋላ በኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ አፈና፣ ግድያው፣ እስራቱ መጨመሩን በመናገር ይኼን ጨቋኝና አፋኝ ስርአት ለማስወገድ እንነሳ በማለት ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን በመጨረሻ እኔ እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ እናንተስ በማለት የፕሮግራሙን ተሳታፊ በመጠየቅ ፕሮግራሙ በተያዘለት ሰዓት ከምሽቱ 20:00 ተጠናቋል ::

እኛ ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ
↧
↧

እየነጋ ነው! (እስከመቼ)

$
0
0

እስከመቼ

ሐምሌ ፪ ቀን፤ ፳፻፯ ዓመተ ምህረት 7/9/2014
( eske.meche@yahoo.com )

Abrha-Desta-Yeshiwas-Assefa-Daneil-Shibeshi-Habtamu-Ayalewአሁን ደግሞ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንዔል ሺበሽ፣ አብረሃ ደስታን አሰሩ። አንዳርጋቸው ፅጌን የማሠራቸው ዜና ገና አቦሉ ሳይጠጣ እኒህን ደገሙ። ለምን? አጭሩ መልስ እየነጋ ስለሆነ ነው። ኢትዮጵያዊ ሆኖ የእኒህን ታጋዮች ማንነትና ተግባር የማያውቅ የለም፤ ቢያንስ በትግሉ ዙሪያ ያለነው ኢትዮጵያዊያን። ታዲያ መንጋቱ እኮ፤ የአውራ ደሮውን ጩኸት፣ የጎኅን መፈንጠቅ፣ የጨለማውን መገፈፍ ይጠይቃል። ይህ ደግሞ በገዛ ፈቃዱና ቁጭ ብለው ስለጠበቁት የሚሆን አይደለም። የመሬትን በፀሐይ ዙሪያ መሽከርከር ተፈጥሯዊ ግዴታ ተከታይ ነው። በጭቆና የሚማቅቅ ሕዝብ፤ ለነፃነቱ መነሳቱና ከመካከሉ ቆራጦቹ ጧፍ ሆነው ከፊት መቅለጣቸው ግዴታ ነው። ይህ ነው የኒህ ቆራጥ ታጋዮች ሕይወት ትርጉሙ። እንደኛው ቤተሰብ፣ ንብረትና ምቾት አልጠሉም። ለወገንና ለሀገር ሠጡት። የሕይወታቸውን ትርጉም፤ በጣሊያን ጊዜ ከፋሽስቶች ለመጋፈጥ ከየመንደሩ በባዶ እግራቸው፤ ከመላ ኢትዮጵያ ጫፍ እስከጫፍ ወጥተው እንደቀሩት አርበኞቻችን፤ የኔ ሕይወት ለነገዋ ኢትዮጵያ ሕልውና ይሁን ብለው ያለማመንታት፤ ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነውን ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራውን መንግሥት በመቃወማቸው እስር ቤት ገቡ። ከኛ የተለዩ ልዩ ፍጡር ሆነው አይደለም። እንደኛ አባትና እናት፣ እህትና ወንድም፣ አክስትና አጎት፣ ባለቤትና ልጆች ያሏቸው ናቸው። ሰው ናቸው። አርበኛ ያደረጋቸው ተፈጥሯዊ ልዩነታቸው ሳይሆን፤ ለሕይወታቸው የሠጡት ትርጉም ነው። የብዙኀኑን የኢትዮጵያዊያን ሕይወት የኔ ብለው፣ ስቃያቸውን እነሱ ተሸክመው፣ ለሕዝቡ ጭዳ ሆነው ተሰለፉ። እንደነ አንዱዓለም አራጌ፣ እስክንደር ነጋ፣ ርዕዩት ዓለሙ፤ ሰግዶ ማደርን አልፈልግም ብለው፤ አረዓያችን ሆኑ። እንዲነጋ ምን ማድረግ አለብን።

አይቀሬው ንጋት እየመጣ ነው። የኛ ኃላፊነት ብዙና የተቆላለፈ አይደለም። እኒህ ቆራጦች የነገሩን ምንድን ነው? ፍርሃትን፤ ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት ቀምቶናል። ከኛ በኩል ፍርሃት ቦታ የለውም። የኢትዮጵያዊያን ጠላት የሆነው ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት በፍርሃት ተውጧል። ምስክርነቱ፤ ማንንም የሚፈራውንና በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አለው የሚለውን ግለሰብ ሁሉ እያሠረ ነው። እኒህ ጀግኖች የታሠሩት የዚህ ወይንም የዚያ ድርጅት አባል ስለሆኑ አይደለም። ከሕዝቡ ጋር ስለወገኑ ብቻ ነው። ለዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት፤ ማንኛውም ከሱ ቁጥጥር ውጪ የተደራጀ ክፍል ጠላቱ ነው። እናም የዚህ ወይንም የዚያ ድርጅት አባል መሆን አይደለም የመታሰሪያ ወንጀሉ፤ ከሕዝቡ ጋር የቆመ መሆኑ ብቻ ነው። የሚያስበረግገውና የሚያንቀጠቅጠው የሕዝብ ወገን የሆነ ማንኛውም ድርጅት ነው። ታዲያ ድርጅቶች በሙሉ አንድ ዓላማ እስከያዙ ድረስ፤ ሕዝቡ አሁን ነው ትግሉ ወደፊት መሄድ ያለበት እስካለ ድረስ፣ ንጋቱ በር አያንኳኳ እስከሆነ ድረስ፤ ተልዕኳችንን አንድ አድርገን ሌቱን እናንጋው።

ምንድን ነው የአሁን ጥያቄ? ይፈቱልን ብሎ ልመና አይደለም። ይህ በታሠሩት ቆራጦች ዓይን ጥቃት ነው። ይህን ብናደርግ ለገዥው ቡድን ኩራት ነው። እንኳን ያሠራቸውን ሊፈታ፤ የሚቀጥሉትን ታሳሪዎች እያዘጋጀ ነው። እነሱም ሆኑ መታሠራቸው፤ ጧፍ ሆኖ መንገዱን መሪያችን እንጂ፤ የመንገዱ ማብቂያ አይደለም። ገና የራሱን ጥላ ለማሠር የሚሯሯጥ ጠላት ነው ያለን። አጥንት ቆጠራውን ለገዥው ክፍል እንተውለት። እሱም እንኳ ለአጥንት ቆጠራው ቦታ እንደማይሠጠው አብርሃ ደስታን በማሠር አሳይቶናል። አብርሃ ደስታ በትግራይነቱ፣ ትግሬዎች እየተጠቁ ነው ብሎ የተደራጀ ነበር። አልሆነም። ኢትዮጵያዊነታችንን እንጎናጸፈው። በኢትዮጵያዊነታችን ይኼን ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት እንታገለው። ሁላችንን ሊያስተባብሩን የሚችሉ አራት የትግል ዕሴቶች አሉን።

፩ኛ፤     የኢትዮጵያዊያን ሉዓላዊነት                                    ፪ኛ፤     የኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት
፫ኛ፤     የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች        ፬ኛ፤     በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት

እኒህ ናቸው የታጋዮችን አንድነት የሚጠይቁ የትግል ዕሴቶቻችን። በነዚህ ዙሪያ ሁላችን መጠማጠም አለብን። የየድርጅቶች ታሣሪዎች መሆናችንን ለነፃነቱ ጊዜ እንተወውና፤ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ፣ ለሀገራችን አንድነት፣ በየእስር ቤቱ ለሚማቅቁ ጀግኖቻችንና አሁን በየዕለቱ ለሚታገቱት ቆራጥ ኢትዮጵያዊያን አርበኞቻችን አንድነታችንን እናጠንክር። ይህ ወደ ድል ይወስደናል። እነዚህን ሁሉን አቀፍ የሆኑ አራት ነጥቦች በሚያኩ ዙሪያ ሀገራዊ አጣዳፊ ጥሪዎች ሰሞኑን ድረገፆቻችንን አሙቀውታል። ጥሪዎቻችሁ ወደ መሰባሰቡ እንዲያመራ ፈልጋችኋል በማለት፤ ጥሪዎችን በተደጋጋሚ ያደረጋችሁ ግለሰቦች፤ እኛው ጀማሪዎች እንሁን የሚል ጥሪ በማስቀደም እንድንገናኝ ይኼው በ ( eske.meche@yahoo.com ) እገኛለሁ።

↧

ሰኔ 25 / 2006 ዓ/ም ታትሞ በወጣው ኢትዮምህዳር ጋዜጣ ከዓረና ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ በርሀ የተደረገ ቃለ መጠይቕ

$
0
0
Berhanu-Berhe-Arena-second-Chair-Person-of-Arena-Tigray

Berhanu-Berhe-Arena-second-Chair-Person-of-Arena-Tigray

ዓረና የምርጫ መቀስቀሻ አጀንዳዎቹ መሰረቱና መነሻው የመድረክ ማኒፌስቶ ነው የሚሆነው ፡፡የመድረክ ሚኒፌስቱ የታወቁ  ናቸው ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ሊታዩ የሚገባቸው ካሉ በመድረክ የሚወሰኑ ስለሚሆኑ ያኔ የሚገለፁ ናቸው የሚሆኑት ፡፡ በዓረና  ደረጃ ከክልሉ አጠቃላይ ሁኔታ ግምት ውስጥ የሚገቡ ጉዳዮች ካሉም በቅርቡ በሚሰበሰብ ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ  የሚወሰኑ ናቸው፡፡ ዞሮ ዞሮ በፖለቲካ ነፃነትና በመንግስት ፖለቲካዊ ኢ ወገናዊነት ፣በነፃ ምርጫና በሕብረ ፓርቲ ስርዓት ችግሮች፣  በመሬት ይዞታ ጉዳይ፣በኢንበስትመንትና በቡዝነስ ዙርያ ፣ በኢኮኖሚ ፖሊሲውና ብድህነት ቅነሳ፣ በአሰተዳደር ብልሹነት ጉዳዮች  የሚያጠነጥን ሳይሆን አይቀርም ፡፡ -— [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]——

↧

ለዳቦ ጥያቆ አንድና አንድ መልሱ ዳቦ ነው። (ዳዊት ዳባ)

$
0
0

ዳዊት ዳባ

Saturday, July 5, 2014

በቅርብ ከአገር ቤት የተመለሰች እህት ምልከታ ታክሎበት።

“When people were hungry, Jesus didn’t say, “Now is that political, or social?” He said, “I feed you.” Because the good news to a hungry person is bread.”

- Desmond Tutu
ሰሞንኛ ስለሆነ ብቻ ወያኔዎች እንኳን ደስ ያላችሁ። ቆራጡን የኢትዮጵያ ልጅ አንድአርጋቸው እጃችሁ ገባ።  ሰቆቃ መፈፀም እንደምትችሉ ስታሳዩን የመጀመርያ ጊዜ ባይሆንም  እንዲታይላችሁ የለቀቃችሁትን ፊልም አይቼላችሗለው። አንድአርጋቸውን ከመያዙ በፊት ስላየሁት በደንብ እንዳሰቃያችሁት ይታያል።  ሞያ ያደረጋችሁት በዜጎች ላይ ሰቆቃ መፈፀም ተሳክቷል ልትሉ ትችላላችሁ።  በግሌ እጨብጭቤያለው ብራቮ በሽተኛ ዘረኛ ውላጆች። የንዴት ነው ብላቸሁ ውሰዱት። ደግሞም የንዴት ነው።

እናንተም በማትክዱት  አንድአርጋቸው ምን አይነት ሰዎች እጅ ላይ እንደወደቀ ያውቃል። ስትይዙት ግን በፍራቻ አልሞተም። ሞተ እንዴ? ዋናውና ዋናው ጉዳይ  ይሄ ነው። ሌላው ሁሉ ግራ ከመጋባት የሚመጣና የተለመደ አካይስትነት ነው። ምን ለማለት እንደፈለኩ ይገባችሗል።

ልታውቁትና ግልጽ ሊሆንላችሁ የሚገባው ዜጎችን በማሰር፤ በመግደልና በማሰቃየት የሚለወጥ፤ የሚለውጠውም ነገር የለም። ለምን ብትሉ  አዎ አካይስቶች ነግሳችሁብናል። እናንተ እንደ አንድ ቡድን ተወስዳችሁ አላችሁ። በሌላው ጎራ ተጨቋኞች፤ መከራ የሚወርድብን፤  የተራብንና እኩይ ድርጊታችሁን በዝርዝር የምናውቅ በሚሊዬኖች ደግሞ አለን። ተፈጥሯዊም ስለሆነም ይሆናል መፈራገጣችንና እንቢኝ ማለታችንን ደግሞ የምናቆመው አልሆነም። እውነት ለመናገር እናንተ እስካላችሁ የሚቆምም አይደለም። በዚህ እንኳ ተስማሙኝና የተደጋገመና አርባዎቹን አመታት ያስቆጠረ ጭካንያዊ ድርጊታችሁ የሚያስቆመን ቢሆን ድሮ ሰጥ ለጥ ባሰኝን ነበር። አልሆነም። እንደውም እንቢታው እያደገ፤ እየሰፋና ጉልበት እያገኘ ነው። ሀብታሙ ባደባባይ አውጇል  “ እመኑኝ ይወድቃል”። እውነቱን ነው ትወድቃላችሁ። በረግጥም ይህ የታሪካችን ምእራፍ ፍፃሜ ይኖረዋል። ጥያቄ የሚሆነው ፍፃሜ የሚያገኘው እንዴት ነው የሚለው ነው?። እስካሁን  እንደታየው እንትናን ዘቅዝቃችሁ ጭስ ስላጠናችሁት፤ እነንትናን  አሸባሪ ብላችሁ ሰብስባችሁ ስላሰራችሁ ወይ  ብልት ስለምታልቡ አልሆነም። በዚህ ፍፃሜው ሊመጣ ካልቻለ ደግሞ   ፍፃሜው በቀረው በሁለተኛው አማራጭ በርግጠኛነት ይመጣል ማለት ይሆናል። ተጨቋኞች እኛ ስናሸንፍ። ሁሌም ሲሆን የነበረውም ይህ ነው። ያ እሲኪሆን እንቢተኛነቱ ይቀጥላል። እኛ የአገሪቷ ዜጎች ሁሉ ስንሆን። እናነተ ጥቂቶች መሆናችሁ ደግሞ ይሰመርበት።

እረሀብ በአገራችን ውስጥ አለ። በዚህ በአሁኑ ሰአት ምግብ ባይናቸው የሚዞር ሰለምግብ የሚብሰለሰሉና  እየራባቸው ያሉ ወገኖቻችን ብዙ ሚሊዬን ናቸው። በገበያው ማሻቀብ ምክንያት ኑሮውን ማሸነፍ ያቃተው ደግሞ አገሬው ሆኗል። አዎ አገሬው ነው።  አዲስአበባ ካሉ ሆስፒታሎች በአንዳቸው ውስጥ የሚሰራ ዶክተር ምርር ባለ ስሜት ያለኝ። “የሁለት ልጆች አባት ነኝ።  መቼም የተንደላቀቀ ኑሮ እኖር ነበር አልልሽም። ሞያተኛ እንደመሆኔ  ዘና ያላ ኑሮ ለምን አልኖርኩም ከሚልም እንዳይመስልሽ።  ዛሬ የኑሮውን ውድነት በሚከፈለኝ ደሞዝ መቋቋም አልቻልኩም። እንደውም በግልጽ ለምን አልነግርሽም።፡ በቤቴ ውስጥ ምግብ አዎ የምንበላው ችግር የሚሆንበት ጊዜ አለ”

