Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኢንጅነር ስመኘው የሞተው አሁን ነው –ከባርናባስ ገብረማሪያ

$
0
0
ራሱ ሕግ አውጪ ፣ ራሱ  ከሳሽ ፣ ራሱ ዳኛ ፣ ራሱ መስካሪ ፣ ራሱ አሳሪና መርማሪ ሆኖ ዘግናኝ በሆነ መልኩ ዜጎችን ሲያሰቃይና ሲያሳድድ የቆየው የህወሓት/ኢሕአዴግ ስርዓት ዛሬም የኢንጅነር ስመኘው አሟሟትን አስመልክቶ ያቀረበው አስደማሚ ፣ አስገራሚና አሳዛኝ የምርመራ ውጤት ድራማ ስመለከት እጅግ አሳዝኖኛል:: እውነትም ኢንጅነሩ የሞተውና የተቀበረው ዛሬ ነው የሚል ውስጣዊ ስሜት አድሮብኛል:: ጨዋና ስነ ስርዓት […]

20 የማይሞሉ ተማሪዎች በመቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

$
0
0
በትግራይ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ:: በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩና አሁን ደግሞ ምደባ እየጠበቁ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ የዩኒቨርሲቲ ጥቂት ተማሪዎች በሌሎች ክልሎች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ሄደን ለመማር ለደህንነታቸን ስምንሰጋ እዚሁ ትግራይ ክልል መድቡን በማለት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ:: ቁጥራቸው ሃያ የማይሞላ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬ ጷጉሜ 3/ 2010 ዓ/ም በትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ፅሕፈት ቤት ተገኝተው በሰለማዊ ሰልፍ […]

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጉዞ ጀመሩ

$
0
0
ነገ ማለዳ አዲስ አበባ ለሚገቡት የ’አርበኞች ግንቦት 7′ ንቅናቄ አመራሮች፤ የመዲናዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ያደርጉላቸዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን መዲናዋ ለዚሁ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት፣ በባንዲራና በፖስተሮች ደምቃለች፡፡ ከአውሮፓ በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ የሚመራ ቡድን እንዲሁም ከአሜሪካ በዶ/ር አዚዝ እና ነአምን ዘለቀ የሚመራ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ጉዞውን ጀምሯል:: ለአመራሮቹ የሚደረገው አቀባበል ከጠዋቱ 12፡30 እስከ ቀኑ […]

ዘ-ሐበሻ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶ/ር አብይ አህመድ እና ባለቤታቸው ዝናሽ ታያቸውን ልዩ ሽልማት ሸለመች:: ቤተከርስቲያኒቱ ሽልማቱን ያበረከተችው ዶ/ር አብይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለተፈጠረው ሰላም ላደረጉት አስተዋጽኦ ነው:: ዶ/ር አብይ ከባለቤታቸው ወ/ሮ ዝናሽ ጋር ካባ ለብሰው ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ባሰሙት ንግግር “ሽልማቱ ያለእረፍት ይህ ነገር እንዲመጣ ሲታገሉ ለነበሩ እና ይህ ለውጥ እንዲመጣ ሲፀልዩ ለነበሩት በሙሉ የሚገባ […]

ጋሞ እና ጎፋ ሊለያዩ ነው

$
0
0
ደቡብ ክልል አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ጥናት አጠናቀቀ የደቡብ ክልል አዳዲስ የዞንና የወረዳ አወቃቀር ምክረ ሐሳብ የያዘ ጥናት አጠናቅቆ ለአመራሮች ውይይት እንዳዘጋጀ ታወቀ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ሊቀመንበርና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ ክልሉ አዲስ አወቃቀር እንደሚኖረው የመንግሥት አገልግሎትን […]

