Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በመንገጫገጭም ውስጥ የሚታይ ደማቅ ለውጥ አለ!! –ሲሳይ አጌና

$
0
0
በኢትዮጵያ አንድ ዓመት ያስቆጠረው ለውጥ በብዙ ፍላጎቶች እንዲሁም ሥልጣናቸውን በተነጠቁ ወገኖች እና የፖለቲካ ንግድ ላይ በቆዩ ሃይሎች ፈተና እየገጠመው መሆኑ ግልጽ ነው።ይህ ዛሬ የሚታየው መንገጫገጭ ግን የትናንቱን የመቃብር ሕይወትና የመቃብሩን ጥልቀት በፍጹም ሊያስረሳን አይገባም። ኢትዮጵያውያን ያለፍንበትን መከራ በማሰላሰል ብቻ ሳይሆን መውጫችን ምንድነው ብለን የተጨነቅንበትን ግዜ መልሰን ስንቃኝ ዛሬ ያለንበት ሁኔታ በጉንፋን የሚመሰል ቀላል ሕመም ሲሆን፥በየአካባቢው […]

አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን) –ልሳን ኢትዮጵያችን ቅጽ 3 ቁጥር 5

$
0
0
ሚያዝያ 05 ቀን 2011 ዓ.ም. ኢሕአዴግና ደጋፊዎቹ የ“ለውጥ” እንቅፋቶች የድምጽ ቅጂውን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ https://www.youtube.com/watch?v=oRK2p86xt7c ኢትዮጵያችን እንደ ሀገር ለመኖሯ ጥርጥር የለንም። ትላንትም ዛሬም ነገም ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች! ይህ ለኢትዮጵያ እንደ ሀገር የህልውናዋ ጉዳይ በበርካታ ሕይወት የተገነባ ነው። ለሀገራችን ልምላሜ ፣ ለዘላለም ሀገር ሆና እንድትኖር የጀግኖች ልጆቿ አጥንትና ደም የዘላለም ሕይወት ሆኗታል ወደፊትም ይሆናታል። በትንሹ የሦስት […]

”ሺ ቢታለብ ያው በገሌ …፡፡“ –በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

$
0
0
  “ ሺ ቢታልብ ያው በገሌ ነው፡፡“ አለች ድመት ይባላል፡፡ “ድመት አለች“ ተባለ እንጂ ፣ ምን ቢደክም ፣ምን ቢለፋ፣ወትት ከምትሰጠው ላም ጋር ስቃዩን ቢያይም ፣ወተቷን አልቦ ሲያበቃ፣ለቀን ሙሉ ድካሙ ፣የማይመጣጠን ምንዳ እንጂ፣ተጨማሪ አንድ ማንኪያ ወተት እንኳን ስለማይሰጡት፣የህንን ኢ- ፍትሃዊ ድርጊት በማስተዋል ነው፤ አላቢው፣ “ ሺ ቢታለብ ያው በገሌ ነው የሚሰጠኝ ፡፡ “ ያለው፡፡ በጥቅሉ ለሥራው […]

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት አባል ጄኔራል ጃላል አል-ዲን አል-ጣይብ አዲስ አበባ ገቡ

$
0
0
ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ኂሩት ዘመነ ተቀብለዋቸዋል። ጄኔራል ጃላል አል-ዲን አል-ጣይብ ከወይዘሮ ኂሩት ዘመነ ጋር በተወያዩበት ወቅት የሱዳን ጦር ፕሬዝዳንቱን ያወረደው በዜጎች የለውጥ ፍላጎት እንጂ ሥልጣን የመያዝ ፍላጎት ስላለው እንዳልሆነ መናገራቸውን የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢቫንካ ትራምፕ እና የልዑካን ቡድናቸውን ተቀብለዉ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

$
0
0
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ሚያዚያ 7, 2011 በጽ/ቤታቸዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት አማካሪ ኢቫንካ ትራምፕ እና የልዑካን ቡድናቸውን ተቀብለዉ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ትናንት ኢትዮጵያ የገቡት ኢቫንካ ትራምፕ ያገራቸዉ መንግስት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት የታቀደው የሴቶች ዓለም አቀፍ ልማት እና ብልጽግና ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ነዉ። PMOEthiopia