ሌላዋ ሀኪም፤- መድሃኒት የዘዝንላቸው ታካሚዎች ተመለሰው መጥተው “ያዘዛችሁልኝን መዳሀኒት ሊገዛ የሚችል ገንዘብ የለኝም ይቀየርልን” ሲሉ ቁርጥ ባለ ይሉሻል። ይህ በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥምሽ እና የተለመደ ሆኗል። አንዳንዴ የላቸውን የገንዘብ መጠን አምስት ብር አስራ አምስት ብር ብቻ ነው ይሉናል።   ያላቸው ገንዘብ ሊገዛ በሚችልው መድሀኒት አይነት እንድንቀይርላቸው ይጠይቃሉ።  በታካሚዎች ጥያቄ መሰረት ለበሽታቸው እንደማይፈይድ እያወቅን ርካሽ በሆነና ብዙውን ጊዜ በማስታገሻ መድሀኒት እንቀይርላቸዋለን። በአሁኑ ጊዜ የበዙት ታማሚዎች ይታከማሉ እንጂ የትኛውንም ርካሽ የሚባለውንም እንኳ መድሀኒት ስናዝላቸው ስሌላቸው  አይገዙትም። የባሰባቸው እግር ላይ ወድቀው ይለምናሉ። ወድቀው ስል ላባባል አይደለም። እግር ላይ ወድቀው ዛሬ እዚህ እረዱኝ ነብስ አይደል ሙጭጭ ይላሉ። በይበልጥ  ጀማሪና የቤተሰብ ጣጣ የሌለባቸው ዶክተሮችና የሀኪም ቤቱ ሰራተኞች የበዛውን ደሞዛቸውን  ለበሽተኛ መዳኒት በመግዛት ተጨማሪ የኑራቸው አካል አድርገንዋል።  መስጠት ያለብን ግን ገንዘብ ብቻ እንዳይመስልሽ። በጠቃላይ በአገሪቷ ውስጥ በገዘፈ የመተኪያ ደም አለመኖር ታማሚያችንን ለማትረፍ ስነል ደማችንንም በተደጋጋሚ መስጠት ግድ ይለናል። እመኚኝ ደም በማጣት ብቻ ብዙ ዜጎች ናቸው የሚሞቱት።

 

ከናቴ ጋር ቤተ ክርሲቲያን ደርሰን ስንመለስ ስኳር መግዛት አለብኝ አለች። እቦታው ስንደርስ ወረፋው ለጉድ ነው። ዝናብ መዝነብም እየጀመረ ስለነበር ይቅርብን የሚያስጨምረውን ጨምረን ከውጪ እንገዛ አልኳት። የደላሽ ገንዘቡ ብቻ መቼ ሆነ ቸግሩ የት አግኝተሽ ነው የምትገዥው አለችኝ። ስኳር ሱቆች ውስጥ የለም? ብዬ ጠየኩ። ባጭሩ የለም ነበር መልሷ። ሁሉም ዜጋ የሸማቾች ማህበር አባል ነው። አውቃለው ከሶስትና ሁለት አመት በፊት አገር ቤት የነበራችሁ እንኳ ለማመን ይቸግሯችሗል። የዛሬይቷ አገራችን ግን ይህን ነው የምትመስለው። ባለራሽን። ዳቦው፤ ስኳሩ፤ ዜይቱ ትራንስፖርቱ ሁሉ ነገር በራሽንና በሰልፍ ነው። ህዝቡ እነዚህን ሰለፎች ብሶት መግለጫ ይላቸዋል። ሄጄ ብሶቴን ልግለጽ ብሎ ነው ዳቦ ሊገዛ የሚሄደው። ወደ ስራ ሲሄድ ብሶቴን ገልጬ ካዛ ወደ ስራ እሄዳለው ብሎ ይሰናበታል። ትራንስፖርት አጥቼ አይልም። ብሶት ስገልጽ ነው የሚለው።ሌላው በጣም በጣም የተለወጠው ነገር ህዘቡ ችግሩን ይናገራል። አገዛዙን በግላጭ ይቃወማል። ነገ ከነገ ወዲያ እነዚህ ሰልፎች ላይ  መፈክር ይዞ መጠበቁ ስለማይቀር እንዳይገርመን።

የአዲስ አባባ ወና መንገዶች በሙሉ ለባቡር ግንባታ ተብሎ ተዘግተዋል። ይሄንኛውን መንገድ ብቻ አፍርሰን እዚህ የሚሰራውን ስራ ከጨረስንና መንገዱን ላገልግሎት ከተከፈተ በሗላ ያንኛውን መንገድ ደግሞ እንዘጋለን። እስከዛውም ጊዜያዊ አማራጭ መንገድ ሊሆን እንዲችል ብሎ የሚጨነቅ ለህዘብ ከበሬታ ያለውና ጠያቂ ያለበት መንግስት ነው። ስላልታደልን ያሉን ስለ ስልጣናቸው ብቻ የሚጨነቁና አልመቸን በሎ የምንቃወማቸውን ዜጎች ያፍንልን ይሆናል ብለው ሶቆቃ ስለሚፈፅሙበት መንገድ የሚብሰለሰሉ  ናቸው።

ለማንኛውም በአንደኛው ቀን  የታክሲው ሹፌሩ  ወናዎቹ መንገዶች በሙሉ ስለተቆፈሩ ዙሪያ ጥምጥም በሆነ መንገድ መንደር ለመንደር ያዞረናል። የኮረኮንች መንገዱ ጎርበጥባጣነት ከመጨቅየቱ ጋር ምቾት ያለሰጣት ዘነጥ ያለች ተሳፋሪ “ይህ የሰፈሩ ሰዎች ስንፍና ነው። ምን አለ አዋጥተው ኩብል እስቶን ቢያስነጥፉ” ስትል በቀናነት ሀሳቧን ትሰጣለች”። በሞላው ሚኒ ባስ ውስጥ ያሉት ተሰፋሪዎች በሙሉ ድርሻ ባደረጉበት  አቢዬት አካሄዱባት ብል አላጋነንኩም። ከስንፍና ጋር ምን አገናኘው? በሚል ጥያቄ ጀመሯት። እየራበው ያለ ህዝብ ኬት አምጥቶ መንገድ ይስራ ብለሽ ነው?፤ ለጆቻችንን እንመግብ መንገድ እንስራ?። የደላሽ አሁን አዎ አሁን እኔ እየራበኝ ነው። ላባይ አዋጡ እያሉ ያስርቡናል አንቺ ደግሞ መንገድ ካልሰራችሁ በይ ምን አለብሽ፤ የማይገባኝ መንገድም እኛ የምንሰራ ከሆነ ለምንድን ነው ታክስ እያሉ የሚዘርፉን። ያልሰማሁት ውግዘትና የምሬት አይነት የለም። ልጅቷ መነሻ ሆነች እንጂ ምሬቱ አገዛዙ ላይ ነው ያነጣጠረው። ተሳፋሪዎቹን ገመገምኳቸው ከወጣት እስከ አዛውንት አሉበት። ሴቶች እንበዛለን። እርቦኛል ያለው ወንድሜ ሲወርድ ያለ ፌርማታዬ ተከትዬው ወረድኩ። አለቀሰ።

ካፌ ውስጥ ጨዋታ የጀመርኩት ቻይናዊ በጫወታ ጫወታ አገር ምድሩን ስላጥለቀለቁትና ገላቸውን ሸጠው ስለሚኖሩ ወገኖቼ መብዛት ያወራኝ ጀመረ። የሰው አገር ዜጋም ስለሆነ ሴትም ስለሆነኩ በመከላከል አይነት ኩሩ ህዝቦች ነን። ችግሩ የኑሮው መክፋትና በተበላሸ መንግስታዊ አስተዳደር ምክንያት እንደገዘፈ  በተቆርቋሪነትና በተከላካይነት አወራው። አስጨርሶኝ ያለኝ ያስደነገጠኝ ነበር። አውቃለው። ችግሩ አንቺ ችግር ከምትይው ግን የከፋ ነው።እንዳላበሰጫሽ እንጂ የበዙት ከመራብ ስለሆነ ጥያቄያቸው ብዙውን ጊዜ ከምግብ የሚያልፍ አይደለም። መንግስታችሁ የውጪ ምንዛሪ ማስገኛ አድርጎ እንደሚያየው ደግሞ አውቃለው። ይህቺ ከተማ በውጪ አገር ዜጎች ለስብሰባ ተመራጭነቷ ለምን ያደገ ይመስልሻል?። እያላገጠ ስለተሟላ አገልግሎት እናደይመስልሽ መብራትና ውሀ የሌለበት ከተማ። ሁሉም ከስራ ግዚያቸው በላይ ቀን ጨምረውና እረፍት ወስደው እነደሚመጡም አውቃለው። መሪዎቻችሁ ያልገባቸው እንዳልኩሽ የልጆቹ ጥያቄ ብዙውን ጊዜ ከምግብ አያልፍም። ከፈለግሽ ጥሩ ምግብ ለመብላት ብለሽ ውሰጂው። መንግስት አንደኛውን እንደታይዋን በመስታወት ውስጥ ቢያቆማቸው ይሻል ነበር። ደግሞም ታያለሽ በቅርብ ይህ መሆኑ አይቀርም አለኝ። ታይዋን ውስጥ መንግስት በመስታወት እንደሚያቆማቸውም አላውቅም። ሁሌ ብሰማውም ሴክስ እንዱስትሪ ተብሎ የሚጠራበት ምክንያትም እስከዛሬ  ዞሮልኝም አያውቅም። ይህን ከሰማው በሗላ ዝም ማለትንና መሰናበትን ነው የመረጥኩት። ምንስ ላወራ እችላለው።

ድግግሞሽ እንዳይሆን ብዬ ነው እንጂ በኑሮው ውድነት የተነሳ ስለሚራቡ ዜጎች የመንግሰት ሰራተኛው ጋር፤ አስተማሪው ጋር፤ ወታደሩ ጋር፤ ተማሪው ጋር ሂዱ የሚሰማው በግልፅ ይህን መከረኛ ሆድ መሙላት አልቻልንም የሚል ብሶት ነው። እሮሮው በዝቷል። ዜጎች ሊሸከሙት ከሚችሉት በላይ ስለሆነ ደግሞ በግልጽ ነው መራባቸውንና አገዛዙ ላይ ያላቸውን ጥላቻ የሚናገሩት። እንደድሮው ካጥር ውጪ ሆኖ እንዲሰማ ድምፅን ከፍ አድርጎ የሚለምን የለም። ሁሉ በተቸገረበትና በራበው አገር ሲደክማቸው ይሄዳሉ ብላችሁ ዝም ልትሉ ነዋ። በር ይንኳኳል ሲትከፍቱ እርቦናል የሚሉ ዜጎች ናቸው። ወጣቶች፤ ሱፍ ለባሾች፤ አሮጊቶች፤ ህጻናት ሁሉንም አይነት ዜጎች አሉበት።  በር መክፈት አስፈሪ ሆኗል። አሳቢ ለሆነ ዜጋ ይህ ጉዳይ ወዴት እንደሚያመራ ለመገመት ከባድ አይሆንም። እኔ እግዚያብሄር ይርዳን ነው የምለው።

ተመስገን ደሳለኝ ህዝባዊ ቁጣው ከቀጣዩ አመት መስከረም የሚያልፍ አይመስለኝም ይላል። በነገራችን ላይ በቅርብ ይታሰራሉ ብዬ ካሰብኳቸው ውስጥ ተመስገንና ይልቃል ቀርተዋል። መቼም ተረስተው አይደለም። ለምን ብለን እንድንጠራጠር መሆኑ ነው። እስከዛሬም እኛም ያው እየሆንን እንጂ የወያኔ ነገር ትናንትም ለከርሞም ያው ነው።  ለማንኛውም  ቸኩዬ ሳይሆን ከምቃርመው የዜጎች ችግርና ምሬት ተነስቼ ይህ ጉዳይ እስከዛ ጊዜ የሚቆይ አልመሰለኝም። ተጨማሪ ሊሆኑ በሚችሉ ሌሎች  ምክንያቶች ለምሳሌ- የቀጣዩ ምርጫ የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ መጠናከር፤ ቃታ መሳብ የጀመሩት ቁጥራቸው እየጨመረ መሄድ። የእስልምና እምነት ተከታይ ዜጎቻችን የጀመሩት ትግል ወይ ንቅንቅ መሆኑ። ያበረ ባይሆንም አማራና የኦሮሞ ክልሎች ውስጥ የሚታየው ከስርና መሬት የረገጠ መነቃነቅ። ስልጣኑን እንዲጠብቁለት መሳርያ ያስያዛቸውን ጨምሮ ከራሱ ከውስጡ  የሚሰሙት ጉርምርምታዎች መጨመር። ህዝብ በራሱ ጊዜ ውሀ አጣን። መብራት እያገኘን አይደልም። የኑሮውን ውድነት መቋቋም አልቻልንም። ቤታችንን አታፈርሱም። እያለ ብሶቱን አደባባይ ይዞ መውጣትና መተናነቅ መጀመሩ።  ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን በማፈኑ ምክንያት ህዝቡ ውስጥ ከተፈጠረው ያልተገመተ አይነት የመጠቃትና የቁጣ ንቅናቄ  ተጨማሪ ሊሆኑ በሚችልበትና የትግል ጓዶቻቸው ጦር ከማደራጁቱ ጎን ለጎን ህዝብን ማንቀሳቀስና መምራቱን እንዲሁ የተጨቆኑ ዜጎችን ለጋራ ግብ ሲባል መመራትን ማለማማዱ ወሳኝ ስለሆነ መላውን እያሰደጉት በመሆኑ በሌሎችም  ብዙ ምክንያቶች ተደማምረው ጊዜውን ከመስከረም ሊያፈጥኑት ይችላል።

ለማሳሰብ ያህል ለለውጥ በሚደረግ ትግል ወሳኝና ዋነ የሆነውን ምሬትና ቁርጠኛነት ከምርጫ 97 በሗላ በነበሩት አመታት በነበረው የዜጎች  በቀላሉ የማይንበብና የማይገለፅ ፈዛዛ ስሜት ተንተርስን ጊዜና ዝግጅት ለሚፈልግ ትግል እያቀድን ያለን የሮሮው ደረጃ ጋር እኩል እየሄድን አይደለም።  የዜጎች የምሬት ደረጃ መብዛት መጽአዊ በሆነ ሁኔታ ሊያስነሳ ለሚችለው ቁጣን ለመምራት ተመጣጣኝ ዝግጅት  ያላደረግን በድጋሚ ስህተት እንዳንሰራ። በይበልጥ በውጪ ያላችሁ  አሁንም መምራቱን መረከባችሁ ግድ ካለ ባስፈላጊው ሁኔታ ዝግጁ በቶሎ ሁኑ። ከአመት ወይ ከስድስት ወር በፊት ባለ መረጃም እንኳ እየሰራችሁ ካላችሁ የምሬቱ ፈጣን እድገትና የችግሩ መክፋት እንደወረርሽኝ በየቀኑ በፍጥነት እየጨመረ እየሄደ ስለሆነ በቂ ዝግጅት ሳይደረግበት እንዳይፈነዳ። አገር ቤት ያላችሁም አብራችሁና ውስጡ ስላላችሁ እንደ ህፃን እድገት ወጣ ገባ እያለ የምሬቱን ደረጃና ስፋቱን በቀላሉ ሊያይ እንደሚችለው ዜጋ ያህል በበቂ ላይታያችሁ የሚችልበት ሁኔታ እንዳይፈጠር።

በትክክል ሁሉ ነገር ወደሰላማዊ ህዝባዊ እንቢታ እያመራና እንዲሁ ሁሉ ነገር ለዚሁ አጋዥና ተጨማሪ ጉልበት እየሆነ መሄድ ቀድሞ የታያቸውና እየወተወቱ ያሉ ዜጎች አሉ።  ሰላማዊ ህዝባዊ እንቢታ ሌላ ምንም አይደለም። ሰዎቹ ቤተመንግስት እንደተቀመጡ  ቀርቅበናቸው በሌላ መመራት መጀመር ነው። አለቀ ይህው ነው። በዚህ ሂደት መሪዎቻችን አዛው ሆነው ሊመሩን እስከቻሉ እንመራለን። ዘሬ ይህን አድርጉ ይሉናል እናደርጋለን፤ ነገ ደግሞ ይህን አታድርጉ ይሉናል ሁላችንም አናደርግም።