የአዲኃን አመራሮች እና ወታደሮች በጎንደር ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

$
0
0
የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርጎ በኤርትራ ሲንቀሳቀስ የነበረው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ (አዴሀን) ከኤርትራ ምድር ተነስቶ ወደ ባህር ዳር ሲያመራ በጎንደር ደማቅ አቀባበል ተደረገለት:: ከኤርትራ በረሃ ኦማህጀር በመነሳት በሁመራ  አድርገው ጎንደር የገቡት የአዴኃን ወታደሮች  በቅርቡ የዶ/ር ዓብይ መንግስት የተከተለውን የለውጥ መስመር በመቀበል ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በሰላም ለመታገል ከአማራ ክልል አመራሮች ጋር በኤርትራ ስምምነት ማድረጉን ተከትሎ ነው […]

አርበኞች ግምቦት 7ን ለመቀበል የወጣው ሕዝብ ስታዲየሙ ሳይበቃው ቀረ

$
0
0
ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ የገባውን የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ለመቀበል የወጣው የአዲስ አበባ ሕዝብ ስታዲየሙ ሳይበቃው ቀረ:: ስታዲየም ውስጥ ካለው ሕዝብ በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ሕዝብ ከስታዲየሙ ውጭ መስቀል አደባባይ ድረስ በመሆን አቀባበሉን ሲከታተል ቆይቷል:: በዚህ አቀባበል ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ‹‹ሳንፈልግ ከሀገራችን ተገፍተን የወጣነው!፤ በዱር በገደሉ የተንከራተትነው! በሀገራችን ሙሉ ነጻነት ያለን ዜጎች ሆነን […]

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ!!! የደቡብ ክልል የኮንሶ ህዝብን የሚጨፈጭፈውእስከመቼ ነው??

$
0
0
ከልጅ ባልቻ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች እንዲሁም የሰብአዊ መብት ተሟጋጆችና ምሁራንስ የኮንሶ ህዝብ በቅጥረኛ የወያኔ ሪዝራዦች የደቡብ ክልል አምባገነን ባለሥልጣናት ትዕዛዝ በመከላከያ ሰራዊት ካለፉት ሶስት አመታት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየተሰቃየና እየተገደለ ህገ መንግስታዊ መብቱን ተነፍጎ ዘርፈ ብዙ ኢ ሰብዓዊ ድሪጊቶች እየተፈፀሙበት እያወቁ ተመልካች ሆነው ዝም የሚሉት እስከ መቼ ነው? የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትስ የኮንሶ ዜጎችን […]

ትግራይ –ቀጣይዋ የሱማሌ ክልል –ነፃነት ዘለቀ

$
0
0
በቅድሚያ ከዘመን ወደ ዘመን መሸጋገሪያ ዋዜማ ላይ ቸሩ ፈጣሪ እንኳን በሰላም አደረሰን! 2011ዓ.ም የበርካታ ሀገራዊ ስኬቶች መመዝገቢያ እንዲሆንልን በግል እመኛለሁ፡፡ ወደሚናፍቋት ሀገራቸውና ሕዝባቸው ነገ የሚገቡትን አርበኞች ግንቦት ሰባትን ጨምሮ ሌሎችም ተመላሾች ላገራቸው ያሰቡትና ያቀዱት መልካም ነገር ሁሉ ፍሬ እንዲያፈራና ሀገራችንና ሕዝባችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ ዐመጠኞችም አስተዋይ ልቦና አግኝተው ሰው እንዲሆኑ እጸልያለሁ፡፡ ሣልረሳው – ጉድ ሳይሰማ መስከረም […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
በዳዑድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ እና በዶ/ር መረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ በኦሮሞ እና ኦሮሚያ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ:: የህዝቡ ድምጽ እንዳይከፋፈል ለማድረግ፤ ፌዴራላዊ ስርዓቱን እውን እንዲሆን በጋራ ለመስራት፤ የራስ መብትን በራስ ለመወሰን በሚሉ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን ድርጅቶቹ ባወጡት መግለጫ አስታወቀዋል:: ከኤርትራ የፊታችን መስከረም 5 አዲስ አበባ […]

በሚኒሶታ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የአንድነት ጉባዔ አድርገው የመስቀል በዓልን በጋራ ሊያከብሩ ተስማሙ