የሃገር መከላከያው ሴክተር ላይ ተደረገ የተባለው “ሪፎርም”–ወንድይራድ ሀይለገብርኤል

$
0
0
በግልፅ እንዳየነው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በአዴፓ ትከሻ ላይ ተፈናጥጠው ስልጣን በተቆናጠጡ ማግስት በቶሎ ተቻኩለው ግዜ ሳይሰጡ የመጀመሪያውን የፖለቲካ ሸፍጥ የተገበሩት የሃገር መከላከያ ሰራዊቱን “ትግራዊ የነበረውን መከላከያ ኢትዮጵያዊ ቅርፅና ይዘት መስጠት” በሚል መሪ ቃል የሰራዊቱን ከፍተኛና ቁልፍ የዕዝ ወንበሮች ከህወሐት ነጥቆ የኦዴፓ/ኦነግ በማድረግ ነው። ይህንን በማድረጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ያልሆነ የኦሮሞ መከላከያ ሀይል በተሳካ ሁኔታ መፍጠር […]

የኛ ወይንስ “ኬኛ”? -የኢትዮጵያ አንድነትና “የተፎካካሪ ፓርቲዎች” ብዢታ –አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)    

$
0
0
ይህን ወቅታዊ ሃተታየን በመፍትሄው ልጀምር። ጥንታዊዋንና ባለ ታሪኳን ኢትዮጵያን ከብሄር ተኮር እልቂት፤ ከድህነት፤ ከፍልሰት፤ ከስደት፤ ከጥገኝነትና ከኋላ ቀርነት ኡደት ራሷን እንደ አንዲት አገር እና ሕዝቧን እንደተባበረ ሕብረ-ብሄራዊ ሕዝብ ነጻ ለማውጣት ከተፈለፈገ፤ ዘረኝነት፤ ጠባብ ብሄርተኝነት፤ የብሄር ትምክኸተኛነት፤ ጽንፈኛነት፤ “የኔ ብቻ” ባይነትና ብሄር ተኮር እልቂት መቀረፍ አለበት። አለያ፤ ዘላቂና ፍትሃዊ ልማት አይቻልም። በዚህ ሃተታየ የምከራከረው ብሄር ተኮሩ […]

ከምንፈጃጅ እንበጃጅ (ሳዲቅ አህመድ)

$
0
0
ዘር አስጠላኝ።ለምን ሰው በሰውነት ማእቀፍ ውስጥ ብቻ አይኖርም? ሰው መሆን አይበቃምን? የሚል ውስጣዊ ሙግት ጋር ግብግብ ገጠምኩኝ።ቀናትን ዘለኩኝ። የዘር ምስጢር አምላክ በክህሎቱ የሰራው ነውና በርሱ ስራ መግባት መስሎም ተሰማኝ።አሁንም እራሴን ጠይቃለሁ።ዘር በሚሉት ነገር መንገፍገፌ ለምንድነው ብዬ ከራሴ ጋር እሟገታለሁ።ለካስ ችግሩ ዘር አልነበረም።በመላው ኢትዮጵያ የጦዘው«ዘረኝነት» ቢሆን እንጂ። • የተጋጋለው ዘረኝነት ዘረኝነቱ ተጋግሏል።ብዝሃኑ አቅሙ በቻለው መጠን ዘረኛ […]

እምቧ በይ ላሚቱ! –በላይነህ አባተ

$
0
0
ትናንትናም ዛሬም ከብቱ ባይረዳው፣ ካራ ደምን አፍሳሽ ነፍስ አጥፊ እሚሆነው፣ ተቀንድ ወይም ተእንጨት ሲገባ ብቻ ነው፡፡   ታዲያ ጊደር ላሟም ቀንዱን ዛቢያ ትተው፣ ጠላት እሚያደርጉት አራጁን ካራን ነው፣ ልክ እንደ ደን ዱሩ ጨፈቃና ጫካው፣ ጠማማውን ትቶ ምሳር እንደሚያማው፡፡   ያርድ እየመሰላት ተዛቢያው ሳይገባ፣ ላም ደም ታፈሳለች በስለቱ ካራ፡፡   ተበሬ ጭንቅላት የበቀሉ ቀንዶች፣ ሰክተው ሰክተው […]