ዜጎች በዋናነት አብረን  ግንዛቤ  ልንወስድበት የሚገባ  ቁም ነገር ግን መጀመሩና መመራቱ ብቻ ሳይሆን  ከምንታገለው ሀይል አፋፋሽነት አኳያ እንዴት ይቀጥል የሚለው ቁም ነገር ነው። መሪዎቻችን በግላጭ እዛው ሆነው አርጉ ያሉንን እንደምናደርግ። ሳይመች ቀርቶ ህቡ ገብተው ሲሉንም እንዲሁ እናደርጋለን ማለት ነው። ለዚህም አላመች ብሎ ደግሞ ውጪ ላሉ ድርጅቶች አመራሩን ካቀበሉት ወይ ከተቀበሉት እንደዛው ባለ አደራ መሪዎች አድርጉ ሲሉን ማድረግ እንዳለበን ማወቁ የዋና ዋና ነው። ያሄ ነው ትግሉን አስቀጥሎ ከሚፈለገው ግብ የሚያደርሰን። ተመራጩ ባንድ ያበረ ሁሉ ዜጋ ሊታዘዘው የሚችል ድርጅት ቢሆንም አስፍተነው አመኔታችንን የሰጠነው ግለሰብም ወደ ነጻነት ሊመራን  ይችላል ብለን እናስብ።

እኔም ግጥም አድርጌ አንድአርጋቸው ነኝ።

 

Comment

 

 

 

↧

የግለሰብ ነፃነት ሲገፈፍና መብቱ ሲረገጥ በለሆሳስና በዝምታ ማለፍ ውጤቱ ሽንፈት ይሆናል፦

$
0
0

ዘረኛው የወያኔ ቡድን የሥልጣን ርካቡን በጠመንጃ ኃይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ስለደረሰው ግፍ፤ሥቃይና መከራ እንዲሁም አገሪቱን በቋንቋና በጐሣ ሸንሽኖ ህልውናዋን እየተፈታተነ ለመሆኑ በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ ተገልጿል።

የዚህን ጠባብ ብሄረተኛ ቡድን እኩይ ተግባር በቡድንም ሆነ በተናጠል በብዕራቸው የተዋጉ፤በድርጅት ዙሪያም ተሰባስበው ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ትግል ያካሄዱ ኢትዮጵያውያን በነቂስ እየተለቀሙ ለእሥር ተዳርገዋል።ከፊሉንም ቤት ይቁጠረውና የደረሱበት ሳይታወቅ እንደወጡ ቀርተዋል።

ሰሞኑንም ይህ መንግሥት ነኝ ባይ ጠባብ ብሄረተኛ ቡድን ከየመን መንግሥት ጋር በመመሳጠር ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብትን ድንጋጌ ጥሶ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የግንቦት ሰባት የፍትህ፤የነጻነትና የዴሞክራሲያው ንቅናቄ መስራች አባልና የንቅናቄውን ዋና ጸሐፊ በማገት ጠልፎ እንደ አንድ ነጻ ዜጋ በየትኛውም አገር የመዘዋወር መብታቸውን ረግጦ በማፈን ወደ ኢትዮጵያ ውስዶ እያሰቃያቸው ይገኛል።

መብቴ ተረገጠ፤ ነፃነቴ ተደፈረ፤በሀገሬ ጉዳይ የመናገር፤የመጻፍና የመደራጀት ዜግነታዊ ሕልውናየ ተጣሰ…ወዘተ ብሎ የሚያምን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከምን ጊዜውም በላይ ይህ የሰሞኑ በወንድማችን ላይ የተፈፀመው ድርጊት አስቸኳይ መልስ የሚጠይቅ ፈተና ከፊቱ ተደቅኖ ይገኛ

ል።ይህን ፈተና ለመጋፈጥ የማይሻ ሁሉ የዘረኛውና የጠባብ ብሄረተኛው የወያኔ መንግሥት ጋሻ ጃግሬ ወይንም ከዚህ ወንበዴ ቡድን ተጠቃሚ የሆነ ብቻ ነው።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መባቻ ላይ የሂትለርን አገዛዝ አጥብቆ የሚያወግዝ ማርቲን ኒሞለር የተባለ ጀርመናዊ የፕሮቴስታንት ቄስ በወቅቱ ሰፍኖ የነበረውንና ናዚስቶች ደረጃ በደረጃ ይፈጽሙ የነበረውን ግፍና መከራ አስመልክቶ የተናገረውን ያስታውሷል፦ይኸውም

“የናዚ አገዛዝ በመጀመሪያ በሶሻሊስቶች ላይ ሲዘምት ምንም አልተናገርኩ ምክንያቱም እኔ ሶሻሊስት ስለአልነበርኩ ።ቀጥለውም በትሬድ ዩኒየን ላይ የግፍ በትራቸውን ሲሰነዝሩ አልተናገርኩም።ምክንያቱም እኔ ትሬድ ዩኒየኒስት አልነበርኩምና። ከዚያም በኋላ በይሁዶች ሲነሱ ዝም አልኩ ምክንያቱም እኔ ይሁዲ አልነበርኩምና።በመጨረሻም ወደ እኔ መጡ ሆኖም ግን ስለ እኔ የሚናገር የቀረ ማንም አልነበረም።”

አሁንም ይህ በአንድ ታጋይ ኢትዮጵያዊ ላይ የተፈጸመውን ዘግናኝ ድርጊት መግለጫ በማውጣት ፤ሰልፍ በመሰለፍ ብቻ ልንወጣው አይቻለንም።በመሆኑም እኛ በኮሎምቦስ ኦሀዮ የምንገኝ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የደረሰው በደል በዝምታና በለሆሳስ ልናስተናግደው በጭራሽ አይቻለንም።ይህ ዓይነት መረን የለቀቀ ግፍ ተራ በተራ በእያንዳንዱ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችና የዴሞክራሲ ጠበቃዎች ላይ ከመድረሱ በፊት በድርጅት መጠናከርንና በመረጃ ልውውጥ ውጤታማ ሆኖ መገኘት አስፈላጊ እንደሆነ የወቅቱ አጠቃላይ ሁኔታ ስለሚያሳይ ለእውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች የሚከተለውን ጥሪ አቅርበናል።

vየየመን መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ የፈጸመችው አሳልፎ የመስጠት ክህደትን ማጋለጥ። የእንግሊዝ መንግሥት የዜጋዋን መብት ለመታደግ በመጀመሪያው ረድፍ መገኘት ስላለባት የሚፈለገውን ሁሉ ስልት በመጠቀም ለጉዳዩ ትኩረት እንድትሰጥበትጫና ማድረግ።

 

vበውጭ አገር የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በያለበትና በሚገኝበት ሥፍራ የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅሞ ለተወካዮች ምክር ቤትና ለሴነተሮች ለማሳወቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ።አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ ዜጋ መሆናቸው እየታወቀ የየመን መንግሥት ዓለም አቀፉን የሰብዓዊ መብት ሕግጋትን ፤ የኮመን ዌልዝ ኔሽንን ፓክት ጥሶ ለዘረኛው መንግሥት አስልፎ የሰጠበትን ምክንያት አጥጋቢ ምላሽ ከሁለቱም መንግሥታት እንዲሰጥ አበክረን እንጠይቃለን።

 

vየወያኔ የዜና አውታሮች የሚያሰራጩትን ነጭ ወሬ የሚያስተጋቡ ግለሰቦች እንዳሉ ይታወቃል። እነዚህ ግለሰቦች  በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚያሰራጩት ወሬ እርባና ቢስ ቢሆንም የአንድነት ኃይሉን የሚጎዳ በመሆኑ ከዚህ ጸረ-ሕዝብ ተግባራቸው መቆጠብ ይኖርባቸዋል። በሌላም በኩል በየአካባቢያችን የሚገኙ የዘረኛው መንግሥት ሰላዮች፤ደጋፊዎችም ሆነ ተባባሪዎች የቆሙበት ዓላማ ርካሽ ሀገርንና ወገንን የሚጎዳ በመሆኑ በመረጃ ላይ  የተደገፈ ተግባራቸውን በማረጋገጥ ከማህበራዊ ግንኙነት ማግለል በእነርሱ በኩል የሚከናወኑ ማናቸውንም ነገሮች ቦይ ኮት ማድረግ።

 

 

vየአንድነት ኃይሎ ተበታትኖ መገኘቱ ለጥቃት በር እንደከፈተ ይታመናል በመሆኑም ሁኔታው ትግላችንንም እየጎዳው የጠባብ ብሄረተኛውን የወያኔን እድሜም እያራዘመው በመገኘቱ የአንድነት ኃይል ነን ብለው የሚያምኑ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ንቅናቄዎች በአስቸኳይ በመገናኘት የኢትዮጵያ አንድነት የተቃዋሚ ኃይልን መመስረት ይገባቸዋል።የዚህ የኢትዮጵያ አንድነት ኃይል መመሥረት ለመንግሥታትም እንደ አማራጭ ኃይል ሆኖ ስለሚቀርብ ይህንኑ ዓላማ ገቢራዊ ለማድረግ የየድርጅቶችም ሆነ የየስብስቦቹ መሪዎች ከዚህ በፊት በባዶ ጉዳይ የሚያናቁራቸውን ሁሉንም ነገር ከበስተጀርባቸው በመተው ለአዲስ ትንሳኤና የድል ጉዞ እንዲነሱ ታፍራና ተከብራ በኖረችውና በእኛ ዘመን ለውርደት በተዳረገችው ታላቋ ሀገራችን በኢትዮጵያ ስም እንጠይቃለን።

 

vበወንድማችን ላይ የተፈፀመውን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በጥሞና ተመልክተን መደረግ ስለሚገባው ልዩ ልዩ የትግል እንቅስቃሴ ስልቶችን የሚነድፍ፤ የሚያጠናና በተግባር የሚተረጉምና የሚመራ ውጤታቸውንም የሚገመግም፤ ራሱን የቻለ በስደት ላይ የሚገኘውን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያሳትፍ አንድ ለስደተኛው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ማዕከል መፍጠር እንደሚገባው እናምናለን።የዚህ ማዕከል መፈጠር በተለያየ መልክ ጸረ-ሕዝብ የሆነው ህወሃት በተቃዋሚ ኃይሎች ላይ የሚያደርሰውን በደል፤ ሰቆቃና መከራ በባለቤትነት ወስዶ መምራት ይሆናል።ይህንን ሀሳብ ግምት ውስጥ በማስገባት ዳብሮ አንድ ውጤት ላይ እንዲደርስ አበክረን እንጠይቃለን።

 

ኢትዮጵያ ለዘላዓለም ትኑር!!

 

በአሸባሪውና ጠባብ ብሄርተኛው ወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ ህዝባዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ትግትነባለች!!!

 

Ethiopians in Columbus Ohio

 

Free andargachew tsige LG

↧
↧

የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!

$
0
0

አምሳሉ amsalugkidan@gmail.com

amsalu

አምሳሉ

ይሄንን ጽሑፍ ታች አምና ከጉራፈርዳና አካባቢው አማራ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይዘው እያለ ሕጋዊ ሆነው የየክልሉ መንግሥት አውቋቸው በሥርዓቱ ግብር እየከፈሉ እየኖሩ የነበሩ ምስኪን ገበሬዎችን “ሕገ ወጥ ሰፋሪዎች”  በሚል ሕገ ወጥነታቸው አግባብነት ባለው የሕግ አካል (ፍርድቤት) ክስ ተመስርቶባቸው ሳይረጋገጥባቸው በጅምላ በግፍና በሕገ ወጥ መንገድ ንብረታቸውን ሁሉ ተወርሰው እንዲወጡ በተደረገ ጊዜ ጽፌው ለጥቂት መደበኛና ኢመደበኛ (Conventional and Social Media) ልኬው ነበር እስከማውቀው ድረስ ለሕዝብ ይፋ አድርገውት ያስነበቡት ወይም ያስደመጡት አልነበሩምና ሕዝብ ሊያውቃቸው የሚገባ በርካታ ቁምነገሮች ስላሉት እንዳያመልጣቹህ በማሰብ ወደ እናንተ አድርሸዋለሁ መልካም ንባብ፡፡

የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ መንግሥታዊ (official) ቋንቋ ማለትም ከውጭ መንግሥታትም ይሁን ከሀገር ውስጥ ነገሥታት መልዕክት ይጻጻፉ የነበረው የቤተ መንግሥት ሥራቸውን ይሠሩ የነበሩት በአማርኛ ነበር፡፡ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ትግሬ ሆነው ሳለ ይሄንን ማድረጋቸው ቅር ያሰኛቸው የትግሬ ሹማምንት በራስዎ በትግርኛ ቋንቋ የማይጠቀሙት ለምንድን ነው? ብለው ጠየቋቸው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛም አማርኛ የአክሱማዊያን ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ለእነሱ በማስታወስ ይህንን መለወጥ እንደማይኖርባቸውና እንደማይገባም በመግለጽ ለሹማምንቶቻቸው ምላሽ ሰጡ፡፡ ይህ አክሱማዊያን አማሮች ነበሩ ወይም አማርኛ የእክሱማዊያን ቋንቋ ነው የሚለውን ታሪክ አክሱም አካባቢ ሄዳችሁ ብትጠይቁ የአክሱም ሰዎች በትውፊት ይዘውት እንደመጡ ማለትም አባቶቻቸው አማርኛ የአክሱም ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ይነግሯቸው እንደነበር ይገልጹላቹሀል፡፡ በላይ ግደይ የተባሉ ጸሐፊም “አክሱም” በተባለው መጽሐፋቸው ይሄንን ገልጸውታል፡፡

ታዲያ ጉዳዩ እንዲህ ከሆነ አማራን ወይም አማርኛን ከአክሱምና አከባቢዋ ማንና እንዴትስ አጠፋው ለሚለው ተገቢ ጥያቄ ታሪክ አጥኝዎችና ተመራማሪዎች እስከአሁን አልደረሱበት ሆኖ ይሁን? ወይም አውቀውት ነገር ግን በአንድም በሌላም ምክንያት መግለጽ ስላልፈለጉ? ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡ ከዚህ አኳያ ይህ ጽሑፍ እስከ አሁን ያልተገለጸ ከታሪክ ኩነት መዞ ወይም ገልጦ መረጃ ይሰጣል፡፡

ጥንት ቋንቋቸው አማርኛ ኖሮ ዛሬ ላይ ቋንቋቸው ትግርኛ የሆነ አክሱሞች ብቻ አይደሉም፡፡ ከዚያው ከአጠገባቸው የወልቃይትና ከፊል ጠገዴን ሕዝብ ታገኛላቹህ፡፡ የእነኚህን አካባቢ ሰዎችን ማንነታቸውን ብትጠይቋቸው አማራ ጎንደሬ እንደሆኑ ይነግሯችኋል፡፡ የሚናገሩት ቋንቋ ግን ትግርኛ ነው፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሀገራቸውን ከጎንደር ቆርጦ ወደ ትግራይ ሲቀላቅልባቸውም ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደተቃወሙ ነው፡፡ በተለያዬ ጊዜ በውጭም በሀገር ውስጥም ያሉ ወልቃይቶች የዚህ መንግሥት አመራርና ነባር ታጋይ የሆኑትም ሳይቀሩ ለመንግሥት ሥራ እውጭ ባሉበት “እኛ ትግርኛ ስለተናገርን ብቻ እንደ ትግሬ ልንቆጠር አይገባም ማንነታችን ይጠና እኛ ትግሬ አይደለንም” በማለት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተደጋጋሚ በተቃውሞ ሰልፉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