$
0
0
ሰሜን አሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናት በመካከላቸው የነበረውን አንዳንድ አለመግባባት በማስወገድ ሁሉም ካህናት አባቶች እና ምእመናን በሚገኙበት የሰላም የአንድነት እና የእርቅ ጉባኤ ለማድረግ እንዲሁም የሁለት ሺህ አሥራ አንድ ዓመተ ምሕረትን የመስቀል ደመራን በአል በጋራ ለማክበር ተስማሙ:: ከተለያዩ ደብሮች የመጡ የደብር አለቆች እና የካህናት ተወካዮች እንዲሁም የሰበካ ጉባኤ አባላት በጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ […]

የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች አዲስ ዓመትን በአንድ ላይ ሊያከብሩ ነው

$
0
0
በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር ከዛላምበሳ ወደ ሰንዓፈ የሚወስደውን መንገድ ዘግቶ የቆየው የድንጋይ አጥር ዛሬ ፈረሰ:: ነገ ጠዋት የአዲስ ዓመት በዓልን የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች በዛላምበሳ ከተማ እንደሚያከብሩ ታወቀ:: በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያዋ ዛላምበሳ እና የኤርትራዋ ሰንዓፈ መካከል የነበረው የድንጋይ ግንብ እንዲፈርስ የተደረገውም ለነገው የአዲስ ዓመት ዝግጅት ማብሰሪያ እንዲሆን ታስቦ ነው የሚሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በአቅራቢያው የነበረው የኤርትራ የጦር ምሽግ […]

ምን ያህል ሱማሌዎች በፌዴራል መ/ቤቶች ተቀጥረው ይሰራሉ?

$
0
0
ከራጆ ምን ያህል ሱማሌዎች በፌዴራል መ/ቤቶች ተቀጥረው ይሰራሉ? የዚህ ጥያቄ መልሱ በጣም ጥቂት ወይም ወይም ቁጥራቸው እዚህ ግባ የማይባል ተብሎ ሊነገር ይችላል፡፡ በአንዳንድ መስርያ ቤቶች ለመድሃኒት ቢፈለጉ አይገኙም፡፡ አስቡት ከአገሪቱ ከሚኖሩት ብሄር ብሄረሰቦች በሕዝብ ብዛት 3ኛው ነው፤ ከኦሮሞና ከአማራ በመቀጠል ማለት ነው፡፡ በመሬት ስፋት ደግሞ ከኦሮሚያ በመቀጠል 2ኛው ነው፡፡ ለምን ይህ ታላቅ ሕዝብ ጥቅት እንኳ […]

ዶ/ር አብይ አህመድ የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ሰው ሆኑ

$
0
0
ላለፉት 8 ዓመታት ተከታዮቹን በማሳተፍ በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ዋዜማ የዓመቱ ምርጥ ሰው የሚሰይመው ዘ-ሐበሻ የዘንድሮው የዓመቱ ምርጥ ሰው ዶ/ር ዓብይ አህመድን አድርጎ መርጧል:: የዘ-ሐበሻ ቡድን ዶ/ር አብይ አህመድን ለምን የዓመቱ ምርጥ ሰው አድርጎ እንደመረጠ ሲያስረዳ; ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ላይ ከወጡበት ቀን ጀምሮ ቃል የገቧቸውን ነገሮች በአብዛኛው እየፈጸሙ መሆኑን እንደ አንድ ምክንያት ይጠቅሳል:: በተደጋጋሚ ቃል የገቡትን […]

የዘንድሮውን አዲስ ዓመት በተሻለ ነጻነት እንድናከብር ውድ ዋጋ የከፈሉ የአማራና የኦሮሞ ልጆች ቤተሰቦች በዓሉን በኩራት ማክበር እንደሚገባቸው ተገለጸ

$
0
0
  የዘንድሮውን አዲስ ዓመት በተሻለ ነጻነት ውድ ዋጋ የከፈሉ የአማራና የኦሮሞ ልጆች ቤተሰቦች በዓሉን በኩራት ማክበር እንደሚገባቸው ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ተናገረ:: የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ መሪ የሆነውና ባለፈው ዓመት በተደረገው ሕዝባዊ ትግል ከ እስር የተፈታው ኮ/ል ደመቀ አዲሱን ዓመት በማስመልከት ባስተላለፈው መልክዕት “ወቅቱ የተለያየ ነገር የተቀላቀለበት ነው። ለውጡ መልካም ነገሮች እንዳሉት ሁሉ ያልጠሩም ነገሮች አሉት። […]

የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር በይፋ ተከፈተ

$
0
0
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሁለቱን ሃገራት በሚያዋሰስነው የቡሬና ዛላምበሳ ግንባር ተገኝተው ከሁለቱ ሃገራት ሰራዊት ጋር አዲስ ዓመትን ማክበራቸው  ይህ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረውን ግንኙነትን የማሻሻል እርምጃን ተከትሎ ተዘግተው የነበሩትን የሁለቱን ሃገራት የድንበር መተላለፊያዎች በመክፈት በኩል ትልቁ እርምጃ ነው ተባለ:: ዶ/ር አብይ አህመድ ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር በመሆን […]

ኦሮሞዎችና ሶማሊዎች የሕዝብ-ለሕዝብ እርቅ ማካሄድ ይኖርባቸዋል!

$
0
0
ከራጆ አብዲ ኢሌ በሥልጣን በነበረበት ወቅት በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች ላይ ከፍተኛ በደል መድረሱ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ በዝያን ግዜ የተፈለገው ለውጡን ለመቀልበስ ብሎም በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል የማይጠፋ ቁርሾ ለመተው አስበው ነበር በሁለቱም ወገን ያሉ አደግዳግዎች የተንቀሳቀሱት፡፡ እነሱ የፈለጉት ሳይሆን አምላክ ያሻው በመሆኑ ሕዝቡ ከዝህ ጥፋት ሊድን በቅቷል፡፡ ይህ ማለት ግን የተከሰተው ሁኔታ አልጎዳውም ማለት አይቻልም፡፡ ብዙ […]

የ ዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ከተማዋ አዲስ ዓመትን ያለ አንዳች እሳት አደጋ አሳልፋለች:: ይህም አስደሳች ዜና ነው ብሎታል:: ___ በቅርቡ ሥራ የጀመረው የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ በተመረቀ በሁለት ሳምንቱ ሥራ አቆመ፡፡ የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ 2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ወጥቶበት፣ ሥራ መጀመር ከነበረበት ጊዜ በሁለት ዓመት ዘግይቶ […]

ሕዝብ ከትናንሽ አጀንዳዎች ወጥቶ የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እንዲያከሽፍ ተመከረ

$
0
0
የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 20111 ዓ.ም አዲስ አበባ የሚገባውን በዳዑድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግን ለመቀበል መንገዶችን የኦሮሞ የትግል ባንዲራን እየቀበሉ ባንዲራ በሚሰቅሉና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት ንብረት ወድሟል:: የኢትዮጵያ ባንዲራን ሳያነሱ የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ባንዲራ ከጎን ማስቀመጥ ነበረባቸው በሚሉ ወጣቶችና ባንዲራውን ባነሱ ወጣቶች መካከል በተነሳ ግጭት ጳውሎስ ሆስፒታል ወይም ፓስተር አካባቢ ብጥብጥ ተነስቶ ነበር:: […]

“ነፃነት፣ ወንድማማችነትና እኩልነት ካለፈዉ ታሪክም ሆነ ከባንዲራ በላይ ነዉ!!”–አዲሱ አረጋ

$
0
0
“ነፃነት፣ ወንድማማችነትና እኩልነት ካለፈዉ ታሪክም ሆነ ከባንዲራ በላይ ነዉ!!” ከአዲሱ አረጋ በሀገራችን የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እና ትዉልድ መስዋዕትነት የከፈለበትን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን እዉን ለማድረግ በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ይታወቃል። በዚህ ሂደትም በሀገራችን የዴሞክራሲ ምህዳር ከመጥበቡ የተነሳ የትጥቅ ትግልን ለማራመድ ተገድደዉ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ትግል ለማድረግ የተፈጠረዉን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ወደ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live