ከጥቃቱ በስተጀርባ…ሳዲቅ አህመድ

$
0
0
ዛሬ ብዙ ግዜ ጽፌ ፖስት ሳለረግ ድሊት አድርጌያለሁ።አገሪቷ አጣብቂኝ ውስጥ ባለችበት ወቅት ይህንን የመሰለውን እርምጃ መውሰድ ለምን? የሚል ጥያቄ ውስጤን በጣም ተሟገተው።ዛሬ ሹመት ያላቸው ነገ ይሻራሉ።አገር ግን ትኖራለች። የዚች አገር ጉዳይ ከሁሉ ነገር በላይ ነውና በዛሬው ችግር ብቻ ነገሮች መመዘን የለባቸውም።እንደምን ዘለቄታዊ መፍትሄ ይገኛል? ይህ ሞጋች ሐሳብ ሐሳብ እጆቼ እንዳይከትቡ ጠፈራቸውና ዋለ። “#የልብን_ሰርቶ_ይቅርታ” እንደሚባለው የማእከላዊ […]

የሕብር ሬዲዮ ሚያዚያ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ፕሮግራም

$
0
0
የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት(ባልደራስ) በጸጥታ ችግር የሰረዘውን ስብሰባ ኧመልክቶ ከጋዜጠኛና የመብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ(ያድምጡት) « የካራ ማራ ድል ትልቅ ብሔራዊ ድል ነው ።በጊዜው ግን የሶማሊያን ወረራ የደገፉት ተቃዋሚዎች ሕወሓት፣ኦነግ፣ኢህአፓ…በመሆናቸው …» ሜ.ጀ/ል መርዳሳ ሌሊሳ ሰል ካራማራ ድል እና ተያያዥ ጉዳዮች በስፋት ለህብር ሬዲዮ በቬጋስ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ (ክፍል አንድ) የኢትዬጵያ […]

‹‹የተወሰደው እርምጃ አግባብነት የሌለው ነው››-የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

$
0
0
አብዱልቃድር መስጂድ ላይ የተወሰደው እርምጃ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ አብዱላዚዝ ወጉ ገለጹ። የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ ትናንት በአብዱልቃድር መስጂድ የተፈጠረው ችግር ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጭ ነው ብሏል። ትናንት ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት አካባቢ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሚገኘው አብዱልቃድር መስጂድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሰዎች ላይ ለሶላት ሲጠቀሙበት […]

ባየር ሙኒክ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ስማቸው ያረፈበትን ማልያ አበረከተ

$
0
0
የጀርመኑ ባየር ሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ስማቸው ያረፈበት የክለቡን ማልያ በስጦታነት አበርክቷል። የባቫሪያን ግዛት ሚኒስትር – ፕሬዚዳንት ማርከስ ሶደርም ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ ከጀርባው 1 ቁጥር የተጻፈበትንና የፕሬዚዳንቷ ስም ያረፈበትን ማልያ አበርክተውላቸዋል። የጀርመኑ እግር ኳስ ክለብ ባየር ሙኒክ በአዲስ አበባ የእግር ኳስ አካዳሚ መክፈቱን አስታወቀ፡፡ በዚህ አካዳሚ በመደበኛነት ከባየር ሙኒክ ክለብ አሰልጣኞች እየመጡ ተጨዋቾንንና […]

“እንፈላለጋለን!” (ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ)

$
0
0
ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ የኢኮኖሚክስ መምህርና ጸሓፊ (ሸክም የበዛበት ትውልድ፡ 2009 እና የምሥራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ) የሀገራችንን ነባራዊ ወቅታዊ ኹኔታ መኾን ካለበትና ሊኾን ከሚገባው ይልቅ እየኾነ ካለው ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ አንጻር ስንመለከት እጅግ በጣም የተለያየ፣ ፈጽሞ ሊቀራረብ የማይችል፣ አብሮ ሊያሰራ የማይችል፣ ፍጹም ተቃራኒ ሀሳብና አቋም ያላቸው ኃይሎችና አካላቶች ሕብረት ፈጥረውና ሕብረት ፈጥረናል ብሎም ተስማምተናል ሲሉ መስማት […]