የአክሱም ነገሥታት አማርኛ የቤተመንግሥት የሚስጥር ቋንቋ አድርገው ከመፍጠራቸው በፊት ቋንቋቸው ሙሉ ለሙሉ ግእዝ ነበር፡፡ አማርኛ ሊቀድም እንደሚችልም የሚያመላክቱ አንዳንድ ጠቋሚ ነገሮችም አሉ፡፡ የአክሱም ነገሥታት ስሞቻቸውን ያዬን እንደሆነም በተለያዩ ምክንያቶች በባዕዳን ማለትም በዕብራይስጥ፣ በጽርእ፣ በሮማይስጥ ስሞች ከተጠሩት ውጪ ስሞቹ ግእዝ ካልሆኑ አማርኛ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎቹ የጠፉ ወይም የተረሱ የአማርኛ ቅላት ሆነው ለመረዳት የሚያስቸግሩ አማርኛዎች ቢበዙም አሁንም ድረስ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ባሉ ቃላት የሚጠሩ የአክሱም ነገሥታት ስሞች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ጥቂቶቹን ብናነሣ ምኒልክ (ምንይልክ) ቅ.ል.ክ 982-957፣ ዙዋሬንብረት 1ኛ ቅ.ል.ክ. 599-558፣ ዙዋሬንብረት 2ኛ ቅ.ል.ክ. 276-260፣ ግርማአስፈር 77-86 ዓ.ም፣ አርፍድ (ገ/መስቀል) ከ357-361 ዓ.ም፣ ወሰንሰገድ 557-572 ዓ.ም፣ ጉም 693-717 ዓ.ም፣ አስጎምጉም ከ717-722 ዓ.ም፣ ለትም ከ722-738 ዓ.ም፣ ተላተም ከ738-759 ዓ.ም፣ አይዞር ለ6 ሰዓታት፣ ውድማአስፈር ከ787-817 ዓ.ም፣ አንበሳውድም (አንበሳአውድም) ከ882-902 ዓ.ም ድልነአድ 902-912 ዓ.ም፣ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ከላይ እንደገለጽኩት ሕዝቡ በዘር አማራ ሆኖ እንዴት ባለ ሁኔታ ይገዛ ቋንቋቸውን አጥፍተው ወይም ትተው ቋንቋቸው ያልነበረውን ትግርኛን ቋንቋቸው ሊያደርጉ እንደቻሉ እንይ፡፡ ይህ ድርጊት ከመጀመሪያውና ለ40 ዓመታት በተከታታይ ያለ ሟቀረጥ ከተፈጸመው እጅግ ከባዱና አሰቃቂው በአማራ ሕዝብ ላይ ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ ዘመኑ 842 ዓ.ም 882 ዓ.ም ድረስ በጨካኟና በክፏዋ “እሳቶ ወይም ጉዲት” በመባል በምትታወቀዋ ዮዲት የተፈጸመ ነው፡፡ የዓረብና የምዕራቡ ዓለም ታሪክ ጸሐፍት “ክርስትና የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ በ አራተኛው መቶ ክ/ዘመን በአብርሃና አጽብሐ ወይም በኢዛናና ሳይዛና ከመታወጁ ጋራ በተያያዘ በመጨረሻ በአማራ አሸናፊነት እስኪጠናቀቅና ተሸናፊዎቹ ፈላሾች በሀገሪቱ አርሶ የመጠቀም መብት ተነፍገው በእጅ ሞያና በጉልበት ሥራዎች የአማሮች አገልጋዮች እንዲሆኑ እስኪፈረድባቸው ጊዜ ድረስ በአማሮችና በፈላሾች (ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩ ቤተ እስራኤሎች) ማለትም አይሁዶች መሀከል እስከ ዮዲት ጊዜ ድረስ ለአምስት መቶ ዓመታት የዘለቀ ጦርነት ተደርጓል” ሲሉ ጽፈዋል፡፡ ልብ አድርጉ “በአማሮችና በፈላሾች” መካከል፡፡

የዮዲት ጉዲት ዘመን ግን ፈላሾች ጦርነቱን አሸንፈው ያሻቸውን ማድረግ የቻሉበት በኢትዮጵያ ታሪክ ሊገለጽ ከሚችለው በላይ ሀገሪቱ ከዚያ ዘመን በፊት የነበራትን ሥልጣኔ የሚያሳዩ ቅርሶችን ከጥቂት ምልክቶች በስተቀር ወድሞ የጠፋበት ዘመን ነበር፡፡ በዚያ ዘመን የክርስትና መታወጅ መጀመሪያ ግጭት ፈጠረ እያደር ግን በሀገሪቱ የአይሁድና የክርስቲያን ቀጠና ለይቶ ሀገሪቱን ለከባድ ኪሣራ ለዳረገና እጅግ ለተራዘመ ጦርነት ምክንያት ሆነ፡፡ ከ500 ዓመታት በኋላም አይሁዶች ወይም ፈላሾች በለስ ቀንቷቸው ጦርነቱን አሸንፈው በገነኑበት በ40 ዓመታት በዮዲት ጉዲት ዘመን ነበር አማሮችን በአክሱምና አካባቢዋ በተቻላትም መጠን በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል እንዲጠፉ ያደረገችው፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለነገሩ ወደ ታችም ወረድ ይላል አንድ ትውፊታዊ አባባል አለ እሱ ምንድን ነው? በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል “አማራ” ማለት የዘር ስም ብቻ አይደለም የሃይማኖትም ስም ጭምር እንጂ፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሰዎች በዘር ትግሬ ወይም ሌላ ቢሆኑም ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ ክርስቲያን ነኝ ለማለት “አማራ” ነኝ ይላሉ፡፡ ይህ አንድ ዐቢይ ነገርን ግልጽ አድርጎ ያሳያል፡፡ በዚያ ዘመን ይደረግ የነበረው ጦርነት በማንና በማን መሀከል ይደረግ እንደነበረ፡፡

በመሆኑም ዮዲት ጉዲት ጠላቶቿ አድርጋ የተነሣችባቸውን በዘርና በሃይማኖት “አማሮች” የሆኑትን አክሱማዊያንን ከመላ ሀገሪቱ ያለ ርህራሔ በጨከነና በማይታጠፉ ውሣኔ ጨርሶ የማጥፋት ዘመቻዋን በመላ ዘመኗ (ለ40 ዓመታት) ስትፈጽም በነበረበት ዘመን አማሮች ከዚያ መቅሰፍት ለመዳን ለመትረፍ ወይም ለማምለጥ ከመሰደድ በመለስ የነበራቸው ብቸኛ አማራጭ አማራነታቸውን ማስተባበል ወይም አማራ እንዳልሆኑና ትግሬ እንደሆኑ ለአጥፊዎቻቸው ለዮዲት ጉዲት ሠራዊት መግለጽ ነበር፡፡ ይህ የመከራ ዘመን የአንድ ትውልድን ዘመን (33 ዓመታት) ጨርሶ የቀጣዩን ትውልድ ዘመንም አጋምሶ ስለነበርና ዮዲት ጉዲት ድል ከተመታችም በኋላ ያ መራራ መከራ ደግሞ ተመልሶ ላለመምጣቱ እርግጠኛ ያለመሆን ሥጋት ችግር እንዲህ ነበርን ከሚለው ትውፊታዊ ውርስ በቀር የአክሱምና የአካባቢዋን ሕዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከማንነቱ ማለትም ከአማራነቱና ከቋንቋው አለያይቶት ሊቀር ቻለ፡፡

ከዚያም በኋላ የቤተክርስቲያንና የሀገራችን ታሪክ ጸሐፍት በሰዓቱ ግልጽ ሆኖ የሚታየውና የሚታወቀው ነገር ልክ በእነሱ ዘመን በግልጽ እንደሚታወቀው ሁሉ በኋላ ዘመንም እንደዚያው በግልጽ ታውቆ የሚቀጥልና ዛሬ ያለው ያ ችግር የፈጠራቸው የታሪክ ባለቤት ማንነት ያለመታወቅና ለተሳሳተ ግንዛቤ የሚዳርጉ ክፍተቶች በኋለኛው ዘመን ላይ የታሪክ መሳከር ወይም መጣረስ ሊያስከትል እንደሚችል ባለመገመታቸው ጦርነቱ ሃይማኖታዊ እንደነበረ ዮዲት ጉዲት በቤተክርስቲያን በሕዝቡና በሀገሪቱ ላይ ያወረደችውን መዓትና ጥፋት እንጂ በአማራና በፈላሻ መሀከልም እንደነበረ አጉልተው ወይም ግልጽ ባለ ቋንቋ ሳይገልጹት ቀርተዋል፡፡

እንግዲህ ይህ ታሪክ ማለትም የዮዲት 40 ዓመታት ዘመን፤ አይደለም በሀገራችን በውጭ ጸሐፍት ሳይቀር በሚገባ የሚታወቅ አሳዛኙ የታሪካችን ገጽታ ነው፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከያኔያን (አርቲስቶች) ሳይቀሩ ንቁ ተሳታፊ ሆነው እየተንቀሳቀሱበት ያሉበት በመጽሐፍ ቅዱስ እንዳልሞተና በእሳት ሰረገላ እንደተነጠቀ የተገለፀው ነብየ እግዚአብሔር ኤልያስ ሰው እንደመሆኑ በዳግም ምጽአት ዋዜማ ሞትን ለመቅመስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመጣ በትርጓሜ መጻሕፍት በግልጽ ተጽፎ እያለ ነብዩ ኤልያስ ኢትዮጵያን ሊታደግ በሁለት አፉ የተሳለ ሰይፍ ይዞ መጥቷል የሚሉ የሐሳዊያን ቡድን ያሰራጨው መረጃ ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ የሚታወቁ እውነቶችን በተቃራኒው በመገልበጥ በፈጠራ ታሪክ መጥፎውን መልካም አጥፊውን ገንቢ ኃጥኡን ቅዱስ እንደነበሩ በማበል ፈጽሞ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ታሪክን የማጠፋፋት ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡

ለምሳሌ በዚህች ሀገር ላይ ያንን ሁሉ ጥፋት በማድረሷ ታሪክ የሚያውቃትን ዮዲት ጉዲትን ቅድስት እና ሠማዕት ናት እንጂ አጥፊ አይደለችም ይላሉ፡፡ እሷን ብቻም ሳይሆን በዐፄ ዘርዓያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በኑፋቄአቸው ወይም በክህደታቸው ምክንያት ንጉሡ የቀጧቸውን ቤተክርስቲያን ያወገዘቻቸውን መናፍቃንን ማለትም ደቂቀ እስጢፋዎችን ከሀዲያን መናፍቃን ሳይሆኑ ቅዱሳን ሠማዕታት ናቸው በማለት በጠራራ ፀሐይ በሀገሪቱና በቤተክርስቲያን ታሪክ ላይ አስገራሚና አስደንጋጭ እጅግ ኃላፊነት የጎደለው የጥፋትና የክህደት ደባውን በመተብተብ ላይ ይገኛሉ፡፡ አንድ የዚህ ቡድን ሌላ ክንፍ ሊሆን እንደሚችል የሚገመት በመንግሥትም ድጋፍ የሚደረግለትና የብዙኃን መገናኛ ሽፋን እየተሰጠው ያለ ሌላ ቡድን የዐፄ ዘርዓያዕቆብንና የደቂቀ እስጢፋን የጥል ጉዳይ ምክንያት ዛሬም ባለው የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ማረጋገጥ የሚቻል ሆኖ እያለ ጎዳዩ ሃይማኖታዊ እንዳልነበረና ፖለቲካዊ እንደነበር ጸቡ የአማራና የትግሬ እንደነበር አድርጐ በሰፊው በመለፈፍ ላይ ይገኛል፡፡ የእነዚህ ሁለት የሐሳዊያን ቡድኖች በአንድ ወቅት አንድ ዓይነት መልዕክትና አቋም ይዘው ብቅ ማለት እንዲሁም በስውር ጥቅሙን ሊያስጠብቁለት የፈለጉት አካል ማንነትና ሌሎች ነገሮች ሲታይ ከእኒህ እንቅስቃሴዎች ጀርባ ይህ የአገዛዝ ሥርዓት መኖሩን ይጠቁማል፡፡

እዚህ ላይ አንድ ገጠመኝን ብናገር ነገሩን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ አንድ ድንግላዊ ነኝ የሚል ግን መነኩሴ ያልሆነ በቅቻለሁ በደመና ተጭኘ ኢየሩሳሌምን ጨምሮ የፈለኩበት ሀገር እመላለሳለሁ ከተሠወሩ ቅዱሳን ጋርም እገናኛለሁ ከሚል ሰው ጋር ጓደኞቼ አስተዋወቁኝ ለጊዜው በጓደኞቼ ወሬ ተሞልቼ ስለነበር እውነትም የበቃ ከቅዱሳን አንዱ መስሎኝ ነበር፡፡ ይህ ሰው እንደላይኞቹ ቡድኖች ሁሉ ዮዲት ጉዲትንና ደቂቀ እስጢፋን የሚያወድስ ከመሆኑም በላይ ትንቢት ነው እያለ የሚያወራው የዚህን ሥርዓት ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችል መልኩ ቀምሮና አበጃጅቶ ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን እየተሠራ ያለውን ደባ ለመግለጽ ስለወደደ ይህ ሰው ማን እንደሆነ የማውቅበትን ጥሩ አጋጣሚ ፈጠሮ እንዳውቅ አደረገ፡፡ እናም ይህ ሰው ድንግላዊ ሳይሆን የቤተሰብ ኃላፊ መሆኑንና ሥራውም እራሱን እየለዋወጠ በየገዳሙና በየጸበሉ እየዞረ የሚሰልል “የመንግሥት” መረጃ ወይም ሰላይ መሆኑን ደረስኩበት፡፡ እንግዲህ እነኝህ ሰዎች ለምን ዓላማ የቱን ያህል ርቀት እንደሚጓዙ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶኛል፡፡

yodit-300x184ወደ ቀደመው ነገራችን ስንመለስ እናም የዮዲት መጨረሻ ሲቃረብ ማለትም ሸዋ መራቤቴ ላይ በተደረገው ጦርነት ዮዲት ጉዲት ከተገደለችና ሠራዊቷም ከተደመሰሰ በኋላ አማሮች ወይም አክሱማዊያን የነበረውን የአክሱም ሥርዎ መንግሥት ለማስቀጠል ሞክረው ነበር ነገር ግን ለ40 ዓመታት ያህል የነበረው መከራ የሥርዎ መንግሥቱን መሠረት እጅግ አናግቶት ስለነበር ለ30 ዓመታት ከቆዩት ሁለት ነገሥታት በኋላ ማስቀጠል ሳይችሉ በዛጉዌ ወይም በአገው ሥርዎ መንግሥት ተገልብጦ የዛጉዌ ሥርዎ መንግሥትም ከ912-1245 ዓ.ም ድረስ ለ333 ዓመታት 11 ነገሥታትን አንግሦ ኢትዮጵያን ሲገዛ ቆይቶ አቡነ ተክለሃይማኖት ሥልጣኑ ለነበረው ለሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት መመለስ አለበት በማለታቸው አቡነ ተክለሃይማኖትና የመጨረሻው የዛጉዌ ሥርዎ መንግሥት የመጨረሻው የነበረውን ንጉሥ ይትባረክ ባደረጉት ሰላማዊ ስምምነት ሥልጣኑ ወደ ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ተመልሶ መቀመጫውን ግን አክሱም ሳይሆን ሸዋ አደረገ፡፡ በእርግጥ የአክሱም ሥርዎ መንግሥት መቀመጫውን ሸዋ ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው አልነበረም ከአብርሃ ወአጽብሐ ከ298 ዓም – አምሲ 461 ዓ.ም ድረስ 28 የአክሱም ነገሥታት ከአክሱም ባሻገር መቀመጫቸውን ሸዋ የረር ላይ ማለትም አዲስ አበባ ምሥራቃዊ ጫፍ ላይ ከሚታየው የረር በመባል በሚታወቀው ከፍታ ቦታ ላይ አድርጎ ቆይቷል፡፡ አሁንም ድረስ የዚያ ታሪክ አሻራዎች በቦታው ይገኛሉ፡፡

ከዚያም ይህ ሥርዎ መንግሥት እስከ ግራኝ መሐመድ በወረራውና በጦርነቱ ከነሕዝቡ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ገፍቶ እስከ ሰደዳቸውና ሁለተኛው የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ ለ15 ዓመታት ያህል እስከተከሰተበት ጊዜ ዐፄ ልብነ ድንግል ድረስ ቆየ፡፡ ዐፄ ልብነ ድንግል በጦርነቱ ከመናገሻቸው ሸዋ ከተረፈው ሕዝባቸው ጋር ተፈናቅለውና ተሰደው ሰሜን ኢትዮጵያ ጫፍ ድረስ ተሰደው አንዳሉ በሞት ተለዩ ግራኝ መሐመድ ለ15 ዓመታት ያህል ክርስቲያኑን (አማራውን) ሕዝብ እያሳደደ ፈጀው በሀገሪቱም ላይ ከዮዲት ጉዲት በከፋና ተወዳዳሪ በማይገኝለት ጨርሶ ኢትዮጵያዊ ወገናዊነት ባልተንጸባረቀበት በፍጹም ባዕዳዊ ስሜት ሀገሪቱን ከሥር ነቀላት አደቀቃት የቤተመንግሥትና የቤተክህነትን ሀብቶችና ቅርሶችን ሁሉ ጥርግ አድርጎ ለእርዳታ ላመጣቸው አረቦችና ለቱርኮች ጦር ሰጠ፡፡

ተንቀሳቀሽ ያልሆኑትንም አፈራረሰ ደመሰሰ ሌላው ቀርቶ በሀገሪቱ አንዲት ዛፍ እንኳን ቆሞ እንዳይቀር እስከ ማድረግ የደረሰ በገሪቱን ከሥር የመንቀል የጥፋት ዓላማ አንግቦ አወደመ፡፡ ሕዝቡንም አልሰልምም ያለውን እየሰየፈ ሞትን ፈርተው እሽ ያሉትን እያሰለመ ሲዋጋ የቀረው ሕዝብ ከንጉሡ ጋር ተሰዶ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተቅበዘበዘ እንዳለ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ቀየውን ጥሎ በመሰደዱ ባዶና ነጻ ሆኖ ያገኙትን መሬት በ15 ዓመታቱ ውስጥ የኦሮሞ ተወላጆች ድንበር ተሻግረው በቦረና በኩል በመግባት ሰፊ መሬት ለመቆጣጠር ዕድል አገኙ፡፡ ዐፄ ልብነ ድንግል ከሞቱ በኋላ ልጃቸው ዐፄ ገላውዴዎስ በስደት እንዳሉ በ1530 ዓ.ም ነግሠው ከፖርቹጋሎች ባገኙት እርዳታ ታግዘው ግራኝን ጎንደር ፎገራ ላይ ገድለው ድል አደረጉት ግራኝን ከገደሉና ሠራዊቱንም የማረኩትን ማርከው የሸሸውም ከሸሸ በኋላ ወደ አባቶቻቸው መናገሻ ሲመለሱ ከሀገሩ የሚበዛው በእንግዶች ማለትም በኦሮሞ ተወላጆች ተይዞ አገኙት፡፡ ንጉሡም የሕዝባቸውን ማለቅ ተመልክተው በጣም የሳሳውን የሕዝባቸውን ቁጥር ለማካካስ እንደሚረዳቸው በማሰብና ፈቃደ እግዚአብሔር እንደሆነ በመገመት ለእንግዳው ሕዝብ የጎሳ አለቆች ሕዝቡ ሀገሬውን መስሎ ለመንግሥት እየገበረ የሚኖር ከሆነ ሕዝቡ ካለበት ስፍራ መኖሩን እንደሚፈቅዱ አስታወቁ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ አለቆችም ይህንን ችሮታ በደስታ በመቀበል ሀገሬውን መስለው እንደሀገሬው ሕዝብ እየገበሩ ለመኖር ቃል በመግባት የኢትዮጵያዊነት ዜግነታቸውን አገኙ፡፡ ሌላ አዲስ ፈላሲ እንዳይገባ ግን የቦረናን በር ዘጉ፡፡ እንግዲህ ይህ ከሆነ ረጅም ወይም በጣም ሩቅ የማይባል ማለትም አምስት መቶ ዓመታት መሆኑ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳል በፋሽስት ጣሊያን የ5 ዓመታት የወረራ ጊዜ የፋሽስትን የጥፋት ምክር በመስማት እንዲሁም የ1983ቱን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ የጥፋት መልዕክተኛ በሆኑት ምክርና ግፊት በሚያሳዝን ሁኔታ የኦሮሞ ተወላጆች ከዐፄ ገላውዴዎስ ጋር አድርገውት የነበረውን ስምምነት አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ በሀገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች እውነቱን እያወቁ ሳያውቁም ሊሆን ይችላል እራሳቸውን እንደባለቤት በመቁጠር ጭራሽ አማራውን ሀገራችንን ለቃቹህ ውጡልን በማለት ከዚያም አልፈው የብዙ ንጹሐን ዜጎችን ደም በጭካኔ አፈሰሱ መጠኑ ከፍተኛ ነው ባይባልም ይህ በአማራ ሕዝብ ላይ የተደረገው አራተኛው የዘር ማጥፋት ወንጀል ነበር፡፡ ሦስተኛው የዘር ማጥፋት ሊባል የሚችለው ኦሮሞዎቹ ሸዋ ላይ የነበረውን ሰሎሞናዊ ሥርዎ መንግሥት መቀመጫውን ጎንደር እንዲያደርግ እስከ መገደድ ድረስ የደረሰ አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን ማውደምን የጨመረ ጥቃት በተለያየ ጊዜ በፈጸሙ ጊዜ ያደረሱት ጥፋት ነው፡፡

ዛሬ ደግሞ ነገሩ ከዚያም አልፎ የኦሮሞን ሕዝብ ስም ያለ ፍላጎቱ መጠቀሚያ ያደረጉ  እንገነጥላለን የሚሉ የጥፋት ኃይሎች ተፈጥረው ቁጭ አሉ፡፡ ኧረ ተዉ ሕሊና ይኑረን እንጂ ምነው? የማንን ሀገር ነው የምትገነጥሉት? ለነገሩ በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ብሔረሰቦች አንዱ ከሌላው ጋር ተቀላቅሉ ተዋልደው ተዋሕደው ወቶላቸዋልና አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ ወዘተ. የሚባል ሕዝብ ባይኖርም ቅሉ አሁን ትላንትና በእንግድነት ተገብቶ ዝም ተብሎ የሰው ሀገር መገንጠል አለ እንዴ? ለዚያ ውለታ ልትከፍሉት የሚገባው ብድራትስ ይሄ መሆን ነበረበት እንዴ? ሁላችንም ዘራችንን ወደ ኋላ ብንቆጥር አንድና ከአንድ በላይ የሌላ ዘር ደም ተቀላቅሎበት እናገኛለን መረጃውን ለማግኘት ውስንነት ወይም የአቅም ችግር ካላጋጠመን በስተቀር፡፡ በመሆኑም የዘር ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ ጨርሶ ሊሠራ አይችልም ለመሥራት ከተሞከረም በእውነት ላይ ያልተመሠረተና ድንቁርና የተሞላ አስተሳሰብ ነው፡፡ ስላለውና ስለምናየው ሳይሆን ስለሌለውና ስለማናየው እናወራለን እንደክማለንና ጅሎችም ነን፡፡ ይሄንን ማለት ግን የአማራ የትግሬ የጉራጌ የኦሮሞ የመሳሳሉት ባሕል ቋንቋና ሌሎችም መገለጫዎች የሉም ማለት አይደለም፡፡ እነሱም ቢሆኑ ግን አንደኛው ከሌላኛው ጋር አልተወራረሰም አልተቀላቀለም ማለት ፈጽሞ አይቻልም፡፡

ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና አፄ ገላውዴዎስ ሸዋ ሆነው ከገዙ በኋላ ከሳቸው በኋላ ከነገሡት ከዐፄ ሚናስ በኋላ ያሉት የዚህ ሥርዎ መንግሥት ነገሥታት መቀመጫቸውን ወደ ጎንደር በማዞር በመጨረሻ በዳግማዊ ምኒልክ ወደ ሸዋ ከመመለሱ በፊት በላስቴው ዐፄ ተክለጊዮርጊስ 1860 ዓ.ም-1863 ለሦስት ዓመታት መቀመጫቸውን ጎንደርና ላስታ በማድረግ ቀጥለውም የትግሬው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከ1863 ዓ.ም-1881 ዓ.ም መቀመጫቸውን መቀሌና ጎንደር በማድረግ ጣልቃ ከመግባታቸው ውጭ ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ መቀመጫውን ጎንደር አድርጎ ቆይቶ ነበር፡፡

እንግዲህ ይሄንን ታሪክ ማለትም በአክሱማዊያን (አማሮች) ዙሪያ ያለውን እውነት የሕወሀት ባለሥልጣናት በሚገባ የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡፡ በሁለት መንገዶች 1ኛ እንደማንኛውም የትግራይ ሕዝብ ተወላጅ በትውፊታዊ መረጃ 2ኛ ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት በአንድ 100 ዓመታትን በራቁ የትግራይ ተወላጅ ሽማግሌ አባት ይሰጣቸው በነበረ ምክርና ትምህርት፡፡ እኒህ አረጋዊ ሰው የኢሕአዴግን ምልክት ንብ እንዲሆን ያስቻሉም ሰው ናቸው፡፡ እኒህ ሰው ሕወሀቶችን እናንተ የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ የካሳ ምርጫ ልጆች ናቹህ እያሉ ይነግሯቸው እንደነበር የሕወሐት አመራሮች ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳ ይህንን እውነት የሚያውቁ ቢሆንም በዮዲት ጊዜ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አሁን ባለው የሕዝብ አሰፋፈር አማሮች ወይም አማርኛ ተናጋሪ አክሱም አካባቢ አለመኖራቸውና አካባቢው በትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መያዙ ቢያንስ ምንም የታሪክ ዕውቀት በሌላቸው ዜጎች ዘንድ አክሱም የትግሬ ተወላጆች እንደነበረ ተደርጎ እንዲታሰብ በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በሰው ወርቅ ለመድመቅ ሲሞክሩና ሲቋምጡ ይታያሉ፡፡

ይሁንና ሥነ ልቡናቸውና ሰብእናቸው ማለትም ሕወሐቶች ለታሪክ ለድንበር ለቅርስ ለመሳሰሉት ሀብቶቻችንና እሴቶቻችን ያላቸው አመለካከት ሲታይ ግን ከአክሱም ሥርዎ መንግሥት ጋር ግንኙነት እንዳልነበራቸው ሲያሳብቅባቸው ወይም ሲያሳጣቸው ይታያል ምክንያቱም ሕወሀቶች ለእነዚህ እሴቶቻችን ባጠቃላይ ለሀገሪቱ ታሪክና እሴቶች ያላቸው ግልጽ የሆነ ጥላቻና ዴንታቢስነት ወይም ለእነዚህ እሴቶቻችን ያላቸው ፍቅርና አቅርቦት ደካማ ወይም የምናውቀውን ያህል ነውና፡፡ ይህ ማለት ግን የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ለታሪካችን ለነጻነታችን ለሉዓላዊነታችን ለድንበራችን ለቅርሶቻችን ወዘተ. ዴንታ ቢስና ግድየለሽ ነው ማለት አይደለም፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የአማራን የባለአደራነት ስሜት ማለትም ለታሪክ ለቅርስ ለድንበር በአጠቃላይ ለሀገር ያለውን ተቆርቋሪነት ያየን እንደሆነ የሚመሰገንና አርዓያነትም ያለው ነው፡፡ እንግዲህ ይሄ ከየትም የሚመጣ ሳይሆን እንደ ንብረት ሁሉ ከቀደሙት ትውልዶች የሚወረስ የባለ አደራነት የባለቤትነት ስሜት መንፈሳዊ ውርስ ሀብት ወይም እርሾ በመኖሩ ነው፡፡ ይሄንንም ስል የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገር ፍቅር ስሜት የለውም እያልኩ አለመሆኔ ይታወቅ፡፡ ትንታኔዬ ያተኮረው ከላይ በተገለጸው አካባቢና ርዕሰ ጉዳይ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡

የ1983 ዓ.ም የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ በአማራ ሕዝብ ላይ በግልጽና በስውር በእቅድና በተጠና መልኩ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬም እንደ ዮዲት ዘመን ለመኖርና ለመብላት በሚል ማንነቱን ማለትም አማራነቱን የካደውና የደበቀው ለአማራነቱ ግድ የለሽ የሆነው ጭራሽም እንዴት እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ ቅንጣት ቁጭትና ጸጸት ሳይታይባቸው ከግፈኞች ጋር ተባባሪ በመሆን በገዛ ማንነታቸው ላይ የዘመቱ ሰዎች ቁጥር የትየሌሌ ነው፡፡ የዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀል መገለጫ ዘርፈ ብዙና የተወሳሰበም ነው፡፡ በገሀድ ከተፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በቅርብ ትውስ የሚሉትን ስናነሣ በእነ ታምራት ላይኔ ዓይነቱ በሕወሃት መራሹ “መንግሥት” ባለሥልጣናት ገፋሪነት ሥልጣን በያዙ ማግሥት በአቦምሳ ወይም በአርባጉጉ በሌሎችም ሥፍራዎች በአማራነታቸው ብቻ ከሕፃን እስከ አረጋዊያን በጭካኔ የተገደሉና በተለያዬ ጊዜም ከበደኖ ከጉራፈርዳ አሁን በቅርቡ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ንብረታቸውን ወርሰው ማባረራቸው የገዛ ሕገመንግሥታቸው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገሪቱ ስፍራ ሠርቶ የማደር ኑሮውን የመመሥረት ሕገመንግሥታዊ መብት አለው እያለ በአንድ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ማፈናቀል በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች ተፈጸመ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ሲጠየቁ ምን ብለው መለሱ ይህ የክልሉ መንግሥት ጉዳይ ነው ሕገወጥ ሰፋሪዎች ናቸው ካለና አልፈልጋቸውም ካለ መብቱ ነው ይችላል በማለት የገዛ ሕገመንግሥታቸውን የሚፃረር ምላሽ ሰጡ፡፡ ይህ መልሳቸውም ይህ ጉዳይ የተፈፀመው በእሳቸው ትዕዛዝ መሆኑን ጠቆመ ለነገሩ በ21 ዓመታቱ የወያኔ መንግሥት አስተዳደር ተሞክሮ እንደምንረዳው እንዲህ ዓይነቱ ከባድና አሳሳቢ ውሣኔ በክልል አስተዳደሮች ደረጃ ሊወሰን እንደማይችል መረዳት አያዳግትም፡፡ አቶ መለስ እንዲህ ብለው ሲሉ እናንተም በጊዜአቹህ እኛ እንዳደረግነው ሁሉ ትግሬን ባዶ እጁን አራግፋቹህ አፈናቅላቹህ ማባረር ትችላላቹህ ማለታቸውና ይህንን አዲስ አዙሪት ባርከው መጀመራቸው እንደሆነ አቶ መለስ ጨርሶ አልገባቸውም፡፡

“አየ ጭንቅላት አየ የኛ አርቆ አሳቢ” የብልህነትንና የአርቆ አሳቢነትን ትርጉም ለማያውቁ ሰዎች አርቆ አሳቢ መሪ ማለት ውሎ አድሮ ምን ሊያስከትል እንደሚችል መገመት ተስኖት በሰላምና በፍቅር የሚኖርን ሕዝብ እንዲናቆር ማሴር እንዲፋጅ እንዲባላ መሸረብና መጣር ቀን እንዲጠባበቅ ማድረግ ሳይሆን እንኳን ያላጣውን ሰላም ፍቅር አንድነት ሕብረት ያጣ ሕዝብ እንኳን ቢሆን ኖሮ እንዲህ የሆነውን ሕዝብ ማስማማት ማግባባት ማፋቀር ማዋደድ መቻል ነው ብልህና ባለአእምሮ መሪ ማለት እንጅ የሚያናቁረውና ለማፋጀት የሚጥረው አይደለም ያ ደደብ ደንቆሮ እንጂ ብልህና አሳቢ ሊባል ከቶ እንዴት ይቻላል? የኢትዮጵያ ሕዝብ አላውቃቸው ብሎና ተስፋ አልቆርጥ ብሎ ነው እንጂ ከእነዚህ መንግሥታዊ ዳሲኘሊን (ሥነ ሥርዓት) ከማያውቁ፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚባል ነገር ጨርሶ ከማይገባቸው፣ የጫካ አውሬዎች የመንደር ወጠጤዎች የስርቻ ወሮበሎች የቆሻሻ ሥነ ምግባር መፍለቂያዎች ከሆኑ ከእነዚህ ጉዶች ከዚህ የተለየ ምን ይጠበቅ ኖሯል፡፡ እድሜ ዘመናቸውን ሳይለወጡና ሳይሰለጥኑ ጭራሽ እየባሰባቸውና እየደነቆሩ ሄደው ቁጭ አሉ፡፡ ይለወጣሉ ብላቹህም ከቶም ተስፋ አታድርጉ፡፡