በአዋሽ ኬላ 3 ሺህ 910 የክላሽ ጥይት በጉምሩክ የፍተሻ ሰራተኞች ተያዘ

$
0
0
መነሻውን ከሀረር መስመር ያደረገ 3 ሺህ 910 የክላሽ ጥይት በጉምሩክ የፍተሻ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ጥይቱ በትላንትናው ዕለት ምሽት 2፡00 አዋሽ ኬላ በጉምሩክ የፍተሻ ሰራተኞች ነው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡ ጥይቶቹ የተያዙት በተሽከርካሪው ላይ በተሰራለት ድብቅ ቦታ ሲሆን የጉምሩክ ተቆጣጣሪዎቹ ያላቸውን ልምድ እና ብቃት በመጠቀም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡ ሚያዝያ 8/2011 ዓ.ም በተመሳሳይ […]

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሦስት ሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ

$
0
0
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሦስት ሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ተሾሙ

$
0
0
የጨፌ ኦሮሚያ ዛሬ ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ አቶ ሽመልስ አብዲሳን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አድርጎ ሾሟል፡፡ ጨፌው አቶ ሽመለስ አብዲሳን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ የመረጠው የቀድሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ነው፡፡ አቶ ሽመልስ የፕሬዝዳንቱን ስራ ደርበው እንደሚሰሩ […]

እኔን ስቀሏት! –ወለላዬ ከስዊድን

$
0
0
“እኔ”፣ “የእኔ” ማለትን ውገሯት፣  ጣር ፍዳ ሞቷን አሳዩአት፣ መቀጣጫ አድርጋችሁ ስቀሏት፣ አርቃችሁ ቆፍራችሁ ቅበሯት። በእኔ መቃብር ላይ “እኛ” በቅሎ ይገኝ ይሁነን መዳኛ እኛነት ስትለመልም ትወልዳለች ሕዝበ ሰላም አገር ምድሩ ያብባል በአንድነት አንድ ይሆናል ፍዳ መዓቱ ይጥፋል ሞትም በሕይወት ይሞታል እናም “እኔ” ማለትን እንናቅ ጉያዋ ስር አንወሸቅ ከጀርባዋ አንደበቅ “እኔ” ናት እኛነትን የበላችው ጠባብነትን የዘራችው ወንጀል […]

ታላቁ የፖለቲካ ቅሌት በኢትዮጵያ፤ ነጠብጣቦቹን ያገናኙና ምስሉን ይመልከቱ!

$
0
0
ፀሃፊ፡- ሰርቤሳ ከ. ተርጓሚ፡- ሢሣይነሽ መንግሥቴ ከሚያዚያ 2018 (እ.ኤ.አ) ቀደም ያለ ቢሆንም፣ በተለይ 2018ና 2017 ላይ በዲያስፖራው አካባቢ  የሚገኙ የኦሮሞ አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞችና ሙያተኞች በርካታ ክፍት፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችንና የኢህአዴግ አገዛዝ ውስጥ ካሉ ‹‹ህዋሶቻቸው›› ጋር ምስጢራዊ ውይይቶችን አድርገው ነበር፤ ህወሓት-መራሹ ኢህአዴግ ከተወገደ በኋላ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት የኦሮሞ የበላይነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል የሚገልጡ ዝርዝር ስልቶችና ዕቅዶችን ለመፍጠር፡፡ ይህኛው ሃሳብ […]

የአራት ኪሎዎቹን መንትያ ሕንፃዎች ለቤተ ክርስቲያን መመለሱን የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ፤“ተከራዮች ባሉበት ይቀጥላሉ”

$
0
0
ሐራ ዘተዋሕዶ ለመኖሪያና ለንግድ የተከራዩ ኹለት ባለ12 ፎቅና ኹለት መለስተኛ ሕንፃዎች ናቸው፤ በመኖሪያነት የሚጠቀሙበትም ኾነ በንግድ የተሠማሩት ተከራዮች ባሉበት ይቀጥላሉ፤ በልዩ ፖሊቲካዊ ውሳኔ እንዲመለሱላት መወሰኑን፣ የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፤ እንዲመለሱላት፣ ያለፉትና ያሉት ቅዱሳን ፓትርያርኮች በተደጋጋሚ ሲጻጻፉ ኖረዋል፤ በአቡነ ቴዎፍሎስ አመራር፣ እስከ 10ኛ ፎቅ ከገነባች በኋላ ነበር በደርግ የተነጠቀችው፤ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 10ሺሕ ቤቶች አንዱ ኾኖ ቆይቷል፤ *** ከተወረሱባት ቤቶችና ሕንፃዎች […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live