ወደ ሌሎቹ አማራን የማጥፋት ወንጀሎች ዓይነቶች ስናልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የአማራ ተወላጅ በስውር ደባ ሠርቶ የመኖር ዕድል መነፈጉ፣ በአንድ ወቅት ላይ በተለይ ጎጃም የወባ ወረርሽኝ ገብቶ ሕዝቡን ሲጨርስ የአገዛዙ አካላት ተነግሯቸውና እያወቁ ፓርላማ ውስጥ መነጋገሪያ እስከመሆን ሲደርስ መንግስታዊ ያልሆኑ የውጭ ደርጅቶች እስኪታዘቡ ድረስ አገዛዙ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ምንም ዓይነት የህክምና አቅርቦት እንዳይሰጥ በማድረግ ሕዝቡ እንዲያልቅ መደረጉ፣ ከዓመታት በፊት የጎንደር ፖሊስ በወገናዊነት ቁጭት በመነሣሣት ጫትን በቸልተኝነት ዝም ብለን በመመልከታችን ትውልዱ እንዳለ የጫት ሱሰኛ እስከመሆን ደረሰ አሁን ደግሞ ይሄ ሺሻ የሚባለውን ዝም ብንል ነገ እንደጫቱ ልንቀለብሰው ከማንችልበት ደረጃ መድረሳችንም አይደለ? በማለት ተነሣስተው ከየጫት ቤቱ ሲሰበስቡ ወዲያውኑ ከክልል ተደውሎ ማን አዛዛቹህ አሁኑኑ በአስቸኳይ መልሱ ተብለው እንዲመልሱና ትውልዱ ሱሰኛና እንኩቶ ብላሽ እንዲሆን ጥረት መደረጉ፣ በሀገሪቱ ሁለት ዓይነት የትምህርት ሥርዓት በመቅረጽ በትግራይና በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ያለውን በመለያየት በተለይ ደግሞ የአማራውን ክልል የትምህርት ጥራት ደረጃ አሳዛኝ በሆነ መልኩ እንዲወድቅ መደረጉ የመሳሰሉት ሲሆኑ በስውር ከሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ደግሞ ሁለቱን ብቻ ልጥቀስ፡-

አንደኛው በአማራ ክፍላተ ሀገራት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ምክንያታቸው ያልታወቁና ያልተገለፁ በየጊዜው የሚከናወኑ የጅምላ ክትባቶች አሉ፡፡ እነኝህ ክትባቶች የተከተቡትን ሰዎች መውለድ እንዳይችሉ የሚያደርጉ ክትባቶች ናቸው፡፡ ይህ ክትባት በተደጋጋሚ ሲፈጸም የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ በክትባቱ ወቅት በመቅረት ሳይከተቡ የሚቀሩ ወገኖች እንዳሉ ታወቀ፡፡ የስውር ደባ ሰለባ እየሆኑ እንደሆነ የገባቸው ተማሪዎች የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ ላለመከተብ የሚያደርጉት ጥረት የአሳዛኙ ቲያትር አስቂኝ ገጽታ ሆኖ ታይቷል፡፡ ወደ ኋላም ሕዝቡ ይሄንን ጉዳይ ጭራሽ የወጉ ማጣፈጫና ማምረራያ አድረጎት አረፈ፡፡ ሽለ ሙቅ የሆነች ሴት ስትታይ “አሀ ይች ከክትባት ያመለጠች ናት” ያባላል ስሜተ ቀዝቃዛዋን ደግሞ፣ “ይች ተከታቢ ናት” እያለ እስኪቀልድበት ድረስ ይህ ጉዳይ የሕልውናውን ጉልህ ሥፍራ እንደያዘና ማወቁን ወይም መንቃቱን ጠቆመ፡፡ ከዚህ የተለየ ግን ምንም ያደረገው ነገር የለም፡፡ በሌሎች ሀገሮች ቢሆን ግን ከዚህ የበለጠ የሕዝብ አመጽ ሊቀሰቅስ የሚችል ምክንያት ባልነበረ፡፡

ሁለተኛው ደግሞ በተለይ 1996/97 ዓ.ም. ፀረ ትራኮማ ክትባት በሚል ሽፋን በበርካታ አካባቢዎች በተለያዬ ጊዜ የተደረጉ ክትባቶች ብዙ ሕፃናትንና ነፈሰጡር እናቶችን ለሞት አብቅተዋል፡፡ በነዚህ የአማራ አካባቢዎች የቀብር ስፍራዎች ብትዘዋወሩ ከቀድሞው በተለየና ባልተለመደ መልኩ በርካታ የሕፃናትና የነፍሰጡር እናቶች መቃብሮችን ታያላችሁ፡፡ እንግዲህ እነኝህና ሌሎች እነኝህን የመሳሰሉ ስውርና ድብቅ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጸም ቆይቷል፡፡ በግልጽ በአደባባይ በዓለም አቀፉ በሕብረተሰብ እይታ ስር በዘራቸው ምክንያት ብቻ የዜጐችን ንብረት ዘርፎ የሚያፈናቅል የሚያባርር የእርዳታ እህል የሚከለክልና በረሃብ የሚያሰቃይ ሌላም በግልጽ የሚታዩ ግፎችን የሚፈጽም ግፈኛ አገዛዝ በስውር ወይም በድብቅ እነኚህን የጠቀስኳቸውንና ሌሎችንም አያደርግም ብሎ የሚጠራጠር ሰው ወይም ዜጋ ካለ እጅግ የዋህና ያልበሰለ መሆኑን ዛሬ ይወቅ፡፡

ወያኔ ቢወድቅ ወይም ከሥልጣን ቢወገድ የሚከተለውን አጸፋ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በተቻለው መጠን በሥልጣን እያለ ይህንን የበቀል እርምጃ ይወስድብኛል ብሎ የሚፈራውን ሕዝብ (አማራን) በግልጽም ይሁን በስውር በሚያደርጋቸው የማጥፊያ ዘዴዎች ለቅሞ ማጥፋት ዋነኛውና ሌት ተቀን የሚሠራበት ዓላማው ነው የሚል ከባድ ሥጋት አለብኝ፡፡ እስከ 1999 ዓ.ም በተሠራው ደባ ያገኙት ድምር ውጤት ከ6 ዓመታት በፊት በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ በሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልታየና እንግዳ በሆነ መልኩ የሌላው ሕዝብ በቅድሚያ ትንበያው መሠረት እና ከዚያም በላይ ሆኖ ሲገኝ የአማራ ሕዝብ ግን ይደርሳል ተብሎ ከተጠበቀው የትንበያ ቁጥር ወይም መድረስ ከነበረበት ቁጥር አለመድረሱ ብቻ ሳይሆን ጭራሽም በሚሊዮኖች (አእላፋት) አሽቆልቁሎ እንደተገኘ ማስታወስ ይቻላል፡፡ ገና ከ4 ዓመታት በኋላ በሚደረገው ቆጠራም ከ1999 ዓ.ም በኋላ በሠሩት ደባ ከዚህም በከፋ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ይገመታል፡፡

በየሙያ መስኩ ሰዎች ስንት ጉድ ያውቃሉ መሰላችሁ ለመናገርና ለመመስከር ጊዜን የሚጠብቁ፡፡ የሚገርመኝና ግራ የሚገባኝ ነገር ቢኖር በዚህ ሕዝብ ላይ እንዲህ ጥርስ የተነከሰውና የተጨከነው ለምንድን ነው? ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር በመሆን የዚህችን ሀገር ነጻነት አስጠብቆ ባቆዬ? ከቀደምት ሥልጡንና ኃያላን ሀገራት ጎራ ባሰለፈ? ለእነኝህና ለሌሎች ኩራቶቻችን ሲል ስንትና ስንት መከራ ባሳለፈ? ለምን? ይህ ያስመሰግነዋል እንጂ በምን ተአምር ነው ለጥፋት ድግስ ሊዳርገው የሚገባው? በኢትዮጵያዊነቱና በሀገሩ ኩራትና ክብር የሚሰማው ባለውለታና የሚያስብ ሕሊና ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል በዝምታና በይሁንታ የሚመለከትበት አቅል ይኖራል ብሎ ማሰብ ይቻል ይሆን? አረማዊያን ሆይ በምሳሩ ላይ ቆማቹሀል ለራሳችሁም ይብስባቹሀል፡፡ አየ የኛ ልማታዊ መንግሥት ለማያውቅሽ ታጠኝ አያ፡፡ አንባቢያን ሆይ ደኅና ሁኑ ከዚህ በኋላ እንኳን የምንገናኝ አይመስለኝም፡፡ (በመግቢያው ላይ ያለው ፎቶ ለማሳያነት የቀረበ)

ኢትዮጵያ ከውድ ልጆቿ ጋር በክብር በነጻነትና በልዕልና ለዘላለም ትኑር!!!

↧

የመኢአድና አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ የባንክ አካውንቱን ይፋ አደረገ

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት

የመኢአድና አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ ስራውን በቅልጥፍና እና በትጋት እየተወጣ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚህም መሰረት ለጉባኤው መሳካት ይረዳ ዘንድ መላው ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩ ጥሪ በማድረግ የባንክ አካውንቱን ይፋ አድርጓል፡፡
የባንክ አካውንት ቁጥር UDJ A/C 47
የባንክ አካውንት ቁጥር AEUP SP 235

udJ&AEUP

↧

ፖሊስ እነ ሐብታሙ አያሌውን ፍ/ቤት አቅርቤያለሁ አለ

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት

ፓርቲውና የታሳሪ ጠበቆች መቼ፣ እንዴትና የት እንደቀረቡ ምንም መረጃ እንሌለ አረጋግጠዋልHabtamu abrhayeshiwas daniel

 

ዛሬ ሀምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም የፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት ሀምሌ 6 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ መብራቱ ታሳሪዎቹን ይዘው እንዲቀርቡ ቢያዝም ኃላፊው ታሳሪዎቹን ሳይዙ ቀረቡ፡፡
ችሎቱ በ3፡30 ተሰይሞ ተከሳሽ ክሱ እንደደረሳቸው ዳኛው ጠየቁ፡፡ ክሱ በንባብ ከተሰማ በኋላ የጽሑፍ ምላሽ እንዳላቸው ሲጠየቁ፣ በጽሑፍ መልስ አላመጣሁም በቃል መልስ እሰጣለሁ በማለት ምላሻቸውን ከዚህ እንደሚከተለው በቃል ሰጥተዋል፡፡


ተከሳሾቹ በሰኔ 30 ቀን 2006 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወጣ የመያዣ ትዕዛዝ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም እንደተያዙና ሐምሌ 2 ቀን 2006 ዓ.ም ፍ/ቤት ቀርበው ቀጠሮ እንደጠየቁባቸውና በህጉ መሰረት መብታቸው ተጠብቆ እንዳለ ገልጸው ጠበቆቹ ከደንበኞቻቸው ጋር ረቡዕ እና ዓርብ መገናኘት እንደሚችሉ የመጡበት ቀን ግን መገናኘት በማይቻልበት ቀን በመሆኑ ነው ያልተገኙት በማለት ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡


የከሳሽ ጠበቆች አቶ ተማም አባቡልጉ እና አቶ ገበየሁ ይርዳው በበኩላቸው ይህ በቃል የተሰጠው ምላሽ በሰነድ ያልተደገፈ ማስረጃ የሌለው በመሆኑ የተከበረው ፍ/ቤት ውድቅ እንዲደረግልን እንጠይቃለን፡፡ ወደ ማዕከላዊ በመሄድ ደንበኞቻችንን ለማናገር እስረኞች አስተዳደር ብናናግርም የፀረ ሽብር ኃላፊውን አናግሩ የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን ኃላፊውን ማናገር አልቻልንም በቀጠሮ መጥተን እናናግራቸው ብንልም በቀጠሮ ሊያገናኙን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ የኛ ጠበቃ ጓደኞች ደንበኞቻቸውን ሲያናግሩ አይተናል እኛ ደንበኞቻችንን እንዳናናግር ተደርገናል፣ አድልዎ ተደርጎብናል፡፡ ምንም እንኳ ሀገሪቷ በወታደራዊ ዕዝ ሥር ብትሆን እንኳ የእስረኞች የእኩልነት መብት አይገፈፍም፡፡ ሌላው የፀረ ሽብር ኃላፊው እንዳመኑት በሳምንት ሁለት ቀን ረቡዕና ዓርብ ብቻ ከእስረኞች ጋር መገናኘት ይችላሉ ያሉት የህግ ጥሰት ነው፣ ለምን በሥራ ቀናቶች ሁሉ መጠየቅ አለባቸው ይህ ህገ መንግስታዊ መብት ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ታሳሪዎቹን ፖሊስ ይዞ እንዲቀርብ ያዘዘ ቢሆንም የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ አክብሮ ታሳሪዎቹን አላቀረበም፡፡ በአቤቱታችን መሰረት ደንበኞቻችን ህጉ ተጠብቆ በህጉ መሰረት ያልተያዙ በመሆኑ አሁኑኑ ከእስር እንዲለቀቁልን፤ ይህ የማይሆን ከሆነ በዋስትና እንዲለቀቁልን ክቡር ፍ/ቤቱን እንጠይቃለን፡፡ የእስር ቦታቸው ተቀይሮ ወደ ተሻለ ጣቢያ ተዛውረው በጠበቃ፣ በወዳጅ ዘመዶቻቻ እንዲጎበኙ እንዲደረግ ክቡር ፍ/ቤት እንጠይቃለን፡፡ በማለት የከሳሽ ጠበቆች ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡


በመጨረሻም ፍ/ቤቱ የመያዣ ትዕዛዝና ፍ/ቤት ያቀረቡበትን ሰነድ የማዕከላዊ የፀረ ሽብር ዲቪዚዮን ኃላፊ ተክላይ መብራህቱ ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ይዘው እንዲቀርቡ አዟል፡፡


የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከሥራ ሰዓት ውጪ ማታና ጠዋት ታሳሪዎችን እንደሚያቀርቡ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

 

 

↧

የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ተቃዋሚዎችን በማፈን የኢትዮጵያን የነጻነት ትግል አያስቆምም!

$
0
0

07/15/2014

 

ሰሞኑን ከዱባይ ወደ አስመራ በመጓዝ የነበሩትን የግንቦት 7 ድርጅት ዋና ጸሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ብትራንዚት ላይ የመን ከተማ ሰንዓ የአየር ማረፊያ እንዳሉ በየመን የጸጥታ ሀይሎች ታፍነው ለትግራይ ነጻ አውጭ ግንብር (ወያኔ) ተላልፈው እንደተሰጡና አሳዛኝና ከስብእና ውጭ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሆ እየሰማን ሰንብተናል። በየመን መንግስት ተባባሪነት፣ በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተፈጸመባቸውና  እየተፈጸመባቸው ባለው ግፍ፣ ድብደባና ሲቃይ ልሳን ግፉዓን አጥብቆ ያወግዛል። ለመሆኑም በውጭ ሀገር ታፍኖ መወሰድ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እንዳልሆኑ ለሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን በሙሉ ማስታወስ እንወዳለን።  የትግራይ  ነጻ አውጭ ድርጅት የትግራይን  የመስፋፋትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማ እንቅፋት ይሆኑኛል የሚላቸውን በሱዳን በስደት ላይ የነበሩትን ያሉትን  የወልቃይት የጠገዴንና የአርማጭሆ አርበኞች፣ ድንበር ጠባቂዎች ከሱዳን የጸጥታ ሀይል ጋር በመተባበር  በ1981 ዓ/ም ህዳር 5 ጀምሮ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ እየታፈኑ ተወስደው ጠፍተዋል፡፡ለምሳሌ ያህል

1. ሻለቃ ጌታቸው ይርጋ

2. ሻለቃ አጣናው ዋሴ (80 አመት አዛውንት በ2009 … ማእከላይ እስር ቤት በደረሰባቸው ጉዳት አረፉ)

3. አቶ ናሩ ገብረህይወት      4. አቶ መከታው አዛናው

5. አቶ አበጀ ፈለቀ            6. አቶ መላኩ ንጉሴ

7. አቶ ዘውዱ አልጣህ        8. አቶ ፈንቴ ገብሬ

9. አቶ ሀጎስ ጌታሁን          10. አቶ አስራደ በየነ ….ይቀጥላል

ሰሞኑንም ለሱዳን የጸጥታ ሀይሎችታስረው(ታፍነው) ለትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት እንዲሰጡ የሚፈለጉ ሰዎች ስም ዝርዝር የተሰጠ እንዳለ ማስረጃ ደርሶናል። ይህንን ህገ ወጥ ተግባርም አበክረን እናወግዛለን፡ እንቃወምም አለን።

ወድ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፤

የኢትዮጵያ ህዝብ ግፍና በደል ጽዋው ሞልቶ እየፈሰሰ ነው። ሀገር ውስጥ መኖር አልተቻለም፤ ውጭም በተለይ በኢትዮጵያ አጎራባች አገሮች ውስጥ በስደት ለመኖር አስቸጋሪ የሆነብት አጣብቂኝ ውስጥ ደርሰናል። ሀገርና መደበቂያ ያጣ ሆኖ መኖር እስከመቸ ነው? አይበቃንም!

ሀገርንና ወገንን ለማዳን አሁኑኑ በጋራና በአንድነት መነሳት የግድ ይላል!

ልሳነ ግፉዓን

voice of victims

↧
↧

በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ስሜን ምስራቅ ድንበር ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል

$
0
0

በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ስሜን ምስራቅ ድንበር ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። #Ethiopia  የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ከባድ መሳሪያዎች ተወልውለው በድንበሩ ዙሪያ ተኮልኩለዋል።

የአንዳርጋቸው ጽጌ መያዝ ፡ የግንቦት ሰባት ጥሪ እና የትሕዴን ሰራዊት መመረቅን ትከትሎ በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ሰሜን ምስራቅ ድንበር ላይ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ለሰሜን እዝ ቅርብ የሆኑ የሰራዊቱ ምንጮቻችን በደረሱን መረጃ አስታውቀዋል።እንዲሁም በአፋር ክልል ውስጥ ክፍተኛ ደህንነቶች በማፍሰስ ሕዝቡን እየሰለሉት መሆኑ ሲታወቅ ከፍተኛ አመጽ በክልሉ እንዳይነሳ ወያኔ መስጋቱ ታውቋል።

newsወያኔ ተጠባባቂ ጦሩ ላይ እምነት ስለሌለው የትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ብቻ በተለያዩ ወረዳዎች በመሰብሰብ አስፈላጊውን መመሪያ የሰጠ ሲሆን በሁምራ ክዚህ በፊት ሰልጥነው የሰፈሩ እና መኖሪያቸውን እዛው ያደረጉ የወያኔ ልዩ ተጠባባቂ ጦር አባላት በነፍስ ወከፍ አዳዲስ ላውንቸር ክላሽንኮቭ እና ከበርካታ ጥይቶች ጋር እንደትድላቸው ታውቋል። እንዲሁም በትግራይ ውስጥ የሰለጠኑ ሚሊሻዎች ከነትጥቃቸው ድንበር አከባቢ ከዚህ ቀደም መሬት ተሰቷቸው የሰፈሩትም ለዚሁ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ተደርገዋል።ታንኮች መድፎች እና ከባባድ መሳሪያዎች ወደ ድንበሩ በመጠጋት አስፈላጊውን አሰሳ እያደረጉ ሲሆን የ24 ሰአት ልዩ ጥንቃቄ የተሞላበት ወታደራዊ የቁጥጥር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ምንጮቹ ጠቁመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ መልክ በጎንደር በጎጃም እና በሰሜን ሸዋ ነዋሪዎችን መሳሪያ ማስፈታት ሊጀመር መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህም የሚያምለክተው አማራው ከግንቦት ሰባት ጋር ይሸፍታል የሚል ስጋት ስላላቸው መሆኑ ታውቋል። በዚህ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን ይቀርባሉ።

 

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

↧

“አሸባሪ”ዎቹን ፍለጋ –ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

    (የሽብር – ዘፍጥረት ፫)

    ….በሁለት ተከታታይ ጽሁፎች የሽብርተኝነትን አነሳስ እና የአልሸባብን አፈጣጠር በደምሳሳውም ቢሆን መቃኘታችን ይታወሳል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ መግባቱ ለምስራቅ አፍሪካው አደገኛ ቡድን መወለድ መንስኤ ስለመሆኑ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች እና ከሞቋዲሾ እስከ ኪስማዩ በደም ከተፃፈው የሠራዊቱ አባላት ገጠመኝ መረዳት ችለናል፤ ይህ ቡድን ዛሬ ከመንግስታዊ ተቋማት ይልቅ ንፁሀን ዜጐችን ዒላማ አድርጎ፣ የቀንዱን አገራት አካባቢ ወደ ሕግ-አልባ የጦር ቀጠናነት መለወጥ የሚያስችለውን ግዙፍ ኃይል አካብቶ አስፈሪ እየሆነ ስለመምጣቱ ማስተዋሉ አዳጋች አይደለም፡፡ ለርዕሰ-ጉዳያችንም መቋጫ የምናደርገው የኢትዮጵያ መንግስት ‹‹ሽብር››ን እንዴት ለፖለቲካዊ ዓላማ እንደሚጠቀምበትና እነማንን በ‹‹አሸባሪ››ነት  ፈርጆ በመወንጀልና በማሳደድ እኩይ ተግባር ላይ መጠመዱን በጨረፍታ መመልከት በመሆኑ ወደዛው እናልፋለን፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

   የሽብር ድንበር…
የሽብር ድርጊትን ለዓላማቸው ማስፈፀሚያ መምረጣቸውን በይፋ አውጀው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች፣ በአሰቃቂ አደጋዎች በሚመነዘሩ ጥቃቶች ንፁሃንን ለህልፈትና ለከባድ ፍርሃት በመዳረግ፣ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ ጥያቄዎቻቸውን በኃይል ለማስፈፀም መሞከራቸው የተለመደ ነው፤ ለዚህ ይቅር ለማይባለው ጭካኔያቸውም የድል ችቦ ለኩሰው ጮቤ ሲረግጡ በሀዘን ተመልክተናል፤ በቅርቡ በጎረቤታችን ኬኒያ ውስጥ የተፈፀሙትን ዘግናኝ የጅምላ ጥቃቶችና ፍንዳታዎችን ተከትሎ ቡድኑ የሰጣቸው መግለጫዎችም ይህንኑ ያስረግጣሉ፡፡ ከሁሉም በፊት ግን ‹‹የሽብር ድርጊት ምንድር ነው?›› የሚለው ጥያቄ ተፍታቶ መመለስ የሚኖርበት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በዳሰሳችን የምናገኘው ምላሽ ዓለም-አቀፍ ማሕበረሰቡን የሚያቀራርብ ቢሆንም፣ በተግባር ሲገለጥ ግን መጣረስ መኖሩን ማስረጃዎች ይጠቁማሉና፤ ስለዚህም የሽብርን አንድምታ ከየመንግስታቱ ባህርያት አኳያ በሁለት ምድብ ከፍለን እንመለከታለን፡፡

የመጀመሪያው በአንፃራዊነት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ማንበር የቻሉ አገራት እና ዓለም-አቀፍ ተቋማት ከሚሰጡት ብያኔ ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ በዚህ ምድብ ሽብርተኝነት የሚያቅፈው ትርጓሜም ሆነ አደጋውን ለመከላከል የሚወጡ ሕጎች በውስጣዊ የፖለቲካ ፍላጎት (በተለይ ሥልጣንን ከሕዝባዊ ሰላማዊ ተቃውሞ ለመከላከል) ያልተቃኙ ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ ‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንና ተቺዎችን ለማጥቃት ይውላሉ› ተብሎ አለመታሰቡ ከሞላ ጎደል ብዙሃኑን የሚያስማሙ (እንከን ባይታጣባቸውም በመግባባት የሚታለፉ) ተደርገው ይወሰዳሉ፤ የእነዚህ አካላት ብቸኛ ዓላማም አገርን እና ሕዝብን ከሰቆቃ መጠበቅ ላይ ያተኮረ እንደሆነ በመረጋገጡ ትርጓሜው ያን ያህል ሲያከራክር አይስተዋልምና ዝርዝር ነገር ከማተት ታቅበን፣ ወደ ሌላኛው ምድብ እንለፍ፡፡

በሁለተኛነት የምናነሳውና ዋነኛው ደግሞ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወጥ-አምባገናዊ አገዛዝ በሚያስተዳድሯቸው አገራት የሚበየነውን የሽብር ድርጊት ነው፤ በእነዚህ ሥርዓታት ውስጥ ድርጊቱ አለቅጥ ከመለጠጡ በዘለለ፣ ለትርጉም አሻሚ የሆኑ አንቀፆች እንዲካተቱበት ስለመደረጉ ጉዳዩን ያጠኑ ምሁራን የደረሱበት ድምዳሜም ሆነ በተጨባጭ የታዩ የሐሰት ውንጀላዎች ያስረግጡልናል፡፡ ኩነቱን ከኢትዮጵያ አውድ አኳያ ካየነው ደግሞ ይሁነኝ ተብሎ የገዥው-ፓርቲን ስሁት ፖሊሲዎች እና አምባ-ገነናዊ ባህሪያት በድፍረት የሚተቹትን፤ እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅት አባላትን ለማጥቃት በ2001 ዓ.ም የፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ አንዳንድ አንቀፆች እንዲካተቱበት መደረጉን በማስረጃነት መጥቀስ እንችላለን፡፡ በተለይም ከአረቡ ፀደይ በኋላ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ‹‹ለሥልጣኔ ያሰጉኛል›› በሚል የጠረጠራቸውን የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ ጋዜጠኞች እና አክቲቪስቶች፣ እንዲሁም ከኦሮሚያ በስመ-ኦነግ አፍሶ ካጎራቸው ንፅሃን እስከ የሙስሊም ኮሚቴዎች ድረስ በሐሰት እየወነጀለ ወህኒ ቤቱን ከአፍ እስከ ገደፉ ለመሙላት ያላዳገተውም በዚህ አስቀድሞ በዘረጋው ወጥመድ ይመስለኛል፡፡

  በርግጥ ይህን መሰሉ የገዥዎቻችን ብልጠት ዛሬ የተጀመረ አለመሆኑ አይካድም፤ ትላንት አርበኛው በላይ ዘለቀ እና ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋርያትን የመሳሰሉ የሀገር ባለውለታዎች፣ በአፄ ኃይለስላሴ አስተዳደር ‹‹አሸባሪ›› (ፀረ-ዘውድ) ተብለው የህይወት መስዋዕትነት መክፈላቸውን እናስታውሳለን፡፡ በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ዘመነ-መንግስትም ቢሆን፣ ከጄኔራል አማን አምደሚካኤል እስከ ጄኔራል ተፈራ ባንቲ፤ ከኢህአፓ እስከ መኢሶን፣ ከኦነግ እስከ ህወሓት፣ ከጀብሀ እስከ ሻዕቢያ… ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ‹‹አሸባሪ›› (ፀረ-ሕዝብ) ተብለው ይሳደዱ፣ ይጨፈለቁና ይገደሉ እንደነበር ከታሪክ ድርሳናት በተጨማሪ እውነታውን ይመሰክሩ ዘንዳ   በህይወት የሰነበቱ የዓይን እማኞች ያስረግጣሉ፤ ኢህአዴግም በምክር ቤቱ በኩል የያዘውን ሥልጣን በመጠቀም አካሄዱን ሕጋዊ ለማስመሰል በአዋጅ የደነገገው ይህንን የቀደመ ስልት በመኮረጅ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ስጋታችን ማነው?
አሸባሪ ቡድኖች ብዙውን ጊዜ የሚያቀነቅኑትን ፖለቲካዊ እና ኃይማኖታዊ አጀንዳዎችን ለማስፈፀም የየትኛውንም አገር ሕግ ከመጣሳቸውም በዘለለ ደም-አፋሳሽን በመሰለ አሉታዊ ገፅ የሚሸፈኑ መሆኑ እውነት ነው፤ ከዚህ ተነስተንም ስለጉዳዩ በምክንያታዊነት እንነጋገር ከተባለ፣ በዛሬይቷ ኢትዮጵያ ቀንደኛው የስጋት ምንጭ ምንድር ነው? ብሎ ወሳኝ ጥያቄ ከማንሳት መጀመርን ግድ ይላል፡- በተጨባጭ ሀገሪቷን በታሪክ-አልባነት ለማፈራረስ ያንዣበበብን አደጋ የቱ ነው? ሥርዓቱ ያነበረው የጎሳ ፌደራሊዝም ወይስ እስክንድር ነጋ? የዕድገት ማነቆስ? አለቅጥ የተንሰራፋው መንግስታዊ ሙስና ወይስ እነርዕዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ? አንገብጋቢው ችግራችንስ? በአስደንጋጭ ሁኔታ እያሻቀበ ያለው ሥራ-አጥነት ወይስ እነአንዱአለም አራጌ እና በቀለ ገርባ? ተቻችሎ የመኖር እንቅፋትስ? የመንግስት በግላጭ በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት ወይስ እነአቡበከር መሀመድ? በርሃብ እንደ ቅጠል ለመርገፋችንስ? አስከፊው ድህነት ወይስ አንዳርጋቸው ጽጌ? የዲሞክራሲ ጋሬጣስ? ከአገዛዙ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት አራማጆችን በኃይል ማፈን ወይስ እነተስፋዓለም ወልደየስ? ለሕግ የበላይነት አለመከበርስ? ፍትህን በገንዘብ ሊገዛ ለከጀለ ባለጊዜ መቸርቸር ወይስ ‹በሰላማዊ መንገድ የሥርዓት ለውጥ እናመጣለን› በሚል የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ማሳደድ? …ለእነዚህና መሠል ጥያቄዎች አመክንዮአዊ ምላሽ ማግኘት ቀዳሚው ተግባር ይመስለኛል፤ ምላሾቹም ለአጠቃላይ አገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ኃይማኖታዊ ችግሮች የማያዳግም መፍትሔ መስጠት
አይሳናቸውም ብዬ አስባለሁ፡፡

ማነው አሸባሪ?
ምንም እንኳ ጥያቄው ተራ ቢመስልም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተስተዋለው የሀገራችን ተጨባጭ እውነታ የሚነግረን ከሚታሰበው በተቃርኖው ነው፡፡ ጉዳዩን ያከረረው ገፊ-ምክንያትም አገዛዙ የሽብርን ትርጓሜ በፈለገ ወቅት ለጥጦ በመጠቀሙ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ሁሉም የሀገሪቱ ዜጋ በማንኛውም ሰዓት ሊወነጀልበት እንደሚችል እያሰበ በፍራሃት ተሸብቦ ሰጥ-ለጥ ብሎ እንዲያድር በማስገደዱም ጭምር ነው፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ኦነግ፣ ኦብነግ እና ግንቦት 7 እንደ አልቃይዳ እና አልሸባብ ሁሉ ‹‹አሸባሪ›› ድርጅቶች ተብለው መፈረጃቸው አይዘነጋም፡፡ ይሁንና እነዚህ አገር-በቀል ድርጅቶች ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻቸውን የጦር መሳሪያ በማንገብ ለመፍታት የሚከተሉት መንገድ ‹ትክክል ነው፣ አይደለም›ን ጉንጭ አልፋ እሰጠ-እገባ ለጊዜው ወደጎን ብለን፣ የትጥቅ ትግል መስመርን ለምን መረጡ? የሚለውን የጨረፍታ ፍተሻ አናስቀድም፡፡
በቅድሚያም የኦሮሞ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ያለፈበትን ጥምዝምዞሽ ብንመለከት የምናገኘው እውነታ፣ ዛሬ በ‹‹አሸባሪ››ነት ከወነጀለው ኢህአዴግ ጋር በመተባበር የደርግ ሥርዓትን ለመቀየር ከመታገሉም በላይ በድሉ ማግስት የጋራ መንግስት መስርቶ፣ ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ አካባቢ በጋራ ሀገር ሲያስተዳድር መቆየቱን የሚያስረግጥ ነው፤ ውሎ አድሮ አብዮታዊ ግንባሩ ‹ኦሮሚያን ያለከልካይ መቆጣጠር› የሚለውን ያደረ ትልሙን ለመተግበር፣ ትልቅ እንቅፋት የሆነበትን ኦነግን ከመንግስታዊው ሥልጣን ማባረር ቀንደኛ የቤት ሥራው በማድረጉ፤ ‹‹ሰላማዊና ሕጋዊ›› ተብሎ የተለፈፈለት የምርጫ ውድድር ሊካሄድ የቀናት ዕድሜ ሲቀሩት በስውር እጁ ጠምዝዞና አዋክቦ ከውድድሩ እንዲወጣ ማስገደዱን እንረዳለን፡፡ ይህንንም ተከትሎ ኦነግ የጣለውን ጠብ-መንጃ አንስቶ በኃይል ሥርዓቱን ለማስወገድ ‹‹ዱር ቤቴ!›› ብሎ ተመልሶ በርሃ መግባቱ ባይካድም፣ ወደዚህ ጠርዝ ለመገፋቱ ግን ዋነኛ ተጠያቂው (ኃላፊነት የሚወስደው›) ማን ነው? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ቀላልና ግልፅ ነው፡፡    ሌላው በዚህ አውድ ሊጠቀስ የሚችለው ግንቦት 7 ነው፤ እንደሚታወሰው የዚህ ድርጅት ግንባር ቀደምት መስራቾች፣ በ1997ቱ ሶስተኛው ሀገር-አቀፍ ምርጫ ቅንጅቱን ወክለው ተወዳድረው እንዳሸነፉ ቢነገርም፣ ኢህአዴግ የቀድሞው ልምዱን በመጠቀም ‹‹ጨዋታው ፈረሰ፤ ዳቦ ተቆረሰ›› ብሎ ሁሉንም ከያሉበት ለቃቅሞ ወህኒ ቤት አጉሯቸው ሲያበቃ፤ እንዳሻው በሚቀልድበት ካንጋሮ ፍርድ ቤት አቅርቦ የዕድሜ ልክ እስራት ቅጣት ማስጣሉ የትላንት ትውስታችን ነው፡፡

እንግዲህ በዚህ አይነቱ በተቀነባበረ ሰው-ሰራሽ እሳተ-ጎመራ እንዲፈተኑ የተገደዱ ፖለቲከኞች፣ ያውም በቅድመ-ሁኔታ ከእስር ሲለቀቁ፣ እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው ‹ለሀገራችን የሚበጅ ርዕዮተ-ዓለም አለን› ብለው ለትግል ከቆረጡ፣ የሚኖራቸው አማራጭ ምን ሊሆን ይችል ነበር? ብለን ብንጠይቅ፣ ሁላችንንም ሊያሳምን የሚችል ድምዳሜ ላይ መድረስ ቢሳነን እንኳ፣ ዛሬ ለመረጡት የትግል ስልት አሁንም ኃላፊነቱ ዞሮ ዞሮ መንግስታዊ ሥልጣን ከያዘው ኃይል ትከሻ ላይ እንደማይወርድ እሙን ነው፡፡
ከዚህ ባለፈ ኢህአዴግ ሀገሪቷ የ‹‹አሸባሪ››ዎች ዒላማ መሆኗን ለማሳየት የሚጠቅሳቸው (ባለቤት ያላቸውም፣ የሌላቸውም)፣ በአዲስ አበባ አንዳንድ ሆቴሎች እና ሚኒባስ ታክሲዎች ላይ የተፈፀሙ ህይወት-ቀጣፊ አሳዛኝ ፍንዳታዎችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ከ‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ጀምሮ ‹‹ፋክት›› መጽሔት ድረስ ባሉ የሚዲያ ውጤቶች በስፋት የተዘገቡ በመሆኑ መድገሙ አስፈላጊ አይደለምና አልፈዋለሁ፡፡ በግልባጩ የአልሸባብ አሸባሪነትንም ሆነ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ያለው ብርቱ ፍላጐት ለማንም ስለማያጠራጥር፣ የመንግስት ቀዳሚ ተግባር ሀገሪቱንና ዜጎቿን ከየትኛውም አደጋ መጠበቅ በመሆኑ፣ ከዚህም በላቀ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት መስጠት እንዳለበት እገነዘባለሁ (ይህ ጥንቃቄ ጥልቅ ከሆነው ድህነታችን አንፃር በጥቅም ተማልለው በግብረ-አበርነት ሊሳተፉ የሚችሉ ወንድም-እህቶችንም በአይነ-ቁራኛ መከታተልን ያካትታል)፡፡ ምክንያቱም እውነተኞቹ የሽብር ኃይሎች (በመለስ ዜናዊ አገላለፅ ‹‹ፕሮፌሽናሎቹ››) የሰናፍጭ ታህል ቀዳዳ ካገኙ ዘግናኝ የሕዝብ እልቂት እና ከባድ የንብረት ውድመት ከማድረስ እንደማይመለሱ ከኬኒያ ክራሞት መረዳት ይቻላል፡፡

በተጨማሪም ከሥርዓቱ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ድርጅቶች፣ ጋዜጠኞች፣ የመብት ተሟጋቾችም ሆኑ ዜጎች… አልሸባብን የመሳሰሉ ኃይሎችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት እኩል ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለባቸው አልዘነጋውም፡፡ ይህ ማለት ግን በተጭበረበረ ምርጫ ባሸነፉ የገዢው ፓርቲ አባላት የተሞላው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ የዓይኑ ቀለም ያላማረውን በሙሉ ‹‹አሸባሪ›› ብሎ እያሳደደ የሚፈርጀውን እንደወረደ በመቀበል ማውገዝ አለመሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ፡፡ በግሌም ከአልቃይዳ እና አልሸባብ በቀር፣ ሌሎቹ ድርጅቶች የሚከተሉት የትግል ስልት ሕጋዊና ሰላማዊ አለመሆኑ ባይካድም፣ የብሔራዊ ቡድናችንን እግር ኳስ ጨዋታ ለመመልከት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚሰበሰበው ዜጋን፣ አሊያም በሕዝብ የመጓጓዣ አገልግሎት ታጭቆ የሚጓዝ ንፁሃንን የጥቃት ዒላማ አድርገው ሲንቀሳቀሱም ሆነ ሲተግብሩ አለመታየታቸውንም፤ አለመሰማታቸውንም እመሰክራለሁ፤ በ‹‹ማኒፌስቶ››አቸውም ውስጥ ሲቪሉ ኢትዮጵያዊን በአሳቻ ቦታ ባጠመዱት ፈንጂ ስለማጋየት የሚያወራ ሽራፊ አንቀፅ አላነበብኩም፤ በአጠቃላይ ሰላማዊ ዜጋን በሽብር ድርጊት ለማመስ የቀመሩትን ‹‹ስትራቴጂ›› የሚያጋልጥ ጥናትም ሆነ የውስጥ-አወቅ መረጃ አጋጥሞኝ አለማወቁን  አልሸሽግም፡፡ …የሆነው ሆኖ በኢትዮጵያችን የ‹‹ሽብር›› ዘፍጥረት ቅድመ-ታሪክ ከሞላ ጎደል ይህን ይመስላል ብዬ አምናለሁ፡፡

   በተቀረ የአል-ቃኢዳውን አይማን አልዘዋሀሪ፣ አሊያም የአልሸባቡን አህመድ አብዲ ጎዳኔ፣ ወይም የቦኮ-ሀራሙን አቡበክር ሼኩ የመሰለ በለዒ-ሰብ፣ ከኢትዮጵያውያን ‹‹አሸባሪ››ዎች መካከል ፈልገን የምናገኝ አይመስለኝም፤ ሌላው ቀርቶ ከሳሹ ኢህአዴግም የታሳሪዎቹን ንፅህና ከማንም በላይ አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ ሆኖም ሀገሪቱ ኢትዮጵያ ነችና፣ በደነበረና ምርጫ በተቃረበ ቁጥር ‹‹አሸባሪ›› በሚል የሀሰት ወንጀላ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የመብት ተሟጋቾችን…  ለእስርና ስቅየት የሚዳርግበት በስዩመ ጠብ-መንጃ ሥልጣን ራሱን ከቀባ ከሁለት አስርታት በላይ ተቆጥሯል፤ መስከረም እስኪጠባም ድረስ ይኸው የነፍጠኝነት ዘመን መቀጠሉ አይቀሬ ይሆናል፡፡   በነገራችን ላይ እስከዚያው አቶ አንድአርጋቸው ጽጌ ሰሞኑን ከየመን ተይዞ ሞት ለፈረደበት የኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱን ሰምተናል፤ በርግጥ የመን ከዚህ የሰው ንግድ ገበያ ምን እንዳተረፈች የተገለፀ ነገር የለም (መቼም በደጉ ዘመን፣ አክሱማውያን ያስገብሯት የነበረችው ምድረ-አረብ፣ ይህ አይነቱን ያውም የራስን ሀገር ክብር የሚነካ ውለታን በብላሽ ፈፀመች ቢባል ማን ያምናል?) እንደዚያም ሆኖ ግን የአምባ-ገነኑ መሪያችን የአቶ መለስ ዜናዊን ህልፈት በሰማን ጊዜ እንደ ሰው እንዳዘንነው ሁሉ፣ እንዳርጋቸው ጽጌም ከአፄው ዘመን ጀምሮ በእምነቱ ፀንቶ ጉልበታም አገዛዞችን ሲገዳድር ከአርባ ዓመት በላይ ዋትቶ ዋትቶ፤ ዛሬ ሞቱን በሚሹ ሰዎች እጅ በመወድቁ ሊደርሰበት በሚችለው መከራና ስቀየት ከልብ ከማዘን ያለፈ የማደርገው ነገር ባይኖርም፣ ‹የኢትዮጵያ አምላክ ብርታቱን ይስጥህ› ማለትን
ወደድኩ፡፡

              እንደ መውጫ
ዘርፈ-ብዙ በሆኑ የግንኙነት ሰንሰለቶች እየተጠላለፈ ከመጣው የዓለም ገፅታ ተገንጥሎ ጉልበተኛ ሥርዓት ይመሰረትበት የነበረው የአምባ-ገነንነት ዘመን ጀምበር እየጠለቀበት ይመስላል፡፡ ከኢኮኖሚያዊ ወዳጅነት እስከ ፖለቲካዊ ስምምነቶች ያሉ የትብብር ውሎችም አስገዳጅ በሆኑ ሕጋዊ ማዕቀፎች መጠፍነግን የመሰለ ጫና ስለማሳረፋቸው ከሁነቱ ለማፈንገጥ የሞከሩ ጥቂት የማይባሉ አገራትን የማታ ውድቀት ማስታወሱ በቂ ነው፡፡ በተለይም ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ የተስተዋሉ ታሪካዊ ክስተቶች ዓለምን በማጥበባቸው፣ በተደጋጋሚ አምባ-ገነን አስተዳደርን ያስተናገዱ አገራት እንኳ ሳይቀሩ፣ በአዲስ ፖለቲካዊ ልምምድ እንዲቃኙ የዕድል በር ተከፍቶላቸዋል፡፡ ነገም  የለውጡን መንፈስ በመቃወም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመንበርከክ አሻፈረኝ የሚሉ መንግስታትም፣ ከድንገቴው ፍርስራሾቻቸው ሥር ትውልዱ የነፃነት ብርሃን ይጎናፀፍ ዘንድ ዘመኑ ስለመፍረዱ ለመናገር ነብይ መሆንን አይጠይቅም፡፡ በእኛይቷ ኢትዮጵያም ተወደደም ተጠላ ከሁለት አስርታት በላይ እንደ ምርጊት የተጣበቀብን ኢህአዴጋዊ አስተዳደር የመጨረሻ ስንብት፣ በዚህ መንገድ ስለመበየኑ አስተማመኝ ፍንጮች መታየታቸውን በድፍረት እመሰክራለሁ፡፡ እልፍ አእላፍ እግሮችም ወደ የለውጥ አደባባዩ የማምራታቸውን ብልጭታ፣ የትኛውም ምድራዊ ኃይል ሊያጨልመው ይችላል ብሎ ማሰቡ ፈርኦናዊ መታበይ ካልሆነ በቀር አንዳችም ፋይዳ አይኖረውም።

ይሁንና አገዛዙ እንዲህ በውድቀቱ ዋዜማ ላይ ቆሞም በክፋት መፀናቱ ጥቂት ጥያቄዎችን እንድናሰላስል ይገፋል፡- ይህ አይነቱ የናዳ መዓት ተንከባሎ እስኪያደባየው ድረስ ስለምን በግትርነት ቆሞ ይጠብቃል? ሊገታው የማይችለውን ማዕበል በመጋፋትስ፣ በእናት አገር የእንባ ጎርፍ ውቂያኖስ መፍጠርን ስለምን መረጠ? እንዲህ የትውልድ ደም በከንቱ ለማፍሰስስ ስለምን አሰፈሰፈ? የሀገሪቱ ዕጣ-ፈንታ በጠብ-መንጃ ብቻ ይወሰን ዘንድ ስለምን ጨከነ? …ርግጥ ነው የእነዚህ ጥያቄዎች ምላሾች ሟርትም ይሁን ገድ፣ በሀገሬ ምድር አዲስ የታሪክምዕራፍ የመገለጡን አይቀሬነት ቅንጣት ጥርጣሬ ውስጥ አይከቱትም፡፡ በአናቱም ዛሬ አገዛዙን በትጥቅ ትግል ለመፋለም ከአስራ አንድ የማያንሱ ቡድኖች ‹‹ክተት›› አውጀው በርሃ መግባታቸው፣ የደርግን የመጨረሻዎቹ ቀናት ማስታወሱ አንዳች የሸሸገው ምስጢር አይኖረውም ማለት ታሪክን በቅጡ አለመረዳት ይሆናል፡፡
የሆነው ሆኖ የኢህአዴግ እምቢ-ተኝነት አውዳሚ ጥፋት ሊያደርስ ቢችልም እንኳ፣ በሂደቱ የምንሻገራቸው አደጋዎች፣ የምንወጣቸው አቀበቶች፣ የምንወርዳቸው ቁልቁለቶች፣ የምናቋርጣቸው ጫካዎች… የማታ ማታ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማዋለዳቸው አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ትንቅንቅ መካከልም ለዘመናት የልዩነት መንስኤ የሆኑት፣ ከርዕዮተ-ዓለም እስከ ኃይማኖት፤ ከኢኮኖሚ ሥርዓት እስከ መሬት ይገባኛል ድረስ የሚመዘዙ ጥያቄዎች የሚያደርሱት ኪሳራ በሀገር ፍርሰት፣ በትውልድ እልቂት ሳይወራረድ በፊት፣ በሰላማዊ መንገድ መፍታት ይቻል ዘንድ የኢህአዴግን እጅ ከመጠምዘዝ ጎን ለጎን ብሔራዊ እርቅን አሳክቶ በድል ጎዳና በዝማሬ ለመትመም ሁላችንም የፖለቲካ ልዩነትን ለጊዜው ወደጎን ብለን በአንድነት እንድንቀሳቀስ ያስገድደናል፡፡ ይህንን ተልዕኮ ለማሳካትም ከክር የቀጠነው ብቸኛ አማራጫችን ደጋግመን የተነጋገርንበት ‹‹የሕዳሴ አብዮት›› ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ኢትዮሚድያ  - Ethiomedia.com

↧

ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ በአቶ አንዳርጋቸው እገታ ዙሪያ ተናገሩ

$
0
0

ከከፍተኛ አሰልጣኝና አብራሪ ካፖቴን ተሾመ ተንኮሉ ጋር በተለይ ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጠለፋና ሊደርስባቸው ከሚችል ስቃይ ጋር በተያያዘ የተደረገ ቆይታ ከመለከት ራድዮ ቫንኮበር ጋር።

ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ በአቶ አንዳርጋቸው እገታ ዙሪያ ተናገሩ

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live